mandag 30. september 2013

ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል በኦስሎ ኖርዌ የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሄደ


ለግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል የገቢ ማሰባሰቢያ በኖርዌ ኦስሎ ከተማ ሴፕቴምበር 28, 2013 ለመጀመሪያ ጊዜ ተካሂዶ በደማቅ ሁኔታ የተከናወነ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ከፍተኛ አመራር ኮማንደር አሰፋ ማሩ እና የግንቦት ሰባት ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲሁም ከተለያዩ ሃገራት የተገኙ እንግዶች የተሳተፉበት ዝግጅት ነበር።

በዝግጅቱ መክፈቻ ላይ የግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይሉ መዝሙር በወጣት ዘማሪያን የቀረበና ህዝቡም በከፍተኛ ስሜት የሃገር ፍቅር እያንገበገበውና ግማሹም በማልቀስ ስሜቱን የገለፀበት ዝማሬ ነበር። በመቀጠል የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጀት በኖርዌ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዳዊት መኮንን የመክፈቻ ንግግር  ካደረጉ በኋላ የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይሉ መድረኩን በመቀበል ስለድርጅታቸው ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ከህዝቡ የቀረበላቸውንም ጥያቄዎች በስፋት አስረድተዋል። አቶ አንዳርጋቸው ፅጌም ለታዳሚው በምስል የተደገፈ ሰፋ ያለ መረጃ ሰጥተው ክህዝቡም የቀረበላቸውን ጥያቄዎች ለህዝብ በሚገባና ግልፅ በሆን ሁኔታ አስረድተዋል።



በተጨማሪ የተለያዩ ቀስቃሽ ሙዚቃዎች፡ ጨረታዎች እንዲሁም ምግብና መጠጥ እንዲሁም የትጥቅ ትግል ለምን አስፈለገ በሚል ገላጭ የሆነ አጭር ድራማ ቀርቧል። በአንፃሩ ይህንን ዝግጅት እንዳይሳካ ለማድረግ የወያኔ ተላላኪዎች እንቅልፋቸውን አጥተው  ሙከራ ቢያደርጉም አይናቸው እያየ ጆሯቸው እየሰማ ዝግጅቱ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ከፍተኛ የገቢ ማሰባሰቢያ ተደርጎ ዝግጅቱ በደማቅ ስነስርአት ተከናውኗል።  



ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር
ዲቦራ ለማ/ኖርዌ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar