mandag 29. september 2014

የታጋይ አንደርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በአውሮፓ ህብረት ምክርቤት ኮሚሽን ውይይት ተደረገበት፤ በአስቸኮይ እንዲፈታም ጠይቀዋል።


ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ በአምባገነኑ ወያኔ እጅ ወድቆ መሰቃየት ከጀመረ 3 ወራት አልፈዋል። ባለፉት ቀናት የአውሮፓ ህብረት የሰበአዊ መብት ም/ቤት በጉዳዩ ላይ ከፍተኛ ውይይት አደርገዋል ። አንዳርጋቸው የፖለቲካ እስረኛ እና ለዲሞክራሲ፣ ለነጻነት፣ ለመልካም አስተዳደር እና ሰበአዊ መብት መከበር የሚታገል የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር ሲሆን ባስቸኮይ ተለቆ ወደ እንግሊዝ እንዲመለስ ኮሚሸነር ተናግረዋል፡፡የተከበሩ አና ጎሜዝ አንዳርጋቸው ብቻ አይደለም በርካታ ኢትዮጵያኖች ታስረዋል ብሎግ ዘጠኝ፣ ጋዜጠኞች፤ ፖለቲከኞች ሁሉም ካለ ምንም ምክንያት መፈታት አለባቸው። የኢትዮጵያን ፓርላማ ባለፈው ሂጄ አይቸዋለሁ በጣም የሚገርም ነው የፖለቲካ እስረኛ ሳይሆን ሽብርተኞች ናቸው ያሉን ሲሉ ከአንድ መንግስት የማይጠበቅ ነው። እስክንድር ነጋ ሽብርተኛ ሳይሆን አለም አቀፍ የብእር ተሸላሚ ነው። ብሎግ 9 ጸሃፊያን፣ ጦማሪያን ናቸው። አንዳርጋቸው ጽጌ የፍትህ ታጋይ ነው። ታዲያ እንዴት ነው የኢትዮጵያ መንግስት ህግን የሚተረጉመው ሲሉ ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ በሁለት ወር ውስጥ ይህን ጉዳይና የኢትዮጵያን ሰበአዊ መብት በተመለከተ እና የአንዳርጋቸው ጽጌን ጉዳይ የሚመለከት ኮሚቴ እንዲሰየም እና እንደገና እንደሚወያዩበት የወሰኑ ሲሆን የአቶ አንዳርጋቸውን በተመለከተ አሳሳቢ በመሆኑ ከእንግሊዝ መንግስት ጋር በመሆኑ ለብቻ በሚቀጥሉት እናየዋለን ሲሉ ዘግተዋል።
በዚሁ ስብሰባ የኢትዮጵያ መንግስት ተወካይ ቀርበው አሁንም የተለመደ ማስተባበያ ሰጥተዋል። እኛ ምንም አይነት ህግ አልጣስንም ብለዋል።

tirsdag 23. september 2014

ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ላይ ዋሽተው ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጉት


  • 501
     
    Share
የኢሳቱ ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና መረጃ ፍለጋ ወ/ሮ አዜብ ጋር ደውሎ ድምፃቸውን ኢሳት ራድዮ ላይ አሰምቶናል። ጋዜጠኛ ሲሳይ ወ/ሮ አዜብ መሆናቸውን ካረጋገጡለት በኋላ መረጃ እንዲሰጡት ጠየቃቸው። አድዋ ስለሆንኩ መረጃ የለኝም በሚል ስልኩን ዘጉት። ለሁለተኛ ጊዜ ደወለላቸውና “ዶ/ር ካሱ ኢላላ ከእርስዎ ጋር ባላቸው አለመግባባት ስላላቸው የመለስን ፋውንዴሽን ለቀዋል የሚባል ነገር አለና ይህን እንዲያረጋገጡልኝ ወይም እንዲያስተባብሉልን ነው የደወልኩት” አላቸው። ምንም አይነት ችግር እንደሌለባቸው ከተናገሩ በኋላ መልሰው እርሳቸው ወ/ሮ አዜብ እንዳልሆኑ በድምጽ ተናግረው ዋሹ። “ድምጽዎት እኮ የአዜብ መስፍንን ይመስላል” አላቸው እርሳቸው ግን ልክ ይህን ሲላቸው ለሁለተኛ ጊዜ ስልኩን ዘግተውበታል። የዛሬው ኢሳት ራድዮ ለዚህ ዘገባ ምላሽ አለው ያድምጡት።

ወ/ሮ አዜብ መስፍን ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ላይ ዋሽተው ስልኩን ጆሮው ላይ ዘጉት




የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኤክስፐርቶች ኢትዮጵያ ፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን ለሰብዓዊ መብት ጥሰት ትጠቀማለች ሲሉ ከሰሱ

-ተቃዋሚዎች ተገቢ ሪፖርት ብለውታል
United-Nations-01-300x220የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የሰብዓዊ መብት ሁሉን አቀፍ የአቻ ለአቻ ግምገማ የውሳኔ ሐሳቦችን ለመገምገም የተሰበሰበው የተመድ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ኤክስፐርቶች ቡድን መስከረም 8 ቀን 2008 ዓ.ም. በጀኔቭ ስዊዘርላንድ ባደረገው ስብሰባ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፀረ ሽብረተኝነት አዋጁን ሐሳብን በነፃነት የመግለጽና የመደራጀት መብትን ለመጣስ መጠቀሙን እንዲያቆም አሳሰበ፡፡
ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያ ያቀረበችውን ብሔራዊ የሰብዓዊ መብት አፈጻጸም ሪፖርትና የሰብዓዊ መብት ይዞታን በአገሪቱ ለማሻሻል የተወሰዱትን ሕጋዊና አስተዳደራዊ ዕርምጃዎች ተከትሎ፣ አባል አገሮች የተለያዩ የውሳኔ ሐሳቦችን መስጠታቸው ይታወሳል፡፡ ያደጉ አገሮች ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው እንዲሻሻል ወይም እንዲሰረዝ የጠየቁት ደግሞ የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን ነው፡፡
የፀረ ሽብርተኝነት ሕግና የሰብዓዊ መብት ጥበቃ፣ የመደራጀትና የሰላማዊ ስብሰባ፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ የዳኞችና የጠበቆች ነፃነትና የኢሰብዓዊ አያያዝና ክብርን የሚያዋርድ ቅጣት መብቶች ልዩ ራፖርተሮች የሆኑት ቤን ኤመርሰን፣ ማይና ካያ፣ ዴቪድ ካዬ፣ ሚቸል ፎርስት፣ ጋብሪኤላ ክናውልና ጁአን ሜንዴዝ በጋራ ያወጡት ሪፖርት የፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት ላይ ያነጣጠረ እንደሆነ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከኢትዮጵያ የወጡ ሪፖርቶች ማመላከታቸውን ይገልጻል፡፡ ‹‹ግርፋትና ኢሰብዓዊ አያያዝ በኢትዮጵያ ማቆያዎች ውስጥ መስተዋሉ ከፍተኛ የመሠረታዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው፤›› ሲልም ሪፖርቱ ይጠቁማል፡፡
የኤክስፐርቶች ቡድኑ ሽብርተኝነትን መዋጋት አስፈላጊ ድርጊት ቢሆንም፣ ትግሉ የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት መሥፈርቶችን ሳይጣረስ መከናወን እንዳለበት ግን አስምሮበታል፡፡ ‹‹ፀረ ሽብርተኝነትን የሚደነግጉ አንቀጾች በኢትዮጵያ የወንጀል ሕግጋት ውስጥ ግልጽ በሆነ ሁኔታ መተርጎም አለባቸው፡፡ ሕጎቹም ላልተገባ ዓላማ ጥቅም ላይ ሊውሉ አይገባም፤›› ሲልም ሪፖርቱ ያትታል፡፡
ሪፖርቱ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጁ የተከሰሱ ግለሰቦች ፍትሐዊ የሆነ የፍርድ ሒደት እያገኙ እንዳልሆነም ይወቅሳል፡፡ በተለይም ከሕግ አማካሪዎችና ከጠበቆች ጋር የመገናኘት መብት እንደማይተገበርም ያስረዳል፡፡ ‹‹ፍትሐዊ የሆነ የፍርድ ሒደት የማግኘት መብት፣ ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብትና የመደራጀት መብት በፀረ ሽብርተኝነት ሕጉ አፈጻጸም መጣሳቸው ቀጥሏል፤›› ሲሉም ኤክስፐርቶቹ ያሳስባሉ፡፡
‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ሽብርተኝነትን በመዋጋት ስም በዘፈቀደ በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን ሁሉንም ሰዎች እንዲፈታ እንጠይቃለን፡፡ ጋዜጠኞች፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች፣ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችና የሃይማኖት መሪዎች መደበኛና ሕጋዊ ሥራቸውን ያለ ዛቻና እስር ሳይፈሩ እንዲቀጥሉ ሊፈቀድላቸው ይገባል፤›› ሲሉም የተመድ ኤክስፐርቶች ጠይቀዋል፡፡ ኤክስፐርቶቹ ኢትዮጵያ የአዋጁን አፈጻጸም ከገባቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ግዴታዎች ጋር እያገናዘበች እንድታስኬድም ጥሪ አድርገዋል፡፡
የፀረ ሽብርተኝነት አዋጁን በመቃወም የሕዝብ ፊርማ እስከማሰባሰብ የደረሰው የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት) ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ግዛቸው ሽፈራው (ኢንጂነር) ሪፖርቱን አስመልከቶ ከሪፖርተር ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ ‹‹ፓርቲያችን አንድነት የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ የሕግ ሳይሆን የፖለቲካ ሰነድ ነው ያለው ከየትኛውም ፓርቲ ቀድሞ ነው፡፡ አዋጁ የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ከኢሕአዴግ የተለየ አቋም የሚያንፀባርቁ ግለሰቦችና ጋዜጠኞችን ለማፈን ታሳቢ ተደርጎ የወጣ ነው፤›› ብለዋል፡፡ አቶ ግዛቸው የሕጉን ተፅዕኖ በማየት ፓርቲያቸው በ2005 እና በ2006 ዓ.ም. ሕጉን ለማሰረዝ ፊርማ የማሰባሰብ ሥራ መሥራቱንም አስታውሰዋል፡፡
የተመድ ኤክስፐርቶች ሪፖርት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለመፍጠር ምን ያህል ጠቃሚ ነው በሚል የተጠየቁት አቶ ግዛቸው፣ ተመድ ሕጉ ጉድለት አለበት ስላለ ሳይሆን አዋጁ ከኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት ጋር የማይጣጣም በመሆኑ ፓርቲያቸው ተቃውሞውን እንደጀመረ ገልጸዋል፡፡ ዜጎች ሐሳባቸውን በነፃነት የመግለጽ፣ የመሰብሰብና የመደራጀት መብታቸው በሕገ መንግሥቱ ቢከበርም እነዚህን መብቶች በመጣስ በሕጉ አማካይነት በርካታ የህሊና እስረኞችን ኢትዮጵያ እንዳፈራችም አመልክተዋል፡፡ አዋጁ ከሕገ መንግሥቱ ጋር ይጋጫል የሚሉ ከሆነ ለምን ጥያቄአቸውን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ወይም ለሕገ መንግሥታዊ አጣሪ ጉባዔ እንዳላቀረቡ የተጠየቁት አቶ ግዛቸው፣ ከሕግ ክፍላቸው ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነና በቅርቡ እንደሚያቀርቡ ጠቁመዋል፡፡
እንደ አንድነት ፓርቲ ሁሉ በአዋጁ ላይ የሰላ ተቃውሞ በማቅረብ የሚታወቀው የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዚዳንት አቶ ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) በበኩላቸው፣ የኤክስፐርቶቹ ሪፖርት የፓርቲያቸውን አቋም እንደሚያንፀባርቅ ገልጸዋል፡፡ ‹‹እንደ ፓርቲም እንደ ግለሰብም በሪፖርቱ በጣም ደስተኛ ነን፡፡ ኤክስፐርቶቹ ገለልተኛና በጉዳዮቹ ላይ ጥልቅ ዕውቀት ያላቸው ናቸው፡፡ ተዓማኒነት ያለው ሪፖርትም በማውጣት ይታወቃሉ፡፡ ይኼ ዲፕሎማሲያዊ ጫና ከመፍጠር አልፎ ተግባራዊ ዕርምጃ ለመውሰድም የሚያስችል ተፅዕኖ ይፈጥራል፤›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡
ከነሐሴ 22 ቀን 2001 ዓ.ም. ጀምሮ የፀናው የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 ተጠቅሶ በርካታ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላት፣ ጋዜጠኞች፣ ጦማሪያንና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ተከሰው ፍርድ ያገኙ ሲሆን፣ በቅርቡም በቁጥጥር ሥር የዋሉ ፖለቲከኞችና ጋዜጠኞች በዚሁ አዋጅ ተከሰው ጉዳያቸው በመታየት ላይ ነው፡፡ መንግሥት ግን ይሠሩት ከነበረው ሙያዊ እንቅስቃሴ ባሻገር በሽብር ተግባር ሲሳተፉ እንደያዛቸው በመግለጽ ራሱን ይከላከላል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በኢትዮጵያ ውስጥ አንድም የህሊና እስረኛ እንደሌለ መግለጻቸውን ባለፈው ረቡዕ ዕትም መዘገባችን ይታወሳል፡፡ በአሁኑ የተመድ ኤክስፐርቶች ሪፖርት ላይ የመንግሥትን ምላሽ ለማግኘት ሪፖርተር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡

mandag 22. september 2014

የኦጋዴን ኡኡታ ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች በወጣትነታችን ብረት አንስተን ጫካ እንድንገባ አደረገን ብለዉ የሚናገሩት በወቅቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ ተንሰራፍቶ ይታይ የነበረዉ በብሄር ብሄረሰቦች ጭቆና ነበር

ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች በወጣትነታችን ብረት አንስተን ጫካ እንድንገባ አደረገን ብለዉ የሚናገሩት በወቅቱ ኢትዮጵያ ዉስጥ ተንሰራፍቶ ይታይ የነበረዉ በብሄር ብሄረሰቦች ጭቆና ነበር። ወያኔዎች በለስ ቀንቷቸዉ አዲስ አበባን ከተቆጣጠሩ በኋላም ቢሆን ለእነሱ ለራሳቸዉ የሚመች ህገ መንግስት ጽፈዉ ትልቁን የኢትዮጵያ ችግር ፈታን ብለዉ የሚናገሩት ይህንኑ ዛሬም ድረስ እናት አገራችንን ኢትዮጵያን እንደ ነቀርሳ በሽታ ቀስፎ ይዞ የሚቆጠቁጣትን የብሄር ብሄረሰቦች ችግር ነዉ። ወያኔ በ1994 ዓም ህገመንግስቱን አጽድቆ የፌዴራል ስርዐት ከመሰረተ በኋላ ድምጹን ከፍ አድርጎ የጮኸዉ ማንም መፍታት ቀርቶ ሞክሮት አንኳን የማያዉቀዉን የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ችግር እኔ ፈታሁት የሚል ለሱና ለደጋፊዎቹ ብቻ የሚሰማ ጩኸት ነበር። ወያኔ የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች ከታሰሩበት ሰንሰለት ፈትቼ “ነፃ” አወጥቼ እራሳቸዉን በራሳቸዉ እንዲመሩ መንገድ ከፈትኩላቸዉ ብሎ ከተናገረ ከሃያ አመታት በኋላ ዛሬም ኢትዮጵያ ዉስጥ የትኛዉም ብሄረሰብ እራሱን በራሱ ማስተዳደር ቀርቶ የአገሪቱ ዜጎች ባሰኛቸዉ ቦታ መኖር እንኳን አይችሉም። የሚገርመዉ ነጻነትና እኩልነት የሠላም ጠላቶች የሆኑ ይመስል ዛሬ ወያኔ ነጻ ወጡ የሚላቸዉ ብሄረሰቦች በሚኖሩበት አካባቢ ሁሉ የሚታየዉ የአገራችንን አንድነት ከፍተኛ አደጋ ላይ የሚጥል ብጥብጥ፤ ግጭትና ክልሌን ለቅቀህ ዉጣ የሚል ወያኔ ይዞብን የመጣዉ መፈክር ነዉ።
ወያኔ ጫካ ዉስጥ እያለ ደርግን በተደጋጋሚ በዘር ማጥፋት ወንጀል ይከሰስ እንደነበር ያኔ ወያኔ ምን ይዞልን ወይም ይዞብን ይመጣ ይሆን እያልን እንከታተለዉ ለነበርን ኢትዮጵያዊያን የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነዉ። ከወያኔ ዉንጀላዎቹ አንዱና ዋነኛዉ ደግሞ ወያኔ እራሱ አቀነባብሮና አዘጋጅቶ ሐዉዜን ዉስጥ በቪድዮ እየተቀረጸ የተካሄደዉ ዉጊያ ነበር። በዚህ ዉጊያ ላይ ደርግ በአዉሮፕላንና በታንክ እየታገዘ መንደሮችን በመደምሰስ ብዙ ሰላማዊ ዜጎችን እንደጨረሰ ወያኔ ዛሬም ድረስ የሚነግረን ዉንጀላ ነዉ። የወያኔ መሪዎች የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያዉቀዉ የማይፈልጉትና እነሱም በፍጹም የማይነግሩን እዉነት ቢኖር ደርግን አሸንፈዉ አዲስ አበባን ሲቆጣጠሩ ከደርግ የወረሱት እነሱ እንደሚሉት ባዶ ካዝና ብቻ ሳይሆን የደርግን ክፋት፤ ጭካኔና ጭፍጨፋ ጭምር መሆኑን ነዉ።
ዘረኞቹኦ የወያኔ መሪዎች ባለፉት ሃያ ሦስት አመታት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የፈጸሙትን ወንጀል መዘርዘር እራሱን የቻለ ትልቅ ፕሮጀክት ነዉና ዛሬ ወደዚያ አንሄድም፤ ሆኖም ይህ ዘረኛ ቡድን ነኝ ብሎ የሚናገረዉን አለመሆኑን ለማሳየት ስንል ብቻ ሁለቱን ትላልቅ የወያኔ የሰዉ ዘር ማጥፋት ወንጀሎች መናገሩ ፍሃዊ ይመስለናል። የወያኔ ዘረኞች በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከፈጸሟቸዉ ወንጀሎች አንዱና ትልቁ በታህሳስ ወር 1996 ዓም በአኝዋክ ህዝብ ላይ የፈጸሙት የሰዉ ዘር ማጥፋት ወንጀል ሲሆን ሌላዉ ደግሞ አሁንም ድረስ እልባት ያላገኘዉና ምስራቅ ኢትዮጵያ ዉስጥ በሶማሌ ወገኖቻችን ላይ የሚፈጽሙት አይን ያወጣ ጭፍጨፋ ነዉ። ፋሺስቱ ደርግ በአዉሮፕላንና በጦር ሂሊኮፕተሮች እየታገዘ ህፃን፤ አዋቂ፤ ሴትና ወንድ ሳይለይ ህዝብ ይጨፈጭፋል እያለ ሲከስ የነበረዉ ወያኔ ዛሬ እሱ እራሱ ከደርግ በከፋ ሁኔታ ኦጋዴን ዉስጥ እንዲህ ነዉ ተብሎ በቃላት ለመናገር የሚያዳግት ሰቆቃ በኦጋዴን ህዝብ ላይ እየፈጸመ ነዉ። ደርግን – ደርግ ለመሬቱ እንጂ መሬቱ ላይ ስለሚኖረዉ ህዝብ ደንታ የለዉም እያለ አምርሮ ይኮንን የነበረዉ ወያኔ የሱም ጉዳይ አጋዴን ዉስጥ አገኛለሁ ብሎ ከሚተማመነዉ የነዳጅ ኃብት ጋር እንጂ ከኦጋዴን ህዝብ ጋር እንዳልሆነ በተደጋጋሚ በዚህ ህዝብ ላይ በፈጸማቸዉና ዛሬም ድረስ በሚፈጽማቸዉ አረመኔያዊ የጭካኔ እርምጃዎች በተግባር አረጋግጧል። የሰላም፤ የፍህና የነጻነት ጠላት የሆነዉ ወያኔ ኦብነግን ከኦጋዴን ምድር አጠፋለሁ በሚል ሰበብ በክልሉ በየቀኑ በሚወስዳቸዉ ፀረ ህዝብ እርምጃዎች የብዙ ሠላማዊ ዜጎችን ደም እያፈሰሰ ነዉ።
በ1983 ዓም የሽግግሩ መንግስት ሲቋቋም የጀመረዉን የትጥቅ ትግል አቋርጦና የታጠቀዉን መሳሪያ አዉርዶ የሽግግሩን መንግስት ከተቀላቀሉት አማጽያን ዉስጥ አንዱ ኦብነግ በሚል ምህጻረ ቃል የሚታወቀዉ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃነት ግንባር ነበር። ይህ ግንባር በታህሳስ ወር 1984 ዓም ኦጋዴን ዉስጥ በተካሄደዉ የአካባቢ ምርጫ ከ80 በመቶ በላይ ድምጽ በማግኘት የክልሉን መንግስት መስርቶ የሽግግሩ መንግስት የስራ ዘመን እስካበቃበት ግዜ ድረስ ኦጋዴንን አስተዳድሯል፤ ሆኖም ክልሎች እራሳቸዉን ችለዉ በራሳቸዉ መርህና የፖለቲካ ፕሮግራም ሲመሩ ማየትና መስማት የማይወደዉ ወያኔ የኢትዮጵያ ሶማሌ ዲሞክራቲክ ሊግ የሚባል ተለጣፊ ድርጅት በመፍጠርና ይህ ተለጣፊ ድርጅት የ1987ቱን ምርጫ እንዲያሸንፍ በማድረግ ሰላም ፈልጎ የመጣዉን ኦብነግ ከጨዋታ ዉጭ በማድረግ ሌሎች አማራጮችን አንዲመለከት አስገድዶታል። በዚህ የወያኔ አሻጥርና የማግለል እርምጃ የተከፋዉና በሠላማዊ መንገድ ለኦጋዴን ችግሮች መፍትሄ ማግኘት ይቻላል በሚል እምነት ትጥቁን ፈትቶ የሽግግሩን መንግስት የተቀላቀለዉ ኦብነግ አንደገና ትጥቁን አንስቶ ጦርነት ዉስጥ ለመግባት ተገድዷል። የወያኔ መሪዎች ፍላጎትም ቢሆን በፌዴራሊዝም ስም በየክልሉ የራሳቸዉን አሻንጉሊቶች እያስቀመጡ በእጅ አዙር ክልሎችን በቁጥጥራቸዉ ዉስጥ ማድረግ ነዉ አንጂ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች እራሳቸዉን በራሳቸዉ እንዲያስተዳድሩ ማድረግ እንዳልሆነ በኦጋዴንና በሌሎችም ክልሎች የወሰዷቸዉ እርምጃዎች በግልጽ ያሳያሉ።
የደርግ ስርዐት በህዝባዊ አመጽ ተደምስሶ አዲስ አበባ ዉስጥ በ19983 ዓም የሽግግር መንግስት ሲቋቋም የኦብነግ መሪዎች ከመሳሪያ ትግል ይልቅ በሽግግር መንግስቱ ዉስጥ መሳተፍ ለመብቱና ለነጻነቱ እንታገላለን ለሚሉት የአጋዴን ህዝብም ሆነ በአጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይበጃል ብለዉ ጫካዉን ጥለዉ ከተማ መምጣታቸዉ የሚያሳየን አንድ ትልቅ ሀቅ ቢኖር ለትግል ያነሳሳቸዉ የፍትህ፤ የነጻነትና የእኩልነት ጥማት መሆኑን ነዉ። ኦብነግ ገዢዎችም ሿሚዎችም እኛ ብቻ ነን በሚሉ ስግብግብ የወያኔ መሪዎች ተገፍቶ የሚያስተዳድረዉን ህዝብ ጥሎ ጫካ ባይገባ ኖሮ ዛሬ ኦጋዴን የሰላም ቀጠና ሆና ኦጋዴንን ለማዉደም የሚወጣዉ ከፍተኛ ወታደራዊ ወጪ ለዕድገትና ለልማት ስራዎች ይዉል ነበር።
የወያኔን መሪዎች ተንኮል፤ አሻጥርና ራስ ወዳድነት ከኦብነግ መሪዎች በላይ የሚያዉቅ ማንም የለም። ሆኖም የኦብነግ መሪዎች መሠረታዊ ፍላጎት የኦጋዴን ህዝብ መብቱና ነጻነቱ ተጠብቆ ፍትህ በሰፈነባት ኢትዮጵያ ዉስጥ ከሌሎች ወገኖቹ ጋር በእኩልነት እንዲኖር ማየት ስለሆነ በወያኔ ዘረኞች ዕብሪትና ተንኮል ተስፋ ሳይቆርጡ ይህ ፍላጎታቸዉ ሊሳካ የሚችልበትን መንገድ በሰላማዊ መንገድ ለማሳካት አሁንም እንደጣሩ ነዉ። ወያኔ ግን ይህንን የኦብነግ መሪዎች የሰላም ፍላጎት እንደ ፍርሃትና ሞኝነት በመቁጠር በጎረቤት አገር መሪዎች አማላጅነት ለድርድር የመጡ የኦብነግ መሪዎችን ለድርድር ከሄዱበት ከናይሮቢ ከተማ አፍኖ ወደ አዲስ አበባ ወስዷል። የወያኔ መሪዎች እንደነዚህ አይነቶቹን ጭፍንና ፀረ ሠላም የሆኑ እርምጃዎችን በኦብነግና በሌሎችም ብረት ባነሱ ኃይሎች ላይ በመዉስድ በአንድ በኩል በሠላማዊ መንገድ በዉይይትና ድርድር ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን አላስፈላጊ ወደ ሆኑ አዉዳሚ ጦርነቶች እንዲያመሩ ሲያደርግ በሌላ በኩል ደግሞ የህዝብን ልብ በማስሸፈት በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራል። ዛሬ አገራችን ኢትዮጵያ ዉስጥ ሃምሳ ኪሎሜትር በማይሞላ ርቀት እራሳቸዉን “ነፃ አዉጭ” ግንባር ብለዉ የሰየሙ አያሌ ድርጅቶች ይገኛሉ። እነዚህ የዚህ ወይም የዚያ ብሄረሰብ ነፃ አዉጭ ግንባር ነን ባዮች የተፈጠሩት የወያኔ ዘረኝንት፤ ዕብሪትና ንቀት ትዕግስታቸዉን ባስጨረሰ ሰዎች ነዉ እንጂ የነዚህ ድርጅቶች መሪዎች እንመራዋለን የሚሉት ህዝብ ችግር ከተቀረዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ችግር ጋር አብሮ እንደሚፈታ ረስተዉት አይደለም።
የሰብዓዊ መብቶች ተንከባካቢ ወይም በፈረንጆቹ ቋንቋ ሂዩማን ራይትስ ዋች የተባለዉ አለም አቀፍ ተቋም እንደ ፈረንጆቹ አመን አቆጣጠር በሁለት ሺ ስምንት በመረጃ አስደግፎ ባወጣዉ ዘግናኝ ሪፖርት ዘረኛዉ የወያኔ አገዛዝ በኦጋዴን ህዝብ ላይ የሚፈጽመዉን የጅምላ ቅጣት በግልጽ አሳይቶን ነበር። ሪፖርቱ ኦጋዴን ዉስጥ የመከላከያ ሠራዊት፤ ልዩ ፖሊስና የአካባቢዉ ሚሊሺያ ሠላማዊ ዜጎችን ከየመንደሩ እየጎተቱ የኦብነግ አባላት ናችሁ ብለዉ እንደሚረሽኑና ቤታቸዉን እንደሚያቃጥሉ ለአለም አቀፉ ህብረተሰብና ለእኛ የጉዳዩ ባለቤት ለሆንነዉ ኢትኦጵያዉያን አሳዉቋል። ይህ በቪድዮ ተደግፎ የቀረበዉ ሪፖርት እናት ልጄ ፊቴ ላይ ተረሸነ፤ አባት የልጆቼ እናት አይኔ እያየ ተደፈረች፤ ህጻናት ደግሞ አይናችን እያየ ወላጆቻችንን ተቀማን ብለዉ እያለቀሱ ሲናገሩ ያሳየን ሪፖርት ነበር። በወቅቱ ይህንን እጅግ በጣም ዘግናኝ የሆነ ቪዲዮ አይቶ ልቡ ያልተነካ ኢትዮጵያዊ አልነበረም።
ሂዩማን ራይትስ ዋች ይህንን ሪፖርት ይፋ ካደረገ ከስድስት አመታት በኋላ ዛሬም ወያኔ በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ የሚፈጽመዉን ለጆሮ የሚዘገንን ወንጀል ከመፈጸም ወደ ኋላ አላለም። እንዲያዉም ኦብነግን ከኦጋዴን ምድር ላይ ጠራርጌ አጠፋለሁ እያለ ግድያዉን፤ አፈናዉን ፤ ድብደባዉንና እስሩን በስፋት ቀጥሎበታል። ዘረኞቹ የወያኔ መሪዎች ዛሬም ኦጋዴን ዉስጥ ሠላማዊ ዜጎችን በዘፈቀደ ይገድላሉ፤ ወጣትና ህጻናት ሴቶችን ይደፍራሉ፤ መኖሪያ ቤቶችን ያቃጥላሉ። ባለፈዉ ማክሰኞ መስከረም አምስት ቀን የኢትዮጵያ ሳቴላይት ቴሌቪዥን በቪድዮ አስደግፎ ባቀረበዉ ዘገባ የወያኔ መሪዎች ምን አይነት ጨካኞች፤ አረመኔዎችና ለሰዉ ልጆች ምንም አይነት ክብር የሌላቸዉ አዉሬዎች መሆናቸዉን በግልጽ አሳይተዉናል። የዛሬ ስድስት አመት ሂዩማን ራይትስ ዋች ባወጣዉ ሪፖርትና ከሰሞኑ ደግሞ ኢሳት ቴሌቪዥን ባቀረበዉ የግማሽ ሰዐት ሪፖርት ዉስጥ የኦጋዴን ዜጎቻችን አሁንም ለእርድ አንደሚጎተት እንስሳ ተጎትተዉ በጥይት እንደሚደበደቡ፤ የኦጋዴን ምድርም ካላይና ከታች በቦምብ አንደሚጋይ በአይናችን ተምልከተናል።በዚህ ሰዉ ሆኖ መፈጠርን በሚያስጠላ ቪዲዮ ዉስጥ የወያኔ አረመኔ መሪዎች ሠላማዊ ዜጎችን እንደ ቅጠል አርግፈዉ “ልቀመዉ” “አምጣና ደርድር” እያሉ የራሳቸዉን ዜጋ በጅምላ በገደሏቸዉ የራሳቸዉ ዜጎች አስከሬን ፊት ቆመዉ ደስታቸዉን ሲገልጹ ታይተዋል። ከዚህ በተጨማሪ አንደኛዉ ወያኔ የአስከሬኑን ጭንቅላት በቪድዮ ቅረጸዉ ሲል ሌላዉ ደግሞ ይሄኛዉ ጆሮዉ ተቆርጧል እያሉ በገደሏቸዉ ሰዎች ፊት ቆመዉ ሲሳለቁ ተሰምተዋል። በዚህም ወያኔዎች ከእነሱ ዉጭ የሆንዉን ኢትዮጵያዊያን በቁማችን ብቻ ሳይሆን ሞተንም እየሰደቡንና እያዋረዱን የሚደሰቱ አርዮሶች መሆናቸዉን በተግባር አረጋግጠዋል።
ይህ በኦጋዴን ወንድሞቻችን ላይ የሚደርሰዉ በደልና የጅምላ ግድያ እኛን አይመለከትም የምንል ኢትዮጵያዊያን ካለን እጅግ ባጣም ተሳስተናል። ወያኔ አዲስ አበባ ዉስጥም ኦጋዴን ዉስጥ ሠላማዊ ዜጎችን ሲገድል ለእኛ ተራዉ እስኪደርሰን ድረስ በህይወት ላለነዉ ኢትዮጵያዉያን የግድያዊ ቦታና የሟቹ ማንነት ምንም ልዩነት የለዉም። አዲስ አበባም፤ ኦጋዴንም፤ አምቦም ወዘተ የምንገደለዉ እኛዉ ኢትዮጵያዉያን ነን: ይንን ግድያና ዉርደት በቃ ብለን በተባበረ ክንድ ወያኔንና ዘረኛ ስርዐቱን ማስወገድ ያለብንም እኛዉ ኢትዮጵያዉያን ነን።
ከኦጋዴን ክልል ዉጭ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ ፍላጎት ሠላም፤ ፍትህ፤ ነጻነት’ እኩልነትና ብልጽግና ነዉ፤ አርግጠኞች ነን የኦጋዴን ወገኖቻችን ፍላጎትም ከዚህ የተለየ አይደለም። ወያኔ በዘር፤ በቋንቋና በሐይማኖት ከፋፍሎን እንዳሰኘዉ እያሰረን፤ እየደበደበንና እየገደለን ለሃያ ሦስት አመት በላይ የዘለቀዉ ስላልታገልነዉ ወይም አሜን ብለን አንገታችንን አቀርቅረን ስለተገዛንለት አይደለም፤ ሁላችንም ወያኔን ለማስወገድና የናፈቀንን የነጻነት አየር ለመተንፈስ አቅማችን የፈቀደዉን ሁሉ አድርገናል። ሆኖም ወያኔ ገመናችንን አንድ በአንድ የሚያዉቅ አገር በቀል ጠላት ነዉና ድካማችንና በሚገባ ያዉቃል። እስከዛሬ የሚያሰቃየብም ደካማ ጎናችንን ስለሚያዉቅና ይበልጥ ደካሞች ሊያደርገን ቀንና ማታ ስለሚሰራ ነዉ። ዛሬ ይህንን ወያኔ በግልጽ የሚያዉቀዉን ድካማችንን ለማስወደግድና እነዚህን ዘረኞች ለማንቀጥቀጥ ለወያኔና ለቅጥረኞቹ መለያየትን፤ጎራ ለይቶ እርስ በርስ መናከስንና አንዳችን ስንበደል ሌሎቻችን ቀመን መመልከትን እምቢ ማለት አለብን። እነዚህ ሦስት ነገሮች በፍጥነት ማድረግ ከቻልንና ፍትፍ፤ ነጻነትና እኩልነት አስተባብረዉን ወያኔን በአንድነት ከታገልነዉ ወያኔ ከአንድ ሳምንት ትገል የማያልፍ ደካማ ጠላት ነዉ።የወያኔ ጥንካሬ የኛ መለያየትና እርስ በርስ መበላላት ብቻ ነዉ። ወያኔን አንድ ሆነን በጋራ ከታገልነዉ የመሳሪያ ጋጋታ አያስፈልገንም፤ አንድነታችን ብቻ ገፍቶ ይጥለዋል፤ተለያይተን ሁላችነም በየፊናችን ከታገልነዉ ግን እስካፍንጫችን ብንታጠቅም እያቆሰልነዉ እኛም እንቆስላለን እንጂ አናሸንፈዉም። ስለዚህ ዛሬ የኦጋዴን እልቂት እንዲቆም፤ የጋምቤላ መሬት ሽያጭ እንዲያበቃ፤ የአማራ፤ የአፋርና የሙርሲ ሀዝብ መፈናቀል ባስቸኳይ እንዲቆምና አገራችን ኢትዮጵያን በማዕከል በጋራ እየመራን በክልል ደግሞ እራሳችንን በራሳችን ማስተዳደር እንድንችል ሁላችንም በአንድነት በወያኔ ላይ ክንዳችንን እናንሳ!!

torsdag 18. september 2014

በህወሓት አገዛዝ በኦጋዴን ሕዝብ ላይ እየተፈጸመ ያለውን የጅምላ ግድያ በጽኑ እናወግዛለን!!!

መስከረም 7 ቀን 2007 ዓ.ም.                                                                                                                            

የአገራችን የኢትዮጵያን በትረ ሥልጣን በጠመንጃ ኃይል የተቆጣጠረው ዘረኛው የወያኔ አገዛዝ የሥልጣን እድሜውን ለማራዘም በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እየወሰደ ያለውን እሥራትና ግድያ አጠናክሮ መቀጠሉን የሚያጋልጡ ማስረጃዎች በየጊዜው ከራሱ ከአገዛዙ እየሾለኩ በመውጣት ላይ ናቸው።
መስከረም 5 ቀን 2007 ዓም በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴለቪዥን በምስል ተደግፎ የቀረበው በኦጋዴን ወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው ጭፍጨፋ ከነዚህ ማስረጃዎች አንዱ ነው ።
የወያኔን አገዛዝ ይቃወማሉ የተባሉና በኦጋዴን ክልል ከሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚዎች ጋር ንኪኪ አላቸው የተባሉ እነዚያ የጅምላ ጭፍጨፋ ሰለባ የሆኑ ምስኪን ዜጎች አስከሬን መሬት ለመሬት እየተጎተተ አንድ ቦታ እንዲከማች ሲደረግ፤ አስከሬኑን ለመሰብሰብ ከታዘዙት የአካባቢው ነዋሪዎች አንዱ የገዛ ወንድሙ አስከሬን ከሚጎተተው መሃል እንደነበረ መስማት ህሊናን የሚሰቀጥጥና የወያኔ የጭካኔ እርምጃ አቻ የሌለው ደረጃ ላይ መድረሱን የሚያመላክት ነው።
በደርግ ዘመን ቤተሰብ የተገደለበትን ሰው አስከሬን ለማግኘት የጥይት ዋጋ ለመክፈል ይገደድ ነበር በማለት ሥርዓቱን በነጋ በጠባ የሚወነጅል አገዛዝ ከሚወነጅላቸው ሥርዓት በባሰ በኦጋዴን የገደለውን ንጹህ ዜጋ አስከሬን የገዛ ወንድሙ መሬት ለመሬት እንዲጎትተው አድርጓል። በዚህም ህወሓት በሰብዓዊነት ላይ ከቀደምቶቹ ሁሉ የከፋ የሚሰቀጥጥ ወንጀል ፈጽሟል። ቀደም ሲል በበደኖ፤ በአርሲ፤ በአርባ ጉጉ፤ በሃዋሳ ፤ በጋምቤላ እና ድህረ ምርጫ 97 በአዲስ አበባና ሌሎች የአገሪቱ ከተሞች ነዋሪዎች ላይ በወያኔ ልዩ ትዕዛዝ ተመሳሳይ የጅምላ ጭፍጨፋዎች ተካሂደዋል። ይህ ሁሉ ወንጀል እየተፈጸመብን አስከዛሬ ወያኔን በጫንቃችን ተሸክመን ለመኖር የተገደድነው እነዚሁ ጥቂት ዘረኞች ሕዝባችንን በዘር፤ በቋንቋና በሃይማኖት በመከፋፈላቸው አንዱ የኅብረተሰብ ክፍል ሲጠቃ ሌላው በዝምታ የሚመለከትበት ሁኔታ በመፈጠሩ ነው።
ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔ በኦጋዴን ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ይህንን አረመኔያዊ እርምጃ አጥብቆ ያወግዛል። ጊዜው ሲደርስ የዚህ ወንጀል ፈፃሚዎች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ብሎ ያምናል። ስለሆነም ወያኔ ሕዝባችንን አቅም ለማሳጣት ላለፉት 23 አመታት በኅብረተሰባችን መካከል የገነባውን የጥርጣሬና የጥላቻ ግንብ በመናድ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በኦጋዴንና በሌሎች የአገራችን ክፍሎች ወገኖቻችን ላይ እየተፈጸመ ያለውን ሰቆቃና እልቂት ለማስቆም እንዲችሉ የተቻለውን ሁሉ ያደርጋል።
ኦጋዴን ውስጥ ለፈሰሰው የንጽሃን ደምና በሰብዓዊነት ላይ እየተፈጸመ ላለው ወንጀል ተጠያቂው ሥልጣንን በኃይል የሙጥኝ በማለት በአገርና በሕዝብ ሃብት ዘረፋ ላይ የተሰማራው ጥቂት የህወሃት አመራር መሆኑ አያጠያይቅም። ይህንን ወንጀለኛ ቡድን ለፍርድ ለማቅረብ ንቅናቄዓችን ግንቦት 7 የሚያደርገውን ሁለገብ ትግል ለፍትህ ለነጻነትና ለዲሞክራሲ የቆመ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲቀላቀል በዚህ አጋጣሚ ጥሪ ቀርቦለታል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

mandag 15. september 2014

ሽመልስ ከማል የሚመራው የአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ስልጠና በጩኸት ተበተነ።

September 15,2014
ምንሊክሳልሳዊ‬

በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ (ቂሊንጦ-አቃቂ) ውስጥ ይሰጣል የተባለው ስልጠና በተማሪው ጉርምርምታ እና ተቃውሞ የተበተነ ሲሆን ስልጠናውን እየሰጠ የሚገኘው ሽመልስ ከማል ብከፍተና ድንጋጤ እና መረበሽ ውስጥ እንደነበር ታውቋል። ትማሪው ከተቃውሞ በተጨማሪ ሽመልስ ሲለፈልፍ የሚሰማው ባለመኖሩ እና ፌስቡክ በመጠቀም ፡የጆሮ ማዳመጫ በማድረግ ሙዚቃ እየስማ ሊለው ደሞ መስማት ደብሮት እያንቀላፋ የስልጠናውን ወንበር ገጥሞ ሲተኛ ተስተውሏል።
ተማሪው እረፍት እንፈልጋለን ወሬ ሰለችን በማለት ቢጮህም ሽምመስ ከማል ዲስኩሩን ቢቀጥልም ተማሪው ተቃውሞውን ስብሰባውን በመርገጥ ወጥቶ ገልጿል። ይህን ተከትሎ ከሰአት በኋላ በየግሩፓችሁ እንድትገኙ ሲል ዩንቨርስቲው ማሳሰቢያ ሰቷል። ተማሪዎቹ ከየክፍለከተማቸው ጥሪ ተደርጎላቸው ትላንትና ወደ ዩንቨርስቲው ግቢ ይተስባሰቡ ሲሆን ከገቡ በኋላ መውጣት አይቻልም ተብሎ ግቢውን በመዘጋጋት ተማሪው በግድ ዩንቨርስቲው ውስት እንዲያድር እና ለዛሬው ስልጠና እንዲገባ ቢደረግን ስልጠናው ሳይሳካ ተበትኗል።
ትላንትና ማታ ኦረንቴሽን የተሰጠ ሲሆን ከግቢው መውትታ የሚቻለው በመጭው ቅዳሜ ከሰአት በኋላ መሆኑ ተነግሯል።የካፌው ምግብን በተመለከተ ደረጃውን ያልተበቀ እና ለጤንነት አስጊ ነው ያሉት ተማሪዎቹ በጥዋት ስልጠና ግቡ ቢባሉም እየተነጫነጩ 2 ሰአት ግቡ የተባሉ 3 ፡10 ገብተዋል፡ ወደ ስልጠናው እንደገቡም ለአንድ ሰአት ያህል ሳይቀጥል ሽመልስ ከማል ምናገር ሲጅምር ጩሀት ስለተጀመረ እና ስልጠናውን አንፈልግም የሚሉ የተቃውሞ ድምጾች በመስማታቸው ረግጠው ለመውጣት ተማሪዎቹ ሲሞክሩ በአስተባባሪዎች በሩ በመዘጋቱ ሁኔታው ስላላማራቸው በሩን በመክፈት ከሰአት ብህውላ በቡድን ስልጠናው እንዲሰጥ በማለት አደራሹ ተዘግቷል።

mandag 1. september 2014

የግንቦት 7 ለነፃነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ በኦስሎ ከተማ የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት አደረገ!!

ዲቦራ ለማ/ ከኖርዌይ
ኦገስት 31, 2014

ኦገስት 31, 2014 በኖርዌ ዋና ከተማ ኦስሎ የግንቦት 7 ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ህዝባዊ ስብሰባና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅቱን በተሳካ ሁኔታ አደረገ። የግንቦት 7 ለፍትህ ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ በተለያዩ ከተሞች እያደረጋቸው ካሉት ህዝባዊ ስብሰባዎች አንዱ የሆነውና በኦስሎ ከተማ የተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ የድርጅቱ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አበበ ቦጋለ በተጋባዥ እንግድነት በስፍራው የተገኙ ሲሆን ይህንን ስብሰባ ያዘጋጀው የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ ነው።

ዝግጅቱ በኖርዌጂያን የሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 1500 ላይ የተጀመረ ሲሆን የድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የመክፈቻ ንግግ አድርገው ባለፉት 23 አመታት በወያኔ የግፍ አገዛዝ ህይወታቸው ላጡ ንፁሀን ዜጎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት በማስደረግ ዝግጅቱን በይፋ አስጀምረዋል።  በመቀጠል የግብረኃይሉ ዋና አስተባባሪ የሆኑት ጠንካራ ሶስት መልክቶችን አስተላልፈው የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እራእይና አላማን እንዲሁም የትግሉን ደረጃ በቪዲዮ የተደገፈ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ከዚህ በመቀጠል የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌ ዋና ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ዮሐንስ አለሙ ይህን ዝግጅት ድርጅታቸው በማዘጋጀቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው እስከዛሬ ከሄድንባቸው የትግል ስልቶች ትግሉን አንድ ደረጃ በማሳደግ የተግባር ስራ መስራት እንደሚገባና ወያኔን ከስልጣን ለማውረድ ሁለገብ ትግላችንን ያለማቋረጥ በተከታታይ ማድረግ እንዳለብን እንዲሁም ያለንበት ሰአት የተግባር ስራን የሚጠይቅ በመሆኑ  ለተግባራዊነቱ የሁላችንንም ቆራጥነት የሚጠይቅ መሆኑን በማሳሰብ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ምክትል ሊቀመንበሩም በተያዘላቸው ሰአት የትግሉን ደረጃና የግንቦት 7ትን ራእይና አላማ ለህዝቡ በዝርዝር በማስተላለፍ በተለይ ወጣቶች የነገ ሀገር ተረካቢ በመሆናቸው ወደ ትግሉ እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል። በቀረበው ጥሪ መሰረት በርካታ ሰዎች የድርጅቱን ፎርም በመሙላት ድጋፋቸውን አጠናክረው ለመቀጠል ግንቦት 7 ትን ተቀላቅለዋል። በስብሰባው መሃልም የአርበኞች ግንባር፣ የትግራይ ህዝብ ንቅናቄ እንዲሁም የግንቦት 7 ህዝባዊ ኃይል ኃላፊዎች በስልክ ለታዳሚው መልክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን በቀጣይ አንዳርጋቸው ፅጌ ማን ነው የሚል የአንዳርጋቸውን ስራዎችና የህይወት ታሪኩን የሚዘክር ቪዲዮም ቀርቧል።

በመጨረሻም የአንዳርጋቸውን ፅጌን ምስል የያዘ ፎቶ ግራፍ ለጨረታ ቀርቦ ህዝቡ በከፍተኛ የገንዘብ መጠን ፉክክሩል አሳይቷል። ከፍተኛውን ገንዘብ በመክፈል የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ጨረታውን በማሸነፉ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ምስል ከአቶ አበበ ቦጋለ እጅ ተረክብዋል። ለዚህ የገቢ ማሰባሰቢያ ሎተሪዎች፣ መፅሀፎት፣ ትኬቶች ምግብና መጠጥ እንዲሁም የተለያዩ ቁሳቁሶች ለሽያጭ የቀረቡ ሲሆን ከሽያጩም ከፍተኛ ገቢ ተገኝትዋል። በመቀጠል የግንቦት 7 ምክትል ሊቀመንበሩ ከተሰብሳቢው ጋር የጥያቄና መልስ ውይይት አድርገዋል። በማጠቃለያም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ ም/ሊቀመንበር የመዝጊያ ንግግር አድርገው በህዝባዊ ኃይሉ መዝሙር ስብሰባው በተያዘለት ሰአት በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል።

ግንቦት 7፤ የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞችና የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች ንቅናቄ ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን የስምምነት ፊርማ ተፈራረሙ

Sep 1,2014
የፋሽስቱ ወያኔን አገዛዝ ለመገርሰስ በተለያዩ መንገዶች ሲታገሉ የቆዩት 3 ቱ ድርጅቶች ወደ ውህደት የሚያደርሳቸውን የጋራ ስምምነት ፊርማ መፈራረማቸውን ለሬዲዮ ክፍላችን የተላከው መረጃ ያመለክታል። የፋሽስቱ ወያኔን ዕድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሰራለን! በሚል ድርጅቶቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ በአገራችን ኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ዘረኛና በታኝ ስርአት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ለማውረድና ሕዝቦቿን ካሉበት አዘቅት በማውጣት የስልጣን ባለቤት የሚሆንበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የጋራ ትግልና መስዋዕትነት ወሳኝ መሆኑን በማመን አንድ ሆነን አገዛዙን በጠነከረ መንገድ ለመፋለም ተስማምተናል ሲሉ በጋራ የመስራቱን አስፈላጊነት ድርጅቶቹ ገልፀዋል።
ይሀ በእንዲህ እንዳለ ውህደት የፈጸሙት 3 ቱ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ህዝብ አርበኞች ግንባር፣ የግንቦት 7፣ የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ እንዲሁም የአማራ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ የተጀመረውን የነፃነት ትግል ከግብ ለማድረስ ህዝባዊ ድጋፍ ይደረግላቸው ዘንድ ጥሪ አቀረቡ የፋሽስቱ ወያኔን ዕድሜ ለማሳጠር በአንድነት እንሰራለን! በሚል በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ድርጅቶቹ በጋራ ባወጡት መግለጫ በአገራችን ኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ፋሽስታዊ ስርአት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ ለማውረድና ሕዝቦቿን ከገቡበት አዘቅት በማውጣት የስልጣን ባለቤት ለማድረግ የጋራ ትግልና መስዋዕትነት ወሳኝ መሆኑን በማመን አንድ ሆነን አገዛዙን በጠነከረ መንገድ ለመፋለም ተስማምተናል ሲሉ የውህደቱን አስፈላጊነት የገለፁት ድርጅቶቹ አያይዘውም አስፈላጊውን መስዋዕትነት በመክፈል የጉጅሌው ወያኔን እድሜ ለማሳጠር በምናደርገው እልህ አስጨረሽ የነፃነት ትግል የኢትዮጵያ ህዝብ ከጎናቸው በመሰለፍ ድጋፍ ያደርግላቸው ዘንድ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። የነፃነት ቀኑ እየተቃረበ መሆኑን ያመላከቱት የድርጅቶቹ ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ ህዝብ ባለበት ቦታ ሆኖ ትግሉን ማፋፋምና መቀላቀል ይኖርበታል ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በአገር ቤት፤ በውጭና በጎረቤት አገር የሚኖር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከድርጅቶቹ ጎን በመሰለፍ የሞራል፤ የገንዘብና የሃሳብ ድጋፍ በመስጠት የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ጥሪ እንዳቀረቡም ለማወቅ ተችሏል። እየተደረገ ያለው ትግል ሁለገብ ትግል መሆኑን ያመለከቱት ድርጅቶቹ በተለይ በውጭ አገራት እንደተጀመረው ሁሉ በአገር ቤት ውስጥም ህዝቡ በተቀናጀ ሁኔታ ለወያኔ አልገዛም ብሎ እምቢተኝነቱን ማሳየት መጀመር እንዳለበት፤ የወያኔን ንግድ ድርጅቶች የሚያዳክሙ ማንኛውም እምጃዎችን መውሰድ መጀመር እና የፋሽስቱ ወያኔ ካድሬዎችንና ተከታዮችን በማግለል ቅጥረኞቹ እንዲሸማቀቁ ብሎም አገዛዙን ሸሽተው የነፃነት ትግሉን እንዲደግፉ አልያም እንዲቀላቀሉ ማድረግ የሚቻልባቸውን ርምጃዎች በተጠናከረ ሁኔታ መውሰድ መጀመር እንዳለባቸው አ ሳስበዋል።
የድርጅቶቹ ውህደት በኢትዮጵያውያን ዘንድ እየተወደሰ መሆኑንም ለማወቅ የተቻለ ሲሆን በተለይ ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች በጋራ ሆነው መታገል ባለመቻላቸው በተናጠል ያደርጉት የነበረው ትግል ውጤት ባለማምጣቱ አገዛዙ ለ 23 አመታት በስልጣን መቆየት መቻሉን በመግለጽ ይሄ አሁን የተጀመረው ሂደት ይህንን ለወያኔ አገዛዝ የተመቻቸ ትግል ይቀለብሳል በማለት ለነፃነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብ ብስራት መሆኑ በስፋት ተነግሯል። ውህደቱ በሰው ሃይል፤ በእውቀትና በገንዘብ ረገድም ድርጅቶቹን መፈርጠም እንደሚያስችላቸውና የተጀመረውን የነፃነት ትግል ዕድሜ እንደሚያሳጥር በብዙዎች ዘንድ እየተገለጸ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል። በመጨረሻም የኢትዮጵያን አንድነት ያስቀደሙት፤ የህዝቦቿን ነፃነት የሚናፍቁና በሁለገብ የትግል እንቅስቃሴ አገዛዙን ለማስወገድ ውህደት ፈፅመው ኢትዮጵያን ለማዳን የተዘጋጁትን እነዚህን ዲሞክራሲያዊ ሃይሎች በተለይ የመከላከያ ሰራዊቱና አገር ተረካቢ የሆነው ወጣት ትውልድ እንዲቀላቀላቸው ጥሪ ማቅረባቸው ታውቋል።