tirsdag 13. januar 2015

የኢትዮጵያ ምርጫ መቆመሪያ ተቋም ገመና

January 13,2014
በዳንኤል ተፈራ

10485535_718983234881727_4513979552309356105_n (1)
ያሳለፍነው ሳምንት በሕወሃት/ኢህአዴግ አገዛዝ ተሰልተው፣ ታስቦባቸው ይፋ ከተደረጉና አሻንጉሊቱ ምርጫ ቦርድ እንዲፈጽመው በህወሃት ሰዎች ቀጭን ትዕዛዝ ተሰጥቶት ገቢራዊ እንዳደረገው የሚጠረጠረው የፖለቲካ ጉዳይ ይፋ የተደረገበት ነበር፡፡ ይሄው ጉዳይ በአይረቤ ሰበብና በምክንያት አልባ ሁነት ግን ዳግም ከቤተ-መንግስት በወጣ ትዕዛዝ በሚመሰል መልኩ አንድነት እና መኢአድ ወደ ምርጫ ፍክክሩ እንዳይገቡ አይን ያወጣና የሰዎችን የስልጣን ብልግና ባጋለጠ መልኩ መግለጫ የሰጡበት ነው፡፡
እንደዚህ ዓመቱ ምርጫ ቦርዱ የተጋለጠበት ጊዜ አለ ብዬ አላምንም፡፡ ይሄው የምርጫ መቆመሪያ ተቋም እንደ ጫጩት ፍፁም ጠቅላላ ጉባዔ አድርገው የሚያውቁ፣ ቢሮም ሆነ ስራ አስፈፃሚ የሌላቸውን ተቃዋሚ ተብዬዎች በጉያው ሸጉጦ በኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ግንባታ ላይ እያላገጠ መሆኑ ሳያንስ የገዥውን ፓርቲ ኃላፊነት የጐደለው ተግባር ተቋቁመው ለሃገራችን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ እየደከሙ ያሉ ፓርቲዎችን እየገፉ ያለበት አግባብ ተቋሙን ከምርጫ መቆመሪያ ማዕከልነት ባለፈ ፋይዳ የሌለው፣ በህወሃት/ኢህአዴግ ማንቁርቱ የታነቀና የራሱ ሳንባ የሌለው ምስኪን ተቋም እንደሆነ ለመገንዘብ ይቻላል፡፡
ይሄው የተጨመደደ ቦርድ ተብየ በኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ገለልተኛነቱ አጠራጣሪ ቢሆንም እንደ ሰሞኑ ገለልተኛ አለመሆኑን በይፋ ያረጋገጠበት ወቅት ያለ አይመስለኝም፡፡ የውስጥ አዋቂ ምንጮች እንደሚጠቁሙት ቦርዱ በዋናነት የሚመራው በፕ/ር መርጋ በቃና ሳይሆን በምክትልነት በተቀመጠው የትግራዩ ሰው ዶ/ር አዲሱ ገ/እግዚአብሄር ነው፡፡ ለዚህም ነው በኢህአዴጉ አፈ-ቀላጤ ፍና እና ሌላው ቀላጤ ኢቲቪ በኩል ፓርቲዎችን በህገ ወጥ መንገድ መገፋታቸውን እየገለፀ ያለው፡፡ ሰውየው የቦርዱን ህገ ወጥ ተግባር ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ የሚችል ሰው ነው፡፡ ዶ/ር አዲሱ የፓርቲዎችን የፋይናንስ ክፍፍል ቀመር አዘጋጅቶ ያቀረበ፤ በዚህ ቀመርም በፓርላማ መቀመጫና በክልል ም/ቤት መቀመጫ 55% እንዲይዝ ለማሳመን የጣረ የህወሃት የቁርጥ ቀን ልጅ ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም 55% ጠቅልሎ የሚወሰደው ኢህአዴግ ነው፡፡
ቦርዱ ገለልተኛ አይደለም ስንል እንዲሁ በግብታዊነት ሳይሆን ተጨባጭ መከራከሪያዎችን የማቅረብ አቅም ስላለን ነው፡፡ አንድ ወዳጄ የኢትዮጵያውን ምርጫ ቦርድ በማገዝ ከመቆሪያ ተቋምነት መገላገል እንደሚገባ ስነግረው ተስፉ በቆረጠ ስሜት ግን ደግሞ በምፀት ፈገግ ብሎ “ወዳጄ ቦርዱ እኮ ግንባሩን ከመሰረቱ ፓርቲዎች አምስተኛው ፓርቲ ነው፡፡ የሚያስፈልገው ቦርዱን ማገዝ ሳይሆን አፍርሶ እንደገና መስራት ነው፡፡ በታሪክ ከሚጠየቁ ተቋማት ግንባር ቀደሙ ነው፡፡” ነበር ያለኝ፡፡ እውነትም መፍረስ የሚገባው አይረቤ ተቋም ነው፤ ራሱን ነፃ ያላወጣና የምርጫ መቆመሪያ ተቋም እንደሆነ ግብሩ አረጋገጠ፡፡
አንድነት ፓርቲ የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኢ/ር ግዛቸው በፈቃዳቸው ስልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ አንድነት በመዋቅሩ በአመራርነት የማያውቃቸው ግለሰቦች ተሰባስበው ኢ/ር ግዛቸውን የተካውን አመራር ህግ የጣሰ ለማስመሰል ጥረት ጀመሩ፡፡ የቦርዱ የፖለቲካ ቁማርም ከዚህ ሁነት ይጀምራል፡፡ አንድነትን አስቀድሞ ከምርጫው ለማስቀረት እነዚህን ተራ ግለሰቦች “ጐሽ፣ ጐሽ” ማለት ጀመሩ፡፡ እነዚህ “አንድነት ነን፣ መርህ ይከበር” የሚሉ ጥቂት ግለሰቦች የተንኮል ፖለቲካው አድራሽ ፈርሶች እንጅ በራሳቸው ምንም አይደሉም፡፡ የእነዚህ አፍራሽ ግለሰቦች ያላቸው ብቃት የሚለካው ከኢትዮጵያዊ ጨዋነት ባፈነገጠ መልኩ ለመዋሸት የማይሳቀቁ፤ ተልዕኳቸውን ለመፈፀም አይናቸውን በጨው ያጠቡ የዘመናችን ባንዳዎች መሆናቸው ነው፡፡
ለዚህ ምሳሌ የሚሆነው የመቆመሪያው ተቋም ሳያፍር “አመራር” እያለ የሚጠራው የማነአብ አሰፋ የሚባል የትግራይ ተወላጅ ሲሆን ዕድሜው በሃያዎቹ መጀመሪያ የሚገኝ፣ በተግባሩ ስለሚያፍር በቆብና በጃኬት ራሱን ደብቆ የሚዞር ወጣት ነው፡፡ ይሄ ልጅ አንድነት ቤት ተቀጣሪ ሆኖ ለተወሰኑ ወራት የድርጅት ጉዳይ ተላላኪ ሆኖ ሰርቷል፡፡ አንገት ደፊና አይናፋር በመምሰል የተወነው ትወና አስደናቂ ነው፡፡ የኢህአዴግ ክትትል እንዳላስቀመጠውና ስራ መቀጠር እንኳን እንዳልቻለ እንባ እየተናነቀው ለመናገር የሚችለው ይሄ ወጣት ምርጫ ሲደርስ እንዲፈነዳ ህወሃት አቀባብሎ ያስቀመጠው ፈንጂ እንደሆነ ያወቅነው ቦርዱ “አመራር” እያለ ቢሮው ጐልቶት ስናገኘው ነው፡፡ ወደ ነጥቡ ስንመለስ እነዚህ “አንድነት ነን” የሚሉ በተግባር ግን የአንድነት ወገን ያልሆኑ ስብስቦች ም/ቤቱ በደንቡ መሰረት የተካውን አመራር “ህገ-ወጥ ነው” በማለታቸው ብቻ የምርጫ መቆመሪያው ተቋም በችኮላ አንድ ደብዳቤ ለፓርቲው ፃፈ፡፡ ይሄ የመጀመሪያው ደብዳቤ ኢ/ር ግዛቸውን ፕሬዝዳንት አድርጐ የመረጠውን ጉባኤ ዕውቅና በመንፈግ ዶ/ር ነጋሶን እንደሚያውቅ የሚጠቅስ ነው፡፡ ቦርዱ በችኮላ በየዋህነት የፃፈው ደብዳቤ ለቁማሩ በጆከርነት የሚያገለግሉ ግለሰቦችን ከጨዋታ ውጭ የሚያደርግበት መሆኑን ሲረዳ ምናልባትም አለቃቸው ህወሃት /ኢህአዴግ ለአንድነት ቦርድ የፃፈውን ዝርዝር ደብዳቤ ሲመለከት ለሴራ ፖለቲካ እንደማይመች ሲረዳ በአስቸኳይ ቀይር ብሎት ይመስለኛል፡- “እሱን ደብዳቤ ተውት” ከሚል መልዕክት ጋር ሌላ 3 ነጥቦችን የያዘ ደብዳቤ ላከ፡፡
የመጀመሪያውን ደብዳቤ ተውት ያለበት ምክንያት ለአፍራሽ ተልዕኮ የተዘጋጁ ገልቱ ግለሰቦች ከጨዋታ ውጭ ስለሚሆኑ ነው፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ግለሰቦች በዶ/ር ነጋሶ የአመራር ዘመን አይታወቁም ወይም የሉም ነበርና፡፡ ባለ ሦስቱ ነጥብ ደብዳቤ ሲመጣ ግን አንድነት የፖለቲካ ዕደንድምታውን በጥንቃቄ ገምግሟል፡፡ ምነው ቢሉ ይሄ ከቦርዱ በስተጀርባ የሚደንስ አካል እንዳለ በመረጋገጡ ነው፡፡ ዳንሰኞቹ ምርጫን ለማስመሰያና ማወናበጃ እንጅ በትክክል ሊጠቀሙበት አይፈልጉም፡፡
የደብዳቤው ሦስት ነጥቦች የሚከተሉት ነበሩ አንደኛው ም/ቤቱ የጠቅላላ ጉባኤ ውክልና እንዳለውና ም/ቤቱ ፕሬዘዳንት መምረጥ እንደሚችል አብራሩ፤ ሁለተኛው የጠ/ጉባኤ ሪፖርት በጊዜ አስገቡና የመጨረሻው የጠቅላላ ጉባኤ የኮረም ቁጥር ግለጹልን የሚል ነበር፡፡ በጣም ቀላልና ተራ ጥያቄ የሚመስል ነበር፡፡ አንድነት በፍጥነት ምላሽ ሰጠ፡፡ የመቆመሪያው ተቋምም የሰጠነውን ምላሽ “በቅንነት” እንደተቀበለው ገልጾ ነገር ግን የጠ/ጉባኤ ቁጥር በደንቡ እንድናካትት የሚጠይቅ ደብዳቤ ፃፈ፡፡ በቅንነት የምትለውን ግን በቅንነት አልተመለከትነውም፡፡ ጉባኤ በፍጥነት መጠራት እንዳለበትና ምርጫ ቦርዱ የጠየቀውን አሟልተን በሙሉ ልብ ወደ ምርጫ መግባት እንደሚገባ በመታመኑ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠርቶ የምርጫ ቦርድ ተወካይ ባለበት በስኬት ተጠናቀቀ፡፡
አንድነትም ገዥዎች ባዳፈኑት የፖለቲካ ምህዳር እና ልፍስፍሱ ቦርድ ቢኖርም ህዝቡን አንቀሳቅሽ በ2007 ዓ.ም የአምባገነኑ ስርዓት ፍፃሜ ይሆናል በሚል ፅኑ እምነት ሙሉ ለሙሉ በስራ ተጠመደ፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜም የህዝብ ታዛቢዎችን ምርጫ በመላ ሀገሪቱ ያሉ ቢሮዎቹን በመዝጋት በንቃት ተከታተለ አጋለጠ፡፡ ህዝቡ የምርጫ ካርድ የሚወስድበትንና በካርዱ ለመጀመሪያ ጊዜ አሸናፊ የሚሆንበትን ስትራቴጂ መንደፍንና ሕዝባዊ ንቅናቄ እንደሚያስፈልግ ይፋ ማድረጉ ተከትሎ የ40 እና 50 ዓመት የመግዛት ህልም ያላቸው “ነፃ አውጭዎች” መንደር ጫጫታና ጭንቀት ፈጠረ፡፡
ይህንን ጭንቀት ለማርገብ አንድነትን ከምርጫ ጫወታ ማስወጣት እንደሚገባ ታመነበት፡፡ ለዚህ ማስፈፀሚያ የመቆመሪያው ተቋም አለ፡፡ በጠቅላላ ጉባኤው ተወካዩን የላከው ቦርዱ ሌላ ታሪካዊ ስህተት ለመስራት ደፈረ፡፡ ከቦርዱ በስተጀርባ ያሉ ዳንሰኞች ማንቁርቱን ስላነቁት ምርጫ አልነበረውም፡፡ ይሄ ተራ ጨዋታ በፋና እና ኢቲቪ ታጅቦ ለህዝብ ቀረ፡፡ ድራማው “የውስጥ ችግሮቻቸውን ካልፈቱ ወደ ምርጫ አይገቡም” የሚል ነው፡፡ የውስጥ ችግር ከማን ጋር? እንዴት? መልስ የላቸውም፡፡ ኢ/ር ግዛቸው በፈቃዳቸው ለቀው ወደ ግል ጉዳያቸው ገብተዋል፡፡ ታዲያ እነዚህ አመራር ተብየዎች እነማን ናቸው? እነዚህ የአንድነት አመራር እንዲደራደራቸውና ችግሩን እንዲፈታ የተጠየቁት ግለሰቦች በፓርቲው የአመራር መዋቅር የማይታወቁ፤ ከየመንገዱ ተለቃቅመው የመጡ ተራ ሰዎች ናቸው፡፡
ህወሃት/ኢህአዴግ በቦርዱ በኩል ይህንን ተራ ድራማ እየሰራ ያለው አንድነት ወደ ምርጫ እንዳይገባ ለመከልከል የወሰነው የፖለቲካ ውሳኔ ስጋ ለማልበስ ነው፡፡ የእርኩም ስጋ፡፡ ሁሉም በሰፈረው ቁና የሚሰፈርበት ቀን እንደሚመጣ ቅንጣት አልጠራጠርም፡፡ እየተካሄደ ያለው ሰላማዊ ትግል ከዚህ ዓይነት ተራ ድራማ በላይም ነው፡፡ ትግሉ የነፃነት የመውጣትና ተደፍቆ የመኖር ነው፡፡ ወደ ምርጫ እንገባለን ስንላቸው በዚህ ደረጃ ተርበትብተዋል፡፡ ምርጫ ቦርድም ያለውድድር ለኢህአዴግ ተጨማሪ የአገዛዝ ዘመን ለመስጠት ዝግጅቱን የጨረሰ ይመስላል፡፡ ይሄ የስርዓቱን የውድቀት ፖለቲካ የሚያሳይ ነው፡፡ የዚች ሀገር ትግል የቦርድ ወይም የሌላ ትግል አይደለም፡፡ ትግሉ በሕዝቡ እጅ ላይ የወደቀበት ታሪካዊ ወቅት ነው፡፡ ታሪካዊ ጊዜ ዴሞክራሲን እናሰፍናለን የሚሉ ሰዎች በግብራቸው ያፈሩበት ታሪክ፡፡ ይህንን በአደባባይ ቆመን የምንናገርበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም፡፡
2007 ለለውጥ!!!

torsdag 1. januar 2015

ቀኑ ሲቃረብ መውጫው ይጠባል!

ኢትዮጵያ ሀገራችን በታሪኳ ከአስከፊ የፈተና አረንቋ ውስጥ ተገፍታ የገባችበት ዘመን ቢኖር ይህ የምንገኝበት ዘመነ ወያኔ ብቻ ነው፡፡ ዜጎችዋ ከፋሽስት ኢጣልያ በከፋ ሁኔታ ይህ ቀረሽ የማይባል የመከራ መአት የወረደባቸውና እየወረ ደባ ቸው የሚገኝበት ዘመን ቢኖር ይህ የምንገኝበት ዘመን ወያኔ ብቻ ነው፡፡ እስር ቤቶች ሞልተው ተጨማሪ እስር ቤቶች መገ ንባት ከልማት ተቆጥሮ የሚፎከርበት ዘመን ቢኖር ይኸው ዘመነ ወያኔ ብቻ ነው፡፡ የሀገሪቱ ብሄራዊ ባንክ ንብረት የሆ ነው ወርቅ በባሌስትራ ለውጦ እስከ መዝረፍ የደረሰ በጠራራ ፀሀይ የህ ዝብና የሀገር ሀብት ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ በጥቂቶች የሚዘረፍበት ዘመን ቢኖር የምንገኝበት ዘመነ ወያኔ ብቻ ነው፡፡ የጅምላ እስር፤ የጅምላ ግድያ፤ የጅምላ ስደትና መፈናቀል፤ ይበልጡንም በታሪካችን ታይቶ በማያውቅ መልኩ ለሞት፤ ለእስር፤ ለመፈናቀልና ለስደ ት ምክንያቱ የተገኘንበት ዘውግ የሆነበት ዘረኛ ዘመን ቢኖር ይኸው ዘመነ ወያኔ ብቻ ነው፡፡

ባጠቃላይ ላለፉት 23 አመታት ወያኔ ማድረግ የሚችለውን አስከፊ ነገር ሁሉ በሀገርና በህዝብ ላይ ሲፈፅም ቆይቷል፡፡ ዛሬ ከ23 አመ ታት በዃላ ሀገራችንና ህዝባችን ያልተዘፈቁበት የችግር ማጥ፤ ያልደረሰ የሀብትና የሰብአዊ ውድመት፤ ያልተፈፀመ የግፍና የሰቆቃ አይነት የለም፡፡ ወያኔ ይህን ሁሉ ሲፈፅም መሳሪያ አድርጎ ከተጠቀመባቸው ተቋማት ውስጥ ዋነኛዎቹ የመከላከያ፤ ፍርድ ቤትና የፖሊስና የደህንነት መሆናቸው ጥያቄ የለውም፡፡ የእነዚህ ተቋማት አባላት ከወያኔ ጥቃት ሰለባ ከመሆን ባይተርፉም የዚህን ወንጀለኛና ዘረኛ ቡድን እድሜ በአንድ ቀን በመጨመሩ ስራ ላይ ከፍተኛውን ድርሻ እንደያዙ ዛሬም መገኘታቸው አሌ የማይባል እውነት ነው፡፡ይህ ሲባል ግን በሀገርና በህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ክህደት፤ ግፍና ሰቆቃ የሚያማቸው፤ መከራው መረራቸው፤ ብሶቱ ብሶታቸው የሆኑ አባላት የሉም ማለት እንዳልሆነ፤ ይልቁንም አብዛኛዎቹ የዚህ ስሌት ተካፋይ ስለመሆናቸው የሚጠራጠር የለም፡፡
ነገር ግን ከህዝብ አብራክ በወጡና ልጆቹን ሳይመግብ በከፈለው ታክስ በተደራጀ የመከላከያ፤ የፖሊስና የደህንነት ተቋማት ውስጥ የምትገኙ አብዛኛውና የግፉ ቀማሽ የሆናችሁ አባላት ዛሬ የምትገኙበት ሁኔታ እንደ አለፉት 23 አመታት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ፤ ከዛሬ ነገ የተሻለን ነገር ተስፋ በማድረግ፤ በግርግሩ ፍርፋሪ ሊወድቅልኝ ይችላል ከሚል ራስ ወዳድነት…… ወዘተ በመሳሰሉ በርካታ ምክንያቶች ለፍትህ፤ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ብሎም ለኢትዮጵያችን ቀጣይ ህልውና በሚደረጉ ህዝባዊ እንቅስቃሴዎች ላይ በመቆም ብሎም የጥቂት ዘረ ኛች ስልጣንና ምቾት እድሜ ለማራዘም የተጓዛችሁበት መንገድ ብዙም ማስኬድ ከማያስችልበት፤ ይልቁንም ዛሬ ከሁለት መንታ መንገድ የ ደረሳችሁበትና ቆም ብሎም ማየትና ማገናዘብን ከሚጠይቅ ወቅት ላይ ትገኛላችሁ፡፡ አንዱ በዘረኝነት በትር እየተወቀጡ የወያኔ ሎሌ ሆኖ መቀጠል፤ ሌላው ከህዝብ አብራክ የተገኛችሁ ናችሁና ከህዝብ ወገን ተቀላቅሎ ሀገርን፤ ወገንንና ራስን ነፃ ለማውጣት መነሳት..
ለመከላከያ ሰራዊት፦ ላለፉት 23 አመታት ከጠመንጃ ተሸካሚነት ላለፈ ለማይፈልጉህ፤ ለአንተነትህ መለኪያው እውቀትህ፤ ችሎታ ህና አገልግሎትህ ሳይሆን የተገኘህበት ዘውግ መስፈሪያህ ለሆነበት ዘረኛ ስርአት፤ መቀየሪያ መለያ ልብስ ተነፍጎህ ቀዳዳ እየጣፍክ የልጆችህን የረሀብ ልቅሶ እያዳመጥክ በአንተ ትከሻ በዘረፉት ሀብት የገነቧቸውን ህንፃዎች ጠባቂ ላደረጉህ፤ ፍትህ ነፃነት ሲል በተራበ አንጀታቸውና በደ ከመ ድምፃቸው በጠየቁ ወገኖችህ ላይ ይህ ቀረ የማይባል ግፍ ሲያ ስፈፅምህ ለቆየው የወያኔ ዘረኛ ቡድን ዛሬም ተገቢውን ምላሽ የመስጠት እድሉ አለህ፡፡አልረፈደምና ተጠቀምበት!!!
የፖሊስ ሰራዊት አባላት፤- ፍትህ ላሉ ጥይትን፤ ነፃነት ላሉ የጭካኔ በትርን፤ ሀገሬን ላሉ ከጨለማ ዘብጥያ መወርወርን.. ዋነኛ ተግባርህ በሆነበት በዚህ ዘረኛና በወንጀል የተጨማለቀ ስርአት ውስጥ የቆየህበት ያለፉት 23 አመታት ለአንተም፤ ለቤተሰብህም፤ ለተገኘህበት ህብረ ተሰብ ሆነ ለሀገርህ የፈየደው አንዳች ነገር ያለመኖሩን ይበልጡኑ ከእሳት ወደ እረመጥ ከሆነው የወያኔ ጉዞ ራስህን አውጥተህ ከህዝባዊው ወገን የምትቀላቀልበት የመጨረሻው ሰአት መሆኑን ተገንዝበህ ምርጫህን ከወገንህ አድርግ፡፡ ለአንተም አልረፈደም!!
የደህንነት አባላት፦ ለሀገር ደህንነት ለህዝብ ሰላም ሲባል በህዝብ ሀብት በተደራጀ ተቋም ተጠቅመህ በሀገርህ ላይ ክህደትን፤ በወገ ንህ ላይ ግፍና ሰቆቃን ስትፈፅም መቆየትህ ከወንጀሎች ሁል የከፋ ወንጀል መሆኑን ተገንዝበህ ለፍትህ ለነ ፃነትና ለዲሞክራሲ ሲሉ በተነሱ ወገኖችህ ላይ ስትሰነዝር የቆየኸውን በትር በፍትህ በነፃነትና በዲሞክራሲ ላይ በቆሙት ዘ ረኛ አዛዦችህ ላይ የማሻው ጊዜ አሁን ነው፡፡ ስለ ዚህም ከህዝባዊው ወገን ተቀላቅለህ ህዝባዊ ወገንተኝነትህን የምታሳይበት ብሎም የበደልከውን የምትክስበት ጊዜውም እድሉ አለህና ተጠ ቀምበት፡፡ላንተም አልረፈደም!!
በመጨረሻም ልጇን የምትጠላ እናት፤ ወገኑን የሚገፋ ህዝብ፤ ዜጎቹን የማይቀበል ሀገር የለምና ይህን በአስከፊነቱ ወደር የማይገኝለት የወያኔ ዘረኛ ስርአት ደግፎ ማቆየት ከማይቻልበት ይበልጡንም እንደ ትሪፖሊና ኢያሪኮ የግፈኞች ግንብ በህዝባዊ ሀይል ከሚገረሰስበት ከ መጨረሻዋ ደቂቃ ከመደረሱ በፊት ከእናታችሁ እቅፍ ከወገናችሁ መሀል ግቡ!! ተቀላቀሉ!! ቀኑ ሲቃረብ መውጫው ይጠባልና ጊዜ ሳታጠ ፉ ፈር ቀዳጅ ወንድሞቻችሁን መከተል ብልህነት ነው እንላለን!!!
የኢያሪኮም የጋዳፊም ግንብ ተንዷል፤ የወያኔም ይናዳል!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

fredag 26. desember 2014

የአምባሰደሩ የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉብኝት ተከትሎ የእንግሊዛዊ ቱሪስት የተቀነባበረ ግድያ ድንጋጤ ፈጥሯል:: - See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/3175#sthash.d7gvvG77.dpuf

  • 1381
     
    Share
የባህር ዳሩ ገዳይ ካለምንም ጥያቄ በቀጥታ ለፖሊስ እጁን ሰቷል::
10675560_577437609056866_2639742903154693736_nባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ካሳንቺስ ከቀድሞ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ጀርባ ከሚገኘው ድብቅ የደህንነት እስር ቤት ውስጥ በመገኘት በከፍተኛ የሴኩሪቲ ጥበቃ የነጻነት ታጋይ የሆነውን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር Greg Dorey እንዳነጋገሩ ሲታወቅ ከአንዳርጋቸው ጋር ያደረጉትን ቆይታ በተመለከተ ዝርዝር ማብራሪያ ባይገኝም በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሲገልጹ የኤምባሲው ምንጮች እንዳሉት ስለ አንዳርጋቸው መረጃ ያላቸው ለስርአቱ ቅርብ የሆኑ ክፍተኛ የደህንነት አባላት እና የአንድ ብሄር ተወላጅ የሆኑ አንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንደሆኑ ገልጸዋል::እንዲሁም አመነስቲ ኢንተርናሽናል አንዳርጋቸውን በተመለከተ ከታፍነ 6 ወር መሆኑን ገልጾ ሁኔታው አሳሳቢ ነው ሲል ለእንግሊዝ መንግስት አቤት ያለበተን መግለጫ ባሳለፍነው ሳምንት መግለጫ አውጥቶ ነበር::
ይህ በ እንዲህ እንዳለ በባህር ዳር ከተማ ውስጥ ድብ አንበሳ እየተባለ በሚጠራው ሆቴል አካባቢ አንድ አርሶ አድር ታጣቂ ሚሊሻ በሚመስል ጸጉረ ልውጥ ሰው የእንግሊዝ ዜግነት ያለው ቱሪስት መገደሉ ታውቋል::የአምባሰደሩ የአንዳርጋቸው ጽጌ ጉብኝት ተከትሎ የእንግሊዛዊ ቱሪስት መገደል ድንጋጤ ፈጥሯል::ገዳዩ ለግድያው እንደተዘጋጀበት በሚያስታውቅ መልኩ በአከባቢው አድብቶ ሲጠባበቅ የነበረ እና ወዲያው እንግሊዛዊውን እንደገደለው ለፖሊስ ያለምንም ጥያቄ እጁን ሰቷል::በአከባቢዉም የታተቁ ፖሊሶች የነበሩ ሲሆን ግድያው ሲፈጸም ምንም ያደረጉት መከላከል አልነበረም::ግድያው የተቀነባበረ ነው ሲል የባህር ዳር ህዝብ እየተናገረ ነው::
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/3175#sthash.d7gvvG77.dpuf

mandag 22. desember 2014

አየር ሃይል የጠፉ አብራሪዎችን መፈለጉን አቆመ

አየር ሃይል የጠፉ አብራሪዎችን መፈለጉን አቆመ


ታኀሳስ ፲፫(አስራ ሦስትቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የኢሳት የአየር ሃይል ምንጮች እንደገለጹት ሰሞኑን ኤም አይ 35 የተባለ የውጊያ ሄሊኮፕተር ይዘው በመጥፋት ወደ አልታወቀ ስፍራ የተጓዙት ሁለቱን አብራሪዎችና አንድ ቴክኒሻንን ለመፈለግ አየር ሃይል በተለያዩ አካበባዎች  አሰሳ ሲያደርግ ቢቆይም በመጨረሻ ፍለጋው እንዲቋረጥ ተደርጓል።
ፍለጋው እንዲቋረጥ የተደረገበት ዋና ምክንያት አብራሪዎቹ ሆን ብለው መጥፋታቸውና ምንም አይነት ጉዳት ሳይደርስባቸው በሰላም ወደአልታወቀ ስፍራ መሄዳቸውን የአየር ሃይል አዛዦች ድምዳሜ ላይ በመድረሳቸው ነው።
ኢሳት መጀመሪያ ላይ በደረሰው መረጃ መሰረት የጠፉት 2 አብረራዎች መሆናቸውን መዘገቡ የሚታወስ ቢሆንም፣ ከአየር ሃይል የደረሰውን መረጃ መሰረት አድርጎ ባደረገው ማጣራት የጠፉት 2 አብራሪዎችና አንድ የበረራ ቴክኒሻን መሆናቸውን ለማረጋገጥ ችሎአል። ከፍተኛ የአብራሪነት ልምድ የነበራቸው ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣  መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ ከበረራ ቴክኒሻኑ ጸጋ ብርሃን ግደይ ጋር በመሆን ሄሌኮፕተሮቻቸውን በመያዝ የተሰወሩ ሲሆን፣ ሰዎቹ በመልካም ጤንነት ላይ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ተችሎአል።
ጉዳዩን በተመለከተ የአየር ሃይል ም/ል አዛዥ የሆኑትን ብርጋዲየር ጄኔራል  ማሾ ሃጎስን ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። ይሁን እንጅ አየር ሃይሉን እና ስምሪቶችን ከጀርባ ሆነው ይመሩታል የሚባሉት የድሬዳዋ አየር ሃይል ምድብ አዛዥ ኮ/ል አበበ ተካን በስልክ ለማነጋጋር ጥረት ያደርግን ቢሆንም፣ ኮሎኔሉ ከየት እንደምንደውል ከጠየቁን በሁዋላ የምንደውልበትን ቦታና ድርጅት ስንነግራቸው፣ ” ለእናንተ ደውለውላችሁ ነበርን ?” ብለው ከጠየቁን በሁዋላ፣ እኛ መረጃ ደርሶን እንደደወልንላቸው ስንገልጽላቸው ” ዝጋ ” ብለው   ስልኩን ዘግተውታል። በዚሁ ዙሪያ ተጨማሪ መረጃውን እየተከታተልን የምናቅርብ መሆኑን እንገልጻለን

søndag 30. november 2014

ምርጫ መሳተፍ በመርዕ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ ወይስ ኢህአዴግን ማጀብ? – ከግርማ ሰይፉ ማሩ

November 30,2014
ሰዎች በማንኛውም መንገድ ሸብረክ ሸብረክ የሚሉ ከሆነ መርህ አልባ መሆናቸውን ከማሳየት ውጭ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም፡፡ ባለፈው ሳምነት ፍኖተ ነፃነት ላይ ወጣቱ ፀሃፊ ኢዮኤል ፍስሃ ዳምጤ ለምን እንደምንፈራ ቁልጭ አድርጎ አሳይቶን ነበር፡፡ የገዢዎቻችን በትር የበረታብን በእነርሱ ጥንካሬ ሳይሆን ከፍርሃት በመጣ ዝምታችን እንደሆነ አስምሮበታል፡፡ መፍትሔውም ከፍርሃት መላቀቅና ዝምታውን ማፍረስ ነው፡፡ በዛሬው ፅሁፌ ማንሳት የፈለኩት ደግሞ ለምን ሸብረክ ሸብረክ እንደምንል ነው፡፡
ለምንድነው ኮሽ ሲል ደንግጠን ከቆምንበት “መርዕ” ከምንለው አስተሳሰብ የምንሸራተት? እንዲህ ከሆነ ቀድሞውንም መርዕ አልነበረንም ማለት ነው፡፡ መርዕ ብለን የምንይዘው አሰተሳሰብ በእኔ እምነት ለምናደርገው እንቅስቃሴ የማዕዘን ድንጋይ መሆን አለበት፡፡ ከዚህ መርዕ ሸርተት ስንል ቀጥሎ የምናገኝው ሌላ የተሻለ ማዕዘን የሚሆን ድንጋይ ሳይሆን ድጥ ወይመ ማጥ ነው የሚሆነው፡፡ ብዙዎች መርዕ የሚመስላቸው በአቋራጭ የሚፈልጉትን ግብ የሚያሳካ አጭር መንገድ አድርገው ይወስዱታል፡፡ ይህ አቋራጭ መንገድ ግን ብዙን ጊዜ ወደ ሌላ ውጥንቅጥ ከመውሰድ አልፎ ለስኬት ሲያበቃ አይታይም፡፡
Girma Siefu
ግልፅ ያልሆነ የህይወት ግብ ያለን ሰዎች የምንሄድበትን ስለማናውቅ ሌሎች በሄዱበት ተከትለን እንነጉዳለን፣ ሌሎች ግባቸውን ሲያሳኩ እኛ የበይ ተመልካች መሆናችን አይቀርም፡፡ ግባችን ግልፅ ያለመሆኑ መድረሻችንን ብቻ ሳይሆን መነሻችንንም ስሚያዛባው ከየት ተነስተን የት እንደምንደርስ፣ እንዴት እንደምንደርስ እንዳናውቅ ያደርገናል፡፡ መርዕ ማለት አሁን ካለንብት ቦታ ተነስተን ወደምንፈልገው ቦታ ለመድረስ የምንጓዝበት ፍኖተ ካርታ ነው፡፡ ይህ ደግሞ በአሰተሳሰብ ብቻ ሳይሆን በተግባርም ልክ መሆን ያለበት ነው፡፡ አንድ አንድ ሰዎች የምንፈልገውን ግብ ለማሳካት ማነኛውንም መንገድ መጠቀም ችግር የለውም ይላሉ፡፡ ይህ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጭው /the end justify the means/ የሚባለው ዓይነት መሆኑ ሲሆን፡፡ ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ ሌሎች የምንሄድበት መንገድ እንደ ወጤቱ ሁሉ መርዕ ላይ መመስረት አለበት የሚሉ ናቸው /The means is equally important as the end/:: በግሌ የማምነውም የምከተለውም የኋለኛውን አማራጭ ነው፡፡ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጭው የስግብግቦች መንገድ ነው ብዬ በፅኑ ስለማምን፡፡
ሰሞነኛ ወደ ሆነው የምርጫ አጀንዳ እና በመርዕ ላይ የተመሰረተው የአንድነት ፓርቲ ምርጫ እሳተፋለሁ ውሳኔ እንዴት መታየት እንዳለበት በአጭሩ ይህን አቋም ለደገፉም ሆነ ለተቃወሙ ማሰረዳት ተገቢ ይመስለኛል፡፡ አንድነት ፓርቲ ስልጣን የሚገኘው በህዝብ ድምፅ ነው የሚል መርዕ አለው፡፡ የህዝብ ድምፅ የሚገኘው ደግሞ በምርጫ ወቅት መራጩ ህዝብ በሚሰጠው ካርድ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ በምርጫ የህዝብ ድምፅ ይገኛል ማለት ነው፡፡ ብዙዎች ምርጫ ለመሳተፍ እኩል ሜዳ ያሰፈልጋል ይላሉ፡፡ ትክክል ነው እኔም አምንበታለሁ፡፡ ሜዳውን ትክክል ከሚያደርገው አንዱ ጉዳይ የምርጫ ቦርድ ገለልተኝነት እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ካልሆነ ማለትም ሜዳው ትክክል ካልሆነ ስልጣን በሌላም መንገድ መያዝ ተቀባይነት አለው የሚል መከራከሪያ ለማቅረብም ሰበብ ይሆናል፡፡
ስልጣን በተለያየ መንገድ ለመያዝ እንደሚቻል አማራጭ ማሳየት አንድ ጉዳይ ሆኖ እኛ የመረጥነው ብቻ ልክ ነው ማለትም ተገቢ አይደለም፡፡ በተገኘው መንገድ ለመያዝ መሞከር ግን መርዕ አልባ ያደርገናል፡፡ ሰላማዊ ትግል እከተላለሁ ብሎ በሰላማዊ ትግል መርዕዎች አምናለሁ የሚል ማታ-ማታ ወይም ቅዳሜና-እሁድ በሌላ መንገድ ልሞክር የሚል ከሆነ መርዕ አልባነት ነው፡፡ በእኔ እምነት ችግር ያለው የምርጫ ሜዳ ላይ ከሆነ የምርጫው ሜዳው ለማስተካከል ምን አድርገናል? ከሚለው መነሳት አለበት፡፡ ስልጣን የመያዣው መንግድ ኮሮኮንች በዝቶበታል ማለት ኮሮኮንቹን እንዴት እናሻሽል ወደሚል ሊገፋን ይገባል፡፡
ሁሉም ሰው መረዳት ያለበት ገዢው ፓርቲ የምርጫ ሜዳውን ያጠበበው ወይም ኮሮኮንች እንዲበዛበት ያደረገው አውቆ ነው፡፡ ሜዳው ደግሞ የጠበበን ደግሞ አማራጭ አለን የምንል ፓርቲዎች ነን፡፡ አማርጭ ለማቅረብ እድል ስንነፈግ መጠየቅ ያለብን አንድ መስረታዊ ጥያቄ አማራጭ የተከለከለው ህዝብ ምንም ማድረግ አለበት የሚለው ነው? አማራጭ የሚፈልግ ህዝብ ድንጋይ ወይም ጠብመንጃ ይዞ አማራጭ አትከልክሉን ቢል ነው የሚሻለው ወይስ የምርጫ ካርድ ይዞ? አንድነት የመረጠው መስመር የምርጫ ካርድ ይዞ ቢሆን ይሻላል የሚለውን ነው፡፡ ይህ በምንም ዓይነት ሌሎች የመረጡት መስመር አይሰራም ማለት አይደለም፡፡ የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጭውን እንደ መርዕ የተቀበለ ብዙ ሌላ አማራጭ ሊያስብ፣ ሊተገብር ይችላል፡፡ ችግሩ የእኛ ካልሆነ ብሎ የሌሎችን ምርጫ ለማክበር አለመፈለጉ ላይ ነው፡፡
ETHIOPIA ELECTIONSበሀገራችን ኢትዮጵያ በ1997 ከተደረገው ምርጫ ውጭ ህዝቡ በምርጫ እንዲሳተፍ የምርጫ ካርድ እንዲወስድ በተቃዋሚ ፓርቲዎች በተገቢው መልኩና ደረጃ ተቀስቅሶዋል የሚል እምነት የለኝ፡፡ ከ1997 በፊት ምርጫ መወዳድር ወያኔን ማጀብ ነው እያልን ምርጫ የሚወዳደሩትን ብቻ ሳይሆን መራጩንም ተሰፋ እያስቆረጥን ኖረናል፡፡ ይህን ምርጫ የማጣጣል ስትራቴጂያችንን በደንብ የተረዳው ገዢው ፓርቲ የራሱን መራጮችና ተመራጮች እያዘጋጀ ውድድር ሲያድርግ ነበር፡፡ እንደዚያም ሆኖ ህዝቡ በምርጫ ካርዱ ቅሬታውን ሲገልፅ እንደ ነበር የገዢው ፓርቲ የኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዴእታ የነበሩት አቶ ኤርሚያስ ለገሠ “የመለስ ትሩፋቶች” በሚለው መፅሃፍ አስነብቦናል፡፡ ስለዚህ የአንድነት ቤተሰቦች ምርጫ እንሳተፋለን ስንል መራጮቻችን እንዲመዘገቡ እናደርጋለን ማለት ነው፡፡ የእኛ መራጮች ሲመዘገቡ፣ ገዢው ፓርቲ የእኔ ብሎ ያስመዘገባቸውም ቢሆኑ እኛን ለመምረጥ እንዲችሉ መሸሸጊያ እንሰጣቸዋለን፡፡
ብዙ ሰው መረዳት ያለበት የምርጫ ቅስቀሳ የሚጀመርበት ወቅት መራጮች ምዝገባ ሊጠናቀቅ ሳምንት ሲቀረው ነው (በ1997 ቀድሞ የምርጫ ቅስቀሳ ተጀምሮ ነበር)፡፡ ለዚህ ነው ገዢው ፓርቲ ሁል ጊዜ የሚጮሁት ካርድ ያልያዙ ናቸው የሚለው፡፡ ያስመዘገባቸውን ስለሚያውቅ ነው፡፡ የእኛ መራጮች ካርድ ባልያዙበት ሁኔታ የፈለገ አማላይ የሆነ ለሀገር የሚጠቅም አማራጭ ብናቀርብ ለማሸነፍ ያለን እድል አነስተኛ ነው፡፡
ማስተላለፍ የፈለኩት ነጥብ ምርጫ እገባለሁ-አልገባም በሚል ዥዋዝዌ ስንጫወት ደጋፊዎቻችን በመራጭነት ሳይመዘገቡ እንዳይቀሩ በአንድነት በኩል የተወሰደው እርምጃ ትልቅ ፖለቲካ ውሳኔ ነው፡፡ የምርጫ ፓርቲ መሆናችን የሚታወቅ ቢሆንም እስከ አሁን በተቃዋሚ ፓርቲዎች መስመር ምርጫ መግባትና አለመግባት በቁርጥ ቀድሞ ስለማይወሰን መራጮች ሁለት ልብ እየሆኑ ከጫወታ ውጭ ሲደረጉ ከርመዋል፡፡ ይህ እንዳይደግም መራጮች እንዲመዘገቡ እና በምርጫው ሙሉ ሂደት በንቃት እንዲሳተፉ ይህን አቋም መያዝ እጅግ አስፈላጊ እና ጠቃሚ ነበር፡፡ ሁሉም እንደሚረዳው ያልተመዘገበ ደግሞ አይመርጥም፣ ያልመረጠ ደግሞ ድምፁ እንዲከበር ዘብ ሊቆም አይችለም፡፡ ድምፃችን ይከበር የሚለው እንቅስቃሴ የሚጀምረው ከህዝብ ታዛቢዎች ምርጫ እሰከ ድምፅ ቆጠራ ድረስ ይዘልቃል፡፡
ጎበዝ ሰላማዊና ህጋዊ ትግል እናደርጋልን ስንል የሰላማዊና ህጋዊ ትግል መርዖዎችን ጠንቅቀን መረዳት የግድ ይለናል፡፡ በስላማዊ ትግል ዋናው ግብ የህዝብን የስልጣን ባለቤትነት ማረጋገጥ ሲሆን፣ ስልጣን መያዝ የሚፈልግ ፓርቲ የህዝብ ይሁንታ ማግኘት የግድ ይለዋል፡፡ ይህ ደግሞ በምርጫ የሚገኝ ነው፡፡ ምርጫውን የህዝብ ፖለቲካ ተሳትፎ መለኪያ አድርገን ለመውስድ ቁርጠኞች መሆን የግድ ይለናል፡፡
ቸር ይግጠመን

እናታችን ፋናዬና ተመስገን በዝዋይ…. (የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም እንደፃፈው)

ከታሪኩ ደሳለኝ 
(የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም)
ያቺ የስምጥ ሽለቆ ከተማ ይበልጥ መንደድ ከጀማመራት አንድ ወር አልፏታል:: በፍትህ መዛባት ስሜቱ የተጎዳ፣ በወገኖቹ ስቃይ መንፈሱ የታመመ፣ ሀገራቸውን ከስቃይ መታደግ በሚችሉበት እድሜያቸው በታሰሩ፣ በተሰደዱና በተገደሉ ወገኖቹ ልቡ ያዘነ፣ ለሀገሩና ለባንዲራው ያለው ፍቅር ጥልቅ የሆነ አንድ ወጣት ጋዜጠኛ በውስጧ ይዛለች፡፡ ዝዋይ፡፡
ከዚህች ከተማ ሦስት ኪሎ ሜትር ገደማ ወደሚርቀው የዝዋይ እስር ቤት ለመሄድ የአስፓልት ዱካ እንዳረፈበት በሚያሳብቀው ኮሮኮንቻማ መንገድ ማለፍ የግድ ይላል፡፡ ከረጅም ዓመታት በፊት ተሰርቶ ዛሬ አስታዋሽ ያጣው ይህ ጎዳና እስረኞችን የመጠየቁን ጉዞ አስቸጋሪ አድርጎታል፡፡ ከፀሐዩ ግለት ትይዩ ያለው የመሬቱ አቧራ በእግሩ ቆሞ ይሄዳል ብል አይበዛበበትም፡፡ ይህን አልፈን ግዞት ቤቱን እናገኛለን፡፡ የእስር ቤቱን መግቢያ ያለበሰው አቧራ ደግሞ ቅጥሩን በቁፋሮ የተገኘ ጥንታዊ ከተማ አስመስሎታል፡፡ የግቢው ገፅታ ለዕይታ በማይስቡ ነገሮች ቢከበብም፣ ተናፋቂውን ብዕረኛ ግን ደጋግሜ እንድጠይቀው ከወንድምነት የሚዘለው ጥንካሬው ይስበኛል፡፡
በአቧራውና በንዳዱ መካከል ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከቀድሞ ይልቅ በጠነከረ ፅናቱ ስለመኖሩ ሳስብ ደስተኛ እሆናለሁ፡፡ እናታችንስ ምን ታስብ ይሆን? የማይበርድ፣ የማይዳፈንና የማይጠፋ የሀገር ፍቅር ስሜቱ ከአቧራውና ከንዳዱ በላይ መሆኑ ለእርሷ ምን ስሜት ያጋባባታል?
yetemesgen enat
እናታችንና ተሜን ሲገናኙ…
ዛሬ ቅዳሜ ህዳር 20/07 ዓ.ም ነው፡፡ እናቴ አብረዋት ከኖሩ ጎረቤቶቿ ጋር በመሆን፣ ዝዋይ እስር ቤት ከከተመ አንድ ወር ያለፈውን ተመስገንን ልታየው ተሰናድታለች፡፡ ዝዋይ ከሄደ ወዲህ አይታው አታውቅም፡፡ እንደናፈቃት ግን የፊቷ ገፅታ ይመሰክራል፡፡ እንደ ልጅነቱ ፀጉሩን ባትደባብሰውም፤ እጁን ልትነካውና በዕርጅና አንደበቷ ‹እንዴት ነህ?› ልትለው ወደዚያው እያቀናች ነው፡፡ ጠዋት ወጥተው ማታ እንደሚገቡት፣ ክፍለ-ሀገር ሰንብተው እንደሚመለሱት እንደ ጓደኞቿ ልጆች ተመስገን እንደማይመለስ የተረዳችው እናታችን ልጇ ጋር እየሄደሰች ነው፡፡
ለሊት 11፡30 ከጀሞ ኮንዶሚኒየም የተነሳችው መኪና ዝዋይ የደረሰችው ከጠዋቱ 2፡20 ላይ ነበር፡፡ አስፋልት መሰል ፍርስራሽ መንገዱን ስለለመድኩት ነው መሰለኝ ዛሬ አልሰጠኝም፡፡ ፍተሻውን አልፈን እስረኛና ጠያቂ የሚገናኘበት ቦታ ላይ ደረስን፡፡ ከነበርነው ሰዎች ይልቅ እናታችን ጉጉት እንዳደረባት ለመናገር ሁኔታዋን ማየት ብቻ በቂ ነው፡፡
እናታችን ተመስገን በልጅነቱ ከዕኩዮቹ ጋር ተጫውቶ ሲመጣ ጠብቃዋለች፣ ትምህርት ቤት ውሎ ሲመጣ ጠብቃዋለች፣ ስራ ውሎ ሲመጣ ጠብቃዋለች፤ አንዳንዴም ሲያመሽ ደውላ ‹‹አልመሸም፤ የቀረው ለነገ ይቆይህ›› ትለዋለች፤ እርሱም ሁሌ እንደሰማት ነበር፡፡ ዛሬ ግን ልጇን የምትጠብቀው ከትምህርት ቤት አልያም ከጨዋታ ወይም ከስራ አይደለም፡፡ ከእስር ቤት ውስጥ እንጂ!
እናታችን እስረኞች ከሚወጡበት በር ላይ ከተቀመጠችበት ደቂቃ ጀምሮ አይኗን አላነሳችም፡፡ በሩ ሲከፈት የወታደር ልብስ የለበሰ ወጣት ወጣ፡፡ ከወታደሩ በኋላ ተሜ እስካርፉን እንዳደረገ ተከተለ፡፡ እናቴ ከመቀመጫዋ ተነሳች፤ ዐይኗቿ እንባ አዘሉ፡፡ በዕስረኛና በጠያቂ መሀል ያለውን አጥር ተደገፈች፡፡ ሌላ ጊዜ አጥሩን መደገፍ የሚከለክሉት ወታደሮች እናታችንን ግን ጥቂት ታገሷት፡፡ ምን ያድርጉ? እነሱም እኮ እናት አላቸው፡፡ ከተመስገን ኋላ ሌላ ወታደር አለ፡፡ በሁለት ወታደሮች መካከል ሆኖ ተሜ እናቱን አያት፤ ፈገግ አለ፡፡ እየቀረበ ሲመጣ ግን ፈገግታው ከፊቱ ላይ ጠፍቶ በሀሳብ ተተካ፡፡ እናቴን በዚህ እድሜዋ አንከራተትኳት ብሎ እንዳላሰበ እርግጠኛ ነበርኩ፡፡ ከዚህ ይልቅ ስንትና ስንት እናቶች በየቦታው እየተንከራተቱና እየተሰቃዩ ስለመሆናቸው እያሰበ የተጨነቀ ይመስላል፡፡ እናትና ልጅ አንገት ለአንገት ተቃቅፈው ቆዩ፡፡ ምን አለ ባይለያዩ? እንዲሁ እንዳሉ ወደ ቤት ቢሄዱስ ምን ነበረበት?
ይሄ ግን አይሆንም፤ ይሄ ቦታ ተሜ ለሀገሩ የከፈለውን፣ እየከፈለ ያለውንና የሚከፍለውን መስዋዕትነት ማቅረቢያው ቦታ ነው፡፡ ተሜ ወደ ቤት አይሄድም፡፡
ተሜና እናቴ የተጫወቱት ብዙ ነው ፡፡ ሲገናኙ የነበረው ድባብ ጠፍቶ ሁለቱም ደስ ብሏቸዋል፡፡ ተሜ ትንሽ አይቷት ‹‹ከስተሻል›› ሲላት ፈገግ እንዳለች ‹‹አረ አልከሳሁም፤ አንተ ግን ጤናህ እንዴት ነው?››፤ ‹‹ደህና ነኝ››… እናቴ በየመሀሉ ጨዋታቸውን ገታ እያደረገች በስስት ታየዋለች፡፡ እናትና ልጅ የሆድ የሆዳቸውን እንዲያወሩ የፈቀዱት ወታደሮችም ሁለቱን በስስት የሚያዩ ይመስላሉ፡፡
ሳይታወቀን 6፡00 ሆነ፡፡ የመሰነባበቻ ጊዜ ደረሰ፡፡ እናቴ እየሳቀች አቀፈችው፤ ተሜም እየሳቀ ተሰናበታት፡፡ እንደ አመጣጡ በሁለቱ ወታደሮች መካከል ሲሄድ ከጀርባው ትክ ብላ አየችው፡፡ የሆነ ነገር ልትል የፈለገች ትመስላላች፡፡ ‹‹ተመስገን›› አለች፤ አልሰማትም፡፡ በሩን አልፎ ገባ፡፡ እሱ ፊት የደበቀችውን እንባ ማቆም አልቻለችም፡፡ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ከፈገግታዋ ጋር አለቀሰች፡፡
እሁድ ህዳር 21/07 ከንጋቱ 12፡00 ሰዓት፡፡ እናቴ ልጇ እስኪፈታ አልጋ ላይ አልተኛም ብላ መሬት መተኛት ከጀመረች 1 ወር ከ17 ቀኗ ነው፡፡ የዛሬውን ለሌት እንዳለፉት ጊዜ አንዴም ተነስታ ‹አይ ልጄ› ወይም ‹እህህ….እህህ….› ሳትል በሰላም ተኝታ በማደሯ ሳልተኛ እያየኋት አደርኩ፡፡ ልክ 12፡10 ሲል ነቃች፡፡ ስታየኝ እያየኋት ነው፡፡ ‹‹ስንት ሰዓት ሆነ?›› ነገርኳት፡፡ አላመነችም፡፡ ተሜ ከታሰረ ጀምሮ እንደ ዛሬ ተኝታ አታውቅም፡፡ ተነሳች፡፡ ‹‹እስከዚህ ሰዓት ስተኛ ዝም ትላለህ?›› አለችኝ፡፡ ‹‹እንዴት ዝም አልልም?›› አልኳት፡፡ ‹ዛሬ የዓመቷ ማሪያም ነች› አለችኝ፡፡ ፊቷ ላይ ድካም አይታይባትም፡፡ … ከደቂቃዎች በኋላ የሀገር ባህል ጥበብ ቀሚስ ለብሳ አየኋት፤ አምሮባታል፡፡ የደስታ ሲቃ ይዞኝ ‹ትላንት እንዴት ነበር?› አልኳት፡፡ በፈገግታ እያየችኝ ‹‹ልጄ ጀግና ነው፤ ጀግና›› ስትል መለሰችልኝ፡፡ እኔም በመስማማት ራሴን ነቀነኩ፡፡ እናቴ በንጋት ፀሐይ ታጅባ የሀገር ባህል ልብሷን እንደለበሰች ስትሄድ በዐይኔ ተከተልኳት፡፡ ይሄ ብርታቷ እስከመቼ እንደሚቆይ እያሰብኩ ነበር፡፡
ተሜ ለሀገሩ ሲልና ሀገሩ እንድትሆን የሚመኝላትን በመፃፉ በግዞት እስር ቤት በአቧራና በንዳድ መሀል እንዲሰነብት ተፈርዶበታል፡፡ ፍትህ የነገሰባት፣ ልጆቿ የማይገደሉባትና የማይሰደዱባት ኢትዮጵያ እንደምትመጣ በተቃጠለ ስሜት እያሰበ፣ በማለዳ የወጣችውን የንጋት ፀሐይ በፈገግታ እያያት እንደሆነ ሳስብ እኔም በደስታ ተሞላው፡፡

fredag 28. november 2014

የሕወሐት/ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ፒ.ኤች.ዲዎችን ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ተቋማት እየገዙ እንዳሉ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ።


እየሩሳሌም አርአያ
የሕወሐት/ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ፒ.ኤች.ዲዎችን ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ተቋማት እየገዙ እንዳሉ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሐጐስ ጐደፋይና ምክትላቸው አቶ አታክልቲ እንደሚገኙበት የጠቀሱት ምንጮቹ ለሁለቱ ባለስልጣናት በመቀሌ ሆስፒታል የሚሰራ የባዮስታቲክስ ባለሙያ በኩል የጥናት ፕሮፖዛላቸውን አሰርተው ፕሮፖዛሉ ፀድቆ ዋናውን ጥናት ይህ ባለሙያ ግለሰብ እየሰራላቸው እንደሚገኝ አያይዘው ገልፀዋል። ባለስልጣናቱ ስለጥናቱ አንዳችም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ምንጮቹ አጋልጠዋል። ሌሎች ስድስት የህወሀት ባለስልጣናትም የማስተርስና ፒ.ኤች.ዲ ጥናት እየፃፈላቸው እንደሚገኝ ምንጮቹ አክለው ገልፀዋል። ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎችም የዚህ ህገወጥ ተግባር ተሳታፊዎች ናቸው ያሉት ምንጮቹ በተለይ ሪፍት ቫሊ የተባለውን የግል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሚስተካከል የለም ብለዋል። የኦህዴድ ባለስልጥናት ባለድርሻ የሆኑበት ይህ ዩኒቨርሲቲ ገንዘብ ለከፈለ ሁሉ ሰነድ አዘጋጅቶ ዲግሪና ማስተርስ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።