torsdag 27. februar 2014

የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረዕት ነጻ ፕሬሶችን አስጠነቀቀ !

ኢዜአ የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማህበር ሊቀመንበርን ጠቅሶ ባስተላለፈው ዜና የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ዳግም በነጻ ፕሬሶች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጦል። እንደ ዜናው ዘገባ በአሸባሪነት ተፈርጀው በህግ ቁጥጥር ስራ  በሚገኙ ዙሪያ አንዳንድ ጋዜጦች የተዛባ ውዥንበር በህዝብ መሃል  በመንዛት ድብቅ አጀንዳቸውን ያራምዳሉ ብሏል።
የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ሰሞነኛ ፉከራ  መጪውን ሃገራዊ ምርጫ ተከትሎ የተቃዋሚ ሃይሎች በህዝብ ዘንድ ድጋፍ እያገኙ እና እያንሰራሩ መመጣታቸው  እንዳስደነገጠው የሚናገሩ ወገኖች  ከብሄራዊ ምርጫ በፊት የህዝብ ልሳን የሆኑትን የነጻ ፕሬስ ጋዜጦችን በማጥፋት የህዝብን ድምጽ፡ለማፈን እያደረገ ያለው  ዘመቻ አንዱ አካል መሆኑንን  ይስማሙበታል ። በ1997 እ.ኢ.አ በኢትዮጵያ የተካሄደውን ብሄራዊ ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ውዝገብ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መግስት ኮሮጆ ገልብጦ ጠንካራ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማጥፋት ብቻውን እሩጦ በዴሞክራሲ ሽፋን አለም አቀፉን ማህበረሰብ  ሲያደናገር የነበር ስረአት መሆኑንን የሚገልጹ የፖለቲካ ተንታኞች ሀግሪቱን ያለተቀናቃኝ ለ20 አመታት ረግጦ መግዛቱን በመጥቀስ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለሰ ዜናዊ ሞት በሃላ  በአባልቱ መሃከል የነበሩ  አለመግባባቶች ፈር እይለቀቁ መምጣታቸውን ተከትሎ    ድርጀቱ ከእንግዲህ እንደ መንግስት መቀጠል እንደማይችል  ይናገራሉ።  ይህ በዚህ እንዳለ  የነጻውን ፕሬስ አባላት በመግደል እና በማፈን የሚታወቀው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መግስት ኢትዮጵያ ውስጥ አቋጥቁጦ የነበርን   ዲሞክራሲያዊ ስረአት በመቀልበስ  በአለም አቀፍ ደረጃ ከለየላቸው አንባ ገነን  መንግስታቶች ግንባር ቀደም  መሆኑ ይታወቃል።
  አቶ   ታምራት ይህደጎ  ከቨርጅኒያ

mandag 24. februar 2014

ወጣቱ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ቦሌ መንገድ ላይ ራሱን አጠፋ


በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው














ዛሬ በምሳ ሰዓት አካባቢ፤ በሱፍቃድ በጋሻው የተባለ ዕድሜው በሃያዎቹ ውስጥ የሚገመት ወጣት በቦሌ መንገድ ላይ ከአራት ጊዜ በላይ በተከታታይ ወደ ሰማይ ከተኮሰ በኋላ ራሱን አጠፋ። ራሱን ከማጥፋቱ በፊት ”ኑሮ መሮኛል” ሲል ተሰምቷል።

ቦሌ መንገድ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በሚገኝ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በጥበቃ ሥራ ላይ የነበረው ወጣቱ በሱፍቃድ ለምሳ ተቀይሮ ሲገባ ከሥራ ባልደረባው ላይ የተቀበለውን የጥበቃ መሣሪያ ተቀብሎ ለጊዜው ምን እንደኾነ ያልታወቀ (እስካሁን እኔ ያላወኩት) ነገር እየተናገረ እየሮጠ ወደ ሰማይ አራት ጊዜ ያህል ከተኮሰ በኋላ አገጩ ላይ አስደግፎ ወደ ጭንቅላቱ በመተኮስ ራሱን አጥፍቷል።
በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው
በአሁኑ ሰዓት አስክሬኑን ሰማያዊ የሚበዛበት ዥንጉርጉር ጨርቅ ሸፍነውት መንገድ ላይ ተኝቷል። የደንብ ልብሱን እደለበሰ ሲኾን፤ አጠገቡ በጥይቱ የተበሳ ኮፍያው ወድቋል። የጭንቅላቱ ስጋ እና አጥንቶቹ ተበታትነዋል።

በሱፍቃድ አጋር የተባለው የጥበቃ ሥራ የሚሠራ ኤጀንሲ ተቀጣሪ መኾኑን እና ሕብረት ባንክ ከመጣ ሁለት ወር አካባቢ እንደኾነው የሥራ ባልደረቦቹ ነግረውኛል። አሁን በተገኘ መረጃ ”ኑሮ መኖኛል” ሲል ተሰምቷል። እዛ አካባቢ ያሉ ፖሊሶች ደግሞ በምን እንዳወቁ አላውቅም ከቤተሰቡ ተጣልቶ ነው ብለዋል። አሁን አስክሬኑኑን የፖሊስ መኪና አንስቶታል።


በቦሌ መንገድ ላይ ”ኑሮ መሮኛል” በማለት ራሱን ያጠፋው ወጣት በሱፍቃድ በጋሻው











ምንጭ ኢትዮጵያ ዛሬ

søndag 23. februar 2014

ከ15 ሺህ ህዝብ በላይ የተሳተፈበት ሰላማዊ ሰልፍ በባህር-ዳር [ፎቶ]

የተለያዩ መፈክር ያነገቡ ሰልፈኞች በባህር ዳር የአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት አካባቢ በመገኘት ሰልፉን ሲጠባበቁ ነበር በአሁኑ ሰዓት ከ15 ሺህ የሚበልጥ ህዝብ ሰልፉን ተቀላቅሏል:: የአንድነት ፓርቲ ፕሬዝዳንት ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሃሪ እንዲሁም የትብብር ለዴሞክራሲ ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ እንዲሁም የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት አባል የሆኑት አንጋፋው ፖለቲከኛ ዶ/ር ኃይሉ አርአያን ጨምሮ ሰልፉን በቀዳሚነት እየመሩ ይገኛሉ::
በአማራ ክልል የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነው መኮንን በአማራ ህዝብ ላይ የሰነዘሩትን ዘለፋ በመቃወም ነው የባህር ዳር ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረገው።
ድል የህዝብ ነው!! ኢትዮጵያዊ አንድነታችን ከልዩነታችን በላይ ነው!!  ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል!!  ብአዴን የአማራውን ሕዝብ አፍኖ መግዛት ያቁም!! የኢሀደግ አምባገነን አገዛዝ ሰልችቶናል!! የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ ይገኛሉ።

የመከላከያ ተቋም ተግባር አገርን መጠበቅ ነዉ ወይስ አገርን መዝረፍ?

የአዉሮፓ ቅኝ ገዢዎች አፍሪካን ሲቀራመቱ ባህር ተሻግረዉ በመጡ የነጭ ባዕዳን ኃይሎች መገዛትን መርጦ የአዉሮፓን ወራሪዎች በሰላም በሩን ከፍቶ ወደ አገሩ ያስገባ እንድም የአፍሪካ አገር አልነበረም፤ የኋላ ኋላ ተሸንፈዉ በቅኝ አገዛዝ ቀንበር ስር ቢወድቁም ሁሉም የአፍሪካ አገሮች እንደ አቅማቸዉ ከወራሪ ኃይሎች ጋር ተፋልመዋል። በአንድ ወቅት የቅርብ ጎረቤቶቻችንን ጨምሮ ብዙዎቹ የአፍሪካ አገሮች በወራሪ ኃይሎች ተሸንፈዉ የቅኝ ገዢዎች ቀንበር ጀርባቸዉ ላይ ሲጫን አገራችን ኢትዮጵያ ብቻዋን የአለም ጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተምሳሌት ሆና የኖረችዉ ጣሊያኖች፤ እንንግሊዞችና ፈረንሳዮች ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ለይተዉ ስለወደዷት ወይም ስላከበሯት አይደለም። ይልቁንም ነፃነታችንና የግዛት አንድነታችን ተከብሮ የኖረዉ ኢትዮጵያ እናት አገሩ በጠላት ስትደፈር ከሚያይ ምትክ የሌላት ህይወቱ ብታልፍ ደስ የሚለዉ የኩሩና የጀግና ህዝብ አገር በመሆኗ ነዉ። የሚገርመዉ ይህ ኩሩና ጀግና ህዝብ ጣሊያንን የመሰለ በዘመናዊ መሳሪያ የታጀበ ኃይል ዉርደቱን ተከናንቦ ወደመጣበት እንዲመለስ ሲያስገድድ እንደ ዛሬዉ የተደራጀ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት አልነበረዉም። ዛሬ አራት ኪሎና ስድስት ኪሎ ላይ የተተከሉት ሁለቱ ታሪካዊ ሀዉልቶቻችን የሚነግሩንም ይሀንኑ የኢትዮጵያ ህዝብ በዘመናዊ መልክ የተደራጀ ሠራዊት ሳይኖረዉ የጎበዝ አለቃ እየመረጠ በጣሊያን ፋሺስቶች ላይ የተጎናጸፈዉን አኩሪ ድል ነዉ።
ኢትዮጵያ ዉስጥ ዘመናዊና የተደራጀ መከላከያ ሠራዊት ጥንስስ የተጣለዉ በዳግማዊ ሚኒልክ ዘመነ መንግስት ሲሆን እሱም ቢሆን ከአድዋ ድል በኋላ ቆይቶ የመጣ ክስተት ነዉ። በአፄ ኃ/ሥላሤና በደርግ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያ ለአንድ ፓርቲና ይህ ፓርቲ እወክለዋለሁ ለሚለዉ ህዝብ ብቻ ሳይሆን ሙያዊ ብቃት የነበረዉ፤ሙያዉን የሚያከብርና ለአገሩና ለወገኑ ታማኝ የሆነ የመከላከያ ሠራዊት ነበራት። የወያኔ ዘረኞች አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ የመጀመሪያ ኢላማቸዉ አድርገዉ ካወደሟቸዉ ዋና ዋና የአገራቸን ተቋሞች ዉስጥ የመጀመሪያዉ ይሄዉ የአገርና የህዝብ ደጀን የነበረዉ ተቋም ነበር። ዛሬ ኢትዮጵያ ዉስጥ የአገር መከላከያ ሠራዊት እየተባለ የሚጠራዉ ተቋም ለጎጠኞች ጥቅምና የስልጣን መራዘም የቆመ፤ በዘረኝነት የተካፋፈለ፤ ይህ ነዉ ተብሎ የሚጠቀስ ሙያዊ ብቃት የሌለዉና የወገንና የአገር ፍቅር እንዳይኖረዉ ተደርጎ የተደራጀ ሰራዊት ነዉ። ይህንን ሠራዊት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ሳይሆን የወያኔ ሠራዊት እያልን የምንጠራዉም በዚሁ ምክንያት ነዉ።
ዛሬ ሙሉ በሙሉ በወያኔ ዘረኞች ቁጥጥር ስር የወደቀዉ የአገር መከላከያ ተቋም የሚታማዉ በዘረኝነት፤ በሙያ ብቃት ማነስና የአንድ ፓርቲ ጥቅም አስከባሪ በመሆኑ ብቻ አይደለም፤ ተቋሙ ከእነዚህ ዋና ዋና ጉድለቶቹ በተጨማሪ በቀድሞዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ተቋም ላይ በፍጹም ያልታዩ ሌሎች ትላልቅ ጉድለቶች አሉበት። ከእነዚህ ጉድለቶች ዉስጥ አንዱ የወያኔ የመከላከያ ተቋም ህገ መንግስቱ ከሰጠዉ ኃላፊነት ዉጭ በንግድና በንብረት ይዞታ ላይ ላይ መሰማራቱ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ከዚህ ፀባዩ ጋር ተያይዞ በመከላከያ ሠራዊት ተቋም ዉስጥ ከላይ እስከታች የሰፈነዉ ቅጥ ያጣ ሙሰኝነት ነዉ። ዛሬ የወያኔን የመከላከያ ተቋም፤ የህወሀትን ፓርቲና ኤፎርት በሚል ምህጻረቃል የሚታወቀዉን የወያኔን የገንዝብ ማምረቻ ድርጅት ነጣጥለን ወይም አንዱን ከሌላዉ ለይተን ማየት የማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰናል።
በላፈዉ አመት ወያኔ እራሱ ያቋቋመዉ ፀረ ሙስና ኮሚሺን የገንዘብ ዝርፊያን፤የንብረት መባከንንና መዝረክረክን አስመልክቶ ለፓርላማዉ ባቀረበዉ ሪፖርት ላይ ከጠቀሳቸዉ መንግስታዊ ተቋሞች ዉስጥ ቀዳሚዉን ደረጃ የያዘዉ የመከላከያ ተቋም ነዉ። ሆኖም ፓርላማዉም ሆነ የወያኔ አገዛዝ ለዚህ ሪፖርት የሰጡት ምላሽ የመከላከያና የደህንነት ተቋሞች ከአሁን በኋላ ያሻቸዉን ያክል ገንዝብ ቢዘርፉ የሂሳብ መዝገባቸዉ “ለአገር ደህንነት” ሲባል በኦዲት ኮሚሺን አይመረመርም የሚል ምላሽ ነበር። እንግዲህ ይህ በሙሰኝነት የተጨማለቀ፤ ለህግ የማይገዛና መጠበቅና መንከባከብ የሚገባዉን የአገር ኃብትና ንብረት የሚዘርፍ ተቋም ነዉ ባለፈዉ ሳምንት “የመከላከያ ቀን” ተብሎ አመታዊ በዐል የተከበረለት።
መናገሻ ከተማችን አዲስ አበባ ዉስጥ በየቦታዉ የሚታዩትን ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ሰርተዉ የሚያከራዩት የወር ደሞዛቸዉ ከ2500 ብር የማይበልጥ መከላከያ ሠራዊት ዉስጥ የተሰገሰጉ የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ፤ኢትዮጵያ ዉስጥ ትርፋማ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ ትላልቅ ሆቴሎች፤ የአገልግሎት ተቋሞችና የንግድ ድርጅቶች ከፍተዉ ቁጥር ስፍር የሌለዉ ኃብት የሚያጋብሱት የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ፤ ድሃዉና የወያኔ ዘረኝነት ሰለባ የሆነዉ ኢትዮጵያ ሰራዊት ለተመድ ተልዕኮ በተሰማራባቸዉ ቦታዎች ሁሉ ተመድ የሚከፍለዉን የቀን አበል ኪሳቸዉ ዉስጥ እየከተቱ ሚሊዮነሮች የሆኑትና በየዉጭ አገሩ ዉድ መኖሪያ ቤቶችንና የንግድ ተቋሞችን የሚገዙት የወያኔ ጄኔራሎች ናቸዉ። የወያኔ መከላከያ ተቋም ጉድ በዚህ ብቻ አያበቃም፤ ይህንን ወንጀለኛ ተቋም ቃላት እየደረደሩ ለመግለጽ ከመሞከር ይልቅ በጥቅሉ ወያኔ የኢትዮጵያን ህዝብ ኃብትና ንብረት እንዳሻዉ መዝረፍ እንዲችል የኃይል ሽፋን የሚሰጥ ተቋም ነዉ ማለት የሚበቃ ይመስለናል።
ወያኔና ስር የሰደደዉ ዘረኛ ስርዐቱ ከኢትዮጵያ ምድር ላይ እስካልተነቀሉ ድረስ ወያኔ ዝርፊያዉን የወያኔ መከላከያ ተቋምም የወያኔንና የደገፊዎቹን ዝርፊያ በመሳሪያ ማጀቡ አይቆምም። የወያኔን ዝርፊያ ለማስቆምና አገራችንን ከተጋረጠባት አሳሳቢ አደጋ ለመታደግ ብቸኛዉ መንገድ ወያኔን ከሥልጣን ማስወገድ ብቻ ነዉ። ግንቦት 7 የፍትህ፤የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የጀመረዉ ህዝባዊ ትግል እንደ አገር መከላያከያ አይነቶቹ ቁልፍ የአገር ተቋሞች በሚሰሯቸዉ ስራዎች ሁሉ የአገርንና የህዝብን ጥቅም እንዲያስጠብቁ ለማድረግ ነዉ። የግንቦት 7 ትግል አላማ የመከላከያ፤ የደህንነት፤ የፖሊስና የፍትህ ተቋሞች የአንድ ፓርቲ ጥቅም ማስከበሪያ መሳሪያዎች መሆናቸዉ አብቅቶ የአገርና የህዝብ አለኝታ እንዲሆኑ ነዉ፤ ሆኖም ይህንን ቅዱስ አላማ ወያኔ በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ ተግባራዊ ማድረግ ስለማይቻል ነፃነት፤ ፍትህ፤ዲሞክራሲ፤ ሠላምና እኩልነት የናፈቀዉ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወያኔን በፍጥነት እናስወግድ ከሚለዉ የአገር አድን አላማ ጎን እንዲሰለፍ ግንቦት 7 የትግል ጥሪዉን ያስተላልፋል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

fredag 21. februar 2014

አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።

andent ena mead
አንድነት እና መኢአድ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን በባህርዳር ቅስቀሳ እያደረጉ ነው።
የአማራ ክልሉ ባለስልጣን፤ “አማራው በባዶ እግሩ ነው የሚሄደው…” ብለው እጅግ የከፋ ዘለፋ ካሰሙ ብኋላ ህዝቡ በያለበት ስለ ሰውዬው ያፈረላቸው ቢሆንም እርሳቸው ግን ሳያፈሩ ትላንት በቴሌቪዥን መስኮት ተከስተው ሲያስቁን ነበር።
ዛሬ እንደሰማነው እና እንዳየነው፤ የመኢአድ እና አንድነት አባላት እሁድ ለጠሩት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ፤ በባዶ እግራቸው በመሆን ባደረጉት ቅስቀሳ “እኛም ጫማ የለንም፤ እኛም በባዶ እግራችን ነው የምንሄደው ቢሆንም ግን የሞራል ለዕልና አለን” የሚል ቅስቀሳ ሲያሰሙ ውለዋል።
በቅስቅሳው ወቅት ፖሊስ ጉልቤውን ሊያሳያቸው ቢሞክርም ህዝቡ ከበባ እያደረግ ሲከላከላቸው አንድነት ዛሬ ከለቀቀው ቪዲዮ አይተናል።
ድረ ገጻችን፤
…የምር ግን ህዘብ እየተዘለፈም እየተዘረፈም እንዴት ይችለዋል…. ???ብላ በትልቁ እየጠየቀች፤ አንድነት ያሰራጨውን ቪዲዮ ላላዩት እንድሚከተለው ታሳያለች።

