mandag 13. juli 2015

5ኛው የመድረክ አባል ተገደለ


 

  • 48
     
    Share
medrekመድረክ ባወጣው መግለጫ ከ2007 ምርጫ በሁዋላ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች የተገደሉ የመድረክ አባላት ቁጥር 5 ደርሷል። የኢህአዴግ አገዛዝ በደቡብና ኦሮምያ የሚፈጽማቸው ድብደባዎችና እስራቶች መጨመራቸውንም መድረክ ገልጿል።
በከፋ ዞን በግንቦ ወረዳ በአድዮ ካካ ምርጫ ክልል በጎጀብ ምርጫ ጣቢያ የመድረክ ምርጫ ታዛቢ/ወኪል ሆነው የሠሩት አቶ አሥራት ኃይሌ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ቅዳሜ ሰኔ 27 ቀን በተፈጸመባቸው አሰቃቂ ድብደባ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን የገለጸው መድረክ፣ ድብደባው የተፈጸመው ጎረቤቶቻቸውና ቤተሰባቸው ወደ ገበያ ሄደው በነበረበት ወቅት ነው።
አቶ አስራት ቦንጋ ከተማ 01 ቀበሌ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ብቻቸውን እያሉ ከረፋዱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ወደ ቤታቸው በመጡና ለጊዜው ማንነታቸው በትክክል ተለይቶ ባልታወቁ ሰዎች ጭንቅላታቸውን ተመትተው ራሳቸውን ከሳቱ በኋላ በተለያዩ የሰውነት አካሎቻቸው ላይ ዘግናኝ ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል። አቶ አስራት ወደ ጅማ ሆስፒታል ተወስደው በመታከም ላይ እያሉ ሰኔ 29 ቀን 2007 ዓ ም ህይወታቸው ማለፉን መድረክ ገልጿል።
የቃለሕይወት ቤተክርስቲያን እምነት ተከታይ የሆኑት የአቶ አሥራት፣ ሰኔ 30 ቀን ወደ መኖሪያቸው ቦንጋ ከተማ አስከሬናቸው የተመለሰ በሆንም፣ የቤተክርስያኑ አባላት ሲቀበሩ በቆዩበት የቀብር ቦታ ላይ የቀብር ሥነሥርዓታቸው እንዳይፈጸም ከኃላፊነታቸው ውጭ በጉዳዩ ጣልቃ በገቡትና የካፋ ዞን አስተዳዳሪ የአቶ አስራት መኩሪያ ወንድምና በከተማው የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ኃላፊ የሆኑት ቄስ መምህር ታፈሰ መኩሪያና በግንቦ ወረዳ ባለሥልጣናትና ፖሊሶች ተከልክሎ መቆየቱን ገልጿል።
ይሁን እንጅ ሕዝቡ ባቀረበው አቤቱታ ረቡዕ ሃምሌ 1 ቀን 2007 ዓ ም የሟቹ አስከሬን መቀበሩን መድረክ አክሎ አስታውቋል።
በካፋ ዞን የመድረክ ተወካይ የሆኑት አቶ አድማሱ አምቦና ሌሎች የዞኑ የፓርቲው አመራር አባላት ሁኔታውን ተከታትለው መረጃ እንዳያስተላልፉ በቢሮ ውስጥ እያሉ ከቢሮአቸው እንዳይወጡ ቢሮው በወታደርና በታጣቂዎች ተከቦ መቆየቱንና ስለሟቹ ማንነትና ስለግዲያው ሁኔታ የማጣራት ሥራ ለማከናወን የተቻለውም የቀብር ሥነሥርዓቱ ተፈጽሞ በመድረክ ጽ/ቤት ላይ ተደርጎ የነበረው ከበባ ከቆመ በሁዋላ መሆኑን ደርጅቱ አስታውቋል።
በኦሮሚያ በሁለት አባላት፣ በትግራይ በአንድ አባል እናንዲሁም በደቡብ በአንድ አባል ላይ ተማሳሳይ ግዲያዎች መፈጸማቸውን የፖለቲካ ድርጀቱ አስታውሷል።
በዚሁ ዞን በፈለገሰላም ወረዳ በጨታ ምርጫ ክልል በቦባ ቀበሌ የመድረክ የምርጫ ታዛቢ ወኪል የነበሩት አቶ ገረመው ቆዲ፣ የምርጫው ቀስቃሾች የነበሩት አቶ አሥራት ሻውአኖ፣ አቶ ገረመው ጋንአቾ እና የሾላይ ቀበሌ ታዛቢ ወኪል የነበሩት አቶ ገዛሃኝ ገንቢ እንደዚሁም በዴቻ ወረዳ ጭሪ ምርጫ ክልል የሚታ ቀበሌ ታዛቢ ወኪል የነበሩት አቶ ተክሌ ቆጭቶ ከሚያስፈሊጋቸውና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ማዳበሪያ እንዲገዙ በቀበሌው አመራሮች ታዘው ትዕዛዙን ለመፈጸም ባለመቻላቸው ተይዘው እንዲደበደቡና እንዲታሰሩ ተደርጓል።
በቤንች ማጂ ዞን ሸዋ ቤንች ወረዳ ደግሞ አቶ መኮንን ሚቱስ፣ አቶ ማሙር ሁሌት፣ አቶ ሉቃስ አለሙ፣ አቶ ቶሳ ሳቁያብ፣ አቶ ዘለቀ ታቹያብ፣ አቶ ሐሰን ዴሪያብ፣ አቶ ተስፋዬ ወ/የስ፣ አቶ ሳሙኤል ቸሪቲ፣ አቶ መላኩ ታርሳ፣ አቶ መንግስተ ሾዳ፣ አቶ ኬሪቲ ቡጢያብ፣ አቶ አድነው ወ/የስ እና አቶ አብርሃም ሳሙኤል የሚባሉ የመድረክ አባላት መስከረም ሲሲ በሚባል ቀበሌ ውስጥ ባለው ፖሊስ ጣቢያ ከአራት ቀን እስከ ሁለት ሳምንታት ያህል ጊዜ ታስረው ከቆዩ በኃላ ተለቀዋል፡፡ ባሎቻቸው እቤት ውስጥ ያልተገኙ 12 ሚስቶች ታስረው ከቆዩ በኃላ እንደተፈቱ ፓርቲው አስታውቋል።
በሸኮ ልዩ ወረዳ የፉዥቃ ቀበሌ ነዋሪና የመድረክ የምርጫ ታዛቢ የነበሩት አቶ ደርጀር ዲኩ እና አቶ ፀጋዬ ፉርጃ በወረዳው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ይገኛሉ። ደቡብ ኦሞ ዞን በማሊ ወረዳም እንዲሁ አቶ ታገሰ ቡርዝጋ፣ አቶ ቦት ቦርታ እና አቶ ነጌ ደምቤ የሚባሉ የመድረክ አባላት ለመድረክ ቅስቀሳ አካሄዳችሁ ነበር በሚል ውንጀላ ታስረዋል፡፡
በዚሁ ወረዳ የኩንታር ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ 26 አርሶ አደሮች የመድረክ ደጋፊና ቀስቃሾች ስለነበራችሁ የእርሻ መሬታችሁን ልቀቁ በመባላቸው በቀበሌው አመራር አባላት የእርሻ መሬታቸውን ተነጥቀዋል፡፡
በጋሞጎፋ ዞን በካምባ ወረዳ ደግሞ በመድረክ በኩል በምርጫው ወቅት የምርጫ ጣቢያ ወኪል/ታዛቢዎች ሆነው የሠሩት አቶ ግዛ ግብሳ እና አቶ ገጦሬ ገባሌ የተባሉ የግብርና ኤክስተንሽን ሠራተኞች ከሚያዚያ ወር 2007 ጀምሮ ከሥራና ከደመወዛቸው
የታገዱ ሲሆን፣ አቶ ሕዝቃኤል ፋንጌ እና መምህር አቴ አይሳ የተባሉት የመድረክ የክልል ም/ቤት ዕጩ ተወዳዳሪዎች ደግሞ የየካቲት ወርና ከሚያዚያ ወር 2007 ጀምሮ እስከአሁን ድረስ ያለው ደመወዛቸው በሥራ ላይ እያሉ ታግዶ ይገኛል፡፡
በወረደው ውስጥ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቁ በርካታ የመድረክ አባላትና ደጋፊ የሆኑ አርሶ አደሮችም ከአቅማቸው በላይ እንዲገዙ የተመደበባቸውን ማዳበሪያ በወቅቱ አልገዙም በሚል ሰበብ እስከ 1000 ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እየተጣለባቸው እንዲከፍሉ ተገደዋል ሲል ፓርቲው አስታውቋል።
በኦሮሚያ በጉጂ ዞን ዋመና ወረዳ አቶ ሮባ ገልቹ፣ በቦረና ዞን መልካ ሶዳ ወረዳ አቶ ጠደቻ አሬሮ፣ በምስረቅ ሻዋ ዞን ሞጆ ወረዳ አቶ ዝናቡ ዳምጤ የሚባሉ የኦፌኮ/መድረክ አባላት በየወረዳዎቻቸው ላለፉት ሁለት ሳምንታት ታስረው ይገኛሉ፡፡
በምሥራቅ ሸዋ ዞን ቦሰት ወረዳ ደግሞ አቶ አሸናፊ ነጋሽ፣ አቶ ለሚ እንዳለማው፣ አቶ ባብሣ ገመዳ፣ አቶ ጉዳታ ቢራ፣ ወ/ሮ ወይንሸት፣ አቶ እሸቱ ዲማ፣ አቶ አንበሳ ያኢ፣ አቶ ታምሩ ቁምቢ፣ አቶ ቀነኒ ደሜ እና ወ/ሮ ደምበልቱ ዳሜ የተባሉ የመደረክ አባላትና ደጋፊዎች የሆኑ 10 አርሶ አደሮች መኖሪያ ቤቶች በቀበሌው አመራሮች እንዲፈርሱ ተደርጓል፡፡ በምዕራብ ሸዋ ግንደበረት ወረዳ የኦፌኮ መድረክ አደራጅና በምርጫው ወቅት የመድረክ ቀስቃሽና ተዘዋዋሪ ታዛቢ የነበረው ተማሪ ጉቱ ሦሬም በምርጫው ቅስቀሳ ወቅት ያልተፈቀደ ስብሰባ አካሄደሃል በሚል መሠረተብቢ ክስ በጸጥታ ኃይሎች ተደብድቦ ታሥሮ እንደሚገኝ ፓርቲው የላከው መግለጫ ያመለክታል።
ከምርጫ 2007 በሁዋላ የተገደሉ የተቃዋሚ ድርጅት አባላት 6 ደርሷል።
Source:: Ethsat

-http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45021#sthash.gMFvpA72.dpuf

ሕግ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ መብታቸዉን ለማስከበር ፣ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ፣ ወንጀል ሳይፈጽሙ በዉሸት ክስ በወህኒ በግፍና በጭካኔ እየሰቃዩ ያሉ የአንድነት አባለት በጥቂቱ፡

ሕግ መንግስቱ በሚፈቅደው መሰረት ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ መብታቸዉን ለማስከበር ፣ ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ፣ ወንጀል ሳይፈጽሙ በዉሸት ክስ በወህኒ በግፍና በጭካኔ እየሰቃዩ ያሉ የአንድነት አባለት በጥቂቱ፡
1. አንድዋለም አራጌ ( ም/ፕሬዘዳነት)
2. ሃብታሙ አያሌው (የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሃላፊና የሚሊዮኖች ድምጽ ሰብሳቢ)
3. አለነ ማጸንቱ (የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል)
4. ዳንኤል ሺበሺ (የድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ ና የምክር ቤት አባል)
5. ፋንቱ ዳኜ (የኦዲት ኮሚቴ ሰብሳቢ)
6. ናትናኤል መኮንን (የምክር ቤት አባል)
7. አንድዋለም አያሌው (የምክር ቤት አባልል)
8. መላኩ ተፈራ (የምክር ቤት አባል)
9. ስንታየሁ ቸኮል (የአዲስ አበባ ምክር ቤት የወጣቶች ጉዳይ ሃላፍ)
10. ሃዲያ መሃመድ (የወላይታ ዞን አንድነት አመራር)
11. መሳይ ትኩ ( ፍቼ፣ ኦሮሚያ)
12. እስማኤል ዳዉድ ( የሚሊዮኖች ድምጽ ሪፖርተር)
13. አሻግሬ መንገሻ
14. ታመነ መንገሻ (መቱ፣ ኦሮሚያ )
15. በድሉ መንግስቱ (ቦረና፣ ኦሮሚያ)
16. ኮንጨራይ ሳፋይ (ቦረና፣ ኦሮሚያ)
17. ብርሃኑ ሳፋይ (ቦረና፣ ኦሮሚያ)
18. ሃብታሙ ገብረ ሚካኤል (ቦረና፣ ኦሮሚያ)
19. ምትኩ ገብረ ሚኤል (ቦረና፣ ኦሮሚያ)
20. ጥላሁን አበበ ( ደጋ ዳሞት፣ ጎጃም)
21. ሻምበል የሺዋስ ይሁን (ባህር ዳር፣ ጎጃም)
22. ኣንጋው ተገኝ (ሰሜን ጎንደር)
23. አባይ ዘዉዱ (አብርሃ ጅራ ጎንደር)
24. እንግዳው ዋኘው (አብርሃ ጅራ ጎንደር)
25. በላይነህ ሲሳይ (መተማ ጎንደር)
26. አለባቸው ማሞ (መተማ ጎንደር)
27. አለበል ዘለቃ ሃይማኖት አየና ( ውሮታው፣ ደቡብ ጎንደር)
28. ጸጋዬ ገበይየሁ (አርማጭሆ)
29. መምህርት ግዛው ( ሰሜን ጎንደር)
30. አውቀ ብርሃኑ (ጎንደር)

søndag 12. juli 2015

አርበኞች ግንቦት 7 የከፈተው ወታደራዊ ጥቃት ከወልቃይት ወደ አርማጭሆ በመስፋፋት እንደቀጠለ ነው

~የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት~ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ በህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት ላይ የከፈተው ወታደራዊ ጥቃት ከወልቃይት ወደ አርማጭሆ በመስፋፋት በእጅጉ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው፡፡ ዘረኛውና ፋሽስቱን የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ቡድን በጠብመንጃ አምበርክኮ ህዝቡን ብቸኛው የስልጣን ባለቤት የማድረጉ የትጥቅ ትግል ከኤርትራ በረሃዎችና ጠረፎች አልፎ በኢትዮጵያ መሬት ላይ በአስተማማኝ ሁኔታ እግሩን በመትከሉ ህወሓት ለእርድ ያሰናዳው ሰራዊት ከአርበኞች ግንቦት 7 አርበኛ ታጋዮች ብቻ ሳይሆን ከወልቃይትና አርማጭሆ ህዝብ በያቅጣጫው እየተከፈተበት የሚገኘውን ፋታ የሌለውና ጠንከር ያለ የተኩስ ናዳ ፈፅሞ መቋቋም አልቻለም፡፡ ከሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች በአውቶብስ እያጋዘ ሰሜን ኢትዮጵያ ላይ ያከማቸው መከላከያ ሠራዊቱ የአርበኞች ግንቦት 7 ጀግና የነፃነት ፋኖዎች ከህዝብ ጋር ተቀናጅተው ባልጠበቀው ጊዜና ሁኔታ የሚከፍቱበትን የጎሬላ ውጊያ ጥቃት ገና ካሁኑ መመከት ተስኖት ከጦር ሜዳ መሸሽ እና መክዳት በመጀመሩ ህወሓት እንደ ድጋፍ ሰጪም እንደተወርዋሪም የሚጠቀምባቸውን የፌደራል ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል፣ ፀረ-ሽምቅ እና ሚሊሻ ኃይሎችን በተጓዳኝ በገፍ አስፏል፡፡ መከላከያን ጨምሮ በእነዚህ ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች መካከል አለመረጋጋት እና በራስ አለመተማመን የወለደው የለየለት መተራመስ በመስፈኑ በህዝቡና በአርበኞች ግንቦት 7 የጎሬላ ተዋጊዎች እየደረሰባቸው ሚገኘውን ጥቃት ተቀናጅተው መመከት አልቻሉም፡፡ በመሆኑም ከትናንት በፊት ሀምሌ 3 2007 ዓ.ም ታች አርማጭሆ ጎደቤ ላይ ልዩ ኃይል እና ፀረ-ሽምቅ ጎራ ለይተው በመሰላለፍ እርስበርሳቸው ውግያ ውስጥ ገብተው በጥይት ተጠዛጥዘዋል፡፡ በእነኚህ ተስፋ የቆረጡ ሁለት የታጠቁ ኃይሎች መካከል በተደረገው ለሰዓታት የዘለቀ ውግያ በትንሹ ስድስት አባላት ሲሞቱ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል፡፡ የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ አርበኛ ታጋዮች ህወሓት በገፍ ያሰለፈውን የመከላከያ፣ ፌደራል ፖሊስ፣ ልዩ ኃይል፣ ፀረ-ሽምቅ እና ሚሊሻ ጦር መውጭያ መግቢያና ማረፊያ ነስተው ቁምስቅሉን ከማሳየታቸው ጎን ለጎን የድርጅቱን ህዝባዊ ዓላማ እና ፕሮግራም በበራሪ ወረቀት መልክ ከመተማ እስከ ጎጃም ለሚገኘው ህብረተሰብ በማድረስ ላይ ይገኛሉ፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/44988#sthash.e2LzGVJP.dpuf

lørdag 11. juli 2015

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ እስሩ ቀጥሏል – ሰማያዊ ፓርቲ

11028370_947380921971173_4082363779974687254_n
 12  0 
 Share0  12
የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ እስሩ ቀጥሏል
በአዲስ አበባና በየክፍለ ሀገሩ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ እስሩ ቀጥሏል፡፡ ትናንትናው ዕለት በሸዋ ሮቢት የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪዎች የሆኑት አቶ ዘነበ ደሳለኝ፣ አቶ መንግስቱ ተበጀ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሀብቴ እንዲሁም አዲስ አበባ ውስጥ አቶ ደብሬ አሸናፊ ታድነው የታሰሩ ሲሆን በዛሬው ዕለት አቶ መርከቡ ሀይሌና አናኒያ ኢሳያስ ለእስር ተዳርገዋል፡፡
መርከቡ ሀይሌና አናኒያ ኢሳያስ ዛሬ ሀምሌ 4/2007 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ አራት ኪሎ አካባቢ በፖሊስና ደህንነቶች ተይዘው ታስረዋል፡፡ እነ መርከቡ በተያዙበት ወቅት ፖሊስና ደህንነቶች ‹‹ብጥብጥ ልታስነሱ እየጣራችሁ መሆኑን ደርሰንበታል›› እንዳሉዋቸው ተገልጾአል፡፡ በተጨማሪም የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ስለሽ ደቻሳ ሀምሌ 1/2007 ዓ.ም ከቤቱ በደህንነትና በፖሊስ ታፍኖ ከፍተኛ ድብደባ ከተፈፀመበት በኋላ ታስሯል፡፡ ስለሽ ደቻሳ በተፈፀመበት ድብደባም እጅና እግሩ ላይ ስብራት እንደደረሰበት ታውቋል፡፡ በተጨማሪም የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢ የነበረው አስፋው ጀማል በትናንትናው ዕለት በፖሊስ ተይዞ መታሰሩን ምንጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ መርከቡ ኃይሌና አናኒያ ኢሳያስ በአራዳ ፖሊስ መምሪያ እንዲሁም ስለሽ ደቻሳ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ እንደታሰሩ ታውቋል፡፡
በተመሳሳይ እስሩ በየ ክፍለ ሀገሩን የቀጠለ ሲሆን በከፋ ዞን ጨላ ወረዳ 8 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ‹‹ማዳበሪያ አልወስድም ብለዋል›› በሚል ለእስር እንደተዳረጉ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በማዳበሪያ ሰበብ ድብደባ እየደረሰባቸው እንደሆነ የገለጹት የዞኑ የፓርቲው አስተባባሪዎች ነሲብ አደነ የተባለ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ከፍተኛ ድብደባ ደርሶበት ሆስፒታል ውስጥ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8587#sthash.u3Mgd3jO.dpuf

torsdag 9. juli 2015

Ethiopia frees journalists ahead of Obama visit – AFP








Addis Ababa (AFP) – Five bloggers and journalists held in Ethiopia for more than a year have been freed after the charges were dropped, their lawyer said Thursday, weeks before US President Barack Obama is due to visit the country.
In a separate case, journalist Reeyot Alemu, jailed in June 2011 after being found guilty of plotting a terrorist act, was released on Thursday, campaigners said.
Four others also arrested in April 2014 remain in jail, accused of planning attacks and collaborating with US-based opposition group Ginbot 7, labelled a terrorist organisation by Ethiopian authorities.
“They have suffered, their rights have been violated, but now we are happy,” defence lawyer Ameha Mekonnen told AFP after the five journalists and bloggers were released on Wednesday.
Ameha said the decision to drop the charges was unexpected.
“We are all surprised. The question is why did it take more than one year? We’ve been crying, shouting to the court, to the government,” he said.
The trial of the four remaining bloggers is due to resume on July 20.
Rights activists welcomed the releases but said more needed to be done.
“It’s very good news that six journalists and bloggers have been released, though they shouldn’t have been imprisoned in the first place,” said Leslie Lefkow, deputy director for Africa at Human Rights Watch.
“The government should show this is only a first step toward releasing all political prisoners and opening up space for Ethiopians to voice dissent on a range of issues.”
Tom Rhodes from the Committee to Protect Journalists (CPJ) called the release, “a welcome turn of events in Ethiopia, where the number of journalists in prison has steadily increased in recent years”.
“We call on authorities to release the remaining Zone 9 bloggers and all the journalists in jail for their work, and to drop all charges against them,” Rhodes said in a statement Thursday.
Reeyot Alemu, who won a UN press freedom prize in 2013, was originally sentenced to 14 years, reduced to five years on appeal.
– Dozen journalists remain in jail –
Rights groups have criticised Ethiopia’s anti-terrorism legislation for being vaguely worded and used to stifle peaceful dissent.
The CPJ said that at least 12 other journalists were still incarcerated, most facing terrorism charges, making Ethiopia the second-worst jailer of journalists in Africa, after its oppressive neighbour Eritrea.
Ethiopia is an ally of the West in the fight against Islamist extremism in East Africa, receiving millions of dollars in foreign aid, but has a dire record when it comes to human rights and press freedom.
In elections in May the ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) coalition, in power since the end of a civil war in 1991, and its allies won every seat in parliament.
Obama is due to visit Ethiopia later this month as part of an Africa tour that includes a trip to Kenya, where his father was born.
In Ethiopia, Obama is expected to meet Prime Minister Hailemariam Desalegn and address the African Union at its Addis Ababa headquarters.
In the unexpected move on Wednesday, state prosecutors dropped all charges against journalists Asmamaw Hailegiorgis, Edom Kassaye and Tesfalem Waldyes, and bloggers Mahlet Fantahun and Zelalem Kibret.
Four other members of Zone 9, a blogging collective, remain in jail while one other was charged in absentia.
“For us, there is no difference between the five released and the four still in jail. For them the case continues and we are ready,” said Ameha.
- See more at: http://www.satenaw.com/ethiopia-frees-journalists-ahead-of-obama-visit-afp/#sthash.SleoEPos.dpuf

tirsdag 7. juli 2015

አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ የሰነዘረውን ድንገተኛ ማጥቃት ተከትሎ ኃይለማርያም ደሳለኝ “ህዝብን አስፈቅደን ከሻብያ ጋር እንዋጋለን” አሉ

July 7, 2015
አርበኞች ግንቦት 7 በተለያዩ ግንባሮች በወያኔ ላይ የከፈተውን ማጥቃት ተከትሎ ከወያኔ ጎራ የተምታቱ ዜናዎች እየተደመጡ ነው።Ethiopian PM Hailemariam Desalegn on Al Jazeera
ቀደም ሲል የተሰነዘረባቸውን ጥቃት “ምንም ነገር የለም” ብለው ለማድበስበስ የሞከሩት የወያኔ ሹማምንትና ካድሬዎች ዜናው በኢሳት ቴሌቪዥን፣ ሬድዮ፣ በተለያዩ ድረ-ገጾች እና በዋንኛነት ደግሞ በማህበራዊ መገናኛ ገጾች በስፋት በመዘገቡ “ምንም ነገር የለም” ከሚለው ወደ ተምታታ ዜና ማሰራጨት ተሸጋግረዋል።
የወያኔዎቹ ቃል-አቀባይ ጌታቸው ረዳ በሚሚ ስብሃቱ ኤፍ ኤም ራድዮ ላይ ቀርቦ “በአካባቢው በመሬት የተነሳ መጠነኛ ግጭት ነበር” በማለት ሁኔታውን ከገለጸ በኋላ ወድያውም “በሻብያ ላይ የማያዳግም ቅጣት” ሊሰነዝሩ እንደሚችሉ ተናግሯል።
አይጋ ፎረም የሚባለውና በአፍቃሪ ወያኔነቱ የሚታወቀው ድረገጽ ደግሞ የመከላከያ ሰራዊቱ በሻብያ ተላኩ ያላቸውን ታጣቂዎች መማረኩን ዘግቧል።
አነጋጋሪ የሆነውና ምናልባትም አብዛኞችን ፈገግ ያደረገው ዜና ደግሞ ኣሻንጉሊቱ ኃይለማርያም ደሳለኝ ለአሻንጉሊቱ የተወካዮች ምክር ቤት ያደረጉት ንግግር ነው፣ “ህዝብን አስፈቅደን ከሻብያ ጋር ጦርነት እንገጥማለን” ነበር ያሉት ኃይለማርያም ደሳለኝ።
የወያኔ ሹማምንት ጥቃት እየሰነዘረባቸው ያለውን “አርበኞች ግንቦት 7ን” በስም ለመጥቀስ እጅግ የፈሩ ይመስላሉ።
አርበኞች ግንቦት 7ን በስም መጥቀስ ለምን ፈሩ? ብሎ ለሚጠይቅ መልሱ ቀላል ነው።
ህዝብ የአርበኞች ግንቦት 7 የነጻነት ታጋዮች ከአብራኩ የወጡ የቁርጥ ቀን ልጆቹ እንደሆኑ ያውቃል። ስለዚህም ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ጦርነት ልንገጥም ነው ቢሉ ማንም እንደማይተባበራቸው ይረዳሉ። ያላቸው እድል “ሻብያ” እያሉ መለፈፍ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝብ የጦርነትን አስከፊ ገጽታ ይገነዘባል ይሁንና የወያኔ አስከፊ ዘረኛ ስርዓት እያደረሰበት ካለው የመረረ ጭቆና ጋር በማነጻጸር ይመስላል አርበኞች ግንቦት 7 በወያኔ ላይ የሰነዘረውን ጥቃት በደስታ ነው የተቀበለው።
በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ ኢሳት ቴሌቭዥን በመደወል ደስታቸውን ሲገልጹና ለአርበኞቹም መልካሙን ሁሉ ሲመኙ ተደምጠዋል።

mandag 6. juli 2015

ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ስለላ ለማድረግ አንድ ሚሊዮን ዶላር ከፍላለች

ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ስለላ ለማድረግ አንድ ሚሊዮን ዶላር ከፍላለች
ኢትዮጵያ የኢንተርኔት ስለላ ለማድረግ አንድ ሚሊዮን ዶላር ከፍላለች
አፕሪል 18፣ 2012 ከሚላን የ”ሐኪንግ ቲም” ቢሮ የወጣው የክፍያ መጠየቂያ የተላከው ለኢንሳ (የመረጃ መረብ ደህንነት ኤጀንሲ)ነው። ክፍያው የተፈጸመለት ሐኪንግ ቲም መቀመጫውን ጣልያን ያደረገ የኢንተርኔት ስለላ መሣሪያዎችና አግልግልቶችን የሚሰጥ ድርጅት ነው።
ዜናው አክሎ እንደሚያተተው፣ ከመለስ ዜናዊ ሞት ከስምንት ወራት በኋላ ቢንያም ተወልደ የተባለ ግለሰብ ከመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ጋራ ግንኙነት ያላቸው ስምንት ዶሜኖችን (የድረ ገጽ ስያሜና አድራሻ፣ የኢሜይል አግልግሎት ወዘተ)አስመዝግቧል ወይም ገዝቷል። ይሁንና እነዚህ ዶሜኖች ድንገት መጥተው ድንገት መሰወራቸው፣ መጀመሪያውኑም የተከፈቱት ለኢንተርኔት ስለላው ሽፋን ለመስጠት እንደሆነ ያስጠረጠራል ተብሏል።
አቶ ቢንያም ተወልድ አፕሪል 4፣ 2013 ለሐኪንግ ቲም በጻፈውና ይፋ በወጣው ኤሜል “አንድ ትልቅ ዋጋ ያለው ኢላማችንን ልናገኘው ችልናል” ብሏል። ይህ ትልቅ ዋጋ አለው የተባለውና የኢሜል ስለላና ጠለፋው ሰለባ የሆነው አካል ማንነት ግን አልተገለጠም። አክሎም ከሐኪንግ ቲም የሚያገኘውን አገልግሎት ወይም ቴክኖሎጂ ከፍ ማድረግ እንደሚፈልግ ገልጿል። የሐኪንግ ቲም የኦፐሬሽን ማናጀር በበኩሉ፣ “ትልቅ ዋጋ ያለውን ኢላማችሁን ስላገኛችሁት ደስ ብሎናል” ሲል መልሶለታል። የአንድ ሚልዮን ዶላሩ የክፍያ መጠየቂያ ከተላከ ከዓመት በኋላ በሁለቱ ወገኖች መካከል ያለው ግንኙነት መቀጠሉ ክፍያው መፈጸሙን አመላካች ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል።
11665363_1590128881239287_7935362988087694071_n
11665363_1590128881239287_7935362988087694071_n
Source Wazema Aler
t
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8367#sthash.v5FQal9G.dpuf