fredag 18. september 2015

ህወሃት ጦርነት ጀመረ፣ ቁስለኞች ታይተዋል


“ሕዝብ አስፈቅደን ውጊያ እንጀምራለን” ሃይለማርያም
omhajer


በነጻ አውጪ ስም አገር እየገዛ ያለውን የትግራይ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሃትን) ለመውጋት ብረት ያነሳው ሌላ የትግራይ ነጻ አውጪ ሃይል /ትህዴን ወይም በትግሪኛ ዴምህት/ መሪ የነበረው “ተጋዳላይ” ሞላ አስገዶም ህወሃትን ከተቀላቀለ ጥቂት ቀናት በኋላ ጦርነት መጀመሩ ተሰማ። የህወሃት ወኪል ሃይለማርያም ደሳለኝ ውጊያው የሚጀመረው የህዝብ ፈቃድ ተጠይቆ እንደሚሆን ተናግረው ነበር።
የጎልጉል መረጃ አቀባዮች ከአዲስ አበባ እንደገለጹት ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ቁስለኞች እየገቡ መሆኑንን እማኞች ነግረዋቸዋል። ጦርነቱ በየትኛው መንደርና ወረዳ እንደተጀመረ ለይተው ያላስረዱት የዜናው ባለቤቶች፣ ውጊያ እየተካሄደ ያለው ኤርትራ ምድር ላይ እንደሆነ ግንአልሸሸጉም።
አንድ የሆስፒታል ሰራተኛ ዘመድ ደውሎላቸው “ቁሰለኞች አሉ ሥራ በዝቶብኛል” ማለታቸውን የጎልጉል መረጃ ሰጪዎች ከአዲሰ አበባ ገልጸዋል። ባለፈው ሳምንት በሁመራ አቅጣጫ የከባድ መሳሪያ ተኩስና ድብደባ መሰማቱን የተለያዩ ድረገጾች ዘግበው ነበር። ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ሻእቢያ “ህወሃት ሊወረኝ ነው” ሲል ክስ ማሰማቱ አይዘነጋም።
ኦምሃጀር በሚባለው ስፍራ የከረረ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን እንደሰሙ የገለጹ በውጊያው የትኛው ወገን ድል እንደተቀዳጀ ለጊዜው መናገር እንደማይቻል አመልክተዋል። ውጊያው ጠርዙን አስፍቶ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።
four front mapከህወሃት በኩል ውጊያው ከሻዕቢያ ጋር እንደሆነ ቢገለጽም ከሌላ ወገን “ህወሃትን የወጋሁት እኔ ነኝ” ባይ ይህ ዜና እስከታተመ ድረስ አልተሰማም። የአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ ህወሃትን በነፍጥ አንበረክካለሁ በማለት ማወጁና አመራሮቹም ወደ ውጊያው አውድ ማምራታቸው ይታወቃል። ህወሃት ኤርትራን በአራት አቅጣጫ የመውጋት እቅድ እንዳለው ጎልጉል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በርካታ የሰራዊቱ አባላት ከሰራዊቱ እየሸሹና እየተሰወሩ መሆናቸው ህወሃትን እንዳሳሰበው፣ ጦሩ የመዋጋት ፍላጎት ያጣል የሚል ሥጋት እንዳለ የሚጠቁሙ ክፍሎች “የአሁኑ የውጊያ አቅጣጫ በዚህ መልኩ እንዲሆን መደረጉ ይህንኑ ለመፈተንም ጭምር ነው” ብለዋል።
በሌላ ዜና በሶማሌ ያለው ሰራዊት የመመለስ ጥያቄ ማንሳቱና ሁለት ጄኔራሎች ጦሩን ለማወያየት ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ስፍራው አቅንተው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። ጦሩ መስዋዕትነት እየከፈለ በተደጋጋሚ የተቆጣጠረውን ቦታ እንዲለቅ ትዕዛዝ ሲቀበል መቆየቱ ሌላው የቅሬታው መነሻ ሲሆን በሶማሌ ያለው የሰላም አስከባሪ ሃይል ይህንኑ ነቅፎ መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል። በህወሃት የሚመሩት የኢህአዴግ ባለስልጣናት በሶማሌ ስለተገደሉት ወገኖች መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸው፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ይህንን አክርረው አለመጠየቃቸው፣ ላለፉት አምስት ዓመታት 99.6 በመቶ ህወሃት የነገሰበት ማኅበርም (ፓርላማ) ለይስሙላ እንኳን ጥያቄ አቅርቦ እንደማያውቅ በርካቶች የሚተቹበት አገራዊ ጉዳይ ነው።

ከጎልጉል የተወሰደ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar