onsdag 22. januar 2014

ፍኖት – የአንድነት ፓርቲ አባል ከጠቅላላ ጉባኤ ምግስት ጀምሮ በእስር እየተንገላቱ ነዉ

አቶ አለማየሁ ለፌቦ የተባሉ በሲዳማ ጭሬ የአንድነት ፓርቲ አባል ከፓርቲው ጠቅላላ ጉባኤ ማግስት ወደ ክልሉ ሲመለሱ አርሲ ሚጣ ነሴቦ ወረዳ ወርቃ ከተማ ታህሳስ 26 ቀን 2006 ዓ.ም እንደተያዙ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ከታሰሩበት ወረዳ ያንተ ጉዳይ የፖለቲካ ጉዳይ ስለሆነ እዚህ አይታይም በማለት ጥር 9 ቀን ወደ ሻሸመኔ ዞን ፖሊስ ተወስደው ታሰሩ፡፡
alemayehu_lessebo
ፖሊስ ጣቢያውም እንድትለቀቅ ከፈለግክ 1ኛ እስከዛሬ የታሰርኩበትን አልጠይቅም 2ኛ ከዚህ በኋላ ወደ ፖለቲካ አልገባም 3ኛ በተፈለኩኝ ሰዓት እቀርባለሁ ብለህ ፈርምና ውጣ የሚል ቅድመ ሁኔታ ቢያቀርብላቸውም አቶ አለማየሁ ግን በሰላማዊ መንገድ የሚታገልና በምርጫ ቦርድ ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ፓርቲ አባል ነኝ ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም፣ በፍጹም አልፈርምም ብለዋል፡፡
በ 5 ክስ ከሰንሃል 4ቱን ውድቅ አድርገናል በአንዱ ግን እንከስሃለን በሚል ለማስፈራራት ቢሞክሩም አቶ አለማየሁ በአቋማቸው ጸንተዋል፡፡ የሻሸመኔ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ተጫን ለምን እስካሁን ፍርድ ቤት እንዳልቀረቡ ለመጠየቅ በተደጋጋሚ ብንደውልም ልናገኛቸው አልቻልንም፡፡ አቶ አለማየሁ በአሁኑ ሰዓት ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በሻሸመኔ ዞን ፖሊስ ጣቢያ በአደራ ታሰረው የሚገኙ እስረኛ ናቸው፡፡

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar