March 4,2015
ቐሺ ሕሉፍ ኸሕሳይ ይባላሉ። በምዕራባዊ ዞን ቓፍታ ሑመራወረዳ በረኸት ከተማ(ቀበሌ) ኑዋሪ የሆኑት የዓረና-መድረክኣባል ናቸው።በፎተው እንደሚታዩት የዓረና-መድረክ ኣባልበመሆናቸው ብቻ ይህ ዘግናኝ ድብደባ ደርሶባቸውሂወታቸው ልታልፍ ምንም ኣልቀረላቸውም ነበር። ይህድብደባ በ17/ 2007ዓ/ም ማታ 1 ሰዓት ኣከባቢ በ1ፖሊስድምብ ልብስ የለበሰ፣ 1 የፈጥኖ ደራሻ ደንብ ልብስ የለበሰ፣ 1የመከላከያ ደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች ከለላነት ተደብቆ የነበረሰው በድንጋይ ደጋግሞ በመደብደብ ለዚህ ኣደጋ እንዲዳረጉኣድርገዋል።
3ቱ የታጠቁ ሰዎች ሰው እርዳታ እንዳያደርግ የተከላከሉሲሆን ደብዳቢውም በቁጥጥር ስር እንዳይውል ከፍተኛ ከለላሰጥተዋል።ቐሺ ሕሉፍ ኻሕሳይ በክረምት 2006 ዓ/ምበቀበሌው ህዝብ ፊት ቀርበው "..ይህ ሰውየ ዓረና ነው፣በቤታቹ ቃጠሎ እንዳያደርስባቹ፣ እንዳይሰርቃቹ.." ወዘተየመሳሰሉ የስም ማጥፋት ዘመቻና ማስፈራርያ ከሌሎች3 የዓረና ኣባላት ጋር ደርሶባቸው ነበር።ኣቶ መዓሾ ኣስመላሽ የተባለ የቀበሌ ኣመራርምሰበካ ጉባኤ(የቤተክርስትያን ሃላፊዎች) በመሰብሰብ "...ቐሺ ሕሉፍ በዓረናነት ስለተጠረጠረ እንዳይቀድስ .." የሚል ትእዛዝ ባስተላለፈውመሰረት ከቅዳሴ ታገዱ።
ቐሺ ሕሉፍ የካድሬው እገዳ ተከትለው ወደ ቀበሌው ፖሊስ ኣቤቱታ በማሰማታቸው የቅስና ምስክር ወረቀታቸው እንድያመጡ በታዘዙትመሰረት ምስር ወረቀታቸው ለፖሊስ በማስረከብ ፍትህ እንዲያገኙ ጥረት ኣደረጉ።
ፖሊስም በተረዋ ምስክር ወረቀታቸው ለሁለት ሳምንት ይዞ ያለ ምንም መፍትሄ ኣቆየባቸው።
የምስክር ወረቀቱ ለማስመለስም ተጨማሪ ክስ ኣስፈለጋቸው። ፖሊስ በስንት ውጣ ውረድ ወረቀታቸው የመለሰላቸው ሲሆን ከዚህ በሗላምስንት ዛቻ ደረሳቸው።
ዘግናኝ ድብደባ የተፈፀመባቸውም ከዚህ ሁሉ ውጣ ወረድና ማንገላታት በሗላ ነበር። ህግ ባለበት ሃገር የሰው ልጅ እንዲህ ተቀጥቅጦ ይጣላልእንዴ...?
እነዚህ ለለውጥ ብለው የተሰዉ 60 ሺ ሰማእታት፣ 100 ሺ ኣካል ጉዳተኞች ውጤታቸው መሆን የነበረበት ይህ ነው...? በጣም ሗላቀርናህወሓት ታግየ ጣልኩት ካለቸው ደርግ በእኩልነት የሚያስመድባት ኣፀያፊ ተግባር ነው። በትግራይ የዓረና መድረክ ኣባል መሆን ይሄ የመሰለመስዋእትነት ያስከፍላል።
በሉ ያገራችን ሰዎች ..! ታፍሩበት ትኮሩበት ዘንድ ይሄውላቹ የኛ ዲሞክራሲ፣ የኛ ፍትህ፣ የኛ ነፃነት።
ይህ ኣስቃቂ ተግባር ሁሉም ዜጋ ሊቃወመው ይገባል።
ነፃናታችን በእጃችን ነው..!
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar