ሠማያዊ ፓርቲ በቅስቀሳ ላይ የነበሩ 25 ወጣት አባላቴ ታስረውብኛል፣ ፓርቲው ሥራውን በአግባቡ እንዳያካሂድም መሰናክል እየደረሰበት ነው ሲል አስታወቀ።
በአዲስ አበባ አስተዳደር የሠላማዊ ሠልፍ ማሳወቂያ ክፍል ለፊታችን እሁድ ዕለት ሠልፍ ለማድረግ አሳውቀን ሠልፉን የምናደርግበት ቦታ ቢነገረንም፤ ፖሊስ ግን በሥራችን ላይ እንቅፋት እየፈጠረ ነው ሲል ፓርቲው ወቅሷል። ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር ስለሁኔታዉ የፓርቲዉን ሊቀመንበር አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል። ይህ ዘገባ ከተጠናቀረ በኋላ የደረሰን ዜና እንደሚያመለክተዉ ደግሞ የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚደንት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት፤ ምክትል ፕሬዚደንቱ አቶ ስለሺ ፈይሳ እንዲሁም የፓርቲዉ የሕዝብ ግንኙነት አቶ ብርሃኑ ተክለ ያሬድ ለቅስቀሳ ከፓርቲዉ ጽህፈት ቤት ሲወጡ በፖሊስ ተይዘዉ ተወስደዋል።
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሰ
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar