NOVEMBER 28, 2014 LEAVE A COMMENT
እየሩሳሌም አርአያ
የሕወሐት/ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ፒ.ኤች.ዲዎችን ከተለያዩ የሀገር ውስጥና የውጭ ተቋማት እየገዙ እንዳሉ የቅርብ ምንጮች አስታወቁ። የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ የሆኑት አቶ ሐጐስ ጐደፋይና ምክትላቸው አቶ አታክልቲ እንደሚገኙበት የጠቀሱት ምንጮቹ ለሁለቱ ባለስልጣናት በመቀሌ ሆስፒታል የሚሰራ የባዮስታቲክስ ባለሙያ በኩል የጥናት ፕሮፖዛላቸውን አሰርተው ፕሮፖዛሉ ፀድቆ ዋናውን ጥናት ይህ ባለሙያ ግለሰብ እየሰራላቸው እንደሚገኝ አያይዘው ገልፀዋል። ባለስልጣናቱ ስለጥናቱ አንዳችም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ምንጮቹ አጋልጠዋል። ሌሎች ስድስት የህወሀት ባለስልጣናትም የማስተርስና ፒ.ኤች.ዲ ጥናት እየፃፈላቸው እንደሚገኝ ምንጮቹ አክለው ገልፀዋል። ሌሎች የአገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎችም የዚህ ህገወጥ ተግባር ተሳታፊዎች ናቸው ያሉት ምንጮቹ በተለይ ሪፍት ቫሊ የተባለውን የግል ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የሚስተካከል የለም ብለዋል። የኦህዴድ ባለስልጥናት ባለድርሻ የሆኑበት ይህ ዩኒቨርሲቲ ገንዘብ ለከፈለ ሁሉ ሰነድ አዘጋጅቶ ዲግሪና ማስተርስ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar