(ዘ-ሐበሻ) አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው “ህወሓት/ኢህአዴግ የትግራይ ህዝብ አማራጭ ሀሳብ እንዳያገኝእያካሄደ ያለውን አፈና አጥብቀን እንቃወማለን” ሲል አወገዘ።
“ህወሓት/ኢህአደግ ክልሉን እንደዋና ካምፕ በማየት በአፈና ውስጥ እንዲኖር አድርጎታል፡፡ የትግራይ ህዝብ የነፃ ፕሬስ ውጤቶችን እንዳያገኝ፤አማራጭ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዳያዳምጥ የተፈረደበት ሕዝብ ነው ማለት ማጋነን አይደለም፡፡ ይሄ እውነትም ሕወሓት/ኢህአዴግ በተለያየ ጊዜበህዝቡ ላይ በፈፀማቸው ኢ-ዴሞክራሲያዊና ኢ-ፍትሃዊ ድርጊቶች የታየ ነው፡፡” የሚለው የአንድነት መግለጫ ” ለዚህ ማሳያ የሚሆነው አምባገነኑህወሓት/ኢህአዴግ አረና ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል አዲግራት ከተማ ሊያደርግ የነበረው ሕዝባዊ ስብሰባ ልክ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉታፍኖበታል፣ አባላቱ ተደብድበዋል እንዲሁም ታስረዋል፡፡ ይሄ የሆነበት ምክንያት የትግራይ ህዝብ አማራጭ እንዳያገኝና በጉልበት የህወሓት አንጡራሀብት ብቻ ሁኖ እንዲያገለግል ከመፈለግ ነው፡፡ ከዚህ በፊትም ፓርቲያችን በመቀሌ ከተማ ሊያደርግ የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ በከፍተኛ አፈናና እስርእንዲያስተጓጉል መደረጉ የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲ የትግራይ ህዝብ አማራጭ ሓሳብ የማዳመጥ፣ የሚጠቅመውን የመምረጥናየመቃወም ሕገ-መንግስታዊ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን በፅኑ ያምናል፡፡” ብሏል።
አማራጭ ሓሳብ በሚያቀርቡ ፓርቲዎች ላይ ህወሓት/ኢህአዴግ እየወሰደ ያለውን ኢ-ዴሞክራሲያዊ ርምጃና አፈና በጥብቅ እንደሚያወግዝያስታወቀው አንድነት “አንድነት የአረና ፓርቲ የሚያደርገውን ዴሞክራሲያዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ ህወሓት/ኢህአደግ ለማደናቀፍ የሚያደርገውንህገወጥ ዘመቻ እንዲያቆም እየጠየቀ አሁንም ተቃዋሚዎችን ‹‹ከጠላቶቻችን ጋር የሚተባበሩ›› በማለት የትግራይን ህዝብ ከሌላው ኢትዮጵያዊለመነጠል የሚካሄደውን ዘረኝነት የተሞላበት ከፋፋይ ርምጃ ለአገራችን እጅግ አደገኛ እንደሆነ አምኖ እንደ ሌላው ህዝብ ሁሉ ለነፃነቱ መከበርየሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ እንዲቀጥልና ሰላማዊ ትግሉን በመደገፍ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን እንዲሆን የከበረ ጥሪ እናቀርባለን፡፡” ሲልመግለጫውን ቋጭቷል።
https://www.zehabesha.com/amharic/archives/12295
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar