torsdag 3. september 2015

በእስር ላይ የሚገኙ ሦስት የሰማያዊ አባላት በዓለም ላይ ከተመረጡ 20 የፖለቲካ እስረኞች መካከል ተካተቱ


 ሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪዎች የአንድ ወር ዘመቻ ያደርጉላቸዋል በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር በአሜሪካ መንግስት ኦፊሳላዊ ድረ ገጽ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አስተባባሪነት በዓለም ላይ ለተመረጡ 20 ሴት የፖለቲካ እስረኞች ለአንድ ወር የሚቆይ ዘመቻና ማስታወሻ ሊደረግላቸው ነው፡፡ ከ20ዎቹ ሴት የፖለቲካ እስረኞች መካከል ሦስቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ፣ ሁሉም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው፡፡ ከዛሬ 20 አመት በፊት ሴቶችን ለማብቃት፣ የጾታ እኩልነትን ለማስፈን እና የልጃ ገረዶችን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ የቤጂንግ መርሃ ጉዞ ተቀምጦ እንደነበር ይታወሳል፡፡ በእነዚህ 20 አመታት ልክ ከዓለም ሀገራት በፖለቲካ እስረኝነታቸው የተመረጡ 20 ሴት እስረኞችን ለማሰብ የሚደረገው ዘመቻ መነሻው ይህ መርሃ ጉዞ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ከኢትዮጵያ ብሌን መስፍን፣ ንግስት ወንዲፍራው እና ሜሮን አለማየሁ የተካተቱ ሲሆን ከቻይና እንዲሁ ሦስት ሴት የፖለቲካ እስረኞች ተመርጠው ይታወሳሉ፡፡ ከብዙ ሴት የፖለቲካ እስረኞች መካከል እነዚህ ጥቂቶች መሆናቸውን የጠቀሰው ድረ ገጹ በመስከረም ወር ‹‹ሴቶችን አብቋቸው፣ አትሰሯቸው!›› በሚል መርህ ዘመቻው ይደረጋል፡፡ በዚህም መንግስታት ሴቶችን በፖለቲካ አመለካከታቸው ማሰር አቁመው ማብቃት ላይ እንዲያተኩሩ መልዕክት ይተላለፍበታል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ዘመቻው ለታሳሪ ቤተሰቦችና ለራሳቸው ለታሳሪዎች ብቻቸውን እንዳልሆኑና እንዳልተዘነጉ ለማሳየት ታስቦ እንደሚካሄድ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ የሰጡት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ በኢትዮጵያ ሦስት ሴት የፖለቲካ እስረኞች በዚህ ደረጃ መጠቀሳቸው በሀገራችን ያለውን ስርዓት ዓለም እንደተረዳውና ኢትዮጵያ በመጥፎ እንድትነሳ እያደረጋት መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡ ዘመቻው እንዲደረግላቸው ከተመረጡት መካከል ከኢትዮጵያና ቻይና ሶስት ሶስት፣ ከቬትናም፣ አዘርባጃንና በርማ ሁለት ሁለት እንዲሁም ከኢራን፣ ግብፅ፣ ኤርትራ፣ ኡዝቤኪስታን፣ ቬንዞዌላ፣ ሶሪያ፣ ሩሲያ/ዩክሬንና ሰሜን ኮሪያ አንድ አንድ ሴት የህሊና እስረኞች ናቸው፡፡ - See more at:
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46394#sthash.c0DUxD3n.dpuf

tirsdag 1. september 2015

ቤኒሻንጉል ክልል በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ግድያ ተፈጸመባቸው

ethiopians-illegally-deported-from-benshangul-region-to-amhara-region-finote-selam-town-photo-addis-admass
 
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኙ የአማራ ተወላጆች ላይ የተቀነባበረ ጥቃት መሰንዘሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። ባለፈው ሚያዚያ ወር መጨረሻ ተፈጸመ በተባለው በዚሁ ጥቃት፣ ከ80 በላይ ሰዎች መገደላቸውንና በአንድ ቀበሌ ውስጥ የሚገኙ አማሮች ሙሉ በሙሉ የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን ዕማኞች ለኢሳት ገልጸዋል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወንበራ ወረዳ መልካ ቀበሌ ከሶስት ወራት በፊት በተፈጸመው በዚሁ ጥቃት 84 ሰዎች መገደላቸውን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ ግድያውም በጦር መሳሪያና በስለት ጭምር የታገዘ መሆኑን አስረድተዋል። ለቀናት አማሮች የሚደርስላቸው በማጣታቸው የተረፉት ንብረታቸውን ጥለው መሸሻቸውን ገልጸዋል።
ሚያዚያ 27 እና 28 ለሁለት ቀናት በወንበራ ወረዳ መልካ ቀበሌ ለቀጠለው ጥቃት መነሻው አንድ የአካባቢው ተወላጅ ባልታወቁ ሰዎች ተገደሎ መገኘቱ እንደሆነም ተመልክቷል።
በአማሮች ላይ በአካባቢው ባለስልጣናት ግፊትና ድጋፍ ለተቀነባበረውና ለቀጠለው ጥቃት የሚደርስ አካል በመታጣቱ፣ ሰለባዎቹ ለቀናት አደጋውን ሲጋፈጡ መቆየታቸውንም መረዳት ተችሏል።
ኢሳት ያነጋገራቸው ሁለት የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት የሟቾቹ አስከሬን የተሰበሰበው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከቀናት በኋላ ወደስፍራው ሲደርሱ ነው።
ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠሩ 10 ያህል ሰዎች የተያዙ ቢሆንም፣ ድርጊቱን በማቀነባበርና በመምራት ተሳታፊ የሆኑ ባለስልጣናት አለመጠየቃቸውን መረዳት ተችሏል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ወንበራ ወረዳ መልካ ቀበሌ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች በአብዛኛው ሲገደሉ፣ የቀሩት በመሸሻቸው በአሁኑ ወቅት በቀበሌው አንድም የአማራ ተወላጅ እንደማይኖር ለኢሳት ምስክርነታቸውን የሰጡ ወገኖች ገልጸዋል።
Source:: Ethsat
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/10083#sthash.3JXrU37K.dpuf

በጀኔራል ሳሞራ የኑስ እየተመራ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው ስብሰባ ያለመፍትሄ ተበተነ

September 1,2015
samora yunus
በጀኔራል ሳሞራ የኑስ እየተመራ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው የመከላከያ  ከፍተኛ አዛዦች ግምገማዊ ስብሰባ ያለመፍትሄ መበተኑን ለማወቅ ተችሏል።በመረጃው መሰረት- በአዲስ አበባ ከተማ በጀኔራል ሳሞራ የኑስ የተመራው የገዥው መንግስት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች ከነሃሴ 12 ቀን 2007 ዓ/ም ጀምሮ ሲካሄድ እንደቆየ የገለፀው መረጃው፤ የስብሰባው አጀንዳም መንግስት አዲስ የመከላከያ ሰራዊት አሰልጥኖ ይለቃል ወደ እናንተ ሲደርስ ግን በርካታው ሰራዊት ይጠፋል ምክንያቱ ምንድንነው? ስራችሁ ምንድንነው? የሚሉና ሌሎችም በመድረክ መሪው በሳሞራ የኑስ የቀረቡ ሲሆን በርካታዎቹ በተቃውሞ ድምፅ ስለተቃወሙት በመካከላቸው ልዩነት ተፈጥሮ ስብሰባው ያለ ፍሬ ነገር እንደተበተነ ለማወቅ ተችሏል።

መረጃው ጨምሮም- ግምገማው በከፍተኛ አዛዦች ዘንድ መረዳዳት ያልነበረው ስብሰባ እስከ ታች እዞች የወረደ ሲሆን በተለይ በሰሜን እዝ ከሚገኙ ሬጂመንቶች በሚጠናቀቀው አመት ብቻ በረከት ያለ ቁጥር ያላቸው ወታደሮች በመጥፋታቸው ዋና መነጋገሪያ አጀንዳ በመሆኑ አንዳንድ አዛዦች ከስራቸው ታግደው በመቐለ ስታፍ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

søndag 30. august 2015

ጎሳን ለይቶ የሚደረግ ጥቃትን ለማስወገድ መሰረታዊ ለውጥ ያሻል

 shengo 
አንድ መንግስት ልማታዊ ሊባል የሚችለው የሚመራውን ሕዝብ ከዃላ ቀርነትና ከድህነት አሮንቓ መንጥቆ ሲያወጣ፣የህዝቡን አንድነትና መልካም ግንኙነት ሲያጠናክር፣የአገርን ብሔራዊ ጥቅምና ዳር ድንበር ሲያስከብር ነው።
ሕዝብ በኑሮ ክብደት የሚሰቃይበትና የበይ ተመልካች በሆነበት፣ወጣቱ ተስፋ ቆርጦ ለስደት ሲዳረግና እግረመንገዱን ለተለያዩ አደጋዎች የሚጋለጥበት፣የጎሳ ስሜት ነግሶ አንዱ ሌላውን እንዲጠላና ሰላም እንዲናጋ፣ዜጋ ለዘመናት ከኖረበት ቦታና መሬት በሃይል እየተፈናቀለ እንዲበታተን የሚያደርግ ስርዓት ያሰፈነ ቡድን የሚመራው መንግስት ጥፋታዊ እንጂ ልማታዊ ተብሎ ሊጠራ አይገባውም።
የሕዝቡን መብት ገፎ፣የአገሩን ሃብትና ንብረት፣ለም መሬት ጭምር ለባዕዳን አሳልፎ እየሰጠ፣እየሸጠና ተባብሮ እየመዘበረ በውጭ አገር ባንክ የሚያካብት ቡድን ስልጣን ላይ ባለበት አገር ውስጥ ልማታዊ መንግስት አለ ብሎ ማመን ቀርቶ መናገሩ የስህተት ስህተት ነው።
ብሔራዊ ስሜትና የአገር ፍቅር፣ለራሱ ሕዝብ አክብሮት የሌለው ቡድን ኪራይ የሚሰበስብባቸው ታላላቅ ሕንጻዎች ስለሰራ፣የውጭ አገር ተባባሪዎቹን ለማስተናገድና ለመሳብ ሆቴሎችንና መንገዶችን በመገንባቱ ብቻ ልማታዊ ነው ብሎ መቀበልና ማስተጋባት ስለልማት ሁለንተናዊነት ሊኖር የሚገባውን ግንዛቤ ይጻረራል።ልማት በአጭሩ ሲተረጎም የሕዝብ ኑሮ መሻሻልን፣የሰብአዊ መብት መከበርን፣የዜጎችን ደህንነትና ሰላማዊ ኑሮ ዋስትና መኖርን፣የዴሞክራሲና የዜጎች መብት መረጋገጣቸውን ማሳየት ይኖርበታል።ሕዝብ በአገሩ ጉዳይ የማይመክርበት፣የማይወስንበት ሁኔታ ካለ ትርጉም የሚሰጥ ልማት ሊኖር አይችልም።ልማት ማለት የትቂቶችን ከርስ ሞልቶ ማደር ብቻ ሳይሆን በህዝብ ውስጥ የመንፈስ እርካታም ጭምር ሲኖር ነው።የአገር ዜግነትና ባለቤትነትም በተግባር ሲገለጽ ነው።
ይህ ከዚህ በላይ በጥቅሉ የቀረበው መንደርደሪያ የህወሃት/ኢሕአዴግን ፖሊሲወች ምንነት ለመግለጽ ከሚያስችሉት አንኳር ነጥቦች ጥቂቱ ሲሆን፣ሰሞኑን ደግሞ አንድ መንግስት አለ ተብሎ በሚገመትበት አገር ቀርቶ ወራሪ ጠላት በሚያስተዳድረው አገር ውስጥ እንኳን ይሆናል ተብሎ የማይጠበቅ ድርጊት፣ሰው ሰውን ቀቅሎ የሚበላበት ፈቃድና ድርጊት መፈጠሩ የስርዓቱን ምንነት በጉልህ ያሳያል።
ዛሬ በጉሙዝ ክልል ውስጥ በአማራነታቸው ተቀቅለው የተበሉት ወገኖች እንደ ወንጀል የተቆጠረባቸው ነገር ቢኖር በኢትዮጵያዊነታቸው የሚያምኑና ሁሉንም ማህበረሰብ እንደራሳቸው ቆጥረው አብረው ለመኖር መወሰናቸውና መኖራቸው ነው።
በጉሙዝ ክልል ውስጥ ለተፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት ሀገርን አሰተዳድራለሁ የሌለው ክፍል በቴሎቪዥን መስኮት ቀርቦ የአዞ እንባ ከማፍሰስ አልፎ ድርጊቱን የፈጸሙትን ሁሉ መንጥሮ እያወጣ በይፋ ለህግ ማቅረብ  ችግሩን በመሰረታዊነት ለመፍታት ደግሞ ከሁሉም ባለድርሻወች ጋር መወያየት ይኖርበታል፣ጉዳት የደረሰባቸውንም ወገኖቹን ለመካስና ተመሳሳይ አውሬያዊ አድራጎት እንዳይፈጸምባቸው ዋስትና ሊሰጣቸው ይገባል። በተጨማሪም ስርአቱ ሁሉም ዜጎች በሁሉም የኢትዮጵያ ምድር በክልሉ አስተዳደር ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንዲሳተፉ መብታቸውን ማክበርና ሁኔታውን ማመቻቸት ይኖርበታል።
ሸንጎ የአማራው ማህበረሰብን ጨምሮ በሁሉም ኢትዮጵያዊ  ላይ በተደጋጋሚ የሚደርሰውን ግፍና መከራ ሲያጋልጥና ሲያወግዝ ቆይቷል። ላለፉት ግፎች ምንም አይነት ሕጋዊና መሰረታዊ መፍትሔ ስላልተገኘላቸው አሁን የደረሰው ዘግናኝና አሳፋሪ ድርጊት እንዲከሰት ዕድልና በሩን የከፈተው በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ፖሊሲና ተግባር እንደሆነ በማመን ከማጋለጥ በላይ በዓለም አቀፍ ሕጋዊና  ሰብዓዊ መብት መድረኮች ላይ ጉዳዩን ለማቅረብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆኑን እየገለጸ በውጭ አገርና በአገር ውስጥ የሚገኙት ድርጅቶችና የሃይማኖት ተቋማት ድርጊቱን በማውገዝ ከሚጠቁት ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጎን እንዲሰለፍና አስፈላጊውን ዕርዳታና ድጋፍ እንዲለግሳቸው ለደህንነታቸውም ዋስትና በሚሰጠው መንገድ ሁሉ እንዲተባበር ጥሪ ያደርጋል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

torsdag 27. august 2015

መልዕክት በድሆች ድህነት ለመክበር መሯሯጥ ላይ ላሉ የዲያስፓራ ማኅበረሰብ አባላት !


August 27, 2015
def-thumbየግል ኑሮን ለማደላደል ሲባል የወያኔ አባል መሆን “ወይን ለመኖር” የሚል ስያሜ ከተሰጠው ዓመታት ተቆጥሯል። “ወይን ለመኖር” ዜጎች ነፃነታቸውን ለጥቅም አሳልፈው የሚሸጡበት፤ የሰው ልጅ ክብር የሚዋረድበት ገበያ ነው። በወይን ለመኖር “የገበያ ህግ” መሠረት እያንዳንዱ ዜጋ ሊያገኘው መብቱ የሆነውን አገልግሎት እንዲያገኝ የህወሓት፣ የብአዴን፣ የኦህዴግ፣ የደህዴግ፣ የአብዴፓ፣ የቤጉህዴፓ፣ የጋህአዴን፣ የሀብሊ ወይም የኢሶዴፓ አባል መሆን፤ አልያም መደገፍ ግዴታ ነው። እነዚህ ሁሉ ድርጅቶች የህወሓት ተቀጽላ ወያኔዎች ናቸው። የእነዚህ ድርጅቶች አባል ወይም ደጋፊ ያልሆነ እንኳስ የመንግሥት አገልግሎት ሊያገኝ ጥሮ ግሮ ያፈራውንም ይነጠቃል።
በዚህም ምክንያት፣ በገጠር ያለው አርሶ አደር ቁራጭ የእርሻ መሬት፣ የግብርና ባለሙያዎች የምክር እገዛ፣ የማዳበሪያና ዘር ግዢ፣ ብድር ወይም እርዳታ ለማግኘት በአካባቢው ባለ የወያኔ ድርጅት አባልነት መመዝገብ፤ አንድ ለአምስት መደራጀት እና የወያኔን የስልጣን እድሜ የሚያራዝሙ ነገሮችን መሥራት ይጠበቅበታል። በከተሞች ውስጥም ሥራ ለመቀጠር፣ ለደረጃ እድገት፣ የመኖሪያ ቤት (ኮንዶሚንየም) ለመግዛት ሲባል መወየን አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ ሆኗል:: በንግዱም ዘርፍ የንግድ ፈቃድ፣ የሥራ ቦታ እና የባንክ ብድር ለማግኝት፣ የመንግሥት ጨረታዎችን ለማሸነፍ፣ ከጉምሩክ እቃ ለማስለቀቅ፣ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት መወየን ግዴታ ነው።
“ወይን ለመኖር” የኢትዮጵያን ሕዝብ ያዋረደ፤ ለትውልድ የሚተርፍ የማኅበራዊ ስነልቦና ኪሳራ ያደረሰ እና ደካማውን ወያኔን ጠንካራ በማስመሰል በሕዝብ የትግል መንፈስ ውስጥ ፍርሃትን የረጨ መሆኑ ግንዛቤ እየዳበረ በመጣ መጠን እየቀነሰ የመጣ ክስተት ነው። በአሁኑ ሰዓት ከቀድሞው እጅግ በተሻለ ኢትዮጵያ ውስጥ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ራሳችንን ከህወሓት ባርነት እያላቀቅን ምሬታችንን በግልጽ መናገር የጀመርንበት ወቅት ነው፤ ከዚያም አልፎ የህቡዕ ተግባራዊ የትግል እንቅስቃዎችን ማድረግ ደረጃ ላይ ደርሰናል።
አገር ውስጥ እየተዋረደ የመጣው “ወይን ለመኖር” በአገዛዙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካይነት በውጭ አገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን (ዲያስፓራ) መካከል ነፃነታቸውን በጥቅም የሚለውጡ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ፍለጋ ተሠማርቷል። አገዛዙ ተስፋ ያደረገው ያህል ባይሆንም ጥረቱ የተወሰነ ውጤት እያስገኘለት ነው። በጥቅማ ጥቅም እየደለለ ካመጣቸው ውስጥ በስርዓቱ ብልሹነት ያዘኑና የተሰማቸውን በግልጽ የተናገሩ መኖራቸው የሚያስደስትና የሚያበረታታ ቢሆንም ከመንደር ካድሬዎች ባነሰ ተለማማጮችና አጎብዳጆች በማየታችን ተሸማቀናል። ኢትዮጵያ ውስጥ ካለነው አብዛኛው ሕዝብ አንፃር ሲታይ በተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ዲያስፓራዎች መካከልም ነፃነታቸውን በጥቅም ለመለወጥ የሚፈቅዱ መገኘታቸው አሳዛኝ ነው። እነዚህ ክብራቸውን በጥቅም የለወጡ ዲያስፓራዎች ዓለም ባንክንና የዓለም የገንዘብ ድርጅትን (IMF) ተክተው ህወሓት ስላስገኘው ፈጣን እድገት በአገዛዙ ራድዮ እና ቴሌቪዥን ሲነግሩን መስማት ያሳፍራል። የህወሓት አገዛዝ “ፍትህን፣ መልካም አስተዳርንና ዲሞክራሲን አስፍኗል፤ ይህንንም መጥተን በዓይኖቻችን ተመልክተናል” እያሉ የግፉን ገፈት እየቀመስን ላለነው ሲነግሩን መስማት ያማል።
እነዚህ ወገኖቻችን ህወሓትን በማሞካሸት የሚያገኙት መሬት ብዙ ድሆች የተፈናቀለቡት፤ ለእነሱ በብላሽ የተሰጠው ብድር በረሃብ ለሚጠቃ ወገን የተላከ እርዳታ መሆኑ ማሳሰብ ይገባል። ከህወሓትና አጫፋሪዎቹ ጋር ተስማምተው ባገኙት ገንዘብ የሚቆርሱት እያንዳንዱ እንጀራ የብዙ ወገኖቻችን ደምና እንባ የፈሰሰበት መሆኑ ማስገንዘብ ያሻል። ከህወሓት ጋር በማበር በወገኖቻችን ድህነትና ችጋር እየከበሩ ያሉ የዲያስፓራ ማኅበረሰብ አባላት ከዚህ እኩይ ሥራቸው እንዲታቀቡ ማስጠንቀቅ ይገባል። እኚህ ወገኖች የራሳቸው ክብር ማጉዳፋቸውን ብቻ ሳይሆን የልጅ ልጆቻቸውም የሚያፍሩባቸው መሆኑን ማስታወስ ይገባል። ከዚህም አልፎ የዛሬ ተግባራቸው ነገ በህግ የሚያስጠይቃቸው መሆኑን ሊያውቁ ይገባል።
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የአገዛዙን እድሜ በማራዘም ላይ የተሰማሩ፤ በድሆች ድህነት ለመክበር በመሯሯጥ ላይ ያሉ፤ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለአገዛዙ ጥብቅና የቆሙ የዲያስፓራ አባላት ከዚህ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ያሳስባል።
አርበኞች ግንቦት 7 “ከህወሓት ውድቀት በኋላ ያለው ጊዜ ለእናንተም ከዛሬው የተሻለ ይሆናል። ዛሬ ከህወሓት ጋር ያላችሁን ሽርክና አቋርጡ። ለነፃነት የሚደረገውን ትግል እርዱ፤ መርዳት ባትችሉ እንቅፋት አትሁኑ፤ አለበለዚያ ግን ከተጠያቂነት የማታመልጡ መሆኑን እወቁ” ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!! !

onsdag 26. august 2015

ከ50 የማያንሱ የመኢአድ የአመራር አባላት በወያኔ ታሥረዋል

aeup-logo-


ቁጥር 001
ቀን 29/10/2007 ዓ.ም
ለሚመለከተው ሁሉ
ጉዳዩ፡- በእስር ላይ ስላሉ አመራና አባላትን ይመለከታል፡፡
የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ጥቅምት 28-30/2007 ዓ.ም በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠው አመራር በምርጫ ቦርድ እውቅና ተነፍጎት ለሁለተኛ ጊዜ ጥር 3/2007 ዓ.ም ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ በምርጫ ቦርድ አስገዳጅነት ሁለት ጊዜ ጉባኤ አካሂዷል፡፡ ሁለተኛውም ተቀባይነትን ተነፍጎ ፕሬዝደንቱን አቶ ማሙሸት አማረን ጨምሮ በፖሊስ ኃይል አመራርና አባላቱ ከመኢአድ ጽ/ቤት በግፍ እንዲወጣ ተደርጓል በምትኩ ጠቅላላ ጉባኤ ያልመረጠው የሥርዓቱ አገልጋይ የሆነው አቶ አበባው መሐሪ ለተባለ ግለሰብ ጽ/ቤቱን በምርጫ ቦርድ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተረክቧል፡፡
ይህ ከጽ/ቤቱ በፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲወጣ የተረገው አመራር እና አባላት በመላ ሀገሪቱ በልዩ ልዩ እስር ቤቶች ታስረው ይገኛሉ፡፡ የአብዛኞቹም አመራርና አባላት ያሉበት ሁኔታ እጅግ አሳስቦናል፡፡
ስለዚህ በስም የጠቀስናቸው 37 (ሰላሳ ሰባት) አመራርና አባላት እንዲሁም በስም ያላወቅናቸው የእነ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን የክስ መዝገብ ሥር የተከሰሱ ሰዎች በእነ ዘመነ ካሴ የክስ መዝገብ ሥር 5 (አምስት) ሰዎች ስላሉበት ሁኔታ በእናንተ በኩል አስፈላጊውን ክትትል ታደርጉ ዘንድ እናሳስባለን፡፡
ከሠላምታ ጋር
በእስር ላይ የሚገኙ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)
አመራር አባላት ስም ዝርዝር
ተ.ቁ ስም ዝርዝር የመኖሪያ አድራሻ አካባቢ ክ/ሀገር በፓርቲ ውስጥ የነበረው ኃላፊነት ታስረው ያሉበት እስር ቤት የታሰሩበት ጊዜ
1 ማሙሸት አማረ አዲስ አበባ ሊቀ መንበር ቅሊንጦ ግንቦት 5/2007 ዓ.ም
2 ዘመነ ምህረት ሰ/ጎንደር/ማክሰኝት/ ም/ሊቀ መንበር ቅሊንጦ ጥር 10/2007 ዓ.ም
3 አብርሃም ጌጡ አዲስ አበባ የውጪ ግንኙነት አ.አ ፖሊስ ኮሚሽን 3ኛ ፖሊስ ጣቢያ ሰኔ 12/2007 ዓ.ም
4 ኢያሱ ሁሴን አላማጣ ማህበራዊ ዘርፍ አላማጣ ህዳር/2007 ዓ.ም
5 ዘመነ ጌጤ አዲስ አበባ የወታት ማህበራዊ ዘርፍ ቅሊንጦ ሚያዚያ/2007 ዓ.ም
6 በላይ ዳኘው አላማጣ አባል /አላማጣ/ ቅሊንጦ
7 ሞላ መለሰ አላማጣ አባል /አላማጣ ቅሊንጦ
8 ጥጋቡ ሙላት አላማጣ አባል /አላማጣ/
9 ጥላሁን አድማሴ ጎንደር አባል /ጎንደር/
10 ጌትነት ደርሶ ጎንደር አባል /ጎንደር/ ቅሊንጦ
11 ጥላሁን አበበ ጎንደር አባል /ጎንደር/
12 መለሰ ሰጠኝ ጎንደር አባል /ጎንደር/ ቃሊቲ
13 አስራት እሸቴ ሰሜን ሸዋ አባል /ሰሜን ሸዋ/ ቅሊንጦ መስከረም/2007 ዓ.ም
14 ተስፋዬ ታሪኩ ጎጃም አመራር /ጎጃም/ ቅሊንጦ መስከረም/2007 ዓ.ም
15 ፻አለቃ ጌታቸው መኮንን ጎጃም አመራር /ጎጃም/ ቅሊንጦ
16 ኢንጂነር መለሰ ሰጤ ጎጃም አባል /ጎጃም/ ቃሊቲ ግንቦት/2003 ዓ.ም
17 አናጋው ተገኘ ጎጃም አባል /ጎጃም/
18 አባይ ዘውዱ ጎጃም አባል /ጎጃም/
19 እንግዳው ዋኘው ጎጃም አባል /ጎጃም/
20 በላይነህ ሲሳይ ጎጃም አባል /ጎጃም/
21 አለባቸው ማሞ ጎጃም አባል /ጎጃም/
22 ታጀበ አለኸኝ ጎጃም አባል /ጎጃም/
23 ዮሐንስ ገደቡ ጎጃም አባል /ጎጃም/
24 አዝመራው ከፍአለ ጎጃም አባል /ጎጃም/
25 ተስፋዬ አስማረ ጎጃም አባል /ጎጃም/
26 ችሎት ጎበዜ ጎጃም አባል /ጎጃም/
27 መለሰ መንገሻ አዲስ አበባ የወጣት ድርጅት ጉዳይ ቅሊንጦ ጥር/2007 ዓ.ም
28 ሞገስ አሰፋ ደሴ አባል ደሴ ሰኔ/2007 ዓ.ም
29 ዘሪሁን በሬ አባል ቅሊንጦ ያልታወቀ
30 አወቀ ሞኝሆዴ አባል ቅሊንጦ ያልታወቀ
31 አማረ መስፍን አባል ቅሊንጦ ያልታወቀ
32 አትርሳው አስቻለው አባል ቅሊንጦ ያልታወቀ
33 አግባው ሰጠኝ አባል ቅሊንጦ ያልታወቀ
34 ወርቅየ ምስጋና አባል ቅሊንጦ ያልታወቀ
35 ቢሆነኝ አለነ አባል ቅሊንጦ ያልታወቀ
36 ታፈረ ፋንታሁን አባል ቅሊንጦ ያልታወቀ
37 ፈረጀ ሙሉ አባል ቅሊንጦ ያልታወቀ
38 አሸናፊ አካሉ ጎንደር አባል ቅሊንጦ 2005 ዓ.ም
39 ደህናሁን መአዛ ጎንደር አባል ቅሊንጦ 2005 ዓ.ም
40 ምንዳዬ ጥላሁን ጎንደር አባል ቅሊንጦ 2005 ዓ.ም
41 አንሙት የኔዋስ ጎንደር አባል ቅሊንጦ 2005 ዓ.ም
42 መንግስቱ አስቻለ ጎጃም አባል ቅሊንጦ 2005 ዓ.ም
43 በላቸው አወቀ ጎጃም አባል ቅሊንጦ 2005 ዓ.ም
44 መምህር ስማቸው ምንይችል ጎጃም አባል ያልታወቀ 2007 ዓ.ም
45 አበባዉ አያለዉ ም/ጎጃም አባል ባሕር ዳር
46 ብርሀኑ ካሳሁን ም/ጎጃም አባል ያልታወቀ ያልታወቀ
47 ብችል ቀሪ ባሕር ዳር አባል ያልታወቀ ያልታወቀ
48 ቴዎድሮስ አያለዉ ሰ/ወሎ አባል ዝዋይ ያልታወቀ
49 እዳልካቸዉ መለሰ ሰ/ወሎ አባል ዝዋይ ያልታወቀ
50 ማንደፍሮ አካልነዉ ላሊበላ አባል ዝዋይ ያልታወቀ
ለገሰ ወ/ሐና
የመኢአድ ም/ሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ

[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/9898#sthash.pakcqJD3.dpuf

mandag 24. august 2015

የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላት “የተቃዋሚዎች ሬድዮ ታዳምጣላቹ በሚል እየታሰሩ ነው

11899854_458103757685979_3718763112024142931_n
በገዢው ስራዓት የመከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ባለው ሰፊ የዓመቱ ግምገማ “የተቃዋሚዎች ሬድዮ መስማት” እንደዋነኛ መገምገሚያ ነጥብ ሆኖ መነሳቱን ተገለፀ።በምንጮቻችን መረጃ መሰረት- በሁሉም የስርዓቱ መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እየተካሄደ ያለውን መጠነ ሰፊ የዓመቱ ግምገማ ወታደሩ ያለማቋረጥ እየፈረሰ በመጥፋት ላይ ያለው የትጥቅ ትግል እያካሄዱ በሚገኙ ድርጅቶች የሚሰራጨውን ሬድዮ መስማት ዋናው ከሆኑ ምክንያቶች አንዱ ስለሆነ ለምን ታዳምጣላችሁ፤ እነማን ናቸው የሚያዳምጡት መታወቅ አለባቸው በማለት እየተካሄደ ባለው ስብሰባ የሰራዊቱ አዛዦች ራሳቸው የስብሰባው መሪዎችና ገምጋሚዎች ሆነው በመቅረብ ለበርካታ የሰራዊቱ አባላት እያባረሩና እያሰሩ መሆናቸው ተገልጿል።
በተለይ በሰሜን እዝ እየተካሄደ ባለው የዓመቱ ግምገማ ላይ የሰራዊቱ አባላት ሓቀኛና ገምቢ ግምገማ ነው ብለው ስላላመኑበት ማንኛውም ሃሳብ ከመስጠት እንደተቆጠቡና የስርዓቱ ተጠቃሚዎች የሆኑት የበላይ መኮነኖች “እዚህ የተሰበሰብነው ሰራዊቱ አንዣቦበት ካለው የመበታተን አደጋ ለማዳን ስለሆነ የተቃዋሚዎች ሬድዮ ለምን ትሰማላችሁ ብለው ላቀረቡት ሃሳብ በተሰብሳቢዎቹ ማንኛውም ሚድያ መከታተል የዜጎች ህገ መንግስታዊ መብት ነው” ብለው የተቃወሙትን የናንተ አመለካከት ከተቃዋሚዎች ጎራ ነው በማለት እንድፋሰርዋቸው መረጃው ጨምሮ አስርድቷል።
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/9822#sthash.qvLwE9KZ.dpuf