ቦሌ መንገድ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በሚገኝ የሕብረት ባንክ ቅርንጫፍ በጥበቃ ሥራ ላይ የነበረው ወጣቱ በሱፍቃድ ለምሳ ተቀይሮ ሲገባ ከሥራ ባልደረባው ላይ የተቀበለውን የጥበቃ መሣሪያ ተቀብሎ ለጊዜው ምን እንደኾነ ያልታወቀ (እስካሁን እኔ ያላወኩት) ነገር እየተናገረ እየሮጠ ወደ ሰማይ አራት ጊዜ ያህል ከተኮሰ በኋላ አገጩ ላይ አስደግፎ ወደ ጭንቅላቱ በመተኮስ ራሱን አጥፍቷል።
በአሁኑ ሰዓት አስክሬኑን ሰማያዊ የሚበዛበት ዥንጉርጉር ጨርቅ ሸፍነውት መንገድ ላይ ተኝቷል። የደንብ ልብሱን እደለበሰ ሲኾን፤ አጠገቡ በጥይቱ የተበሳ ኮፍያው ወድቋል። የጭንቅላቱ ስጋ እና አጥንቶቹ ተበታትነዋል።
በሱፍቃድ አጋር የተባለው የጥበቃ ሥራ የሚሠራ ኤጀንሲ ተቀጣሪ መኾኑን እና ሕብረት ባንክ ከመጣ ሁለት ወር አካባቢ እንደኾነው የሥራ ባልደረቦቹ ነግረውኛል። አሁን በተገኘ መረጃ ”ኑሮ መኖኛል” ሲል ተሰምቷል። እዛ አካባቢ ያሉ ፖሊሶች ደግሞ በምን እንዳወቁ አላውቅም ከቤተሰቡ ተጣልቶ ነው ብለዋል። አሁን አስክሬኑኑን የፖሊስ መኪና አንስቶታል።
ምንጭ ኢትዮጵያ ዛሬ
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar