ወ/ሮ አዜብ መስፍን ለሕወሐት ማ/ኮሚቴ የመልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ምንጮች አስታወቁ። ከባለቤታቸው ህልፈት በኋላ በፓርቲው የነበራቸው ተሰሚነትና የበላይነት እየተሸረሸረ በመምጣቱና ከኤፈርት ሃላፊነታቸው በመነሳታቸው እንዲሁም ጓጉተውለት የነበረው የአዲስ አበባ ከንቲባነት ስልጣን በማጣታቸው፣ ተስፋ መቁረጥ ውስጥ በመግባታቸው ምክንያት ለፓርቲው የመልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ምንጮቹ አስረድተዋል። በተጨማሪ አዜብ ይተማመኑባቸው የነበሩት ሹማምንት ከስልጣን እየተገፉ ገሚሶቹም እስር ቤት መወርወራቸው እንዲሁም በስብሃት ነጋ ቡድን እየተወሰደባቸው ያለው ፖለቲካዊ የበላይነት መቋቋም ስለተሳናቸው ከፓርቲው በግዜው መሰናበት እንደመረጡ ከምንጮቹ መረዳት ተችሏል። አዜብ መስፍን ላቀረቡት የመልቀቂያ ጥያቄ ፓርቲው በቅርቡ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ያመለከቱት ምንጮች፣ አያይዘውም ጥያቄው ተቀባይነት ካገኘ አዜብ በሲውዲን ወይም አሜሪካ ቨርጂኒያ በገዙት መኖሪያ ቤት ጠቅልለው ሊገቡ እንደሚችሉ አመልክተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ጄ/ል ሳሞራ የኑስ ከኢታማጆር ሹመታቸው በማስነሳት በምትካቸው በቅርቡ ሌ/ጄ ተደርገው የተሾሙትን ጄ/ል ዮሃንስ ገ/መስቀልን ለመተካት መታቀዱን ምንጮች ጠቁመዋል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar