ሴፕቴምበር 1, 2016
ከዲቦራ ለማ/ኖርዌይ
በመጀመሪያ
እግዚአብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ለሰው ልጆች የሚያስፈልገውን ሁሉ ባህሩን የብሱን፣ ብቻ ምንአለፋችሁ ሁሉንም ሰርቶ፣ አበጃጅቶ
ለመኖር ምቹ አድርጎ ከጨረሰ በኋላ አዳምን ፈጠረ፣ ለአዳምም ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም እልዳልሆነ አየና ረዳት እንድትሆነው ሄዋንን
ከጎኑ አጥንት አበጀለት። ከዚያም ታሪኩ ብዙ ነው፣ እግዚአብሄር አዳምና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ብሎ ባረካቸው። እንግዲህ
ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሰው በምድር ላይ እንደፈለገ እየተባዛ እንዲኖር ተፈቅዶለታል። መፅሀፍ ቅዱስ ላስተምራችሁ አይደለም! እንዲያው
ለሰው ልጆች በሙሉ በነፃ የተሰጠውን ተፈጥሯዊ መብቶች በመፃረር በሀገራችን
ያለው የወያኔ ስርአት እየፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማውገዝ ያህል መንደርደሪያ እንዲሆነኝ ነው።
ዘረኝነት ከብዙ ዘመናት በፊት በተለያዩ አህጉራት እንደ
አሜሪካና አውሮፓ በመሳሰሉት ሀገራት በጥቁሮችና በነጮች መካከል ጎልቶ ይታይ የነበረ ቢሆንም አሁን ባለንበት 21ኛ ክፍለ ዘመን
ግን ዘረኝነት የኃላ ቀር አስተሳሰብ በመሆኑ አሁን ባለንበት ዘመን እንደቀድሞው ጎልቶ አይታይም። በዚያን ጊዜ የነበረው ዘረኝነት
ነጮች በአፍሪካውያን ጥቁሮች ላይ ያሳዩት የነበረ የበላይነት እንጂ አሁን በሐገራችን ያለው አምባገነን ስርአት የራሱን ህዝብ በገዛ
ሀገሩ ባሪያ አድርጎ እንደሚያሳየን አይነት ዘረኝነት አልነበረም።
በርግጥ ወያኔ ከአመሰራረቱ ገና ከደደቢት በረሀ ይዞት የተነሳው አላማ ኢትዮጵያ የምትባልን ሀገር አፈራርሶ ታላቋ ትግራይ የምትባል
የኢንዱስትሪ ከተማ መስርቶ ትግራይን ከኢትዮጵያ የመገንጠል አላማ ይዞ የተነሳ የማፍያ ቡድን ነው። ይህንንም እኩይ የዘረኝነት አላማ
ለማስፈፀም ይዞ የተነሳው እስትራቴጂ ህዝቡን በዘር፣ በጎሳ፣ በሀይማኖት በመከፋፈል ከፋፍለህ ግዛው በተሰኘ አጋንንታዊ አስተሳሰብ
ነው። በተለይ ያሰጉኛል ያስፈሩኛል ያላቸውን የአማራንና የኦሮሞን ህዝብ በጠላትነት በመፈረጅና ሁለቱን ብሄሮች በማጋጨት ከፍተኛ
ወንጀል በኦሮሚያና በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ ሲፈፅም ቆይቷል። አሁንም እየፈፀመ ነው።
ወያኔ የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ አንድነት ድርድር የማያውቅ
መሆኑን አስቀድሞ ያውቅ ስለነበረ
ይህንን ህዝብ ለማጥፋትና ቁጥሩን ለማመናመን እጅግ በርካታ
እኩይ ተግባራትን እየፈፀመ ይገኛል። የአማራውን ህዝብ ከተወለደበትና ካደገበት፣ የእድሜውን እኩሌታ ከኖረበት፣ ሀብት ንብረት ካፈራበት
አካባቢ በማፈናቀልና ሜዳ ላይ ተበትኖ በገዛ ሀገሩ እንደስደተኛ መፃተኛ ሆኖ እንዲኖር አድርጎታል። የአማራው ህዝብ በተለያዩ አካባቢዎች
የጅምላ ግድያ ተፈፅሞበታል። ይህ አልበቃ ብሏቸው እህቶቻችንን ተፈጥሮ የለገሳቸውን የመውለድና የመባዛት መብት በመገደብ መካን አድርጎ
የሚያስቀር ክትባት እየሰጡ እንዳይዋለዱና ዘራቸው እንዳይቀጥል በማድረግ እህቶቻችን ልጅ ፍለጋ በየፀበሉ እንዲንከራተቱ አድርገዋል።
ይህ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል በአማራ ተወላጆች ላይ በዘረኛው ወያኔ ተፈፅሟል። ይህ ወንጀል እግዚአብሄር የሚፈርድባቸው እንዳለ
ሆኖ በአለም አቀፍ የዘር ማፅዳት ወንጀል የሚያስጠቅይ አደገኛ ወንጀል ነው። ይህንን አይነት ወንጀል ወያኔ በገዛ ህዝቡ ላይ ሲፈፅም ምን ያህል ጥላቻ ለህዝቡ እንዳለውና በርግጥም ከደደቢት
በረሃ ይዞ የመጣውን አማራን የማጥፋት ተልኮ በፍጥነት እየተገበረ መሆኑንም ያሳያል።
ከላይ እንደገለፅኩት በተፈጥሮ ከመባዛት በተጨማሪ በተፈጥሮ
የተሰጠን ሌላ መብት አለን። ይህውም ማንም ሰው እዚህ ቦታ ከዚህ ብሄር መወለድ እፈልጋለሁ ብሎ የተወለደ የለም ሁላችንም ኢትዮጵያ
ውስጥ ተወልደናል በተወለድንበት ሀገር ውስጥ ደግሞ የትኛውንም አይነት ዘርና ቋንቋ ይዘን መወለዳችን በተፈጥሮ የተሰጠን መብታችን
ነው። ማንም ሊከለክለን ወይም ሊሰጠን የማይችለው መብታች ነው። ሆኖም ግን ወያኔ ኢህአዴግ ይህንን ተፈጥሯዊ መብታችንን በመጋፋት
በዘርና በቋንቋችን እያጥላላ ዘራችንን እየጠቀሰ አማራ፣ ኦሮሞ እያለ ሲሰድበን ኖሯል። ትግሬ ከመሆን ውጪ በተይ አማራ ሆኖ መገኘት
ነፍጠኝነት ሆኗል። የፖለቱካ እስረኞች ሳይቀሩ አንተኮ አማራ ነህ ኦሮሞ ነህ እየተባሉ በዘራቸው እየተሰደቡ እንደሚደበደቡ ብዙዎች
ተናግረዋል። ወያኔ ይህንን ጠባብ አስተሳሰቡን ወደሌላው ብሄር ለማጋባት ብዙ ቢሞክርም አልተሳካም ወደፊትም አይሳካም ህዝቡ አንድ
ነው። ብሄር፣ ቋንቋ፣ ሀይማኖት ሳይለየው ለብዙ ዘመናት በመተሳሰብና በመከባበር አብሮ የኖረ ህዝብ ነው።
በአማራው ላይ የሚፈፀመው በደል ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም።
ያስገረመኝ! በቅርቡ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ’’ህዝበ አማራው’’ አማራ እንደሆነ እየታወቀ፣ ወያኔ ትግራይን ሲገነጥል ግዛቱን ለማስፋት
ሲል ህዝቡን እናንተ አማራ አይደላችሁም ትግሬዎች ናችሁ ተብለው በግድ ትግራዊነት የተቸራቸው የወልቃይት ጠገዴ ህዝቦች ኧረ እኛ
ትግሬ አይደለንም አማራ ነን ድንበራችንም ተከዜ ድረስ ነው ትግሬ እንጂ ተከዜ ድንበር ተሻግሮ አያውቅም ብለው የማንነት ጥያቄ አቀረቡ።
መንግስት ያለ መስሏቸው ኮሚቴ አቋቁመው ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ጥያቄያቸውን እስከ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ቢያቀርቡም፣
ኮሚቴዎቹ የገጠማቸው እስርና እንግልት ነበር። ህዝቡም ይህንንኑ አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ ቢያደርግም አይምሬው ወያኔ ያሰረውን አስሮ
የገደለውን ገድሎ የተሰጣችሁን ትግራዊነት ተቀብላችሁ ተቀመጡ ብሎት እርፍ አለው። ሰው የማንነት ጥያቄ ይዞ እንዴት ዝም ይላል ዝም
አይልም ትግሉም እንደቀጠለ ነው።
ወያኔ ብሄር የሚሰጠን እሱ የሚነጥቀን እሱ ሆኖ ሳለ የብሄር
ብሄረሰቦችን መብት ለማስከበር ነው የትግራይ ተወላጆች አጥንታችንን ከስክሰን ደማችንን አፍስሰን የታገልነው ምናምን እያሉ ይደሰኩሩናል
እነሱ እንደሚያስቡን ደንቆሮ መስለናቸው። መልክት ለወያኔዎችና ተላላኪዎቻቸው ለማንኛውም ዘረኝነት ለማንም አይበጅም፣ አሁን ጊዜው
በጣም እረፍዶባችኋል ሀገር ማስተዳደር ካቃታችሁ ቆይቷል። በአራተኛ ክፍል ተማሪ ጀነራሎች ሀገር ቀርቶ ቀበሌ አይመራም፣ የአንድ
ብሄር የበላይነትም ሆዳምነት ነው፣ እንደምታስቡትም ኢትዮጵያ አትፈርስም ህዝቡ ነቅቷል፣ ይበቃናል ትላላችሁ ብለን ታግሰን ነበር
አሁን ግን እኛ በቃ ብለናል ጊዜው ቀርቧል የሁላችን ቁጣ በያለንበት ገንፍሏል፣ ፅዋው ሞልቷል ሀገራችንን ነፃ የምትወጣበት ጊዜው
እውን ሆኖ በቅርብ ታዩታላችሁ። እንደምንፋረዳችሁም ማወቅ አለባችሁ ወንጀል ሰርቶ የትም መሰወር አይቻልም አለም አንድ ናት።
ዝምታ ወርቅ ነው ብሎ አንገቱን ደፍቶ ለ25 ዓመታት የተቀመጠውን
ህዝብ ቆስቁሰው ቆስቁሰው የተዳፈነውን እሳት አነደዱት። የማያዳፍኑት እሳት
በየአቅጣጫው ሲነሳ ወያኔ ማጣፊያው አጥሯት ግራ ገብቷታል። አንዴ መግለጫ አንዴ ምናምን ብታንጋጋም ግርግር ብትፈጥሩም
ጊዜው እረፍዷል። ለ25 አመት ታፍኖ ሲናቅና ሲሰደብ፣ ሲገዛ፣ ስትረግጡት የነበረው ህዝብ አሁን ባንድነት በቃ ብለን ተነስተናል
መመለሻ የለንም ጉድ ፈላብሽ ወያኔ የዘመናት ብሶት የወለደው .............. ብላችሁ ነበር አይደል ያኔ ስትገቡ አሁን ደግሞ
እኛ በተራችን ‘’የዘመናት ብሶት የወለደው የህዝብ ድምፅ የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት / ህወሀት/ ሲጠቀምበት የነበረውን የኢትዮጵያ
ህዝብ ራዲዮ ተቆጣጥሮታል’’!!! ብለን ሀገራችንን ነፃ የምናወጣበት ቀኑ እሩቅ አይደለም።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar