mandag 30. mai 2016

መንግስት የ12ኛ ክፍል ፈተናው መሰረቁን አምኖ ዛሬ ሊሰጥ የነበረው ብሔራዊ ፈተና እንዲቋረጥ አደረገ

      



fetena2
(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ባለፉት 4 ወራት በነበረው የሕዝብ ተቃውሞ ተማሪዎች በአግባቡ ትምህርታቸውን ሳይማሩ ቀርተዋል:: ይህን ተከትሎም ያልተምሩትን እንዳይፈተኑ; ለፈተናም በቂ ዝግጅት ባለማድረጋቸው እንዲራዘም ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ቢያቀርቡም ጥያቄው ውድቅ በመደረጉ በስርዓቱ ውስጥ ያሉት የውስጥ አርበኞች ተቃውሟቸውን ለማሳየት ፈተናውን በኢንተርኔት ለቀውት ነበር::
shiferaw-shigute
ትናንት የትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ “የተሰረቀ ፈተና የለም; ብሔራዊ ፈተናው በታሰበለት እና በታቀደለት ጊዜ ይካሄዳል” ቢሉም ፈተናው ግን በሶሻል ሚድያዎች መራባቱን ቀጥሎ ነበር:: ዛሬ ጠዋት እንደገና እኚሁ የትምህርት ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ “እንደማንኛውም ሰው ፈተናው በኢንተርኔት ቀድሞ መበተኑን አይቻለሁ” በሚል ፈተናው እንዲቋረጥ መታዘዙን አስታውቀዋል::
ፈተናው ከመቋረጡ በፊት ዛሬ ጠዋት የተወሰኑ የትምህርት ዓይነቶች ፈተና ተስጥቶ እንደነበርም ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል::
እንደ አቶ ሽፈራው ገለጻ በሃገሪቱ 800 የፈተና ጣቢያዎች እንዳሉና ከየትኛው ቦታ ተሰርቆ እንደወጣ መንግስት የሚጣራ ይሆናል::

One Response to መንግስት የ12ኛ ክፍል ፈተናው መሰረቁን አምኖ ዛሬ ሊሰጥ የነበረው ብሔራዊ ፈተና እንዲቋረጥ አደረገ

  1. በዚህ ምክንያት ብዙ ኪሳራ እንሚደርስ መንግስት ማስተዋል አለበት

tirsdag 17. mai 2016

አዲስ አጭር መረጃ ስለታላቁ የነጻነት ታጋይ አንዳርጋቸዉ ጽጌ!!

በመላዉ ኢትዮጵያዊያን ልቦና ዉስጥ ሰርጾ መግባት የቻለና የማይበርድ የትግል ምእራፍን በመንደፍ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ነጻነትን የቀለመ አባት ነዉ ! እ.ኤ.አ በግንቦት ወር /2014 የየመን ዋና ከተማ ሰናአ ላይ ተሰወረ! የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ለወንበሬ ያሰጋኛል ብሎ በጠላትነት የተነሳበት የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ ክቡር አንዳርጋቸዉ ጽጌ በግፍ ለወንጀለኛዉ የወያኔ ቡድን ተላልፈዉ ተሰጡ!
andargachew new picture
ነጻነት ላያንቀላፋና ነጻነት ላይታሰር አንድነትና ኢትዮጵያዊነትን በጫንቃዉ ተሸክሞ በማረፊያዉ ወቅትና ሰአት የጎረመሰዉ አባት አንዳርጋቸዉ ጽጌ ብዙሃንን አፍርቷል!! ዛሬ የፍሬዉ ትሩፋቶች አደራቸዉን ተቀብለዉ ሐገራቸዉንና ትዉልዳቸዉን ለመታደግ ዳር በደረሱበት ወቅት ወያኔያዉያን ግን ታላቁን አባት ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ላይ ይገኛሉ! ከሰሞኑ በደረሰን መረጃ መሰረት የተከበሩት የነጻነት አባት ክቡር አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ የፌደራል ፖሊስ ህንጻ ስር ምድር ቤት ዉስጥ ( underground ) ክፍል ዉስጥ መወሰዳቸዉን የሚያረጋግጡ ሲሆን የብሔራዊ መረጃ ምንጮቻችን በበኩላቸዉ ሌሎች ተጨማሪ ግለሰቦች በዚያዉ በፌደራል ፖሊስ የምድር ቤት ብቸኛ ክፍል ዉስጥ ከታላቁ የነጻነት አባት ጋር እንደሚገኙ ፍንጭ ሰጥተዋል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

onsdag 11. mai 2016

ኖርዌይ ኢትዮጵያውያን የፓለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በግዳጅ ወደ ሀገራቸው ለመመሰስ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ያደረገችውን ስምምነት የሚቃወም ታላቅ ሰልፍ ተካሄደ!!


 ሜይ 11፣2016
ዲቦራ ለማ/ኖርዌይ
 
ኢትዮጵያውያን በስደት ከሚኖሩባቸው የተለያዩ የአውሮፓና ስካንዴኔቪያን ሀገሮች አንዷ የሆነችው ኖርዌይ ስትሆን በኖርዌይ ሃገር ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባል ኢትዮጵያውያን የፓለቲካ ስደተኞች ይገኛሉ። እነዚህ ስደተኞች ከሌላው ሀገር ለየት የሚያደርግ ጠንካራ የፓለቲካ አቋም ያላቸው መሆኑም ይታወቃል። ስደተኞቹ በተለያየ ጊዜያት የገዢውን ፓርቲ ብልሹ አስተዳደር የሚያጋልጡ የፓለቲካ ስራዎችን ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወሳል።

ሆኖም ግን የኖርዌይ መንግስት እ.ኤ.አ በ2012 ከቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ ጋር በኖርዌይ የሚኖሩ ጥገኝነት ጠያቂዎችን አስገድዶ ወደ ሃገር ለመመለስ የሚያስችል ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል። ሆኖም ግን ይህ ስምምነት በተለያዩ ምክንያቶች ተግባር ላይ ሳይውል ቀርቷል። ኖርዌይ በድጋሚ አሁን በያዝነው አመት በፌብርዋሪ ወር እንደገና ስደተኞችን አስገድዶ ወደ ሀገር የመመለሱ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ቴዎድሮስ አደሃኖም ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በኖርዌይ የሚገኙ ታላላቅ የዜና አውታሮች ሲዘግቡ ሰንብተዋል። 

ይህንኑ ስምምነት አስመልክቶ በኖርዌይ የሚገኘው የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማህበር ስምምነቱ ትክክል እንዳልሆነ ተቃውሞውን ለመግለፅ በሜይ 10፣ 2016 ታላቅ ሰልፍ አዘጋጅቷል። ይህ የተቃውሞ ሰልፍ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል። ስደተኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተለይ በቅርቡ በሀገራችን በአደባባይ እየተገደሉ ያሉ ወገኖቻችንን የያዙ ምስሎችንና የኖርዌይ ዜግነት ያላቸውና ከደቡብ ሱዳን ታፍነው በኢትዮጵያ እስር ቤት እየማቀቁ ያሉንትና አሁን ለዘጠኝ አመት የተፈረደባቸው የአቶ ኦኬሎ አኳይ ፎቶግራፍ እንዲሁም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ፎቶግራፎች በመያዝ ስለነሱም አያይዞ ለኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ እየታወቀ ሰዎች በየሰከንዱ እየተገደሉ ባለበት ወቅት ሀገሪቱ በብዙ አቅጣጫ የህዝብ አመፅ ባለበትና ገዢው ፓርቲም ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ሰዎችን እየገደለና እያሰረ ባለበት ሁኔታ ስደተኞችን አስገድዶ ለመመሰል ስምምነት ማድረጉ ለምን እንዳስፈለገ፤ እንዲሁም የኖርዌይ መንግስት ለኖርዌጅያን ዜጎች በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች መዘዋወር አደገኛ መሆኑን መግለጫ እየሰጠ ባለበት ሁኔታ የፓለቲካ ስደተኞችን አሳልፎ መስጠት ሰብአዊነት የጎደለውና የስደተኛ መብት ህግን የሚጥስ መሆኑን ኢትዮጵያውያኑ በሰልፉ ላይ ተናግረዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የስደተኞቹን ጉዳይ የሚከታተሉ የግብረ ሃይሉ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አያሌው ይመር ንግግር ያደረጉ ሲሆን ዝግጅቱም በተያዘለት ሰአት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

ኢትጵያ ለዘላለም ትኑር!!