tirsdag 18. februar 2014

Ethiopian political refugee living in London alleges he was victim of ‘unprecedented example of espionage on British soil’

The National Crime Agency has been asked to investigate the alleged use of computer software to spy on an Ethiopian political refugee living in London in an unprecedented example of espionage on British soil.
The charity Privacy International has made a criminal complaint to the agency’s National Cyber Crime Unit following the detection of the surveillance software FinSpy on a computer belonging to Tadesse Kersmo, who fled to Britain from Ethiopia in 2009.
FinSpy, a “Trojan” programme which was developed and produced by the British-German company Gamma International, allows a remote user to gain full access to a targeted computer and even to turn on functions such as microphones and cameras to record the computer’s owner without their knowledge.
Mr Kersmo, a university lecturer, claimed that he had been the victim of espionage by the Ethiopian Government because of his involvement with the political opposition group Ginbot 7. “I felt that the United Kingdom was a safe and free country but I was wrong and I feel very disappointed,” he said.
The FinSpy surveillance software first appeared on his computer in 2012 and was only detected after the issue was highlighted in a study by the Citizen Lab at the University of Toronto, which reported on a campaign to infect computers with FinSpy by sending a rogue email containing pictures of Ginbot 7 members.
Mark Scott, a lawyer with London firm Bhatt Murphy, said there was no legal justification for the software. “If your computer is in the UK and it’s intercepted and that’s without lawful authority then that is a crime. It’s very difficult to see what lawful authority.”
Mr Scott said he knew of no other similar incidents.
Mr Kersmo told a London press conference on Monday that documents and audio clips from Skype conversations involving him and other Ginbot 7 members had been published in doctored format online in order to discredit him. He said that the leaders of Ginbot 7 – a pro-democracy group formed from Ethiopian exiles in the United States and Europe – had feared they had a mole in their ranks. “The main purpose was probably to create suspicion among the executive committee members and it did to some extent.”
Calling on the NCA to investigate, he said: “It’s not only (about) my own personal liberty but also the UK’s interests and other Ethiopian citizens who live in the UK.”
Eric King, head of research for Privacy International, said: “Even when someone flees persecution in their own country, western-made surveillance technologies such as FinSpy can still be used by repressive regimes to monitor the moves of political activists anywhere around the world.”
The charity said that FinSpy was extremely difficult to detect. Trojan programmes are usually triggered by opening an email or download containing the invasive software.
According to the Citizen Lab research, command and control servers for FinSpy have been set up in 35 countries, including Ethiopia, Turkmenistan, Bahrain and Malaysia. Privacy International has asked HMRC to say whether Gamma International has an export licence for distributing the software to these regimes. Mr Scott said: “If the software needs to be exported to a country outside the European Union it requires an export licence. As far as the information we have, there has been no licence granted to Ethiopia or indeed any other country.”
John Campbell, a senior lecturer at the University of London’s SOAS, said the FinSpy case had “extensive implications” for the Home Office and could lead to more asylum claims if political opponents were being subjected to computer espionage. He said that scores of Ethiopian political dissidents had been arrested since the 2005 national elections and that some had been given life sentences.
Gamma International could not be reached for comment

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጠለፈበትን ምክንያት ለማወቅ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንደቀጠሉ ነው


የካቲት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አየር መንገዱ ከአዲስ አበባ ወደ ሮም ጣሊያን በማምራት ላይ በነበረበት ጊዜ ረዳት አብራሪው የጉዞውን አቅጣጫ   በመቀየር   ጄኔቭ  አውሮፓላን ማረፊያ በማሳረፍ እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል።የኢትዮጵያ መንግስት የኮሚኒኬሽን ባለስልጣን የሆኑት ሬድዋን ሁሴን አየር መንገዱ የተጠለፈው ሱዳን በቆመበት ጊዜ በተሳፈሩ ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ነው በማለት መጀመሪያ ላይ ለረዩተርስ መግለጫ ቢሰጡም፣ የስዊዘርላንድ ፖሊስ ግን ፈጥኖ ጠላፊው የአየር መንገዱ ረዳት አብራሪ መሆኑንና የደህንነት ስጋት እንዳለበት በመግለጽ እጁን በሰላም መስጠቱን አስታውቀዋል።በአለም የጠለፋ ታሪክ ያልተመደ ክስተት ነው የተባለው ይህ የአውሮፕላን ጠለፋ፣ የፖለቲካ ይዘት ያለው ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል።ማንነቱ ያልታወቀው ረዳት ፓይለት በ30ዎቹየእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ ሲሆን፣ ጄኔቭ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሰ በመስኮት በኩል በመውጣት እጁን በሰላም ለፖሊስ ሰጥቷል። ፖሊስ እንዳስታወቀውም ጠላፊው ምንም አይነት የጦር መሳሪያ አልያዘም።በአውሮፕላኑ ውስጥ በነበሩ ተሳፋሪዎች ላይ ምንም አይነት ጉዳትም አልደረሰም።
ጄኔቭ የሚገኘው የኢሳት ወኪል እንደዘገበው ምንም እንኳ ጄኔቫ አየር ማረፊያ ከሰአታት በሁዋላ ተራግገቶ ስራውን ለማከናወን የቻለ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር እስከ ቀኑ 9 ሰአት ድረስ ተሳፋሪዎች ወደ ሮም አልተመለሱም፣ አውሮፕላኑም ባለበት ቆሞ ይታይ ነበር። ከቀኑ 9 ሰአት ከሰላሳ አካባቢ አውሮፕላኑ ለጥገና ወይም ተሰፋራዎችን ወደ ሮም ለመመለስ ሲንቀሳቀስ መታየቱን ወኪላችን ገልጾ፣ ጠላፊውን ለማግኘት የተደረገው ሙከራ በፖሊስ ጥብቅ ቁጥጥር የተነሳ ሊሳካ አልቻለም።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች በተለያዩ ጊዜያት በአስተዳደሩ እንደሚማሩ ይታወቃል። አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በማንሳት ጠለፋውን ከፖለቲካ ጋር በማያያዝ ለማየት እየሞከሩ ነው።
ረዳት ፓይለቱ አላማው ጥገኝነት መጠየቅ ቢሆን ኖሮ አውሮፕላኑን ሮም ላይ ካሳረፈ በሁዋላ ጄኔቭ ገብቶ በሰላም እጁን መስጠት ይችል እንደነበር ጁኔቭ የሚገኙ አንዳንድ አስተያየት ሰጪ ይናገራሉ።  ረዳት ፓይለቱ ይህ እድል እያለው እና አውሮፕላን መጥለፍ ወንጀል መሆኑን እያወቀ እንዲህ አይነት እርምጃ ለመውሰድ የተነሳሳው አንድ ከባድ ምክንያት ቢኖረው ነው በማለት እኝሁ አስተያየት ሰጪ ገልጸዋል።
በስዊዝ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጠበቆች ረዳት ፓይለቱን ለማግኘትና ጠበቃ ቐጥረው ለመከራከር ፍላጎት እንዳላቸው ለኢሳት ገልጸዋል።
ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት በአውሮፕላኑ ወስጥ ተሳፍራ የነበረች አንዲት ወጣት አግኝተናል። ወጣቱዋ እንደምትለው አውሮፐላኑ የተጠለፈው ከሮም ወደ ሚላን በሚመበርበት ጊዜ ነው። ሮም ማረፉንና መንገደኞችን ማሳፈሩን ወጣቷ ተናግራለች። አቶ ሬድዋን በበኩላቸው አውሮፐላኑ ሮም ሳያርፍ ወደ ጄኔቭ መሄዱን ተናግረዋል። ወጣቱዋ አብራሪው ረጅም ና ጠይም መሆኑንሮም ላይ ሻንጣውን ማውረዱንና ፊቱ ላይ አለመረጋጋት ይታይበት እንደነበር ገልጻለች።
source ESAT news

ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ

ለተፈጥሮ ሃብት የጠየቀው ዓለምዓቀፋዊ እውቅና ውድቅ ሆነ
eiti
ኢህአዴግ የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ለተሰኘ ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ ከተገመገመ በኋላ መመዘኛዎቹን ማሟላት ባለመቻሉ መውደቁ ተሰማ። ኢህአዴግ የእውቅና ማመልከቻ በድጋሚ ማስገባቱን አስቀድሞ ያወቀው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት (Human Rights Watch) ጉዳዩን ከሚከታተሉ ጋር ባገኘው መረጃ ኢህአዴግ የEITI መስፈርት የማያሟላና በሰብአዊ መብት ጥሰት የተወነጀለ ድርጅት መሆኑንን ማስረጃ አስደግፎ በመጥቀስ መሟገቻ ደብዳቤ ለድርጅቱ አስገብቶ ነበር።
EITI የዛሬ 11ዓመት አካባቢ የተቋቋመ በተፈጥሮ ሃብት ዙሪያ ዕውቅና የሚሰጥ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ የተፈጥሮ ሃብት የህዝብ መሆኑን የሚያምን ሲሆን ማንኛውም የተፈጥሮ ሃብት – ማዕድን፣ ዘይት፣ ብረታብረትና ጋዝ – ከመሬት በሚወጣበት ጊዜ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚኖረውን ያህል ግልጽነትና ተጠያቂነት በሌለባቸው አገራት ድርጊቱ ለሙስና እና ግጭት በር እንደሚከፍት ይናገራል፡፡ በመሆኑንም ድርጅቱ አገራት ለሚያቀርቡት የዕውቅና ጥያቄ ማሟላት ያለባቸውን መስፈርት በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ልማትና እድገት በሚል ሰበብ የሕዝብ ሃብት የሆነውን የተፈጥሮ ሃብት በማውጣት የህዝባቸውን መብት ለሚረግጡ አገራት የሚያቀርቡትን የዕውቅና ማመልከቻ ውድቅ ያደርጋል፡፡
የጎልጉል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ምንጭ እንደጠቆሙት ኢህአዴግ ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ውድቅ መደረጉ እውነት ነው። ምንጩ እንዳሉት ኢህአዴግ በውሳኔው በመበሳጨት ይግባኝ ለመጠየቅ በዝግጅት ላይ ነው። ድርጅቱ (EITI) አንድ አገር ለሚያቀርበው የእውቅና ማመልከቻ በመስፈርቱ መሰረት ግምገማ ካካሄደ በኋላ እውቅና እንዲሰጥ ሲያምን በራሱ ድረገጽ ላይ የዚያን አገር ስም በመመዝገብ ተጠቃሹ አገር ከተፈጥሮ ሃብት ጋር በተያያዙ ኢንቨስትመንቶች የሚገኘው ትርፍ ለህዝብ ጥቅም እንዲውል ያደርጋል የሚል እውቅና በመስጠት ምስክርነቱን ያሰፍራል፡፡
ኢህአዴግ የመጀመሪያው የማመልከቻ ጥያቄ ያቀረበው በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር በ2009 አካባቢ ነበር፡፡ ከEITI አምስት መስፈርቶች መካከል አንዱ፤ ማመልከቻ የሚያቀርቡ አገራት ከመያዶች (መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች) ጋር ለመስራት ያላቸው ፍላጎት ተጠቃሽ ነው፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግ በመያዶች ላይ አፋኝ ሕግ አውጥቶ የነበረ በመሆኑ እውቅና ሰጪው ድርጅት – EITI – የኢህአዴግን ማመልከቻ ውድቅ አድርጎታል፡፡ የEITI ቦርድ ይህን ዓይነት ውሳኔ ሲያስተላልፍ ያሰፈረው ነገር ኢትዮጵያ በእጩ አባልነት ለመመዝገብ በመጀመሪያ በመያዶች ላይ ያወጣችውን ሕግ ማስወገድ አለባት የሚል እንደነበር የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት በድረገጹ ላይ አስቀምጦታል፡፡ በወቅቱ የተሰጠው ይህ ብያኔ በEITI እውቅና አሰጣጥ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያ እንደሆነ ተጠቁሞም ነበር፡፡
የEITI ዕውቅናን ለማግኘት ቋምጦ የነበረው ኢህአዴግ በድርጅቱ ውሳኔ ባለመደሰት ጥቂት ዓመታትን ቆጥሮ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ በአቶ ሃይለማርያም በመመራት በድጋሚ ዕውቅና የማግኘት ዘመቻውን ማጠናከር ጀመረ፤ በይፋም እንቅስቃሴውን ቀጠለ፡፡ የማዕድን ሚ/ር መ/ቤትም ዕውቅና ማግኘቱ በጣም የሚያስፈልግ እንደሆነ በይፋ በመናገር ዘመቻውን አጧጡፎ ነበር፡፡ ከዚህም አልፎ ለዓመታት ሲጠቀምበት የነበረውን አሠራር በዓለምአቀፉ ድርጅት ላይ ተግባራዊ በማድረግ ኢህአዴግ Ethiopia Revenue Transparency Initiative (ERTI) የሚባል “ተለጣፊ” ተቋም በመመሥረት እንቅስቃሴ ሲያደርግ እንደቆየ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ለEITI በጻፈው ደብዳቤ ላይ ገልጾዋል፡፡
ጉዳዩን በቅርብ ይከታተሉ የነበሩ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ኢህአዴግ በአውሮጳውያኑ አቆጣጠር 2013ዓም በድጋሚ ማመልከቻ የማቅረብ ዓላማ እንዳለው ለዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት አሳወቁ፡፡ በወቅቱ ኢህአዴግ ማሻሻያ እያደረጉ ነኝ የሚል ማስመሰያ ለማቅረብ የሞከረ ቢሆንም የመያዶችና የጸረ አሻባሪነት አፋኝ ሕጎቹ በተጨማሪ በቴሌኮሙኒኬሽን በኩል በስልክና ኢንተርኔት የሚያደርውን ህዝብን የመሰለል ተግባር አጠናክሮ የቀጠለበት እንደሆነ በመጥቀስ ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ክፍሎች EITI ዕውቅና እንዳይሰጥ መወትወታቸውን ተያያዙ፡፡
እነዚሁ ወገኖች በተደጋጋሚ ያደረጉት “የወረቀትና የፔቲሽን ትግል” እየተባለ የሚቃለለው ትግል ውጤት በማምጣት ኢህአዴግ በደጋሚ ያስገባው የአባልነት ማመልከቻ ሰሞኑን ውድቅ መደረጉ ተሰምቷል፡፡ እንደ መረጃው ከሆነ EITI ማመልከቻ በሚመዝንበት በሁሉም መስፈርቶች ኢህአዴግ ወድቋል፡፡
አነስተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙና ኢህአዴግ “ልማታዊ” የሚላቸው ኢንቨስተሮች ሳይሆኑ በከፍተኛ ደረጃ የሚመደብ መዋዕለ ንዋይ የሚያፈሱ ባለሃብቶች ኢንቨስት የሚያደርጉበትን አገር ለመምረጥ የመጀመሪያው መለያቸው የEITI ድረገጽ የአባል አገራት ዝርዝር እንደሆነ ስለ አሰራሩ የሚያውቁ ይናገራሉ። ኢህአዴግም አስፈላጊውን የምዝገባና የማመልከቻ መስፈርት በማሟላት የተቋሙን እውቅና የጠየቀው በድርጅቱ ድረገጽ ላይ ለመመዝገብ ነበር። የሁለት ጊዜ ሙከራው መክሸፉ ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ህግ መታፈኑ የሚያመላክት እንደሆነ የሚጠቅሱ ክፍሎች፤ ከኢህአዴግ ከፍተኛ ፍላጎት አኳያና ሰሞኑን በተለያየ አቅጣጫ እየተወጠረ ከመምጣቱ አንጻር ሁኔታው አጣዳፊና ፋታ የማይሰጥ በሽታ ምልክት እንደሆነ በምጸት ይናገራሉ፡፡
ስለEITI ውሳኔ ባጭሩ እንዲያብራሩልን የጠየቅናቸው ባለሙያ እንዳሉት “አንድ ዩኒቨርሲቲ ህንጻ በማስገንባቱና አስተማሪዎችን በመቅጠሩ ብቻ ዩኒቨርስቲ ተብሎ ሊጠራ አይችልም። ዩኒቨርስቲው ዓለም ዓቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስለመሆኑ በዓለም አቀፍ መስፈርት መሰረት ተገምግሞ እውቅና የሚሰጠው መስፈርቶቹን በሙሉ አሟልቶ ስለመገኘቱ ምርመራ ተደርጎበት ፈተናውን ሲያልፍ ብቻ ነው። በዚሁ መሰረት አልፎ እውቅና ያላገኘ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ገብቶ መማር የተሳትፎ ያህል ነው። መስፈርቱን አሟልተው እውቅና ካገኙት ጋር መወዳደር ስለማይችል ተመራጭ አይሆንም። በተመሳሳይ Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) የተባለው ድርጅትም ከየአገራቱ እውቅና እንዲሰጥ የሚቀርብለትን ጥያቄ /ማመልከቻ/ የሚመዝንበት መስፈርቶች አሉት። ኢህአዴግ የተፈተነው በዚሁ አቅልጦና አንጥሮ በሚያወጣው መመዘኛ ነው ብለዋል፡፡”
ስለጉዳዩ የተጠየቀው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ የህዝብ ግንኙነት ግብረ ኃይል ጉዳዩን በጥልቀት የሚያውቀውና ገና ከጅምሩ ሲከታተል የቆየው መሆኑን በመግለጽ በበርካታ ፈርጆች ከሚያካሂደው ትግል አንጻር በዕቅድ ሲያከናውነው የቆየ መሆኑን አመልክቷል። የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ ለጎልጉል እንዳለው ከሆነ “የEITI ውሳኔ ኢትዮጵያን እንደ አገር የሚጎዳ መሆኑ ግልጽ ነው፤ ሆኖም ውሳኔው ኢህአዴግ በራሱ ግትረኝነትና እብሪት ያመጣው ጣጣ በመሆኑ የራሱን ተግባር ተከትሎ የተወሰነው ውሳኔ በአገሪቱ ላይ በማንኛውም መልኩ ለሚያደርሰው ኪሳራ ተጠያቂው ኢህአዴግና ህወሃት ናቸው” ብሏል። በማያያዝም የጋራ ንቅናቄው ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ መግለጫ በማውጣት አስፈላጊ ናቸው ለሚላቸው ወገኖች እንደሚበትንና ተቋሙ በውሳኔው እንዲጸና የሚቻለውን ሁሉ በማድረግ ላይ ለተሰማሩ መልዕክት እንደሚያስተላልፍ አመልክቷል።

fredag 14. februar 2014

አንድነትና መኢህአድ በባሕር ዳር ሰላማዊ ሰልፍ ጠሩ

ebruary 14, 2014
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የአማራው ብሄረሰብ በጅምላ መሰደቡንና መወገዙን በመቃወም ከመላው ኢትዮጵያ ህዝብ አንድነት ድርጅት (መኢህአድ) ፓርቲ ጋር በመተባበር እሁድ የካቲት 16፣ 2006 በባህር ዳር ከተማ የሰላማዊ ሰልፍ ጠራ።
አቶ አለምነህ መኮንን የተባሉት የአማራው ክልል ምክትል አስተዳዳሪ እና የብአዴን አመራር ከካድሬዎቻቸው ጋር ባደረጉት ስብሰባ ውቅት በአማራውን ብሄር ላይ ተራ እና ዘረኝነት የተሞላበት ዘለፋ ማካሄዳቸው ይታወቃል።
ይህ በዚህ እንዳለ… የአቶ አለምነህን ዘለፋ ያዳመጡና በነገሩ የተበሳጩ የባህር ዳር ወጣቶች ሰሞኑን የባለስልጣኑን መኖርያ ቤት በድንጋይ እሩምታ ማጥቃታቸውን “ፍኖተ ነጻነት” ዘግቧል።
ECADF Ethiopian News

torsdag 13. februar 2014

በርካታ ወጣቶች ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት እየተጋዙ ነው

ኢህአዴግ በጀመረው አዲስ አሰሳ በሀገሪቱ አንድንድ ቦታዎች ኢንተርኔትን ጨምሮ ስልክ እንዳይሰራ የተደረገ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎችም የመከላከያ ሀይል ተበትኗል፡፡ የዚህን ዜና ዝርዝር  በሌላ ጊዜ ይዘን እንቀርባለን። በሌላ ዜና ደግሞ ብአዴን ከፍተኛ የሞራል ውድቀት የደረሰበት መሆኑን ምንጮች ገለጹ።
የብአዴን የጽፈት ቤት ሃላፊ እና የአማራ ክልል ም/ል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ አለመነው መኮንን የሚመሩት ህዝብ  ጸያፍ ስድብ መሳደባቸውን ተከትሎ ብአዴን የሞራል ውድቀት እንደደረሰበት ከክልሉ የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
የክልሉ ህዝብ ያሳየው ቁጣና በብአዴን የንግድ ድርጅቶች ላይ የጣለው ማእቀብ ያሰጋቸው አቶ በረከት ስምኦን ወደ ባህርዳር በማቅናት ፣ የደረሰውን ኪሳራ ለመቋቋም ያስችላሉ የሚሉዋቸውን አማራጮች ሁሉ ለመጠቀም ከሌሎች አመራሮች ጋር እየመከሩ ናቸው።
የብአዴን አመራሮች ባደረጉት የመጀመሪያ ግምገማ “የአማራ ህዝብ ፊት ለፊት የምንናገረውና ከጀርባ የምንናገረው ነገር የተለያየ ነው” ብሎ እንዲያስብና እምነቱን እንዳይጥልብን አድርጓል” ብለዋል። ብአዴን በመጪው ምርጫ ላይ በክልሉ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ ሊደርስበት እንደሚችልም በግምገማው ወቅት ተነስቷል።
የክልሉ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፣ በኢሳት የቀረበው የአቶ አለምነው ድምጽ አይደለም ብለው ማስተባበል ሳይችሉ ቀርተዋል። ፕሬዚዳንቱ በባህርዳር ስብሰባ መካሄዱንና ድምጹም በጊዜው የተቀረጸ መሆኑን በተዘዋዋሪ መንገድ ያመኑ ሲሆን፣ መክትላቸው የተናገሩትን በቀጥታ ከማስተባበል ይልቅ አቶ አላምነው ለአማራው ህዝብ ስላላቸው ፍቅር መግለጽን መርጠዋል።
አቶ አለምነው እራሳቸው ቀርበው ለምን መግለጫ እንዲሰጡ እንዳልተፈለገ ግልጽ አይደለም። የክልሉ ህዝብ የብአዴን ንብረት የሆነውን ዳሸን ቢራን እንዳይጠጣ የሚደረገው ቅስቀሳ አግባብ አይደለም ሲሉ አቶ ገዱ ተናግረዋል።
ድርጊቱን ያወገዙት አንድነትና መኢአድ  የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ደብዳቤ ማስገባታቸው ታውቋል። ፓርቲዎቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ ”  ህዝብ ያዋረዱ አመራሮች በተገቢው ፍጥነት ለፍርድ እስኪቀርቡ ድረስ የተቃውሞ ሰልፉ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎችም ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል” ብለዋል፡፡
የተቃውሞ ሰልፉ ከጣቱ በሶስት ሰአት ከቀበሌ 12 ( ግሽ አባይ ተነስቶ)፣ በክልሉ መስተዳድር ጽ/ቤት ከቀኑ ስምንት ሰአት ላይ ያበቃል። የባህርዳር እና አካባቢዋ ህዝብ በስፍራው ተገኝቶ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት በህዝቡ ላይ ያወረዱትን ዘለፋ እንዲያወግዝ ፓርቲዎቹ ጠይቀዋል።

በተባበረ ሃይላችን ክብረ-ስብእናችንን እናስመልስ! ተዋርዶ መኖር ይብቃን! በቃ!


የወያኔ ሹማምንትና አደርባይ ሎሌዎቻቸው አንገቱን አስደፍተው የሚገዙትንና የሚዘርፉትን ህዝብ ይበልጥ ስብእናውን አዋርደው ሊገዙት ለምን እንደሚፈልጉ የማይገባን ጥቂቶች አይደለንም። እነዚህን ግፈኞች ቀረብ ብሎ ላያቸው ግን ይህ ድርጊታቸው እንቆቅልሽ አይደለም።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ህዝብ አይሰማንም ብለው በር ዘግተው ከሚያካሂዷቸው ጉባኤዎች እያፈተለኩ የሚወጡ የቪዲዮና የድምጽ መረጃዎች የነዚህን ግፈኞች ስነ ህሊና ግልጽ አድርገው ያሳያሉ።
ከወራት በፊት የሶማሊያ ክልል ፕሬዝዳንት የሀገር ሽማግሌ ሰብስቦ የወያኔ አላማ ከእሱ ጎሳ ጋር ተባብሮ ሌላውን ብሄረሰብ የበታች አድርጎ መግዛት መሆኑን ሲናገር የሚያሳይ ቪዲዮ ተመልክተን ነበር። የክልሉን ህዝብ የሚጨፈጭፈው ለዚህ ሲባል መሆኑን ለማሳመን ነበር በሩን ዘግቶ የተናገረው።
ሰሞኑን ደግሞ አንድ የአማራ ክልል የወያኔ ሹምና ሎሌ አንደ እንደሶማሌ ሹም ካድሬዎቹን ሰብስቦ በአማራው ህዝብ ላይ ተሳለቀ፤ ለ እግራቸው ጫማ የላቸውም በሚላቸው የአማራው ተወላጅ ላይ ለሰሚ በሚሰቀጥጥ ቋንቋ ያወርደው የነበረ ስድብ የሚነግረን ተጨማሪ ነገር ተመሳሳይ የወያኔን ምንነትን ነው።
እነዚህ ግፈኞች በህዝብ ላይ የሚሰሩትን አዋርዶ የመግዛት ግፍና ዝርፊያ አሳምረው ያውቃሉ። ከዚበላይ ደግሞ የዚህ ሁሉ ንቀትና ጥላቻ ሰለባ የሆነው ህዝብ እንደሚጠላቸውና ቀን እንደሚጠብቅላቸው ያውቃሉ። ስለዚህም ህዝቡን ይፈሩታል። ከፍርሃታቸው የሚያስታግስላቸው ህዝቡን ይበልጥ ቅስሙን ለመስበር ከቻሉ ስለሚመስላቸው በተዘጋ ቤት ውስጥ እየተሳለቁ ያስጨበጭባሉ።
የወያኔ ሹማምንት የህዝብ ብሶትና እሮሮ ማየሉን ሲሰሙ መልሰው ህዝቡን የሚሰድቡትና የሚያጠቁት፣ እንዲሁም ግንቦት 7 ሲጠነክርባቸውና የመውደቂያ ቀናቸው ሲያስቡ አሸባሪ ብለው የሚሸበሩትም ለዚህ ነው።
ህዝቡ ቅስሙ ከተሰበረ ሰላም ያገኙ ይመስላቸዋል። ወያኔዎችና የሲቪል ሰርቪስ ሎሌዎቻቸው በር ዘግተው በተሰበሰቡ ቁጥር ይህንን ፍራቻቸውን የሚያስታምሙት ህዝቡን ቅስሙን መስበራቸውን ለማረጋገጥ በሚያካሄዱት ወይይት ነው። ለዚህ ነው ህዝባችን እርስ በርሱ የሚባላበትን፤ እርስ በርሱ ጎሪጥ የሚተያይበትን መንገድ ሲቀይሱ የሚውሉት በዚህ ምክንያት ነው።
ወያኔዎች በየክልሉ እንደ አለምነው መኮነን አይነት ከጭንቅላታቸው፣ከህሊናቸው ይልቅ አፋቸው የሚቀድም ጥራዝ ነጠቅ ሎሌዎችን የሚያሰማሩትም የህዝብን ቅስም የሰበሩ አየመስላችዉ ነው::
 ወያኔና ሎሌዎቹ ህዝብየሚያታልሉበት ካርድ ከእንግዲህ አልቋል። አዋርደውናል፣ ገድለውናል፣ አስረውናል፣ አስርበውናል፣ ለስደት ዳርገዉናል፣ አለያይተውናል። ከዚህ በላይ ምን ሊያደርጉን ይችላሉ? ስለዚህ ቀኑ መሽቶባቸዋል እናበፍጥነት  ሊወገዱ ይገባል
በዚህ ወሳኝወቅት ሁሉምየኢትዮጵያእንደ አንድ ህዝብ በአንድ ላይ በመነሳት የወያኔ ጉጅሌና አጎብጓቢ ሎሌዎቻቸው ያዘጋጁልንን ወጥመድ መስበርና ክብራችንን ማስመለስ ይኖርብናል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተዘጋው የወያኔ በር እየተዋረደ፣ እየተገረፈ ነውና።
ግንቦት 7 እንደሁልግዜው ዘላቂ መፍትሄ የሆነው ዴሞክራሲያዊ አንድነታችን እንዲጎለብት፣ ማንነታችን ክብራችን እንጂ መሳለቂያ እንዳይሆን በተባበረ ሃይላችን የክብራችን ባለቤት እንድንሆን ጥሪውን ያቀርባል።
በተባበረ ሃይላችን ክብረ-ስብእናችንን እናስመልስ! ተዋርዶ መኖር ይብቃን! በቃ!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!