torsdag 30. juli 2015

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ) ሶስተኛ ጉባዔ ተከናወነ



ከሰኔ ፳፮ እስከ ፰ ፪ ሺህ ፯ ዓ. ም  (July 3rd to July 5th 2015) በዋሺንግተን ዲሲ የተካሄደው የሸንጎው ሦስተኛ ጉባዔ  በጥሩ ሁኔታ ተካሂዷል። ጉባዔው ሸንጎ ባለፉት ሁለት ዓመታት ያካሄዳቸውን ዘርፈ ብዙ ስራዎችና የልዩ ልዩ የስራ ግብረ ኃይሎች ሪፖርት ገምግሞ በሚቀጥሉት ዓመታት ትኩረት ለሚያደርግባቸው ግቦች ስኬታማነት፤ የሰው፤ የገንዘብና ሌላ ቁሳቁስ፤ የመረጃ፤ የመገናኛና የሕዝብ ግንኙነት፤ የዲፕሎማሲ፤ የወጣቶችና ሴቶች ተሳፎ፤ በሃገር ቤትና በውጭ ከሚንቀሳቀሱ መሰል ድርጅቶች ጋር የግንኙነት አቅሙን ለማጠናከር… ወዘተ ከመቸውም የበለጠ ጥረት እንደሚያደርግ ወስኗል። አንደሚታወቀው  ሸንጎ እንዲመሰረት ያስገደደው ዋና የፖለቲካ አደረጃጀትና የአመራር ክፍተት የተበታተነውና እርስ በእርሱ የሚጠላለፈው አገር ወዳድ ተቃዋሚ ኃይል ተባብሮ፤ ተመካክሮ፤ ተናቦ፤ ተደራጅቶ፤ ብቁነት ያለው አመራር መስርቶና የጋራ ሰነድ አዘጋጅቶ በተከታታይ ትውልድና ታሪክ ሊጠቀስ የሚችል አስተዋፆ ለማድረግ ሲችል ብቻ ነው የሚል እምነት ስላለው ነው። አሁንም እንዳለፉት ሃያ አራት አመታት የሚታየው የፖለቲካ ሁኔታ ከህወሓት/ኢህአዴግ ጥንካሬ ይልቅ የተቃዋሚው ዘርፍ መፍረክረክ፤ መከፋፈል፤ መጋጨት፤ መነታረክ፤ አለመተማመን፤ መጠላለፍ፤ ራሱን ለሰርጎ ገቦች ማጋለጥ… ወዘተ ነው። በጉባዔው ትንተናና እምነት የተቃዋሚው ኃይል አብሮና ተባብሮ ለመስራት አለመወሰን ለአፋኙ፤ በዝባዡና፤ ጠባብ ጎሰኛው አምባገነን የህወሓት/ኢህአዴግ ስርዓት በገንዘብ ሊገዛው የማይችል አስተዋፆ እያደረገለት ነው። በመግለጫውና ሃተታው እንደምናብራራው ተሳስቦና ተቻችሎ በአንድነት ከመስራት ውጭ ሌላ አማራጭ የለንም። ሰብሳቢ የሆኑ የአንድነት ኃይሎች በሙሉ የሚጋሯቸው፤ ለጋራ ሰነድ ዝግጅት ጠቃሚ ይሆናሉ ብለን የምንገምታቸው አስኳል ጉዳዮች አሉ። ለዚህ ይጠቅማል ብለን የምንገምተው በሸንጎ ውስጥ የተጣመሩት የፖለቲካና የማህበረሰብ ድርጅቶችና የታወቁ አገር ወዳድ ግለሰቦች ተስማምተውና ተጋርተው የሚመሩባቸውን አምስት መርሆዎች መገምገም ነው። እነዚህም፤ አንድ፤ በኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፤ በመላው ሕዝቧ የሥልጣን ባለቤትነትና ሉዑላዊነት ጽኑ ዕምነት ማስተጋባት፤ ሁለት፤ በሕግ ፊት የሁሉም የሀገሪቱ ዜጎች እኩልነትንና የሰብአዊ መብቶች መከበር ወሳኝ መሆናቸውን መቀበል፤ ሶስት፤ ፍትኅ የሰፈነበትና የህግ የበላይነት የተረጋገጠበት ሥርዓት መመስረት አስፈላጊ መሆኑን ማመን፤ አራት፤ በድርጅቶች ውስጥና መሃከል ዴሞክራሲያዊነትን መመሪያ አድርጎ በስራ ላይ ማዋልና፤ አምስት፤ በስልጣን ላይ የሚገኘው የህወሓት/ኢህአደግ አገዛዝ ለዴሞክራሲ መስፈን፤ ለእርጋታ፤ ለሰላም፤ ለዘላቂና ፍትሃዊ እድገት እንቅፋት የሆነ ስርዓት በመሆኑ መወገድ እንዳለበት መቀበልና ያልተቆጠበ ጥረትና አስተዋፆ ማድረግ ናቸው። ጉባዔው፤ እነዚህን ግቦች ስኬታማ ለማድረግ የመጀመሪያዎቹ ጊዜ የማይሰጡ ትኩረቶች ኢትዮጵያን ከመፈራረስ (አገር ለማዳን) እና ሕዝቧን ከእርስ በእርስ እልቂት ለማዳን በአንድነት መነሳት ነው የሚል ነው። ኢትዮጵያ ከጠፋች ሌላው ትግል ትርጉም የለውም ከሚል ስምምነት ላይ ደርሰናል። ጉባዔው እነዚህ መርሆዎች አሁንም አግባብ እንዳላቸው ተቀብሎ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ላይ በጥናቶች የተደገፈ ጥልቀትና ስፋት ያለው ሰፊ ውይይት አድርጓል። ከእነዚህ መካከል ትኩረት የሰጣቸው አስኳል ጉዳዮች የግንቦቱ የይስሙላ “ምርጫ” ትርጉመቢስነት፤ የገዢው ፓርቲና የተቃዋሚው ጎራ ጠንካራና ደካማ ጎኖች፤ አገር ቤትና ውጭ ከሚገኙ የአንድነት ዘርፍ የተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ተከታታይ ውይይት በማድረግ ሰፊና ጠንካራ የሆነ ግንባር መስርቶ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አግባብ ያለው አማራጭና የጋራ ሰነድ በማዘጋጀት፤ ወጣቶችና ሴቶች በሰፊው የሚሳተፉበትን ሁኔታ በማመቻቸት፤ በብሄር/ብሄረሰብና በየክልሉ ስም ተደራጅተውና ታጥቀው ትግል እናካሂዳለን የሚሉት ቡድኖች ከኢትዮጵያ አንድነት አንፃር እንዴት እንደሚታዩ በመዳሰስ፤ በአፍሪካ ቀንድና በሌሎች አካባቢዎች በተከሰቱት ሁኔታዎች፤ ለምሳሌ፤ የሃገራት መፈራረስ፤ የሽብርተኛነት መስፋፋትና የኃያላን መንግሥታት ሚና በኢትዮጵያ ላይ ያለው ጫና ምን አስከትሏል፤ ያስከትላል እና የወደፊቱ የትግል ስልታችን ምን መሆን አለበት… ወዘተ በሚሉት ላይ ነው። የይስሙላውን “ምርጫ” በተመለከተ ሸንጎ ምርጫው ከመካሄዱ ከአንድ ዓመት በፊት የምርጫው ሂደት ነጻ፤ ፍትሃዊና አግባብ ያለው እንዲሆን ከተፈለገ ዘጠኝ ነጥቦችን ያቀፈ ቅድመ ሁኔታዎችና ዝግጅቶች መሟላትና መተግበር እንደነበረባቸው ገልጾ ነበር፡፤ ሆኖም አንዳቸውም ስራ ላይ እንዳልዋሉ አስታውሶ፤ ጉባዔው ህወሓት በበላይነት የሚያሽከረክረው ኢህአዴግ የመንግሥት ለውጥ በምርጫ እንዲካሄድ የማይፈቅድና በሕገ መንግሥቱ መመሪያ መሰረት የሚደረገው የሰላማዊ ትግል ጭላንጭል ሙሉ በሙሉ እንደተዘጋ ተስማምቶበታል። በሕገ መንግሥቱና በዓለም ህጎች መሰረት የመንግሥት ለውጥ በሰላም ሊደረግ አይችልም ብሎ ጭካኔውን፤ አፈናውን፤ ግድያውንና ማሳደዱን ከመቸውም በሚዘገንን ደረጃ የሚያካሂደው ህወሓት የሚያዘውና የሚቆጣጠረው ኢህአዴግ የሚያሳየው ባህርይና ድርጊት ካለፉት ስህተቶች ሊማር አለመቻሉን፤ የበላይ አለቆቹና ተተኪዎቹ ራሳቸው በፈጠሩት የጥላቻና የቂም በቀል ርእዮት ተበክለው በፍርሃት ዓለም ውስጥ የሚኖሩ መሆኑን፤ ይህ ፍርሃት መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ የበከለው መሆኑን… ወዘተ ያሳያል። የማህበረሰብ ሆነ የፖለቲካ፤ የኃይማኖት ሆነ የሰብአዊ መብቶች መከበር ጠበቃ የሆነ ግለሰብና ተቋም ድምፁን ሲያሰማ የሚደርስበት ተከታታይ ክስና የሃሰት መረጃ “ሽብርተኛ ነህ/ነሽ” የሚል ብቻ ነው። በጥላቻና በቂም በቀል የተበከሉት የህወሓት መስራቾችና ተተኪዎች በተደጋጋሚ ሊያስታውሱን የሚሞክሩት ሃቅ “እኛ በትጥቅ ትግል መስዋእት ከፍለን ያገኘነውን ስልጣን” ልትነጥቁን የምትችሉት እናንተም ተመሳሳይ ትግል አካሂዳችሁ ብቻ ነው የሚል እብሪተኛና ትምክህተኛ የሆነ ብሂል ነው። ይህ አብሪትና ትምክህተኛነት ሁለት የማያሻሙና መፈታት ያለባቸው ችግሮችን ያንፀባርቃሉ፤ አንድ፤ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ የመንግሥት አመራርና ስርዓት ለውጥ ወይንም ሽግግር በሰላም ሊተገበር አለማቻሉን፤ ይኼም ለዲሞክራሲ ምስረታ ማነቆ መሆኑን፤ ሁለት፤ በሃገር ውስጥ የእርስ በእርስ ጦርነትና በውጭ ወረራ ምክንያቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ በህይወቱና በኃብቱ ብዙ መስዋእት መክፈሉ፤ መራቆቱ፤ መድከሙ፤ መማረሩ፤ ክብሩን መገፈፉ፤ ሉዐላዊነቱና ትሥስሩ መውደሙ ናቸው። ጉባዔው ይኼ ዑደት (Cycle) እና ሁከት (Cycle of Violence) ልክ እንደ ተራ ነገር የተለመደ መሆኑ ለሃገራችን ህልውና ዘላቂነትና ለስብጥር ሕዝቧ አብሮና ተቻችሎ ማደግና መኖር ፀር መሆኑንና አዲስ የፖለቲካ ምእራፍ መክፈት ብልህነት መሆኑን ተስማምቶበታል። አዲስ ፖለቲካ ስንል፤ ከጥላቻና ከቂም በቀል የፖለቲካ ባህል ወደ መቻቻል፤ መወያየት፤ መከባበር፤ መደማመጥ፤ አብሮ ችግሮችን ወደ መፍታት፤ መደጋገፍ… ወዘተ ባህል እንዙር ማለታችን ነው። የህወሓት/ኢህአዴግን የጥላቻ ባህል ይዘን ዲሞክራሳዊ ስርዓት ልንመሰርት አንችልም። ህወሓት ይኼን የተያያዘ ጊዜ ያለፈበት የጥላቻና የቂም በቀል ፖለቲካ ባህል ይዞ መቀጠሉ ለተገንጣዮችና ኢትዮጵያ እንድትፈራርስ ለሚመኙ የውጭ ኃይሎችና ለሽብርተኛነት በር ከፍቷል። የይስሙላው ምርጫ ያባባሰው ይኼን የማይካድ ሁከት ነው። ይኼን በተመለከተ፤ ኢትዮጵያን አፍኖ ለሚገዛው  ቡድን አሳፋሪ ሁኖ ያገኘነው ክስተት ገዢው ፓርቲ ከ547 የፓርላማ ወንበሮች “424 አሸንፊያለሁ” ብሎ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ማቅረቡ ብቻ ሳይሆን የቀሩትን ወንበሮች ራሱ ለፈጠራቸው፤ ታማኝና ታዛዥ ለሆኑ ተጠላፊ ፓርቲዎች መስጠቱ ነው። የዛሬ አምስት ዓመት “በ 99.6” አሸነፍኩ ያለውን የዓለም ሕዝብ ያልተቀበለውን ውጤት ከፍ አድርጎ “መቶ በመቶ አሸነፍኩ” ሲል ስርዓቱን በሕዝብ ድምፅና በሰላም ለመለወጥ አትችሉም የሚል የማያሻማ መልእክት አቅርቦልናል። ስለሆነም፤ የጉባዔው ዘገባና ድምዳሜ አንድና፤ አንድ ብቻ ነው። ይኼውም፤ ሕግ መንግሥቱ የሚፈቅደው የምርጫ ሂደትና ለሃገሪቱ ሕዝብ አገልግሎት ይሰጣሉ ተብለው የተቋቋሙት ተቋሞች–የምርጫ ቦርድ፤ ፍርድ ቤቶች፤ የፌደራል ፖሊስ፤ መገናኛ፤ ደህንነት፤ መከላከያ…ወዘተ–ለገዢው ፓርቲ ማፈኛና መቆጣጠሪያ፤ መቆያና የኃብት ማካበቻ መሳሪያዎች ሁነዋል የሚል ነው። የምርጫ ቦርድ የፖለቲካ መሳሪያ መሆኑን በተደጋጋሚ አይተናል። በአለፉት አምስት ምርጫዎች ህወሓት/ኢህአዴግ ከዓለም የምርጫ መስፈርቶች ጋር የተጻረረ፤ እውነተኛ የሆኑ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያፈራረሰ፤ መሪዎችን ያሳደደ፤ ያሰረና፤ ምርጫውን ካሸነፈ በኋላም የገደለ፤ በመግደልና በማሳደድ ላይ ያለ፤ የሕዝብ እምቢተኛነት ሲከሰት ችግሩን ሁሉ በአፈናና በመሳሪያ ኃይል እፈታለሁ የሚል አምባገነናዊ አገዛዝ ሆኗል። በአጭሩ፤ ህወሓት በበላይነት የሚያሽከረክረው አገዛዝ ሃገሪቱን ለከፋ አደጋ ያጋለጠና የእርስ በእርስ ጥላቻና እልቂት እንዲካሄድ ያመቻቸ ሆኖ አግኝተነዋል። በጉባዔው ዘገባ፤ ዲሞክራሳዊ ለውጥ ጊዜ የማይሰጥ አስቸኳይ ጉዳይ ሆኗል። ጉባዔው ለማጠናከር የፈልገው መልእክት፤ ህወሓት የሚያካሂደው “የከፋፍለህ ግዛው”፤ የብሄር/ብሄረሰብና የኃይማኖት ጥላቻና ጎሳዊ አድልዎ ለሃገራችን አንድነትና ሉዐላዊነት” እና ለመቶ ሚሊዮን ሕዝቦቿ ሰላም፤ ደህንነት፤ አብሮና ተሳስሮ መኖር ዋናው አደጋ ፈጣሪ ሆኗል። ለማጠናከር፤ ጉባዔው ከዚህ ዘገባና ድምዳሜ ለመድረስ ያመዛዘናቸውን አደገኛ ሁኔታዎች በአጭሩ እናቅርባለን። ሌላውን ሁሉ መረጃ ወደ ጎን ትተን፤ ባውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 የአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት “የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ዓመታዊ” ሪፖርትን፤ ባለፈው ዓመት መጨረሻ (2014) የወጣውን  የ አሜሪካ ኢንተለጀንሰ መስሪያ ቤት ያዘጋጀውን ዘገባ( “U.S. National Intelligence Council Documentary on the TPLF”) እና መንግስታዊ ያልሁነው ፈንድ ፎር ፒሰ (The Fund for Peace, )  በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኙ መንግስታት (“Failed and Failing States”  ) በሚል ያቀርቧቸውን አስጊ ሁኔታዎች እንጠቅሳለን። አንድ፤ የገንዘብና የተፈጥሮ ኃብት ዘረፋ—ህወሓት እንደ ፓርቲ የሚቆጣጠራቸውና የፈጠራቸው የኢኮኖሚና የፋይናንስ ተቋሞች–ለምሳሌ ኤፈርት የተባለው ሞኖፖሊ፤ በበላይነት የሚቆጣጠረው መንግሥት፤ ጥቂት ምርጥ ግለሰቦች፤ የስለላ፤ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ የበላዮች አብዛኛውን ዘመናዊ ኢኮኖሚ ተቆጣጥረውታል። የጠባብ ጎሳ የበላይነትን ከኢኮኖሚና የተፈጥሮ ኃብት ባለቤትነትና የበላይነት ጋር አጣምረውታል። ገቢና ኃብት የሚገኝባቸውን ምንጮች ሙሉ በሙሉ የራሳቸው የግልና የቡድን አድርገውታል። ህወሓት የነጋዴዎች፤ የኪራይ ሰብሳቢዎች፤ የአትራፊዎችና የዘራፊዎች ስብስብ ቡድን ሆኗል። ሌላውን “አጥፊ ተቃዋሚ” እያለ በመወንጀል እራሱ ወንጀለኛ ከሆነ አመታት አልፈውታል። ይኼን ነው፤ ዶኪውሜንተሪው “Ethnocracy combined with Plutocracy” ኢትዮጵያ በዓለም እርዳታ ከሚያገኙ ሃገሮች መካከል አራተኛውን ደረጃ፤ በአፍሪካ አንደኛውን ደረጃ ይዛ ሕዝቧን ለመመገብ አልቻለችም። ከሚለገሰው ግዙፍ እርዳታ ምን ያህሉ ድህነትን ለማጥፋት እንደሚውል አናውቅም። የምናውቀው የህወሓት የበላዮችና ጥቂት አጋሮቻቸው ታይቶ የማይታወቅ ድርጅታዊ ምዝበራ እያካሄዱ፤ ኃብት እንዳካበቱና በልጆቻቸውና በሌላ ዘዴ ብዙ ቢሊየን ዶላር ከሃገር እንዳሸሹ፤ የግል ኩባንያዎች እንዳቋቋሙ ተደርሶበታል። Global Financial Integrity, 2000-2009 ባወጣው ዘገባ $11.7 ቢሊዮን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ተሰርቆ ወደ ውጭ ተልኳል፤ በዚህ ዓመት መጀመሪያ የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝደንት እምቤኪ የመራው ግብረ ኃይል ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ከኢትዮጵያ ተሰርቆ የሸሸው $10 ቢሊየን ነው። ህወሓት የማይክደው $21 ቢሊየን ዶላር ከሃገር ተሰርቆ ሸሽቷል። ስንት የስራ እድል ይፈጥር ነበር? ለዚህ ተጠያቂው ማን እንደሆነ አከራካሪ አይሆንም። ሁለት፤ የዘር ፍጅት፤ ማጽዳት ዘመቻ (Genocide and ethnic cleansing)— የህወሓት  መሪዎችና ተተኪዎች ሌሎች ጠባብ ጎሰኞችን አሳምነው በአማራው ሕዝብ ላይ ከፍተኛ የተቀነባበረና ተከታታይ የዘር ፍጅት ዘመቻ አካሂደዋል፤ አሁንም እያካሄዱ ነው። የብሄር ጥላቻን እንደ ትግል ስልት ተጠቅመው ሌላውን በጥላቻ በክለውታል። ወጣቱ ትውልድ እንዲያምን የተገደደው ጥላቻን፤  የራስን ጥቅም የበላይነት…ወዘተ እንጅ አገራዊና ብሄራዊ ፍቅርንና ጥቅምን አይደለም። ህወሓት ከጅምሩ፤ የትግራይን ሕዝብ “ያዳከመው፤ ያደኸየው፤ ያገለለውና ያጠቃው የአማራው ብሄርረሰብ ነው” በሚል ብሂል፤ የጥላቻ ጦርነት ሲያካሂድ ቆይቷል። ዘገባዎችና መረጃዎች የሚያሳዩት በጅጅጋ፤ በደቡብ ሸዋ፤ በጉራ ፈርዳ፤ በቤኒ ሻንጉል ጉሙዝ፤ በጋምቤላ፤ በወልቃይት ጠገዴና ሌሎች ቦታዎች የሚዘገንንና በፍርድ የሚያስጠይቅ ፍጅት አካሂደዋል። የራሱ የገዢው ፓርቲ የሕዝብ ቆጠራ ያሳየው ቢያንስ ሁለት ሚሊየን አምስት መቶ ሽህ የአማራ ሕዝብ በጥቂት አመታት ውስጥ የት እንደደረሰ አይታወቅም፤ ሌሎች (ለምሳሌ ኢኮንሚስቱ ዶር ብርሃኑ አበጋዝ በምርምር የተደገፈ ማስረጃ) ይኼ ቁጥር ከአምስት ሚሊየን በላይ ሕዝብ መሆኑን ያሳያል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ይህ ሕዝብ የት ደረሰ፤ ተሰደደ፤ ተገደለ፤ ማንነቱን እንዲለውጥ ሆነ? ለዚህ ጉዳይ ተጠያቂው ማነው? በኛ አመለካከት ህወሓትና አጋሮቹ መሆናቸው አያከራክርም። በተጨማሪ፤ የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ ችግሮችን በሰላምና በመደራደር በመፍታት ፋንታ በአኟክና (2003)፤ በኦጋዴን ኢትዮጵያዊ ሶማሌ ሕዝብ ላይ (በተደጋጋሚ)፤ የሚዘገንን፤ በቪዲዮ የተቀረጸ በፌደራል ፖሊስ የተመራ በዘር ፍጆት የሚመደብ ወንጀሎች ፈጽሟል። በተጨማሪ፤ በተራው የጋምቤላ፤ የኦሞ ሸለቆና ሌሎች ነዋሪዎች ላይ ሂውማን ራይትሰ ዋች፣ አምንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ኢንተርናሽናል ሪቨርስ፣ ኦክላንድ ኢንስቲትዩት ፣ ጋርዲያን ጋዜጣና ሌሎቹም (Human Rights Watch, Genocide Watch, Amnesty International, International Rivers, Oakland Institute, the Guardian and others) የመዘገቡት የመሬት ነጠቃና ከዚህ ጋር የተያያዘው ነዋሪዎችን ከቀያቸው የማባረር ወንጀል በተደጋጋሚ ተፈጽሟል። ገዢው ፓርቲ እነዚህን የመሳሰሉ ወንጀሎች ሲፈፅም “በልማትና በፀጥታ አስፈላጊነት” ስም ነው። በተጨማሪ፤ እየለየ በድብቅ የሚገድላቸው፤ የሚያስራቸው፤ የሚደበድባቸው፤ ንበረታቸውን የሚገፋቸው፤ እንዲሰደዱ የሚያስገድዳቸው የሃገር ፍቅር ያላቸውን፤ ደፋሮቹን፤ መሪ ለመሆን ብቃት ያላቸውን፤ ለፍትህና ለዲሞክራሲ የቆሙትን ነው። ምርጫውን “አሸነፍኩ” ካለ በኋላ የገደላቸው ደፋርና አገር ወዳድ መሪዎች ምን ወንጀል ሰሩ? ማን ገደላቸው፤ በማን ትእዛዝ? የገደሉት ለምን አልተያዙም? የተገደሉበት ዋና ምክንያት ለህወሓት ተወዳዳሪ የሆነ አገር ወዳድና በፍትህ የሚያምን ትውልድ እንዳይፈጠር መቀጣጫ ለማድረግ ነው። ሶስት፤ የሰብዓዊ መብቶች፤ የኃይማኖትና የፕሬስ ነጻነት አፈና— ከላይ እንዳቀረብነው፤ ያለፈው ምርጫ የፖለቲካ ምህዳር መዘጋት ነፀብራቅ ነው። አምንስቲ ኢንተርናሽናል፣ ሂውማን ራይትስ ዋች፣ ፍሪደም ሀውስ፤ የጋዜጠኞች መብት ተከራካሪው ሲፒጄ ያሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን፡ የአውሮፓ ማህበርና ሌሎችም የሚጋሩት የኢትዮጵያ አገዛዝ ለማህበራዊ (ለሰብአዊ) መብቶች ፀር መሆኑንና ይኼ ሁኔታ ከቀጠለ ለሃገሪቱ መፈራረስና ለእርስ በእርስ ጦርነት መዘዝ መሆኑን ነው። ሲፒጄ (CPJ) ባደረገው ጥናት መሰረት “ኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን በማፈንና ከሃገር እንዲለቁ በማድረግ፤ ከዓለም አራተኛ፤ ከአፍሪካ ሁለተኛ” መሆኗን በተደጋጋሚ አስምሮበታል። ሽብርተኛ ተብለው ከታሰሩት መካከል እስክንድር ደስታ፤ ተመስገን ደሳለኝ፤ ውብሸት ታየ፤ አንዱ ዓለም አራጌ፤ ሃብታሙ አያሌው፤ አቡበከር አህመድ፤ አብርሃ ደስታ፤ የሸዋስ አሰፋ፤ ዳንኤል ሽበሽና ሌሎች ብዙ ሽዎች የፖለቲካ እስረኞች ይገኙበታል። ቢያንስ ሰባ ዘጠኝ ጋዜጠኞች ከሃገር ተሰደዋል፤ ይኼ “በዓለም የመጀመሪያውን ደረጃ” የያዘ ሃቅ ነው። ከላይ የጠቀስነው ዶኪሜንተሪ እንዳሳየው  የኢትዮጵያ መንግስት ከጋዳፊና ባለማችን ከታዩት ሌሎችም ጨካኝ አምባገነኖች የማይለይ መሆኑን ነው ህወሓት ሁሉንም ተቋሞች ለመቆጣጠር በተከተለው ዘዴ መሰረት፤ ስልጣን በያዘ ማግስት የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኃይማኖትን አመራር በቁጥጥሩ ስር እንዲውል አድርጓል፤ አግባብ ያላቸውን ፓትሪያርክ አስወግዶ ለህወሓት ታዛዥና ታማኝ የሆኑ የትግራይ ተወላጅ ሹሟል። እንደ ዋልድባ ያሉ የማይተኩ ገዳሞችን ህልውና ለማሳጣት ሞክሯል፤ የዋልድባ አባቶችና እናቶች የሚተዳደሩበትን መሬት ለስኳር አገዳ ማምረቻ እንዲውል አድርጓል። ኃይማኖትን የፖለቲካ የበላይነት መሳሪያ ማድረግ ለሃገሪቱ አደጋ ፈጥሯል፤ ለውጭ ኃይሎች መግቢያ ቀዳዳ ሆኗል። በተመሳሳይ፤ የእስልምና ኃይማኖት አመራር ህወሓት በሚፈልገው መንገድ እንዲቋቋምና እንዲመራ አድርጓል፤ መሪዎችንና አባላትን አስሯል። ገዢው ፓርቲ አስደናቂ እድገት እያሳየሁ ነው በሚላት የምግብ ጥገኛ ሃገር፤ ለወጣቱ ትውልድ የስራ እድል ለመፍጠር አልተቻለም። ዛሬ ሃገሪቱ ከምትታወቅባቸው አንዱ ወጣቱ ትውልድ በተከታታይ መሰደዱ ነው። በየዓመቱ፤ ብዙ ሽህ ወጣቶች በጅቡቲ፤ በሶማሊያ፤ በሰሜንና ደቡብ ሱዳን፤ በኬንያ ወይንም የመውጫ ፈቃድ አግኝተው በቦሌ ወደ ውጭ ይሰደዳሉ። ከወጡ በኋላ የህወሓት/ኢህአዴግ  አገዛዝ መብታቸውን አያስከብርም። የኢኮኖሚው አመራር በሕዝብ የበላይነት የሚመራ ካልሆነ፤ ሕዝብን የእድገት ማእከል ካላደረገና የእድገቱ ውጤት ለሕዝብ አገልግሎት ካልዋለ የኑሮው ቀውስና ስደቱ አያቆምም። አራት፤ ከመንግሥት ባለቤትነት የመነጨ የመሬት ነጠቃ—አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚተዳደረው በእርሻና ተመሳሳይ ስራ ነው። በገጠር ሆነ በከተማ የመሬት ባለቤትነት የዜግነት መታወቂያና የኑሮ መመኪያ ነው። ህወሓት በበላይነት የሚመራው አገዛዝ የተፈጥሮ ኃብትን በሙሉ “የመንግሥት ነው” በሚል ዘዴ መሬትን ለንግድና ለግል ጥቅም አውሎታል። የመሬት ቅርምት (Land Grab) ተብሎ የሚጠራው የኢትዮጵያውያንን አንጡራ የተፈጥሮ ኃብት ለውጭ አገር ኢንቬስተሮች ቸርችሮታል። ሳውዲ ስታር፤ የህንዱ ካሩቱሪ፤ ሩች ሶያ፤ የህንድ ድንች አምራቾች ተቋምና ሌሎች ጋምቤላን ሙሉ በሙሉ ተቀራምተውታል ለማለት ይቻላል። ብዙ ሚሊየን ሄክታር ለም መሬትና ወንዝ ለውጭና በሃገር ቤት ታማኝ ለሆኑ አትራፊዎች ተቸርችሯል። በጋምቤላ ብቻ የታወቀው ለውጭ ኢንቬስትሮች የተሰጠውና የግል የሆነው መሬት በዝቅተኛ 650,000 ሄካታር በከፍተኛ 2,000,000 ሄክታር ይደርሳል። የከተማና የገጠር መሬት ለግል ትርፍና ለሙስና ቁልፍ ሆኗል። በከተማ ቦታ ምደባ፤ ስደተኛውም ተጠቃሚ ሁኖ የከተማ መሬትን ዋጋ የማይቀመስ አድርጎታል። ይኼ በፖለቲካ የበላይነት የሚወሰን የመሬት አስተዳደር ሁኔታ እስካልተለወጠ ድረስ ፍትሃዊ የሆነ የመሬት አጠቃቀም ሊኖር አይችልም። አምስት፤ የስለላ፤ የደህንነት፤ የመከላከያ፤ የፍርድና የፌደራል ፖሊስ ፍፁም የበላይነት —እነዚህና እንደ ጉምሩክ፤ መገናኛ ቁልፍ ሚና ያላቸው ተቋሞች የሚያገለግሉት ህወሓትን ነው። የፓርቲው ተቀጥላዎችና አገልጋዮች ከሆኑ ቆይተዋል። በ2009 የተገኘ መረጃ ያሳየው ከጠቅላላው የኢትዮጵያ የመከላከያ እዝ አስራ ሰባቱ ጀኔራሎችና አርባዎቹ ኮሎኔሎች የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ፤ አንድ የአገው ተወላጅና አንድ የአማራ ተወላጅ ጀኔራሎች ነበሩ። አንድም የኦሮሞ ጀኔራል የለም፤ በኮሎኔል ደረጃ ሌሎች ብሄረሰቦች አልተወከሉም። በፖለቲካው፤ በኢኮኖሚው፤ በባንኩና ፋይናንሱ፤ በመገናኛው፤ በአስተዳደሩ፤ በደህንነቱ፤ በመከላከያው፤ በፌደራል ፖሊሱ፤ በጉሙሩኩ ዘርፎች የፖሊሲና የውሳኔ ኃላፊዎች የትግራይ ተወላጆች ናቸው። እንደዚህ አይን ያወጣ አድልዎ የትም ሃገር አይታይም። ቢያንስ ዘጠና አምስት በመቶ የሚሆነው የደህንነቱን፤ የፌደራል፤ የልዩ ፖሊሱንና የመከላከያውን እዝ በበላይነት የሚመሩት ለህወሓት ታማኝ የሆኑ የትግራይ ብሄረሰብ አባላት ናቸው። ይኼ አይን ያወጣ  አድልኦ መሆኑ አያከራክርም።  ይኼ ለበላይነት የተዋቀረና እጅግ ጠባብ የሆነ  አመራር ለሃገሪቱ ደህንነትና ዘላቂነት፤ ለሕዝቧ ሉዐላዊነትና አንድነት፤ ለሕግ የበላይነትና ለዴሞክራሲ አደገኛ መሰናክል ፈጥሯል።  ህወሓት ይኼን የበላይነት ያጠናከረው ኢትዮጵያዊ የሆኑ ተቋሞችን በማውደም፤ የኢትዮጵያን ታሪክ በማጥፋት፤ የትምህርት ይዘቱን ክልላዊና ጎሳዊ በማድረግ፤ አገር ወዳድ የሆኑ መምህራንን በማባረር፤ የጥላቻ ባህል ጥልቀትና ስፋት ይዞ አዲሱ ትውልድ እርስ በእርሱ እንዳይተማመንና ብሎም እንዲጋጭ በማድረግ ነው። ዛሬ ልክ ዩጎስላቪያ እንደሆነው፤ ሕዝብን ከሕዝብ ጋር የሚያያይዙ ባህሎችና ልምዶች በህወሓት ወድመዋል ለማለት እንችላለን። ይኼ ሁኔታ ለእርስ በእርስ ግጭት፤ ለዘር ፍጅት፤ ለተገንጣይ ኃይሎችና ለውጭ ጠላቶች የጥቃት መግቢያ ሆኗል። ስድስት፤ የውጭ መንግሥታት፤ በተለይ የአሜሪካ መንግሥት ሚና አሳሳቢነት–የምእራብ ሃገሮች፤ በተለይ የአሜሪካ መንግሥት ከሰብዓዊ መብቶች መከበር ይልቅ ለመረጋጋትና ለፀረ-ሽብርተኛነት ዘመቻ ቅድሚያ እየሰጠ አምባገነኑን የህወሓት/ኢህአዴግ አገዛዝ መደገፉ ለራሱ ጉዳት እንዳመጣ እናምናለን። የኢትዮጵያና የአሜሪካ ከመቶ አስር ዓመታት በላይ የቆየ ግንኙነት አስተማማኝ በሆነ ደረጃ ሊቀጥል የሚችለው አፋኙን አገዛዝ በማውገዝና የሚሰጠው የገንዘብና ሌላ እርዳታ እንዲቆም በማድረግ እንጅ ድጋፉን በመቀጠል አይደለም። የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ቀውስ ውስጥ መግባት፤ መባባስ፤ የሰብአዊ መብቶች መረገጥ፤ የኃይማኖት ነጻነት መታፈን፤ በፀረ-ሽብርተኛነት ሽፋን የገዢው ፓርቲ ሕዝብ አሸባሪ መሆን፤ የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ መባከን፤ ከመቶ በላይ የሚገመቱ በጎሳ የተደራጁና የታጠቁ ፖለቲካ ፓርቲዎች የሃገሪቱ ሁኔታ ተባብሶ የመገንጠል ዓላማቸውን ስኬታማ ለማድረግ መዘጋጀት፤ ለልማት መዋል የሚችል ግዙፍ የሆነ ኃብት ከሃገር እየሸሸ መውጣቱ…ወዘተ ለአሜሪካም ዘላቂ “ጥቅም” ጉዳት እንደሚያመጣ እንገምታለን። ለዚህ አግባብ ያለው፤ የማያሻማ መልእክት ለኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ መስጠት ነው። ጉባዔው በቅርቡ ሸንጎ ለፕሬዝደንት ኦባማ የጻፈውን ግልፅ ደብዳቤ መሰረት አድርጎ፤ የአሜሪካ መንግሥት ለሚከተሉት መተክሎች (Principles) እና እሴቶች ትኩረት እንዲሰጥ የዲፕሎማቲክ ዘመቻ ማካሄድ ይኖርበታል በሚል ተስማምቷል። አንድ፤ የፖለቲካ እስረኞች፤ ጋዜጠኞች፤ ብሎገሮችና የኃይማኖት መሪዎችና ተከታዮች በሙሉ በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤ ጥቂቶቹን ለይስሙላ ፈትቶ ሌሎችን እያሰቃየ ነው፤ ሁለት፤ የመገናኛ ብዙሃን፤ የኃይማኖት፤ የመናገር፤ የመሰብሰብ፤ የመንቀሳቀስና የመደራጀት ነጻነት እንዲከበሩ፤ የማህበረሰብ ድርጅቶች እገባ እንዲቆም፤ የፀረ-ሽብርተኛው ሕግ እንዲነሳ፤ ሶስት፤ የፍርድ ቤት፤ የፌደራል ፖሊስ፤ የመከላከያና የምርጫ ቦርድ ተቋሞች ከገዢው ፓርቲ ቁጥጥር ነጻ ሁነው መላውን ሕብረተሰብ እንዲያገለግሉ፤ አራት፤ ነዋሪዎችን ከመሬታቸው እንዲገለሉ የሚደረገው ዘመቻ እንዲቆም፤ አምስት፤ በዘር ፍጅት የሚታወቁ ባለስልጣናት ለፍርድ እንዲቀርቡና የዘር ፍጅት ዘመቻው በአስቸኳይ እንዲቆም። ከላይ የቀረቡት መተክሎች አሜሪካ የምታምንባቸው እሴቶች እንደመሆናቸው መጠን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደተግባር ካልተተረጎሙ የአሜሪካ መንግሥት ለህወሓት/ኢህአዴግ የሚሰጠውን እርዳታ በጥንቃቄ መመርመር ይገባዋል። ጉባዔው  ይኼን በሚመለከት የሸንጎ አመራር ለፕሬዝደንት ኦባማ ልዩ ደብዳቤ እንዲፅፍ አሳስቧል። የትግል ስልት ከላይ የቀረበውን ኃሳብና አቅጣጫ መሰረት በማድረግ ጉባዔው ስለ ትግል ስልት ሰፊ ውይይት አድርጎ በሚከተለው ተስማምቷል። ህወሓት/ኢህአዴግ የፖለቲካውንና የማህበረሰቡን ነጻነት ተስፋ፤ ምኞትና የመንቀሳቀስ ምህዳር ሙሉ በሙሉ በመዝጋቱ በሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መብት መሰረት በሰላም ለውጥ ለማምጣት የማይቻል መሆኑን አምኗል። ጉባዔው፤ ተቃዋሚዎች፤ የተለያዩ የትግል ስልቶች ቢከተሉም፤ ኢትዮጵያን እንታደግ፤ ለአገራዊና ብሄራዊ ስሜት እንታገል፤ መጠላለፍ እናቁም፤ እንደጋገፍና እንተባበር ከሚሉ አገር ወዳድ ከሆኑ የአንድነት ኃይሎች ጋር አብሮ ለመስራት ያደረገውን ጥሪ አሁንም ያድሳል። ሸንጎ በመግቢያው የቀረቡትን መርሆዎች ስኬታማ ለማደረግ ከዚህ በፊት በተከታታይና በቆራጥነት ያልተሞከሩ የትግል መንገዶች ሁሉ መስተናገድ አለባቸው የሚል እምነት አለው። በተጨማሪ፤ ህወሓት/ኢህአዴግ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ሲያስተጋባ ከቆየው የብሄር/ብሄረሰብና የኃይማኖት ከፋፋይነት፤ የጥላቻና የቂም በቀል የፖለቲካ ባህል ወደ ዴሞክራሲያዊ ባህል መሸጋገር ወሳኝ መሆኑን እናምናለን። ምንም እንኳን የሃገሪቱ የተፈጥሮ ኃብትና እድገት ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ጥቅም ይዋል፤ መሰረታዊ ሰብአዊ መብቶች ይከበሩ፣ የሀገር አንድነት ይጠበቅ…ወዘተ የሚል እምነት ይዘው ገዢውን ፓርቲ  ሲታገሉ ብዙ ታጋዮች ቢገደሉም፤ ቢታሰሩም፤ ቢደበደቡም፤ ከሃገር ቢሰደዱም፤ አሁንም በሃገር ቤት ሁነው የሚታገሉ አገር ወዳድ፤ ደፋርና ለውጥ ፈላጊዎች ብዙዎች ናቸው። እነዚህን ደፋር፤ ቆራጥና አገር ወዳድ  ወገኖቻችንን በማንኛውም መንገድ መደገፍ አቅማቸውንም ለመገንባት በሚያደርጉት ጥረት ማገዝ  አስፈላጊ ነው። በመርሆዎቻችን መሰረት ኢትዮጵያውያንን ያማከለና ያሳተፈ  የተጠናከረ ሰላማዊ ትግል እንዲካሄድና አፋኙ አገዛዝ በዴሞክራሲያዊ  አስተዳደር እንዲተካ ያልተቆጠበ ጥረት እናደርጋለን።  በሰላማዊ ትግል እናምናለን የሚሉ የፖለቲካ፤ የማህበረሰብ፤ የኃይማኖት፤ የሞያና ሌሎች ድርጅቶች፤ ታዋቂ ግለሰቦችና ሌሎች የሚያካሂዱት ትግል ውጤታማ ሊሆን የሚችለው የዓላማ አንድነት ተከትለው (ተከትለን) በትግል ስልት የተለያዩትንም ሲያካትቱ (ስናካትት) ነው። ጉባዔው የተለያዩ የትግል ስልቶች መኖራቸውን ተቀብሎ የትግሉን ዘላቂነትና ውጤታማነት የሚወስነው ሕዝብን ማእከል፤ አጋርና አሳታፊ ማድረግ ከቻለ መሆኑን አስምሮበታል። ሕዝብን ያሳተፈ፤ ሕዝብ በባለቤትነት የያዘው ትግል በምንም ሊጠቃ አይችልም። ዴሞክራሲያዊ  አስተዳደር አስተማማኝ ሊሆን የሚችለው የሕዝብን አመኔታ ሲያገኝ ብቻ ነው የሚለውን ግብ ጉባዔው ተቀብሎታል። ትግሉ በከተማና በገጠር የተያያዘና የተቀነባበረ እንዲሆን ድርሻችን ከመወጣት ወደ ኋላ አንልም። ለሰላማዊ ትግሉ ውጤታማነት  የሚጠቅመው የተሳሰረና የተቀነባበረ አመራር ያለው አገር አቀፍ እምቢተኛነት ነው የሚል እምነት አለን።  ለምሳሌ፤ ከተሜው፤ ገጠሬው፤ ወጣቱ፤ አዛውንቱ፤ ድሃው፤ ባለ ኃብቱ የተባበረበት የየካቲትን ወይንም የግንቦት ዘጠና ሰባትን የሚመስል የሕዝብ እምቢተኛነት ትግል፤ አንዱ ወገን ሲጠቃ ሌላው ድምፅ የማሰማት ትግል፤ የስራ ማቆም አድማ፤ ሰላማዊ ሰልፍ፤ የህወሓት/ኢህአዴግ የግል የንግድ ተቋሞች እቀባ፤ በሃገር ቤትና በውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች የዲፕሎማሲ ትብብር ገዢውን ፓርቲ የማጋለጥ ዘመቻ፤ የተጠናከረ የዘመናዊ መገናኛ ብዙሃን ተጠቅሞ ህወሓት/ኢህአዴግ ወጣቱን ትውልድ የሃገሩን ታሪክ፤ የጀግኖቿን ጀብዱ ስራ፤ የሕዝቡን ተቻችሎ መኖር ወዘተ የሃሰትና የሰው ሰራሽ ታሪክ መሰሪነት አውቆ ለሃገሩና ለወገኑ ተባብሮ የሚነሳበት ዘመቻ፤ በውጭ የሚገኘውን የህወሓት/ኢህአዴግ የስለላ መረብ የማጋለጥና ሰላዮችን ለፍርድ የማቅረብ ዘመቻ፤ ከሃገር ተሰርቆ የሸሸውን ኃብት የማጋለጥና የማስመለስ ዘመቻ፤ በጥናትና ምርምር የተመሰረተ የእርቅና የሠላም ድርድር ዘመቻ፤ የአንድነት ኃይሎች መተባበርና ውጤት የሚያስገኝ ትግል ዘመቻ ወዘተ። እነዚህና ሌሎች በተከታታይነት ያልተሞከሩ የትግል ዘርፎች ናቸው። የህወሓት/ኢህአዴግን ፈቃደኛነት አይጠይቁም። ከላይ እንዳሳየነው፤ እብሪተኛው ገዢ ፓርቲ ለእርቅና ለሰላም የሚደረግ ጥሪን እንደማያስተናግድ እናምናለን። ሆኖም፤ ጥረቱ በጥላቻ፤ በቂም በቀልና በራስ ወዳድነት ለተበከለው የአዲስ ትውልድ ክፍል ትምህርታዊ ግብዓቶችን ያበረክታል፤ የዓለምን ሕብረተሰብ ልቦና ያንቀሳቅሳል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የመንግሥት ለውጥ በመሳሪያ ብቻ እንጅ በመወያየትና በመደራደር አይታሰብምና ተቃዋሚዎች የሚፈልጉት ዲሞክራሲን ሳይሆን ስልጣንን ነው የሚለውን ከእውነቱ የራቀ  የህወሓት/ኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳ የማይቀበሉ የአንድነት ኃይሎች እንዳሉ ያሳያል። እነዚህን ሁሉ ለማድረግ ቆራጥነትና ተባባሪነት ያስፈልጋል፤ በፅሁፍ መቅረባቸው ብቻ በቂ አይደለም።   በትጥቅ መንገድ እንታገላለን ከሚሉት ውስጥ ከዓላማችን ጋር የሚመሳሰል ዓላማ ካላቸው ጋር መተባበር እንዳለብን ጉባዔው ተወያይቶ ተስማምቷል። ሆኖም፤ ሁሉም በትጥቅ ትግል ህወሓት/ኢህአዴግን የሚፈታተኑት ለኢትዮጵያ ግዛታዊ አንድነት፤ ዘላቂነትና ጥቅም፤ ለመላው ሕዝቧ ሉዐላዊነት ትሥስርና እውነተኛ እኩልነት፤ ለፍትህና ለሕግ የበላይነትና ሁሉን የማህበረሰብ ክፍሎች ለሚወክል ዲሞክራሳዊ ስርዓት ይታገላሉ ማለት አይቻልም። በዚህ አኳያ ልናስብበት የሚገባን  ያለፈው የፖለቲካ ሂደት አንዱ ትምህርት አንድ አምባገነን አስወግዶ ሌላ አምባገነን መተካት እንዳይከተል ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያሰፈልግ ነው። ህወሓት/ኢህአዴግን በመጥላት ከታጠቁ ተገንጣይ ኃይሎች የሚከሰተውን የኢትዮጵያን መፈራረስ፤ አደጋ የእርስ በእርስ ግጭትና የዘር ፍጅት ሴራዎች ሙሉ በሙሉ እንቃወማለን። ኤርትራን በተመለከተ ኤርትራ ከጥንቱ ጀምሮ የኢትዮጵያ ኣካል የሆነች ክፍለ-ሃገር ነች። ከ1890ቹ ጀምሮ ክፍለ-ሃገሪቱ የብዙ ፖለቲካ ምስቅልቅሎችና የትጥቅ ትግሎች ሰለባ ሆና እንደቆየች ኣይካድም። በዚህ ሂደት ህዝቡ የዴሞክራሲያዊ መብቱ ተከብሮ ስለመፃኢ ዕድሉ በነፃነት ሊወስንበት የቻለበት ሁኔታ ከተውንም አላገኘም። በ1993 (እ.አ.አ) በኢሳያስ ኣፈወርቂና በመለስ ዜናዊ ኣቀነባባሪነት ኤርትራ ተገንጥላ ‘ነፃ’ ሃገር እንድትባል መደረጉ የዚሁ ሂደት ኣካል ነው። ተካሄደ የተባለው ሬፈረንደም ተቃዋሚዎችን ያላሳተፈ፤ ህዝቡንም ምርጫ የሌለው ውሳኔ እንዲቀበል ያስገደደ፤ በጠብመንጃ ግፊት የተፈፀመ በመሆኑ ተቀባየነት የለውም። ስለዚህም ሸንጎው ኤርትራን እንደ ‘ነፃ’ ሃገር ሳይቀበል የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እስኪመሰረት ድረስ ትግሉን ይቀጥላል። ብሄራዊ መግባባት እርቅና ሰላም በህወሓት ላይ የሚደረገው ልዩ ልዩ ትግልና ጫና እንዳለ ሆኖ፤ ጉባዔው ሰፊ ምርምርና ጥናት አድርጎ፤ ከህወሓት/ኢህአዴግ የጥላቻና የጎሳ ፖለቲካ ወደ ነጻና ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ወደሚያሳትፍ ብሄራዊ መግባባት እርቅና ሰላም ውይይት መሸጋገር ለዴሞክራሲ ወሳኝ መሆኑን ተቀብሏል። ምንም እንኳን እብሪተኛው ህወሓት ለዚህ ዓይነቱ ድርድር ዝግጁና ፈቃደኛ አለመሆኑን ብናውቅም፤ የእርቅና ሰላም ጽንሰ ሃሳብ በሃገር ቤትና በውጭ ከፍተኛ ውይይት እንዲካሄድበት ጉባኤው አሳስቧል። ሸንጎ ለዚህ ለተቀደሰ አማራጭ ያልተቆጠበ ድጋፍና እርዳታ ያደርጋል። በመጨረሻ ጉባዔው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያቀርበው አደራ፤ ለኢትዮጵያ ዘላቂነት፤ ለዴሞክራሲ፤ ለፍትህ፤ ለሕግ የበላይነት፤ ለመገናኛ ብዙሃን ነጻነት…ወዘተ ስኬታማነት እውን የሚሆነው በጋራ ዓላማ ላይ የተመሰረተ፤ የተቀነባበረ ሕዝባዊ ትግል ሲካሄድ ብቻ እንደሆነ ነው። ህወሓት ሊያፈራርሳቸው ቢሞክርም፤ አገር ቤት የሚንቀሳቀሱ የአንድነት ዘርፍና አካል ተቃዋሚ ፓርቲዎች ወሳኝ የሆነ ሚና ለመጫወት ስለሚችሉ ኢትዮጵያን ሆሉ የሞራልና የቁሳቁስ ድጋፋችሁን ለግሷቸው፤ እኛም የተቻለንን እናደርጋለን እንላለን።  በተመሳሳይ፤ ሸንጎ በሃገር ቤትና በውጭ ከሚታገሉ የአንድነት ስብስቦችና ግለሰቦች ጋር ተባብሮ ለመስራትና ለመታገል ዝግጁ መሆኑን በድጋሜ ቃል ይገባል። ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ! - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45464#sthash.jXh8ZY9O.dpuf

mandag 27. juli 2015

‹‹ኢህአዴግ የጠራው የቅንጦት ግብዣ ላይ መገኘት የህዝቡን ሰቆቃ እንደመርሳት እቆጥረዋለሁ›› ኢ/ር ይልቃል

July 27,2015
ኢ/ር ይልቃል መንግስት ለፕሬዝደንት ኦባማ ያዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ እንደማይገኙ አስታወቁ
• ‹‹ኦባማ ኢህአዴግን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠ ነው ማለታቸው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ውሃ የሚቸልስ ነው››
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ሀምሌ 20/2007 ዓ.ም ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ ቤተ መንግስት ውስጥ ለአሜሪካው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የሚያደረገው የእራት ግብዣ ላይ እንደማይገኙ ለነገረ ኢትየጵያ ገልጸዋል፡፡ የራት ግብዣው ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጥሪ የተደረገላቸው ኢ/ር ይልቃል ‹‹ አሸባሪ አድርጎ የሚቆጥረን ኢህአዴግ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ሲመጡ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ለማስመሰልና ዕውቅና ለማግኘት ያደረገው በመሆኑ አልገኝም›› ብለዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል አክለውም ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ ጭቆና እና ስቃይ ውስጥ ባለበት በአሁኑ ወቅት ኢህአዴግ የጠራው የቅንጦት ግብዣ ላይ መገኘት የህዝቡን ሰቆቃ እንደመርሳት እቆጥረዋለሁ›› ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት ኢህአዴግ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነው ማለታቸው ቅር እንዳሰኛቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ኢህአዴግን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነው ማለት የሰላማዊ ታጋዮችን ስቃይ የሚክድና ለአምባገነኖች ይሁንታ የሚሰጥ ነው›› ሲሉ የፕሬዝደንት ኦባማን ንግግር ነቅፈውታል፡፡ ፕሬዝደንት ኦባማ የጠበንጃ ትግልን አለመደገፍን ለመግለፅ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንትን ጨምሮ ሌሎች የአሜሪካ ተቋማት ኢ-ዴሞክራሲያዊ መሆኑን አረጋግጠውት፣ መቶ ፐርሰንት ምርጫ አሸንፌያለሁ የሚልን ፓርቲ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንደተመረጠ መግለፃቸው እንዳሳዘናቸው ኢ/ር ይልቃል ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል ኢ/ር ይልቃል በነገው ዕለት የአሜሪካ ኤምባሲና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በጋራ ያዘጋጁት ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

lørdag 25. juli 2015

በሕወሓት ወታደሮች ውስጥ አለመተማመኑ ነግሷል – በጀነራል ሳሞራ የኑስ ቡድን እና በሌ/ጀነራል አብረሀ ወ/ማርያም ቡድን መካከል ያለው ልዩነት ተካሯል

  • 1931
     
    Share

* ህዝባዊ‬ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በሚቆጣጠረው መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እርስበርስ አለመተማመንና ጥርጣሬ አይሏል፡፡
‪* የህወሓት‬ አገዛዝ ከሱዳን ጋር የተፈጠረውን ወታደራዊ ግጭት የህዝቡን ትኩረት ሊያስቀይርበት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡
* የህወሓት አገልጋይ የሆኑ “የአማራ ክልል” ባለስልጣናት ወደ ወልቃይት ሄደው በአካል ህዝቡን እንዲያነጋግሩ ከህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ቀጭን ትዕዛዝ መተላለፉ ታወቀ፡፡

አርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ ራድዮ እንደዘገበው
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በሚቆጣጠረው መከላከያ ሰራዊት ውስጥ እርስበርስ አለመተማመንና ጥርጣሬ አይሏል፡፡
በከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ማለትም በጀነራል ሳሞራ የኑስ ቡድን እና በሌ/ጀነራል አብረሀ ወ/ማርያም ቡድን መካከል ተፈጥሮ የቆየው ጎራ ለይቶ መሰላለፍና አንዱ ቡድን ሌላኛን ለማስወገድ የሚያደርገው ፍትጊያ በእጅጉ ከሯል፡፡
samora and azeb
በመሆኑም አለመተማመኑ ስር ሰዶ እስከ ታች ድረስ በመውረዱ በተዋጊው ሰራዊትና በአዛዦቹ፣ በአዛዦችና በአዛዦች፣ በአዛዦችና በህወሓት ባለስልጣናት፣ በተዋጊውና በተዋጊው እንዲሁም በተጨማሪ ባጠቃላይ በትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች እና በሌሎች ቋንቋዎች ተናጋሪዎች መካከል ከፍተኛ ጥርጣሬ ነግሷል፡፡
ለህወሓት ታማኝና ቅርብ ነው የሚባለው አግአዚ ኮማንዶ ጦርም ባለመተማመኑ ማዕበል ተመትቶ መሰረቱ ተናግቷል፡፡ በዋና አዛዡ መቶ አለቃ ታፈሰ እና በምክትሉ ሻለቃ ባሻ ሰለሞን ኃ/ማርያም የሚመራው አንድ ሻምበል የአግአዚ ጦር ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት ፈጥሯል በሚል ጥርጣሬ መሽጎ ከቆየበት ሁመራ አካባቢ ዲማ የተባለ ቦታ ወደ ኋላ 30 ኪ.ሜ እንዲያፈገፍግ ተደርጎ ኩሃጂ ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡
የህወሓት አገዛዝ ከሱዳን ጋር የተፈጠረውን ግጭት የህዝቡን ትኩረት ሊያስቀይርበት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡
የሱዳን መከላከያ ሰራዊት ድንበር ጥሶ ወደ ኢትዮጵያ የጠረፍ መንደሮችና እስከ መሀል ከተሞች ዘልቆ እየገባ በህዝብ ላይ ጭፍጨፋ እና የንብረት ውድመት በተደጋጋሚ እየፈፀመ መመለሱ ያስቆጫቸው አንዳንድ የህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት አባላት የአዛዦቻቸውን መመሪያ በመጣስ የፈፀሙት አፀፋዊ ጥቃት ያስከተለውን ግጭት በመንተራስ የህወሓት አገዛዝ ቅጥረኛ ካድሬዎች ሱዳን በጉልበት የወሰደችብንን መሬት ልናስመልስ ስለሆነ እርዱን በማለት ህዝቡን እየሰበኩ ከተጀመረው የነፃነት ትግል ለማዘናጋት ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡
በተጨማሪም ካድሬዎቹ ሱዳን እና ኤርትራ የኢትዮጵያን መሬት ወረዋል የሚል ምክንያትና የገንዘብ መደለያ በማቅረብ ከመከላከያ የወጡ የቀድሞ አባላትን እንዲመለሱ በመማፀን ላይ ናቸው፡፡
የህወሓት አገልጋይ “የአማራ ክልል” ባለስልጣናት ወደ ወልቃይት ሄደው በአካል ህዝቡን እንዲያነጋግሩ ከህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣናት ቀጭን ትዕዛዝ መተላለፉ ታወቀ፡፡
ከአርበኞች ግንቦት 7 ጎን በመሰለፍ ለነፃነቱ እየተዋደቀ የሚገኘው እና “ክልል ሶስት እና ክልል አንድ የሚባል አናውቅም እኛ የጎንደር በጌምድር ተወላጅ ኢትዮጵያዊያን ነን” በማለት ለህወሓት ዘርን መሰረት ያደረገ አስተዳደር አልገዛም ብሎ በአንድነት የተነሳው የወልቃይት ህዝብ በህወሓት ህልውና ላይ ከፍተኛ ስጋት በመደቀኑ ነው የአማራ ክልል የህወሓት አገልጋይ ባለስልጣናት ወደ ቦታው ሄደው ህዝቡን በአካል በማግኘት ሰብከው ሃሳቡን እንዲያስለውጡና እንዲማፀኑም ጭምር በጌቶቻቸው የታዘዙት፡፡
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45352#sthash.O9h10TwX.dpuf

የዜጎችና የአገር ውርደት ይብቃ!(አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ)

arbegnoch-ginbot7-300x300
  • 18
     
    Share
የህወሓት አገዛዝ ፋሽስታዊ ባህርያት እያደር መረን እያጣ፤ ነውረኛ እየሆነ መጥቷል። በአሳለፍነው ሣምንት ብቻ እንኳን አስነዋሪ ይዘት ያላቸው ሁለት ፋሽስታዊ ክስተቶችን አስተውለናል።
አንዱ በምርመራ ስም በታሳሪዎች ላይ የሚደረገው አሳፋሪ ሰቆቃ ነው። በገላቸው በሚያፌዙና በሚሳለቁ ተቃራኒ ፆታ መርማሪዎች ፊት ለሰዓታት ተመርማሪዎች ራቁታቸውን እንዲሆኑ የሚደረግበት እና እየተፌዘባቸው የሚደበደቡበት ሥርዓት መኖሩ የጉዳቱ ሰለባዎች ይፋ ሲያወጡ እፍረቱ ለመርማሪዎቹ ብቻ ሳይሆን ይህንን ጉድ ተሸክመን ለኖርነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ነው። በተለይም ደግሞ እንዲህ ዓይነት ክብረነክ ሰቆቃ በሴቶች ላይ እየተፈፀመ መሆኑን ስንሰማ አገራዊ ውርደቱ ያሸማቅቀናል። እንዲህ ዓይነቶችን በሰው ስቃይና እፍረት የሚዝናኑ ጉዶችን ተሸክመን የምኖር መሆናችን ሁላችንን ያዋርደናል። ይህንን አስነዋሪ “የምርመራ ዘዴ” ያጋለጡት የዞን 9 ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞችና ፓለቲከኞች ክብርና ሞገስ የሚገባቸው ጀግኖች ሲሆኑ የተዋረዱት እነሱ ሳይሆኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን መሆናችን ሊሰማንና “ውርደት በቃ” ልንል ይገባናል።
ሁለተኛው አሳፋሪ ድርጊት ደግሞ ወገኖቻችንን በግፍ ባረደው አይሲስ በተሰኘው አሸባሪ ድርጅት ላይ የህወሓት አገዛዝ የተለሳለሰ አቋም ወስዷል ብለው ራሱ ህወሓት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞዓቸውን ባሰሙ ወጣቶች ላይ አገዛዙ የወሰደው የኃይል እርምጃና ከዚያም ወዲህ እየተደረገ ያለው ነገር ነው። አገዛዙ ለፕሮፖጋንዳው ይጠቅመኛል ብሎ በጠራው ሰልፍ ወጥተው ተቃውሞዓቸውን የገለፁ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ በጅምላ ወደ እስር ቤቶች ተግዘዋል። የአገዛዙ ካድሬዎች ወገኖቻችንን የፈጀውን አይሲስን በመቃወም ፋንታ የራሱ የህወሓትን ውል አልባ ህግ አክብረው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉትን ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን እና አረና ፓርቲን እየወነጀሉ መሆኑ አጅግ አሳፋሪ ነገር ነው። የአይሲስን አረመኔአዊ ድርጊት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር ለማገናኘት በህወሓት የደህንነት ቢሮ አማካይነት እንቅስቃሴ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ለወጣቱ በብዛት መሰደድ በምክንያትነት የሚያቀርቡት ደላሎችን መሆኑ አላዋቂነት ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቅራኔው በኢትዮጵያዊያን መካከል እርስ በርስ እንዲሆን ያለመ መሠሪነት ነው። ከዚህም አልፎ የትግራይ ወጣቶችን ነጥሎ በመሰብሰብ “ትምክህተኞች ሊበሉህ ነውና ታጥቀህ ሳይቀድሙህ ቅደም” እያሉ መቀስቀስ በመንግሥት ደረጃ የእርስ በርስ እልቂትን ከማደራጀት ተለይቶ አይታይም። የሥርዓቱ ይሉኝታ ቢስነት የደረሰበት ዝቅጠት ገላጭ ከሆኑ ነገሮች አንዱ “እስከምርጫ መጨረሻ ድረስ ልጆቻችሁን አስረን እናቆይላችሁ” እያሉ ወላጆችን እስከመጠየቅ መድፈራቸው ነው።
ከላይ በአጭሩ የተዘረዘሩት ኩነቶች የሚያረጋግጡት ህወሓት የተማከለ አመራር አጥተው መንገድ የጠፋቸው፤ ሆኖም ግን እጃቸው ውስጥ የገባው ስልጣንና ሀብት ላለማጣት ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ አውሬዎች ስብስብ መሆኑ ነው። እንዲህ ዓይነቱን የአውሬዎች ስብስብ የሚገዛው የህግም ሆነ የሥነ-ምግባር ገደብ የለም። ህወሓት እስር በርሳችንን አባልቶ አገራችንንና ሕዝቧን ወደ ማንወጣው አዘቅት ከመክተቱ በፊት ራሱ ህወሓትን ማስወገድ እና በምትኩት ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን መገንባት የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው። ይህ ካላደረግን አሁን በወህኒ ቤቶች የሚደረገው ዜጎችን ልብስን አስወልቆ የማዋረድ አስነዋሪ ተግባር ነገ በአደባባዮች የማይደረግ ስለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ይህ ትውልድ ኃላፊነቱ ካልተወጣ ህግን አክብረው ከአገዛዙ የተለየ ሀሳብ እናራምዳለን የሚሉ ወገኖቻችን በሙሉ አደጋ ውስጥ ናቸው። በህወሓት መሠሪ ተግባራት ሳቢያ በክርስትናና እስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን መካከል ያለው መግባባት እንዲሻክር እየተደረገ ነው። ዜጎችን በማዋረድ የሚደሰት አገዛዝና ለመዋረድ የፈቀደ ሕዝብ እስካለ ድረስ የቁልቁለቱ ጉዞ መጨረሻ የለውም። ይህንን ማስቆም ያለብን እኛ ሁላንችንም ነን። በአደባባይ መደራጀት ሲከለከል በምስጢር መደራጀትን መልመድ የኛ ኃላፊነት ነው። የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓልን ስናከብር ከቀደምቶቻችን ልንወርስ ከሚገቡን እሴቶች አንዱ ለክብራችን ዋጋ መክፈል ያለብን መሆኑን ጭምር ነው። የኢትዮጵያዊያን ክብር በወያኔ ሲዋረድ እያየን ዝምታን ከመረጥን ከዚህም የባሰ እንዲመጣ መፍቀዳችንን እንወቀው።
አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የዜጎችና የአገር ውርደት ይብቃ! በተባበረ ክንድ ህወሓት ይወገድ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመሥረት መሠረት እንጣል፤ ይህንን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት በኅብረት እንነሳ ይላል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8984#sthash.0vzJcsP7.dpuf

fredag 24. juli 2015

ከፍተኛ ወታደራዊ የወያኔ ባለስልጣን መሰወራቸዉና ወደ አርበኞች ግንቦት 7 መቀላቀላቸዉ

11144995_814272385352811_3462902730849957444_o
  • 3357
     
    Share
አንድ ለጊዜዉ ማንነታቸዉ እንዲገለጽ ያልተፈለገ ከፍተኛ ወታደራዊ የወያኔ ባለስልጣን መሰወራቸዉና ወደ አርበኞች ግንቦት 7 መቀላቀላቸዉ በወያኔ በኩል ከባድ እራስ ምታት ፈጥሯል። የእኚሁን ባለስልጣን ጉዳይ በተመለከተ አርበኞች ግንቦት 7 ምንም የሰጠዉ መግለጫ ባይኖርም በወያኔ በኩል ግን ያለዉ የደህንነት ክንፍ አጣርቻለዉ ብሎ መረጃዉን ማሳለፉን ለመረዳት ተችሏል።
በተያያዘ ዜና ከአርበኞች ግንቦት 7 የጥቃት ማግስት ጀምሮ የተለያዩ የነጻነት ሐይሎች ጦርነት እያካሄዱ እንደሚገኙ ከወያኔ ወታደራዊ ግንኙነት ክፍል የወጣ መረጃ አመለከተ። መረጃዉ እንደሚጠቁመዉ ኦነግና የኦጋዴን ነጻ አዉጪ ሀይሎችም ተመሳሳይ የሆነ ሽምቅ ዉጊያ ተያይዘዉታል። የአሜሪካዉ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማን መምጣት ምክንያት ባደረገ መልኩ ኢትዮጵያ ምንም አይነት የጦርነት አዋጅ እንደማታዉጅ ወታደራዊ ደህንነቱ ለየ እዝ ባለስልጣናቱ ሚስጢራዊ ትዕዛዝ በማሳለፉ የእዝ አመራሮችን ያበሳጨ ነዉ ተብሏል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የወያኔ ንብረት የሆነዉን በጎንደርና በተለይም አዘዞ ላይ የሚገኘዉን ሱር ኮንስትራክሽን የደመሰሰና ያቃጠለ ሲሆን በቅርበት የሚገኙ ወታደራዊ ተቋማት የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው ይታወሳል
አሰግድ ታመነ
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8977#sthash.82Vx139t.dpuf

torsdag 23. juli 2015

(VOA) በአርባ ምንጭ ወረዳ ከይዞታቸው የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች ጉዳይ – በሰመጉ ሪፖርት

6CB8338A-E676-47D6-B1D9-DDD4A9D3089E_w640_r1_s
  • 127
     
    Share
በደቡብ ክልል በጋሞ ጎፋ ዞን ከ4 መቶ በላይ አርሶ አደሮች በኅጋዊ መንገድ የተሰጣቸውን መሬት ተነጠቁ፤ ሲል መንግስታዊ ያልሆነው የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በቅርቡ ይፋ ባደረገው መግለጫው አስታወቋል።
ሰመጉ ባለፈው ሳምንት መገባደጂያ ያወጣውን የጥናት ዘገባ አስመልክቶ ሊቀ መንበሩ አቶ ብዙአየሁ ወንድሙ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ዝርዝሩን ይዟል።
 

- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8925#sthash.wjqZ2DVm.dpuf

onsdag 22. juli 2015

ኢህአዴግ ቢቸግረው “አሜሪካ የኢህአዴግ አድናቂ ትሆናለች” ብሎ ማሰብ ጀመረ!

Obama 78
  • 22
     
    Share
ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ
ኋይት ሀውስ
1600 ፔንሲልቫኒያ አቬኑ ኤንደብልዩ
ዋሽንግተን፣ ዲሲ 20500
ውድ ፕሬዚዳንት ኦባማ፡
ሰላም ለእርስዎ ይሁን! ሚስተር ፕሬዚዳንት፡፡
በዚህ በያዝነው በሀምሌ ወር ሁለተኛው አጋማሽ ወደ ኢትዮጵያ በመጓዝ ከሀገሪቱ መንግስት እና ከአፍሪካ ህብረት አመራር ጋር አባላት ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያደርጉ በሰማሁ ጊዜ ከፍ ያለ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ እንደዚህ ያለ ስብሰባ በአሕጉሪቷ ማድረግ ተገቢ ነው።
የኢትዮጵያ ህዝቦች እጆቻቸውን ዘርግተው እንደሚቀበሉዎት እና ከልብ የመነጨ ሰላምታ እንደሚያቀርቡልዎት ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ኢትዮጵያውያን በእንግዳ ተቀባይነታቸው ከዓለም ተወዳዳሪ የሌላቸው ህዝቦች ናቸው የሚል ጽኑ እምነት ያለኝ፡፡
ለመጨረሻ ጊዜ አንደዚህ በደስታ ተውጨ የነበረው ከስድስት ዓመታት በፊት እ.ኤ.አ ሀምሌ 2009 በጋና አክራ ላይ ተገኝተው ለጋና ፓርላማ አድርገውት በነበረው ንግግርዎ ነበር፡፡
በአክራ ከተማ በመገኘት ያደረጓቸው የንግግር ቃላት ስሜትን ቀስቃሽ እና የእኔን ልብ ብቻ የማረኩ ሳይሆን በአፍሪካ የሚኖሩ እና የነጻነት አየር ለመተንፈስ ይቋምጡ የነበሩ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ህዝቦችን ቀልብ የሳቡ ነበሩ፡፡
እርስዎ ልዩ ቦታ ላይ በመገኘት ለአፍሪካ ህዝብ መልካም ነገርን በማሰብ እንደዚህ የሚሉትን እና መሆን ያለባቸውን መሳጭ ንግግሮች አድርገው ነበር፡
እንዳትሳሳቱ፡ ታሪክ ከእነዚህ ጀግኖች አፍሪካውያን ጎን እንጅ በመፈንቅለ መንግስት ስልጣንን ከሚይዙ እና በስልጣን ማማ ላይ ተፈናጥጠው ለመኖር ሲሉ ሕገመንግስትን ከሚያሻሽሉ አምባገነኖች ጎን አይደለም፡፡ አፍሪካ ጠንካራ ሰዎችን አትፈልግም፣ ይልቁንም አፍሪካ የምተረፈልገው ጠንካራ ተቋማትን ነው፡፡
ልማት በመልካም አስተዳደር ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ በበርካታ ቦታዎች ላይ ለበርካታ ጊዚያት የጠፋው ታላቅ ነገር ይህ መልካም አስተዳደር የሚባለው ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ለውጥ የሚደረግ ከሆነ ነው የአፍሪካን የወደፊት የእድገት ዕጣ ፈንታ ቁልፍ መክፈት የሚቻለው፡፡ ይህም ኃላፊነት እውን ሊሆን የሚችለው በሌላ በማንም ኃይል ሳይሆን በአፍሪካውያን ብቻ ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ጋናውያን ባረጀ እና ባፈጀው የፈላጭ ቆራጭ ንጉሳዊ አገዛዝ ምትክ ሕገ መንግስታዊ አስተዳደርን በመምረጥ ህዝባችሁ ለዘለቄታው ኃይሉን አስተባብሮ በልማት ጎዳና ላይ ለመጓዝ የሚያስችሉ የዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ብልጭታዎች በጠንካራ መሰረት ላይ ተጥለው ይታያሉ፡፡ ለብዙሀኑ ህዝብ ጥቅም እና መብት ሲሉ ሽንፈትን በጸጋ የሚቀበሉ መሪዎችን እየተመለከትን ነው፡፡
የሕግ የበላይነት በአምባገነናዊ የጭካኔ አገዛዝ እና ሙስና በተንሰራፋበት የአገዛዝ ስርዓት ውስጥ መኖር የሚፈልግ ሰው የለም፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ ስርዓት ዴሞክራሲ አይደለም፣ ይልቁንም የሀገሬውን ዜጋ እና የዓለምን ህዝብ ለማደናገር አንዳንድ ጊዜ ብቻ በሚደረግ የይስሙላ ምርጫ ዜጎችን በስቃይ የሚያማቅቅ አምባገነናዊ ስርዓት ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ እንደዚያ ያለው አስቀያሚ ስርዓት ከስሩ ተመንግሎ መጣል ያለበት እና የህልውናው የማብቂያ ጊዜ ነው፡፡
የውጭ እርዳታ ዓላማ አስፈላጊ የማይሆንበት እና ሀገሮች እራሳቸውን ችለው መንቀሳቀስ የሚያስችላቸው ምቹ መደላድል መፈጠር አለበት፡፡ የእኔ አስተዳደር በሚቀርቡለት የሰብአዊ መብቶች ዘገባ መሰረት ሙስናን ለመዋጋት ልዩ ትኩረት በመስጠት የሚንቀሳቀስ ይሆናል፡፡
ባለፉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በርካታ ከፍተኛ ከበሬታ ያላቸው የሰብአዊ መብቶች እና የመገናኛ ብዙሀን ድርጅቶች እርስዎ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ባቀዱት ጉዞ ላይ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ሲያሰሙ እንደነበር ግንዛቤው አለኝ፡፡
ሮበርት ኤፍ. ኬኔዲ የሰብአዊ መብቶች ማዕከል/
Roberet
F. Kennedy Center for Human Rights የተባለው የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት እንዲህ በማለት የተደቀነበትን ስጋቱን ገልጿል፣ “በዚህ ሳምንት ብቻ ሶስት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አባላት ተገድለው ባለበት ሁኔታ ፕሬዚዳንት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉዞ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታን የሚፈጥር ጉዳይ ነው፡፡“
በተመሳሳይ መልኩ ዋሽንግተን ፖስት የተባለው የዜና ወኪል እርስዎ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉት ጉዞ እንቆቅልሽ እንደሆነበት እና ይልቁንም ይህንን ጉዞ በመሰረዝ ሌላ ሀገር ቢጎበኙ የተሻለ ሊሆን እንደሚችል እንዲህ በማለት ሀሳቡን ግልጽ አድርጓል፣ “ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ በመጣው ከፍተኛ የሆነ ጭቆና፣ የነጻውን ፕሬስ ጉሮሮ አንቆ በመያዝ እና ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲ አባላትን መብት በመርገጥ አላንቀሳቅስ በማለት የፖለቲካ ምህዳሩን ዘግቶ የተቀመጠ ስርዓት በመሆን ኢትዮጵያ ከአፍሪካ የቀዳሚነቱን ስፍራ ይዛ ትገኛለች፡፡ በውል ለክቶ ለማወቅ በማይቻል መልኩ ኢትዮጵያውያንን እያሰቃየ እና እየጨቆነ ላለ የሰብአዊ መብት ደፍጣጭ መንግስት ሙሉ ጊዜን ሰጥቶ ለመጎብኘት መንቀሳቀስ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ታሪካዊ፣ ሰላማዊ እና ዴሞክራሲያዊ የስልጣን ሽግግር ያደረገችውን ናይጀሪያን ጓዳዊ ያልሆነ እይታን በማሳየት ለመጎብኘት አለመፍቀድ ግራ የሚያጋባ እንቆቅልሽ ነገር ነው፡፡“
የውጭ ፖሊሲ መጽሔት/Foreign Policy Magazine እርስዎ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዙ በመቃወም እንዲህ የሚል ትችት አቅርቦብዎታል፣ “ዋሽንግተን በአፍሪካ ቀንድ የተረጋጋ አጋር ትፈልጋለች፡፡ ሆኖም ግን በአዲስ አበባ ከሚገኘው ጨቋኝ መንግስት ጋር አጋርነትን መፍጠር የተሳሳተ መንገድ በመሆኑ ሌላ እውነተኛ ወዳጅነት ያለው እና የዜጎችን መብት የሚያከብር አጋርነትን መፈለግ የተሻለ መንገድ ነው፡፡“
በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 የተካሄደውን የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ በማስመልከት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ፖሊሲ የሚከተለውን ምልከታ በማድረግ እንዲህ የሚል ትችት አቅርቧል፣ “በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ሙሉ በሙሉ 547ቱንም የፓርላማ መቀመጫ ወንበሮችን በማሸነፍ እራሱን ከሰሜን ኮሪያ እና የሳዳም ሁሴን ብቸኛ የፓርቲ አገዛዝ ጋር በእኩል ደረጃ አስቀምጦ ይገኛል፡፡“
ጋርዲያን የተባለው መጽሔት በርካታ የሆኑ ተቃውሞዎቹን በማጠቃለል በእርስዎ ጉብኝት ላይ እንዲህ የሚል ምልከታውን አቅርቧል፣ “የባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን የመጎብኘት ውሳኔ የሰላማዊ ዜጎችን መብት በመደፍጠጥ ላይ ለሚገኙት የአፍሪካ ጨቋኝ አምባገነኖች የተሳሳተ መልዕክት ያስተላልፋል በማለት የሰብአዊ መብት ወትዋቾችን በእጅጉ ያስደነገጠ ጉዳይ ሆኗል፡፡“
በርካታ የኢትዮጵያ ሲቪል የሰብአዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች፣ ድርጅቶች እና የማህበረሰብ መሪዎች የእርስዎን የኢትዮጵያ ጉዞ በግልጽ እና ከፍተኛ በሆነ ስሜት ተቃውመውታል፡፡
እ.ኤ.አ ሀምሌ 3/2015 የኢትዮጵያ እና የኢትዮ-አሜሪካ ዜጎች ከኋይት ሀውስ ፊት ለፊት በመሰለፍ እርስዎ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ በመቃዋም ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል፡፡
በርካታ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ቡድኖች፣ የብዙሀን መገናኛ ድርጅቶች እና የፖሊሲ ተንታኞች እርስዎ ወደ ኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉዞ በመቃወም እያቀረቧቸው የሚገኙትን የተቃውሞ ሀሳቦች እኔም እጋራቸዋለሁ፡፡ እነዚህ ቡድኖች እና ድርጅቶች እያቀረቧቸው ላሉት ጉዳዮች ልዩ ትኩረትን እንደሚሰጡት እና ለተነሱት ጉዳዮች ተገቢውን ምላሽ እንደሚሰጡ እምነት አለኝ፡፡
እንደ ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ግንባር ቀደም ተሟጋችነቴ እና አንድም ጊዜ ሳይቋረጥ በየሳምንቱ ሰኞ የሚወጡ ትችቶቼ እና ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ ጥረት ሳደርግ እንደመቆየቴ መጠን የአሁኑ የእርስዎ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረገው ጉዞ ምቹ መደላድል የሚፈጥር እና ፍሪያማ ነገሮችን ያስገኛል የሚል እምነት እንዳለኝ በመግለጽ የመከራከሪያ ጭብጤን እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡፡
የዚህን አዎንታዊ ዕንደምታ የተስፋ ፍንጣቂ ገና ኢትዮጵያ ውስጥ ከመድረስዎ በፊት በአሁኑ ጊዜ ባሉት ቀናት ውስጥ እያየን ለመሆናችን ምስክርነት ለመስጠት እወዳለሁ፡፡
እ.ኤ.አ ሀምሌ 8/2015 የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ (ጋተኮ)/Committee to Protect Journalists (CPJ) “በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል ዞን 9 እየተባለ የሚጠራውን እና በኢትዮጵያ ነጻ አስተሳሰብ እንዲሰርጽ በመታገል ላይ የነበሩትን ሁለት ጦማሪያንን እና ሌሎች ሶስት ጋዜጠኞችን ከእስር ቤት ለቋል፡፡ በእነርሱ ላይ ተመስርተው የነበሩት ሁሉም ክሶች ውድቅ ሆነዋል፡፡“ የሚል ዘገባ አውጥቷል፡፡
እነዚህ ወጣት ጦማሪያን እና ጋዜጠኞች እ.ኤ.አ ከሚያዝያ 2014 ጀምሮ በህገወጥ መልኩ በቁጥጥር ስር ውለው በአምባገነኑ የመለስ ዜናዊ እስር ቤት ሲማቅቁ የቆዩ ናቸው፡፡
እንደ እነርሱ ያሉ አሁን በማጎሪያው እስር ቤት ውስጥ ከህግ አግባብ በሆነ መልኩ ታፍነው በእስር ቤት ውስጥ በመማቀቅ ላይ የሚገኙ እና እነርሱም ካልሰሩት ወንጀል ነጻ ሆነው እንዲወጡ የእርስዎን መድረስ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ በርካታ ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን ይገኛሉ፡፡
እ.ኤ.አ ሀምሌ 9/2015 የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ (ጋተኮ) ከፍተኛ ደስታ በተቀላቀለበት ሁኔታ እንዲህ የሚል ዘገባ አውጥቷል፣ “ርዕዮት ዓለሙ በመፈታቷ በጣም ደስ ብሎናል፣ ሆኖም ግን በመጀመሪያ ደረጃ በምንም ዓይነት ሁኔታ በፍጹም መታሰር አልነበረባትም፡፡ የጤንነቷ ሁኔታ ተጓድሎ ባለበት ሁኔታ እና በጣም ክልከላ በበዛበት የእስር ቤት አያያዝ ከአራት ዓመታት በላይ በእስር ቤት እንድትማቅቅ ተደርጓል፡፡“
ርዕዮት ለአንዲት ቀን እንኳ መታሰር አልነበረባትም፡፡ በእስር ቤት ለመቆየት እና ላለመቆየት ቁልፉ ያለው በአንችው እጅ ነው በማለት ተነግሯታል፡፡ ርዕዮት እንድታደርግ የተፈለገው ጥፋት አጥፍቻለሁ ብለሽ በሰራሽው ስተት አምነሽ ፈርሚ እና ከእስር ቤት ትወጫለሽ የሚል ነበር፡፡
ሆኖም ግን ርዕዮት እንደዚያ ዓይነት ነጻ በሆነ መልኩ ሀሳቧን ከመግለጽ በስተቀር ምንም ዓይነት ጥፋት እና ወንጀል ባልሰራችበት ሁኔታ ለአምባገነኖች እብሪት ሲባል አሳምነን እና በትዕቢት የተወጠረን እንደጎማ አስተንፍሰን ነው የምንለቅ ከሚል ዕኩይ እብሪት በመነሳሳት ነጻዋ ጋዜጠኛ ህሊናዋን ሸጣ አዎ አጥፍቻለሁ ማሩኝ ብላ በእግር ላይ እንድትንበረከክ ነበር የተፈለገው፡፡ ጀግናዋ ርዕዮት የእናንተ የሸፍጥ ይቅርታ በአፍንጫው ይውጣ በማለት መታሰሯን መርጣ ቆይታለች፡፡
ርዕዮት ለአራት ዓመታት ከ17 ቀናት ያህል በእስር ቤት ስትማቅቅ መቆየቱን መርጣለች፣ ምክንያቱም ጀግናዋ ወጣት ጋዜጠኛ ከእርሷ ከእስር ቤት የመፈታት ነጻነት ይልቅ ለእውነት ሙሉ ዋጋ በመስጠቷ ነው፡፡
አሳሪዎቿ ከእስር ቤት ወጥታ እንድትሄድ ከመፍቀዳቸው በፊት ርዕዮት እንዲህ የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጥታቸው ነበር፣ “ባላጠፋሁት ጥፋት ምንም ዓይነት ይቅርታ ሳልጠይቅ ከማጎሪያው እስር ቤት ወጣሁ ብዬ ለህዝብ ስናገር መልሳችሁ ወደ ማጎሪያው እስር ቤት ልታመጡኝ ትችላላችሁ፣ እኔ ግን በዓላማዬ ጸንቼ እቆያለሁ፡፡ ስለእኔ ከእስር መፈታት ሀሰት ብትናገሩ እውነቱን ለህዝብ ይፋ አደርጋለሁ እናገራለሁ፡፡“
ለዚህ ነው ርዕዮት ዓለሙን “የኢትዮጵያ እውነት ተናጋሪዋ” በማለት የሚጠሯት፡፡
ርዕዮትን በሚገባ አውቃታለሁ፡፡ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን የጀግና ተምሳሌት ቀንዲል ናት፡፡
ርዕዮት የኢትዮጵያ ሮሳ ፓርክስ ናት፡፡
ለሌላ ለምንም ምክንያት ሳይሆን ስጋ እና ደም የለበሰችውን እና በእሳት ተፈትና የወጣችውን ታላቅ ሰው ክብር እና ሞገስ ለማየት ስትሉ ብቻ ርዕዮትን በግል እንድታገኟት እጠይቃለሁ፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ የእርስዎን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ምክንያት በማድረግ በአሁኑ ጊዜ የጋዜጠኞች እና የጦማሪያን ከእስር መለቀቅ ለወደፊቱ ብሩህ ነገርን አመላካች ጉዳይ ነው፡፡
የእርስዎ መሄድ እና ወደ አቃቂ የማጎሪያ እስር ቤት በር ጋ የመድረስዎ እና አምስቱን ጦማሪያን እና ጋዜጠኞችን የማስፈታቱ ዜና እንደተሰማ እርግጠኛ ነኝ ለማይሳነው አምላኬም ጸሎት አደርጋለሁ፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኙ እስር ቤቶችን በሮች ሁሉ ክፍት በማድረግ በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ለበርካታ ዓመታት ታስረው በመማቀቅ እና በመሰቃየት ላይ የሚገኙት በሺዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ሁሉ ነጻ ይሆናሉ የሚል እምነት አለኝ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የሲኤንኤን/CNN ዘጋቢ ጋዜጠኛ ኤሪን ቡርኔት እ.ኤ.አ ሀምሌ 2012 በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ እንደሆነችው የሚያደርግ ምንም ዓይነት አጋጣሚ እንደማይመጣብዎ ተስፋ አለኝ ጸሎትም አደርግልዎታለሁ፡፡ ቡርኔት በዚያ ቦታ ላይ የደረሰባትን ተሞክሮ እንደሚከተለው ገልጸዋለች፡
በላፈው ወር በኢትዮጵያ በነበርኩበት ጊዜ የአፍሪካ የፖሊስ መንግስት ምን እንደሚመስል በተጨባጭ ያየንበት ጊዜ ነበር…በአየር ማረፊያው ቅጥረ ግቢ ውስጥ የጉምሩክ ጉዳዮችን ለመፈጸም አንድ ሰዓት ወስዶብኛል…በሰልፉ መርዘም ምክንያት እንዳይመስላችሁ ሆኖም ግን በዚያ ግቢ ውስጥ በሚደረገው ፍተሻ እና የተንዛዙ ጥያቄዎች መቅረብ ምክንያት ነው፡፡ ባለስልጣኖች ለበርካታ ጊዚያት ወደ መንግስት ተሸከርካሪዎች ይወስዱናል፣ ከዚያም ወዴት እንደምንሄድ የሚያውቁት ነገር የለም፡፡ በአየር ማረፊያው ውስጥ በመቶዎች እና በሺዎች ዶላር የሚያወጡ የቴሌቪዥን ጊሮችን ስናቀርብ ብቻ ነው ትንሽ ውጥረቱ መርገብ የጀመረው…ፕሬዚዳንት ኦባማ “የአባቴ ህልሞች“ በሚለው የእርስዎ መጽሐፍ ላይ እንዲህ የሚሉ ቃላትን አስፍረው እንደሚገኙ አምናለሁ፡
ምንም ዓይነት ተስፋ የሌላቸውን እና አቅም የለሾችን ተመልክቻለሁ፡ በጃካርታ ወይም ደግሞ በናይሮቢ መንገዶች የልጆች ህይወት እንዴት እንደተጣመመ የተመለከትኩት ነገር በተመሳሳይ መልኩ ደግሞ በችጋጎ ደቡባዊ ክፍል በውርደት እና ባልተቋረጠ ንዴት በህጻናቱ ላይ እደረሰ ያለው የመብት ጠባብ መንገድ ህጻናቱን ለከፍተኛ የኃይል ጥቃት እና ተስፋየለሽነት የሚዳርግ መሆኑን በውል ተመልክቻለሁ፡፡ ለእንደዚህ ዓይነቱ ስርዓተ አልበኝነት ጉልበተኞቹ ምን ዓይነት ምላሽ እንደሚሰጡ አውቃለሁ፡፡ በሌላ በኩል እንደዚህ ያለው ችግር እና የደስታ እጦት እየበዛ ሄዶ ስርዓተ አልበኝነት ገደቡን በማለፍ ከፍተኛ የሆነ ቸግር ሲፈጠር ያልታሰበ እና ቀጣይነት ያለው ኃይል መጠቀም፣ ለረዥም ጊዜ እስራት እና የተራቀቁ የጦር መሳሪያዎችን በማዘጋጀት የሚደረገው አፈና በቂ የተግባር እንቅስቃሴ ሆኖ አይገኝም፡፡ የአክራሪነት አቋም መያዝ፣ ጽንፈኝነትን መታቀፍ እና ጎሰኝነትን ማራመድ ለሁላችንም ጎጂዎች እንደሆኑ አውቃለሁ፡፡
በኢትዮጵያ በህዝቦች ፈቃድ ሳይሆን በጠብመንጃ ኃይል በስልጣን ኮርቻ ላይ ተንጠልጥሎ ያለው ገዥ አካል በጃካርታ እና በናይሮቢ ያዩትን ነገር አዲስ አበባን በሚጎበኙበት ጊዜ አንዳያዩ ሊደብቆት ይሞክራሉ፡፡
የእርስዎን ጉብኘት ከግንዛቤ በመውሰድ በሺዎች የሚቆጠሩ የመንገድ ላይ ለማኞችን እና ከገጠር ወደ ከተማ በመፍለስ የሚኖሩትን ቤት አልባ ዜጎች በማፈስ አድራሻቸውን በማጥፋት በእርስዎ የመኪና አጀብ ላይና በሚያንጸባርቁ መስታዎት ህንጻዎች ላይ ጥላቸዉን አንዳይታይ ገዥዎቹ ይሞክራሉ። ሆኖም ግን በአንክሮ የሚመለከቱ ከሆነ ቢያንስ ጥቂቶችን በየህንጻው እና በየአጥሮች ዳርቻ ላይ ወድቀው ሊመለከቱ ይችላሉ፡፡
አማካይ በሆነ መልኩ በመንገድ ላይ ከሚያገኟቸው ወጣት ኢትዮጵያውያን ጋር መነጋገር ቢችሉ በመጀመሪያ ሊነገሩዎት የሚፈልጉት እንክዋን ደህና መጡ ነው፡፡ ከዚያም በመቀጠል በጨካኙ እና በሙስና ተዘፍቆ በሚገኘው ገዥ አካል አማካይነት ህይወታቸው ምን ያህል እንደተጣመመች እና እየተሰቃዩ እንዳሉ በሹክሹክታ ድምጻቸውን ዝቅ አድርገው ይነግሩዎታል፡፡ በየዕለቱ የሚደርስባቸውን ውርደት እና በደም ስሮቻቸው ሁሉ ተሰራጭተው ስለሚዘልቁ ቁጣዎች ዝርዝር አድርገው ይነግሩዎታል፡፡ ስለተዳፈነው ተስፋቸው እና ስለመከኑት ህልሞቻቸው አንድ በአንድ ይነግሩዎታል፡፡
እንዲህ የሚሉትን የላንግስተን ሁይስ ጊዜ የማይሽራቸውን ጥያቄዎች ያቀርቡሎት ይሆን?
የዘገዬ ህልም ምንድን ነው ሊሆን የሚችለው?
በጸሐይ ላይ እንዳለ ሙጫ ከእናካቴው ይደርቃልን?
ወይስ ደግሞ እንደ ቁስል ማመርቀዝ ይጀምር እና መምገሉን ይቀጥላል?
እንደበሰበሰ ስጋ ይጠነባል ወይስ ደግሞ በላዩ ላይ ስኳር እንደተመረገበት ሹሮፕ የሚጣፍጥ ይሆናል?
ምናልባትም ታላቅ ጭነት እንዳለው ነገር ወደ ታች ይለነበጣል ወይስ ደግሞ ይፈነዳል?
የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀን እ.ኤ.አ ግንቦት 1/2015 በተከበረበት ዕለት ላደረጉት ንግግር ታላቅ አድናቆት አለኝ፡፡
ዴሞክራሲ ባለበት ስርዓት ላይ ነጻ ፕሬስ የሚጫወተውን ጉልህ ሚና ካሰመሩበት በኋላ የሚከተለው አውጀው ነበር፡
ጋዜጠኞች እንደ ዜጋ ለሁላችንም ስለሀገሮቻችን ስለእራሳችን እና ስለመንግስታችን እውነታውን እንድናውቅ ዕድል ይሰጡናል፡፡ ይህ ድርጊት የተሻልን እንድንሆን፣ ጠንካሮች እንድንሆን ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በመሆን፣ ኢፍትሀዊነትን በማጋለጥ እና እንደ እኔ ያሉት መሪዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ያስችላል…እንደ አጋጣሚ ሆኖ በዓለም ዙሪያ ባሉ በርካታ ቦታዎች ነጻው ፕሬስ እውነታውን ለማጥፋት በሚፈልጉ መንግስታት በከፍተኛ አደጋ ላይ ይገኛል…በጋዜጠኞች ላይ የማስፈራራት ድርጊቶች ይፈጸማሉ፣ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ይገደላሉ፣ ነጻ የዜና ምንጮች እንዲዘጉ ይደረጋል፣ መብቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ የሚጠይቁ ዜጎች በኃይል ጸጥ እንዲሉ በማድረግ ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነት ይታፈናል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ እ.ኤ.አ በ2010 የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን ምክንያት በማድረግ እንዲህ በማለት የሰጡትን መግለጫ አስታውሳለሁ፣ “ህዝቦች ከምንጊዜውም በላይ በኢንተርኔት፣ በተንቀሳቃሽ ስልኮች እና በሌሎች ተገጣጣሚ ቴክኖሎጂዎች አማካይነት መረጃዎችን የማግኘት ዕድላቸው እየጨመረ በመጣበት በአሁኑ ጊዜ እንደ ቻይና፣ ኢትዮጵያ፣ ኢራን እና ቬንዙዌላ ያሉ ሀገሮች በተጻራሪው ሀሳብን በነጻ የመግለጽ ነጻነትን ሙሉ በሙሉ በመገደብ እና እነዚህን የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጠቀም እንዳይችሉ በመከልከል ላይ ይገኛሉ፡፡“
እ.ኤ.አ በሀምሌ 2015 የሚጎበኟት ኢትዮጵያ የጋዜጠኞች ተከላካይ ኮሚቴ ባወጣው ዘገባ መሰረት “በፕሬስ ነጻነት ጨቋኝነት ከዓለም በአራተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሀገር ስትሆን ከአፍሪካ ደግሞ በአስከፊ የፕሬስ አያያዝ የሁለተኛነት ደረጃውን ይዛ ትገኛለች፡፡”
በኢትዮጵያ ጋዜጠኝነት ከአሸባሪነት ጋር እኩል የሚያስመድብ ነው፡፡
ጋዜጠኝነት በኢትዮጵያ ወንጀለኛት ነው፡፡
ጋዜጠኞች አሸባሪዎች እና የመንግስት ጠላቶች ተደርገው ይፈረጃሉ፡፡
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ታስረው የሚገኙት ጋዜጠኞች እና ጦማሪያን በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው ለበርካታ ዓመታት በፍትህ አካል ሳይቀርብ በእስር ቤት በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ገዥ አካል የሐክ ቡድን/Hack Team እየተባለ ከሚጠራው ኩባንያ በርካታ የሆኑ ለስለላ ተግባር የሚያገለግሎ የሶፍት ዌር መሳሪያዎችን ግዥ በመፈጸም ብዙ ሚሊዮን ዶላሮችን ያፈሰሰ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ይኸ ዜና እርስዎ እ.ኤ.አ በ2010 የዓለም የፕሬስ ነጻነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉትን መልዕክት እና “መንግስታት ለህዝቡ የኢንተርኔት ተደራሽነት እንዳይኖር በጥቅም ላይ እየዋለ ያለውን የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ክልከላ” እያደረጉ መሆናቸውን የገለጹበትን ሁኔታ አስታወሰኝ፡፡
እንደዚሁም ሁሉ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አካል የሐክ ቡድን/Hack Team እየተባለ የሚጠራውን ኩባንያ የምርመራ ቴክኖሎጂ ውጤቶች በመጠቀም ገዥው አካል የእርስዎን ወደ ኢትዮጵያ የመምጣት ዜና ሰምቶ ከጥቂት ቀናት በፊት ከእስር ቤት ፈትቶ የለቀቃቸውን ጥቂት የዞን 9 ጦማሪያንን በቁጥጥር ስር ለማዋል እና ወደማጎሪያው እስር ቤት ለመጣል እጅግ በጣም አስከፊ እና የሞራል ስብዕና የዘቀጠበት ድርጊትን አከናውኗል፡፡
በአሁኑ ጊዜ የእርስዎ ወደ ኢትዮጵያ መድረስ ለእርስዎ ጥቂት ተጻራሪ የሆኑ ነገሮች እንደሚገለጹ አውቃለሁ፡፡
እ.ኤ.አ ሀምሌ 2009 ለጋና ህዝብ እና በእነርሱ በኩልም ለመላው የአፍሪካ ህዝብ ባስተላለፉት መልዕክት የሕግ የበላይነት ለሕገ አራዊትነት ቦታውን በሰጠበት እና የዓለምን ህዝብ ለማታለል ሲባል አንዳንድ ጊዜ የይስሙላ ምርጫ እያካሄደ በሚያጭበረብር ስርዓት ውስጥ ማንም ዜጋ ቢሆን ለመኖር እንደማይፈልግ በግልጽ አስቀምጠው ነበር፡፡
እ.ኤ.አ መስከረም 2014 ከህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የይስመላው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና አብሮት ወደ ኋይት ሀውስ ሄዶ ከነበረው ልዑክ ጋር በመገናኘት እንዲህ ብለው መናገርዎ የሚታወስ ነው ፣ “በኢትዮጵያ በዚህ ዓመት ጠቅላይ ሚኒስትር እና መንግስታችሁ ምርጫ ታካሂዳላችሁ፡፡ ስለዚያ ጉዳይ ጥቂት የማውቀው ነገር አለ…ስለሆነም ስለሲቪል ማህበረሰቡ እና ስለመልካም አስተዳደር እንደዚሁም የኢትዮጵያ እድገት እና ምሳሌነትን ወደ ሲቪል ማህበረሰቡ እንዴት ማስተላለፍ እንደሚቻል ለመወያየት ዕድል ይኖረናል…“
ደህና፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ዳሳለኝ እና የእርሱ መንግስት እርስዎ ስለተናገሩለት ምርጫ ጉዳይ እ.ኤ.አ ግንቦት 24/2015 የይስሙላ ምርጫ ተደርጓል፡፡ የይስሙላ የቅርጫ ምርጫውን መቶ በመቶ አሸንፈዋል፡፡ አዎ፣ በመቶ ፐርሰንት!
በዘርፉ ላይ እውቀቱ እና ክህሎቱ ያላቸው አስተያየት ሰጭዎች በ21ኛው ክፍለ ዘመን እንደዚህ ያለ የምርጫ ውጤት ሊኖር የሚችለው በሰሜን ኮሪያ እና በሳዳም ሁሴኗ ኢራቅ ብቻ ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2008 ለእጩ ፕሬዚዳንትነት የቅስቀሳ ዘመቻ እያካሄዱ ባሉበት ወቅት እንዲህ ማለትዎ የሚታወስ ነው፣ “ዓሳማን ለማቆንጀት የዓሳማዋን ከንፈር የከንፈር ቀለም በመቀባት ለማቆንጀት ይቻላል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አንድን አሮጌ ዓሳ በወረቀት ላይ ጠቅልሎ ለውጥ ማለት ይቻላል፡፡ ሆኖም ግን ከስምንት ዓመታት በኋላም ቢሆን መጠንባቱን አይተውም፡፡“
እ.ኤ.አ በ2015 ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚባለው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የአምባገነንነቱን የቅርጫ ምርጫ በድምጽ መስጫ ወረቀት በመጠቅለል ዴሞክራሲ ብሎ በመጥራት ለህዝብ አቀረበ፡፡ ሆኖም ግን ስልጣንን ከህዝብ ፈቃድ ውጭ በጠብመንጃ አፈሙዝ ይዞ መግዛቱን ከጀመሩ ከ23 ዓመታት በኋላም ቢሆን መጠንባቱን አልተወም፡፡
በየዓምስት ዓመቱ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የእርሱን ኢሰብአዊነት፣ አረመኔነት እና የእርሱን የዘቀጠ ሙሰኝነት ለመሸፋፈን ሲል የይስሙላ የቅርጫ ምርጫ ያካሂዳል፡፡
እ.ኤ.አ በ2005 አሁን በህይወት የሌለው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ የቅርጫ ምርጫ አካሂዶ ነበር፡፡ በምርጫው የመራጮች ድምጽ ውጤት ሲያጣ እና በአደባባይ መሸነፉን ሲያውቅ የህዝብን ድምጽ በኃይል ነጥቆ ሲወስድ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ምንም ዓይነት መሳሪያ ሳይዙ ወደ አደባባይ በወጡ ባልታጠቁ ሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ቅጥር ነብሰ ገዳዮችን በማዘዝ እና በማሰማራት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች እንዲገደሉ አድርጓል፡፡
በዚያ ኃላፊነት በሌለው የዕልቂት ተግባር ላይ ያለቁትን ዜጎች ባይሆን ኖሮ ይህን ደብዳቤ አልፅፍሎትም ነበር ብዬ አምናለሁ።
መለስ በፈጸመው ዕልቂት ምክንያት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ እንዲሁም በሌሎች ሰብአዊ መብቶች በሚደፈጠጡባቸው ቦታዎች ሁሉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ለመሆን የበቃሁት እና ያለምንም ማመንታት የማይበገር የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሆኘ የቀጠልኩበት ምክንያትም ከዚሁ ድርጊት የሚመነጭ ነው፡፡ የዶ/ር ማርቲን ሉተር እንዲህ የሚሉት ምክሮች ነብሴን ሁሉ ያንቀሳቅሱታል፣ “አንዳንድ ነገሮች ሲደረጉ እያየን ዝም በምንልበት ጊዜ በዚያች ዕለት ህይወታችን ማብቃት ይጀምራል፡፡“
በመለስ ዕልቂት የጠፋው ህይወት ሊያሳስበን ይገባል፡፡”
ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እና ለመለስ ዜናዊ ምንም ነገር ያልሆ ተራ ጉዳይ እንደሆነ አድርገው ነው የሚመለከቱት፡፡
ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የህዝቦች ዕልቂት ደንታው አይደለም፡፡ እናም በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ቢያልቁም ከቁብ የሚቆጥሩት ጉዳያቸው አይደለም፡! እንደዚሁም ሁሉ በአሁኑ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች በመለስ ዜናዊ የማጎሪያ እስር ቤት ገብተው ቢማቅቁ ለወያኔዎች ጉዳያቸው አይደለም፡፡
ሆኖም ግን የመለስ ዜናዊ የዕልቂት ሰለባ የሆኑት ወገኖቼ በቃላት ለመግለጽ ከምችለው በላይ ለእኔ ከምንም በላይ ያሳስቡኛል፡፡
እነዚያ የጨካኞች ሰለባ የሆኑት ወገኖች እንደ ሰው ፍጡርነታቸው ለእኔ ያሳስቡኛል፡፡
ሊታረቅ በማይችል የሕግ የበላይነት ጥሰት ዕልቂት የተፈጸመባቸው ወገኖቼ ከምንም በላይ ያሳስቡኛል፡፡
ከብዙ አስርት ዓመታት በፊት ፍጹም ላለመመለስ ምሎ እንደተሰደደ የኢትዮጵያ ተወላጅ ልጅነቴ ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ግን ትታው አንዳልሄደች ዜጋ የእነዚህ የዕልቂት ሰለባ የሆኑት ወገኖቼ ጉዳይ ያሳስበኛል፡፡
እንደ ኩሩ ኢትዮ-አሜሪካዊ የነጻነትን ስጦታ ዕድል እንደተጎናጸፈ ዜጋ በሬፐብለኩ ሰነድ ምሰረታ ላይ ወደፊት ብሩህ ነገር መምጣት እንዳለበት ይታየኛል፡፡ አዎ፣ ያ የተጣረሰ እና ትክክል ያልሆነ ሰነድ ወደ ባርነት የሚያመራ እና ጆሮ ዳባ ልበስ ተብሎ አላይም፣ አልሰማም ተብሎ የተተው ሰነድ ሀዘን፣ ለቅሶ እና እንደ የአፍሪካ ህዝቦች መጽሐፍ ቅዱስ ስብስቦች ቆንጆ ነው ተብሎ የተጻፈ ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2009 በአክራ ላይ በመገኘት እንዲህ ብለው ነበር፡
ይህ ሁኔታ ምርጫዎችን ከማካሄድ በላይ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በምርጫዎች መካከል ምን እየተደረገ ነው ስለሚለው ጉዳይ ነው፡፡ ጭቆና ብዙ መገለጫዎች ሊኖሩት ይችላል፣ እናም ለበርካታ ሀገሮች ምርጫን ያካሄዱ እንኳ ህዝቦቻቸውን ለከፋ ድህነት በማጋለጥ በበርካታ ችግሮች ተተብትበው ይገኛሉ፡፡ የመንግስታት መሪዎች 20 በመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱን ትርፍ በእራሳቸው ኪስ እያጨቁ የምጣኔ ሀብቱን እየበዘበዙ ባሉበት ሁኔታ የትኛውም ሀገር ቢሆን ሀብት ሊያፈራ አይችልም…መንግስት 20 በመቶ የሚሆነውን የሀገሪቱን ትርፍ ለግል ጥቅሙ እያዋለ ባለበት ሁኔታ ምንም ዓይነት የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ሊኖር አይችልም፡፡
የእርስዎ ምልከታ ሙሉ በሙሉ ትክክል ናቸው፡፡
ኢኮኖሚስት የተባለው መጽሔት እ.ኤ.አ ግንቦት 2012 ባወጣው ዘገባ የሚከተሉትን ምልከታዎች አስፍሮ ነበር፡
በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ድፍረትን የተላበሰ እንቅስቃሴ አይደለም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ለዚህ ዓመት የተተነበየው ብሄራዊ ገቢዋ 38.5 ቢሊዮን ዶላር የሆነ እና ህዝቧም 85 ሚሊዮን በመሆን ከዓለም ደኃ ሀገሮች ደረጃ ውስጥ ተመድባ ትገኛለች፡፡ የመንግስት ከፍተኛ የሆነ ወጭ አስጊ የሆኑ አደጋዎችን ከፍተኛ የዋጋ መናርን ጨምሮ (በመጋቢት 32.5 በመቶ ካለፉት ዘጠኝ ወራት ዝቅተኛው) እና ከፍተኛ የሆነ የመንግስት ብድር ሆኖም ግን ለግል ዘርፉ ብድርን የሚከለክለው አሰራር አሳሳቢ ጉዳዮች ናቸው፡፡ ከዚህ የበለጠ ለመበደር እና ግዙፍ ወጭ ለማድረግ ዕቅድ ተይዟል፣ አስፈላጊ እንደሆነም ታምኖበታል፡፡ የኢትዮጵያ መናገሻ እምብርት የሆነችው ከተማ ከቻይና በሚገኙ ብድሮች በቻይና እና በጣሊያን የስራ ተቋራጮች ግዙፍ የሆኑ ህንጻዎች እና ድልድዮች በመገንባት ላይ ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ሌሎቹ የአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ክፍሎች የቆሻሻ መጣያ መንገዶች እና በቆርቆሮ ቤቶች የተሰሩ በጣም ኋላቀር እና የተረሱ የከተማው አካል ሆነው ይገኛሉ፡፡
ክቡር ፕሬዚዳንት እ.ኤ.አ በ2009 ለጋና ሕዝቦች እንዲህ በማለት ነግረዋቸው ነበር፣ “አመራራችሁን በማጠናከር በእኛ የሰብአዊ መብት በሚወጣው ዘገባ መሰረት ለሙስና ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት ተንቀሳቀሱ፡፡“
በኢትዮጵያ ላይ ተንሰራፍቶ ስለሚገኘው ሙስና ጉዳይ የሚያስጨንቃችሁ ምንም ዓይነት ችግር የለም፡፡ የዓለም ባንክ ይህንን ስራ ጥሩ አድርጎ አንድ በአንድ ዝርዝር ጥናት በማድረግ ሰርቶ አቅርቦላችኋል፡፡
እ.ኤ.አ በ2012 የዓለም ባንክ “በኢትዮጵያ ሙስናን መመርመር/Diagnosing Corruption in Ethiopia“ በሚል ርዕስ ባለ417 ገጽ ዘገባ አቅርቦ ነበር፡፡
ይህ ዘገባ ሙስና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሰውነት ውስጥ እንደተስፋፊው ነቀርሳ ዘርፎችን እያዳረሰ እንደመጣ ግልጽ አድርጓል፡፡ ለዚህም ነው የዓለም ባንክ ዝርዝር የሆነ የምርመራ ጥናቱን ለማካሄድ የተገደደው፡፡
በዘርፉ ልሂቃን እየተነገረ እንዳለው ሙስና በአጭር ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያን ህዝብ እና የምጣኔ ሀብት እንደሚያወድም ግልጽ ተደርጓል፡፡
እ.ኤ.አ በ2014 የሙስና መለኪያ መስፈርት መሰረት ከ175 ሀገሮች መካከል ኢትዮጵያ የ136ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡
በሁሉም እውነተኛ መመዘኛዎች ከብዙ ጊዜ ጀምሮ ሁለት ጥያቄዎችን ሳሰላስል ቆይቻለሁ፡፡ የእርስዎ ወደ ኢትዮጵያ መሄድ እየተቃረበ በመጣ ቁጥር እነዚህ ጥያቄዎች እንቅልፍ በመከልከል እረፍት ነስተውኛል፡፡ እነዚህም ጥያቄዎች እንዲህ ይቀርባሉ፡፡
1ኛ) እርስዎ አሁን ያሉበትን የፕሬዚዳንትነት ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጋር ሲነጻጸር አፍሪካ በአሁኑ ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ላይ ትገኛለችን?
2ኛ) እርስዎ አሁን ያሉበትን የፕሬዚዳንትነት ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጋር ሲነጻጸር ኢትዮጵያ በአሁኑ ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ላይ ትገኛለችን?
እነዚህን ጥያቄዎች የማቀርበው ለተጠያቂነት እና በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው፡፡
በመጀመሪያ ደረጃ በቢሊዮን ዶላር የሚቆጠሩ የአሜሪካ ግብር ከፋዮች ገንዘብ ካለፉት ስድስት ዓመታት ጀምሮ በልማት፣ በደህንነት እና በዴሞክራሲ ስም ወደ በገፍ ኢትዮጵያ ይፈስሳሉ፡፡ የአሜሪካ ሕዝብ ግብር ከፋይ ገንዘብ በኢትዮጵያ ከህዝቦች ፍላጎት ውጭ በጠብመንጃ ኃይል ተንጠልጥሎ የሚገኘውን አረመኔ አምባገነን ገዥ አካል ከማጠናከር የዘለለ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም የፈየደው ነገር አንደሌለ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
እ.ኤ.አ መስከረም 2014 ኢትዮጵያ “ጉልህ የሆነ ምልክት እና እድገትን በአፍሪካ እያሳየች ያለች ሀገር ናት፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ውጭ ሌላ በዓለም ላይ በፈጣን ዕድገት በመገስገስ ላይ ካሉ ሀገሮች መካከል የሚሻል በምሳሌነት የሚነሳ ሀገር የለም“ በማለት ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የልዑካን ቡድን መግለጫ መስጠትዎ የሚታወስ ጉዳይ ነው፡፡
በፈጣን እድገት ላይ የሚገኝ የምጣኔ ሀብት የሚለው ሀረግ ከመገናኛ ብዙሀን ጠቀሜታ አንጻር ጥሩ ሊሆን ይችላል፣ ሆኖም ግን ይህ አፍ እንዳመጣው የሚነገር የዘፈቀደ አባባል በመረጃ ላይ የተደገፈ አይደለም፡፡
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ/United States Agency for International Developmenmt (USAID) የተባለው ድርጅት “በኢትዮጵያ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎቱ ዘርፍ መጠነ ሰፊ የሆነ እድገትን አስመዝግቢያለሁ” በማለት በተደጋጋሚ እና ያለምንም ማቋረጥ ሁልጊዜ እንደሚለው እምቧ ከረዩ ዓይነት አባባል ነው፡፡
USAID በኢትዮጵያ ፈጣን የምጣኔ ሀብት ዕድገት እንዲመዘገብ አስችያለሁ ስለሚለው ነገር ይህ ጉዳይ እውነተኛ ስለመሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡
እ.ኤ.አ በ2010 የመንግስት መምሪያ ዋና ተቆጣጣሪ እንዲህ የሚል ዘገባ አቅርቦ ነበር፣ “በኢትዮጵያ USAID/ኢትዮጵያ ያቀረበው የኢትዮጵያ ዕቅድ እና የአፈጻጸም የኦዲት ዘገባ ዕቅድ እና አፈጻጸሙን በትክክል ያመዛዘነ አልነበረም፣ ምክንያቱም የድርጅቱ ሰራተኞች ተገኘ የተባለው አፈጻጸም እንዴት እንደተገኘ ማሳየትም ሆነ ላቀረቧቸው ተገኙ ለተባሉ ውጤቶች ድጋፍ ሊሰጥ የሚችል ነገር ማቅረብ አልቻሉም፡፡“
የዕድገት ቁጥሮች ናቸው ተብለው የቀረቡት አሃዞች እንዲሁ ተቀቅለው የወጡ ሊሆኑ ይችላሉን?
በቢሊዮኖች የሚቆጠሩት የአሜሪካ ግብር ከፋይ ህዝብ ዶላሮች የኢትዮጵያን ህዝብ በትክክል ለመርዳት ስለመዋላቸው ሊያሳይ የሚችል መረጃ የለም፡፡ ይልቁንም፣ ለመሪ ተብዬዎች፣ ለድርጅቱ አባላት እና ለወያኔ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ደጋፊዎች ታላቅ ነገር እንዳደረጉላቸው ግልጽ ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2011 ግልሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ/Global Financial Integrity የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት የሚከተለውን ዘገባ አቅርቦ ነበር፡
ዓመታዊ የነፍስ ወከፍ ገቢዋ 365 ዶላር የሆነችው ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2000 እና በ2009 ባሉት ዓመታት መካከል 11.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር ከሀገር እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ እ.ኤ.አ በ2009 በሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር በጠቅላላ 3.26 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እንዲወጣ በማድረግ ካለፉት ሁለት ዓመታት በሁለት እጥፍ ብልጫ ያሳየ ገንዘብ ከሀገር ውስጥ በህገ ወጥ መልክ ወጥቷል…
እ.ኤ.አ 2008 ኢትዮጵያ 829 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በልማት ዕርዳታ ስም ተቀብላለች፣ ሆኖም ግን ይህ ገንዘብ በከፍተኛ ሕገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እዲመነምን ሆኗል፡፡ የኢትዮጵያ የካፒታል ከሀገር ወደ ውጭ የሚያደርገው ፍልሰት ከፍተኛ የሆነ መጠንን እየያዘ በመሄድ እ.ኤ.አ ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከላከቻቸው ምርቶች ዋጋ 2 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር በመብለጥ በሕገ ወጥ መልክ ወደ ውጭ የወጣወው ገንዘብ 3.26 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለመሆን በቅቷል፡፡
ግሎባል ፋይናንሻል ኢንቴግሪቲ እንዲህ የሚል መደምደሚያ ሰጥቷል፣ “የኢትዮጵያ ህዝቦች ደማቸው በሙሉ እንዲመጠጥ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ካለባቸው የከፋ ዕጦት እና ድህነት ለመውጣት በማሰብ ሕገ ወጥ የገንዝብ ዝውውርን በማካሄድ በወንዙ ላይ ወደ ላይ በመዋኘት ላይ ይገኛሉ፡፡“
መነሳት ያለበት ጥያቄ የትኞቹ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው በሕገ ወጥ መልክ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር ከሀገር ውስጥ እንዲወጣ ማድረግ የሚያስችል አቅም ያላቸው የሚለው ነው፡፡
የኢኮኖሚስት መጽሔት እ.ኤ.አ መጋቢት 2013 ባወጣው ዘገባ መሰረት “በዓለም በፈጣን ዕድገት ላይ ከሚገኙ ሀገሮች መካከል አንዷ በሆነችው“ ሀገር ላይ እንዲህ የሚል አስተማማኝ ዘገባ አውጥቷል፣
በመንግስት በሚወጡ አሀዞች ላይ የገዥው አካል ደጋፊዎች እንኳ እምነት የላቸውም፡፡ በግብርና ዓመታዊ ምርታማነት ላይ የሚታየው ዕድገት ምናልባትም ከ5-6 በመቶ አይበልጥም የሚል ዘገባ በመንግስት በኩል በሚወጡ አሃዞች ይነገራል፡፡ ሆኖም ግን ከ2-3 በመቶ ያም ሆኖ በጣም የሚስብ ዕድገት ተብሎ ሊወሰድ የሚችል ዕድገት ሊኖር ይችላል፡፡
ባለስልጣኖች ዕቅዶችን ያስቀምጣሉ፣ እናም ታላላቆቹ ባለስልጣናት ምን መስማት እንደሚፈልጉ በመገንዘብ ዘገባዎች እንዲቀርቡላቸው ይደረጋል፡፡ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች 11 በመቶ ዓመታዊ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ለታዕይታ ብቻ በመንግስት በኩል በሚለቀቀው አሀዝ ላይ ጥርጣሬ አላቸው፡፡ እነዚህ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎች የሚሉት መንግስት ከሚለው በግማሽ ባነሰ ወደ ከ5-7 በመቶ አካባቢ የሚሆን ዓመታዊ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ሊኖር ይችላል የሚል እስከ አሁንም ድረስ እንደተከበረ በመናገር ላይ ያሉትን ሀሳብ ያቀርባሉ፡፡
ሌሎች ገለልተኛ የሆኑ የምርምር ድርጅቶች ደግሞ እጅግ በጣም አስደንጋጭ እና ተስፋ አስቆራጭ የሆኑ እውነታዎችን ያወጣሉ፡፡
እ.ኤ.አ በ2014 የኦክስፎርድ የድህነት እና የሰው ልማት ተነሳሽነት (ኦድሰልተ) ዘርፈ ብዙ የድህነት መለኪያ/Oxford Poverty and Human Development Initiative (OPHDI) Multidimensional Poverty Index) በቀድሞ አጠራሩ ዓመታዊ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የሰዎች የድህነት መለኪያ/U.N.D.P Human Poverty Index) እየተባለ ይጠራ የነበረው ዓለም አቀፋዊ ድርጅት ኢትዮጵያ በፕላኔቱ ከሚገኙት ደኃ ሀገሮች ሁሉ በተከታታይ ለ4ኛ ጊዜ በድህነት በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ዘገባ አቅርቧል፡፡ አዎ፣ በዓለም ላይ ሁለተኛዋ ደኃ ሀገር!
እ.ኤ.አ በ2010 ኦድሰልተ/OPHDI በኢትዮጵያ በአስከፊ ድህነት ላይ የሚገኘው ህዝብ ቁጥር (በቀን ከአንድ ዶላር በታች የሚያገኘው ሰው) በመቶኛ ሲሰላ 72.3 በመቶ ነው የሚል ዘገባ አውጥቷል፡፡
የኦድሰልተ/OPHDIየ2014 ዓመታዊ የድህነት አሀዛዊ ዘገባ የበለጠ አስደንጋጭ ሁኔታን ያመላክታል፡፡ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖረው 82 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በከተሞች ከሚኖረው እና 18 በመቶ ከሚሆነው ህዝብ በበለጠ ሁኔታ “በአስከፊ ድህነት” ውስጥ ይገኛል፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 በኢትዮጵያ “በአስከፊ የድህነት” አደጋ ውስጥ ከሚኖረው ህዝብ መካከል በሚከተሉት ክልሎች ላይ ይገኛል፡ ሶማሊ (93%)፣ ኦሮሚያ (91.2%)፣ አፋር (90.9%)፣ አማራ (90.1%) እና ትግራይ (84.5%) ይሸፍናሉ፡፡
በኦድሰልተ/OPHDI መለኪያ መስፈርት መሰረት ድህነት ማለት ገንዘብ ማጣት ብቻ አይደለም፡፡
ድህነት በዋናነት መጥፎ የጤና አጠባበቅ፣ መጥፎ የትምህርት ስርዓት፣ መጥፎ የምግብ ሁኔታ፣ ከፍተኛ የሆነ የህጻናት ሞት፣ መጥፎ የውኃ አቅርቦት እና የኤሌክትሪክ አቅርቦት፣ እንዲሁም መጥፎ የቤት እና የንጽሀን ሁኔታ ነው፡፡
በኢትዮጵያ ዋና የድህነት መንስኤ የመልካም አስተዳደር እጦት ነው!
ባለፉት “አስር ዓመታት ውስጥ ባለሁለት አህዝ የምጣኔ ሀብት ዕድገት ተመዝግቧል” እየተባለ የሚነዛው የቅጥፈት አባዜ እንዳለ ቢኖርም እንኳ ኢትዮጵያ በመጥፎ ሁኔታ ላይ ትገኛለች እናም ለዚህም ነው ኢትዮጵያ በፕላኔቷ ከሚገኙት ሀገሮች በድህነት በሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች እየተባለ ያለው!
በሁለተኛ ደረጃ የአሜሪካ ግብር ከፋዮች ለኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ለሰጡት በቢሊዮኖች ለሚቆጠር ዶላር ምትክ የሚሆን ምን እንደሚያገኙ ለማወቅ ጉጉት አለኝ፡፡
ዩኤስ አሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ያዘነበለችው በደህንነት ጉዳዮች ላይ በአፍሪካ ቀንድ እና በምስራቅ አፍሪካ ያለውን ከፍተኛ ሸክም መሸከም እንድትችልላት ለማድረግ ለመሆኑ ጥርጥር የለኝም፡፡ ከዚያ ውጭ ሌላ አዲስ ነገር አለ የሚል እምነት የለኝም፡፡ በድህረ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ዩኤስ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ዋና የጦር መሳሪያዎች እና ስልጠናዎች አቅራቢ ነበረች፡፡
ዩኤስ አሜሪካ እ.ኤ.አ ከ1943 እስከ 1977 ድረስ ባሉት ዓመታት ውስጥ በሰሜን ኢትዮጵያ የቃኘው ጦር ሰፈርን በመያዝ “የቀዝቃዛው ጦርነትን ማዳመጫ ጣቢያ” አድርጋ ስትጠቀምበት ነበር፡፡
የኢትዮ-አሜሪካ ግንኙነት እ.ኤ.አ በ1974 በኢትዮጵያ የሶሻሊስት ወታደራዊ አምባገነን በመፈንቅለ መንግስት ስልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ ተበላሸ፡፡
በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ምንም ይሁን ምን የዩኤስ አሜሪካ እና የኢትዮጵያ ስልታዊ የደህንነት ትብብር እና አጋርነት በአፍሪካ ቀንድ አሸባሪነትን በማስወገዱ ረገድ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ኢትዮጵያውያን በአፍሪካ ቀንድ አሸባሪነትን በመዋጋት የአሜሪካንን ጥረት በመደገፉ ረገድ ምንም ጥርጣሬ የለም፡፡
ከቂት ወራት በፊት አሸባሪነት በዜግነት እና ባላቸው እምነት ምክንያት በሊቢያ የ30 ንጹሀን ዜጎችን አንገት ቀልቷል፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ባሉበት ቦታ ሁሉ የአሸባሪነትን መጥፎ ጥላ ከስሩ መንግሎ ለመጣል እና ሰላም ለማውረድ ጥረታቸውን እንደሚቀጥሉ ጥርጥር ሊኖር አይችልም፡፡ ኢትዮጵያውያን የፈለገውን ያህል ጊዜ የሚፈጅ ቢሆንም የዜጎቻቸውን አንገት የቀላውን እና በሰው ልጆች ላይ ወንጀል የፈጸሙትን አሸባሪዎች የፍትህን ረዥም ክንድ በመጠቀም ለመያዝ እና ለፍርድ እንደሚያቀርቧቸው ጥርጥር የለውም፡፡
ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የተባለው ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ ለጸረ ሽብር ትግሉ ጠቅላይነት የለውም፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ ዩኤስ አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ በአሸባሪ የስም ዝርዝር የመረጃ ቋት ውስጥ ስሙ ሰፍሮ ከሚገኘው እና እራሱ አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀው ከህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ድርጅት ጋር የጸረ ሽብርተኝነት አጋርነትን መስርታ የመገኘቷ ጉዳይ ነው፡፡ ዋናው አሸባሪ የማፊያ ቡድን እንዴት አሸባሪነትን ሊያጠፋ ይችላል ተብሎ ይተሰባል! ሌባን ለመያዝ ሌባን መወዳጀት የሚለውን ስልት ለመጠቀም ካልሆነ በስተቀር፡፡
ሆኖም ግን የቀድሞ አሸባሪዎች በመካከላችን ውስጥ ሆነው የበግ ለምድ ለብሰው እያተራመሱ የሚገኙ ተኩላዎች ቢሆኑም ጽዋው ሲሞላ አንድ ቀን ዶግ አመድ ሆነው እንደሚጠፉ በልባችን ውስጥ ዘላለማዊ ተስፋን ሰንቀናል፡፡
በአንድ ወቅት ሌላው አሸባሪ ቡድን ወያኔው አራሱ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “በግንባር በመሆን አጋሮቻችንን በመርዳት እኛን የሚያሰጉንን አሸባሪዎች ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ይህንን ስልት ለበርካታ ዓመታት በየመን እና በሶማሌ በመተግበር ስኬታማ ሆነናል፡፡“
የዩኤስ አየር ኃይል ለአሸባሪነት ተልዕኮ ወታደራዊ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን/drones ሩቅ ከሆነው እና በደቡብ ኢትዮጵያ ከሚገኘው የሲቪል የአውሮፕላን ማረፊያ በማስነሳት በየመን እና በሶማሌ መሽገው የሚገኙትን አሸባሪዎች ለመደምሰስ ጥረት እያደረገ እንዳለ የሚታወቅ ነገር ነው፡፡
በእኛ ላይ ስጋትን የሚደቅኑ አሸባሪዎችን ወይም ደግሞ ማንኛውንም ሰላም ወዳድ ሀገር የሚያተራምሱትን ነውጠኛ ሽብርተኞች በማጥፋቱ ረገድ ችግር የለኝም፡፡
እንደ ሲቪል ሕገ መንግስታዊ የሕግ ባለሙያነቴ ጥፋተኝነትን ለማውጣት በሚቀመረው የፖሊሲ መርህ መሰረት በመጀመሪያ ግደል ከዚያም ጥያቄዎችን አቅርብ በሚለው መርህ ላይ ተቸግሪያለሁ፡፡
ይህንን ጉዳይ ለሌላ ጊዜ አቆየዋለሁ፡፡
የእኔ ጉዳይ በአሁኑ ጊዜ ዩኤስ አሜሪካ አሸባሪዎችን ለማደን በሚል ሀሳብ በአፍሪካ ቀንድ አሰማርታው ያለው የደህንነት እና የጸረ ሽብር አጋርነት በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን፣ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችን እና ሌሎችንም ሰላማዊ ዜጎች ሳይቀር በማደን ላይ የመገኘቱ ሁኔታ ነው፡፡
የዩኤስ አሜሪካ የመንግስት መምሪያ እ.ኤ.አ በ2014 በኢትዮጵያ ስላለው የሰብአዊ መብት አያያዝ አስመልክቶ ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ በሲቪል ህዝቦች ላይ ያደረሰውን ሰብአዊ ድፍጠጣ በማስረጃ አስደግፎ ማውጣቱ የሚታወስ ነው፡፡ ከዘገባው ከፊሉ እንዲህ የሚል ነበር፡
ዋነኛው የሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ችግር የሚከተሉትን ያካትታል፡ ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት በህትመት ግንኙነቶች እና በኢንተርኔት የሚደረጉ ገደቦችን ጨምሮ መገደብ፣ በነጻ የመደራጀት፣ በቁጥጥር ስር ማዋልን ጨምሮ መብትን መከልከል፣ ፖለቲካዊ እንደምታ ያላቸውን የፍትህ ሂደቶች ለይስሙላ እንዲካሄዱ ማድረግ፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አባላትን እና ጋዜጠኞችን ማስፈራራት እና ማሸማቀቅ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡ መንግስት የበጎ አድራጎት እና ማህበራት የሚል ቀያጅ አዋጅ በማውጣት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን የስራ እንቅስቃሴ ቀጣይነት ባለው ሁኔታ በመገደብ ነጻነትን ገድቦ ይገኛል፡፡ ሌሎች የሰብአዊ መብቶች ችግሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ የዘፈቀደ ግድያ፣ ንጹሀን ዜጎችን በዘፈቀደ የማሰቃየት፣ የመደብደብ፣ ከህግ አግባብ ውጭ ስልጣንን የመጠቀም እና በደህንነት ኃይሎች የእስረኞች አያያዝ መጥፎ ሆኖ የመገኘቱ ሁኔታ፣ የእስር ቤቶች አያያዝ ሁኔታ ለህይወት አስጊ ሆነው የመገኘት ችግር፣ ከህግ አግባብ ውጭ በዘፈቀደ ንጹሀን ዜጎችን በቁጥጥር ስር ማዋል እና ማሰር፣ ምንም ዓይነት ክስ ሳይመሰረት ማሰር፣ በውንጀላ በእስር ቤት የሚገኙትን ዜጎች የፍርድ ቤት ቀጠሮ ረዥም እና የተንዛዛ ማድረግ፣ ደካማ የሆነ የፍትህ አካል መኖር እና ለፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ምቹ ሆኖ የመገኘት ሁኔታ፣ የዜጎችን ግላዊ መብቶች ማለትም ህገወጥ ፍተሻን፣ በመንግስት የሰፈራ ፕሮግራም አፈጻጸም ውንጀላን፣ የአካዳሚክ ነጻነትን፣ በነጻ የመሰብሰብ ነጻነትን፣ በነጻ የመደራጀት እና ከቦታ ወደ ቦታ የመንቀሳቀስን፣ በኃይማኖትች ጣልቃ መግባትን፣ ዜጎች በእራሳቸው ችሎታ እና አቅም የመንግስትን ፖሊሲን፣ አስተዳደራዊ እና የፍትህ ሙስናን ለመለውጥ እንዳይችሉ ማድረግን፣ ኃይልን መጠቀምን እና ህብረተሰቡን በሴቶች እና በህጻናት በማለት መከፋፈልን ጨምሮ መብቶችን መዳፈር የሚሉት ይገኙበታል፡፡
ባለፉት በርካታ ዓመታት በአፍሪካ በተለዬ ሁኔታ ያሳዩት ለነበረው ተነሳሽነት ያለኝን አድናቆት ለመግለጽ እወዳለሁ፡፡
በአህጉሩ የኤሌክትሪክ አገልግሎት በስፋት እንዲሰራጭ በማሰብ “አፍሪካን በኃይል ማጠናከር” የሚል የህዝብ እና የግል አጋርነት መስርታችኋል፡፡
በአንድ ዓረፍተ ነገር ውስጥ ኃይል እና አፍሪካ የሚሉ ቃላትን ማየቴ እንድጨነቅ እና እንድጠራጠር አድርጎኛል፡፡
ኃይል ለአፍሪካ እውነተኛ ችግር ነው፡፡
ጥያቄዎች ግን ሁልጊዜ አንድ ዓይነት ናቸው፡ ማን ነው ኃይል ያለው? ማን ነው ኃይል የሌለው እና አቅመ ቢሱ? ኃይል ያላቸው ኃይል የሌላቸውን ዜጎች መብቶች ከህግ አግባብ ውጭ እንዳይደፈጥጡ እንዴት ነው መከላከል የሚቻለው?
ለተራ አፍሪካውያን “ኃይል ለአፍሪካ” የሚለው ሀርግ “ኃይል ለአፍሪካ አምባገነኖች” ከሚለው ሀረግ ጋር ሊያሳስት ይችላል፡፡
ይህ ተነሳሽነት “አፍሪካውያንን ማጠናከር” መባል ነበረበት የሚል ሀሳብ አለኝ፡፡ አፍሪካውያንን በተለይም ወጣቱን ኃይል ማጠናከር አለብን የሚል እምነት አለኝ፡፡
እንደዚሁም ሁሉ የእርስዎን “ወጣት የአፍሪካ መሪዎች ተነሳሽነት” በሚል የማንዴላ ዋሽንግተን ፌሎውሽፕን ዋና መሰረት አድርጎ የተነሳውን ተነሳሽነት እወደዋለሁ፡፡ ይህ ተነሳሽነት በወደፊቷ አፍሪካ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ የእርስዎን ሁለገብ ጥረት ያካተተ ነው ይባላል፡፡
500 የሚሆኑ ምርጥ እና ብሩህ አዕምሮ ያላቸውን የአፍሪካ ወጣቶችን በማምጣት “የቢዝነስ እና የስራ ፈጠራ ፕሮግራሞችን እንዲሁም የህዝብ አመራር እና አሰተዳደር ስራዎችን” ዕድሎች እንዲያገኙ በማድረጉ ረገድ የሚደገፍ ጉዳይ ነው፡፡
“ወጣት የአፍሪካ መሪዎች ተነሳሽነት” የሚለው የእርስዎ ፕሮግራም (W.E.B. Du Bois) ዱ ቦይስ ህልዮት “አስሩ በተፈጥሮ የታደሉ የልዩ ተሰጥኦ ባለቤቶች” የሚለውን እና ከአስር ጥቁር አፍሪካውያን አንዱ በዓለም ላይ ለዘሩ መሪ ይሆናል የሚለውን አስታወሰኝ፡፡
ዱ ቦይስ ባዘጋጁት የጥናት ጽሁፋቸው ላይ እንዲህ የሚል ነገር ጽፈው ነበር፣ “የባሮች ዝርያ በእርሱ ልዩ በሆኑ ሰዎች ይጠበቃል፡፡ በባሮቹ ላይ ያለው የትምህርት ችግር እንግዲህ ተሰጥኦ ባላቸው በእነዚህ አስር ሰዎች መፈታት አለበት፡፡ የዚህ ዘር ምርጥ የሆኑ ሰዎች የማግኘት ችግር ነው ሚሆነው እናም ብዙሀኑን ከብክለት እና በመጥፎ ነገር ከመሞት እንዲተርፉ መምራት አለባቸው፡፡“
ምናልባትም የእርስዎ “ወጣት የአፍሪካ መሪዎች ተነሳሽነት” የአፍሪካን አስር በተፈጥሮ የታደሉ ምርጦች ያስገኝ ይሆናል፡፡
ምናልባትም የአፍሪካ ወጣት መሪዎች አፍሪካን ከብክለት፣ ከሰው ዘር ማጥፋት እና በሰው ልጆች ላይ ከሚፈጸሙ ወንጀሎች ሊታደጓት ይችሉ ይሆናል፡፡
ሆኖም ግን ምንም ዓይነት የትምህርት፣ የጤና አጠባበቅ እና የስራ ዕድል ላላገኙት፣ በመቶ ሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ የአፍሪካ ወጣቶች ምን ተነሳሽነት አዘጋጅተውላቸው እንደሆነ ለማወቅ አጓጓለሁ፡፡ የተባበሩት መንግስታት 70 በመቶ የሚሆነው የአፍሪካ ህዝብ እድሜው ከ35 ዓመት በታች ነው ይላል፡፡ እነዚህ ወጣቶች በአህጉሪቱ ተንሰራፍቶ ካለው አምባገነናዊ አገዛዝ ነጻ ለመውጣት የእርስዎን እገዛ ይፈልጋሉ፡፡ የቀረውን ነገር እራሳቸው መያዝ ይችላሉ፡፡
እ.ኤ.አ ነሀሴ በ2014 በኋይት ሀውስ የዩኤስ-አፍሪካ መሪዎችን ጉባኤ ሲያካሂዱ በነበረበት ጊዜ ልቤ ተሰብሯል፡፡
በዓለም ላይ ከሚገኙ የአፍሪካ አምባገነን መሪ ተብዬዎች ጎን ቆመው ባየሁዎት ጊዜ “አፍሪካ ጠንካራ ሰዎችን አትፈልግም፣ አፍሪካ የምትፈልገው ጠንካራ ተቋማትን ነው” ብለው ሲናገሯቸው የነበሩት ቃላት ስሜትን ወረሩት፡፡
በዚያ ጉባኤ ላይ ከፓውል ቢያ፣ ከብላይሴ ኮምፓሬ፣ ከቴዶር ኦቢያንግ ንጉማ ባሶጎ፣ ከኃይለማርያም ደሳለኝ ቦሸ፣ ከፓውል ካጋሜ፣ ከጆሴፍ ካቢላ ካባንጌ፣ ከኢድሪስ ዴቢ፣ ከንጉስ ምዋ 3ኛ፣ ከዮሪ ሙሴቤኒ፣ ከዴኒስ ሳሶው ንጉሶ እና ከመሳሰሉት ትከሻ ለትከሻ ተቃቅፈው ቆመው ይታዩ ነበር፡፡
በዚያ ቦታ ላይ በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በፍርድ ሂደት ላይ ካለው ከኡሩ ኬንያታ ጋር ቆመው ነበር፡፡
ዊሊያም ሸክስፒር እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “መጥፎ ድርጊቶች ይነሳሉ/መሬት ለሰው ልጆች ዓይን ሁሉንም ነገር እስካሳየች ድረስ፡፡“
በአፍሪካ እና በሌላውም ዓለም ረሀብን፣ የምግብ ንጥረ ነገር እጦትን እና ድህነትን ለመቀነስ እና “የወደፊቱን ትውልድ የመመገብ ተነሳሽነት” የሚለውን ፕሮግራምዎን አደንቃለሁ፡፡
ኮፊ አናን እንዲህ ብለው ነበር፣ “የወደፊቱን ትውልድ መመገብ የሚሉት ፕሮግራሞች ፈጠራን በመደገፍ፣ የቴክኒክ የእውቀት ድጋፍ በመስጠት እና ለአነስተኛ ገበሬዎች ምርቶች የገበያ ዕድሎችን በመፍጠር ጉልህ ሚናን ይጫወታሉ፡፡“ ኮፊ ትክክል ናቸው፡፡
ሆኖም ግን “ወንዶች እና ሴቶች በዳቦ ብቻ አይኖሩም” ከሚለው ቅዱስ አባባል ጋር ከእኔ ጋር እንደሚስማሙ እርግጠኛ ነኝ፡፡
እ.ኤ.አ ሰኔ በ2009 እንዲህ ብለው ነበር፡
አሜሪካ ሰላማዊ የሆነ የምርጫን ውጤት በማንሳት ትክክለኛው ይኸ ነው እንደማትል ሁሉ ለእያንዳንዱም ሰው የሚሻለው የትኛው ነው የሚለውን ለማወቅ አትፈልግም፡፡ ሆኖም ግን ሁሉም ህዝቦች ለአንድ ነገር ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው የማይናወጥ እምነት አለኝ፡ አዕምሮ የፈቀደውን የመናገር መብት እና እንዴት እየተዳደረ እንዳለ ሀሳብ የመስጠት፣ በህግ የበላይነት ላይ እምነት የመጣል እና ሁሉንም ፍትሀዊ በሆነ መልኩ የማስተዳደር፣ ግልጽነት ያለው መንግስት እና ከህዝቡ ዘንድ ስርቆት የማይፈጽም እና አንድ ሰው እንደመረጠው የመኖር መብት ሊከበርለት ይገባል፡፡ እነዚህ ሁሉ የአሜሪካ ሀሳቦች አይደሉም፡፡ ሰብአዊ መብቶች ናቸው፡፡ ለዚህም ነው በየትም ቦታ እነዚህን እየደገፍን ያለነው፡፡
የአፍሪካ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች የአፍሪካ የወዲፊት አለኝታዎች ያለምንም ገደብ ነጻነትን ይፈልጋሉ-የመናገር ነጻነት፣ የማምለክ ነጻነት፣ የመሰብሰብ እና ቅሬታዎችን የማቅረብ ነጻነት ይፍልጋሉ፡፡
የአፍሪካን ወጣት እዕምሮ እና ሰውነትን ለማጥፋት ማሰብ እና ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ አስቸጋሪ ነገር ነው፡፡
በአሁኑ ጊዜ ምንም ዓይነት የመነጋገሪያ ጉዳዮች ጋር ግንኙነት ከለሌላቸው ነገሮች ጥቂት የግሌን ቃላት ለማለት ወደድሁ፡፡
ምናልባትም እነዚህ ቃላት በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ የሰብአዊ መብቶች ውትወታ ላይ ስላለኝ አቋም የተወሰኑ ምልከታዎችን ሊሰጡዎት ይችላሉ፡፡
እ.ኤ.አ በ1960ዎች ሁለተኛ አጋማሽ እና በ1970ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ ዩኤስ አሜሪካ ከመጡት ሁለተኛ ዙር ወጣቶች መካከል አንዱ ነበርኩ፡፡
የእርስዎ አባት የአፍሪካ ህዝቦች የመጀመሪያውን ዙር ቅኝ ያለመገዛት ትግል ካካሄዱ በኋላ እና የከፍተኛ ትምህርታቸውን በዩኤስ አሜሪካ አጠናቅቀው እ.ኤ.አ በ1960ዎች ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ወደ አፍሪካ ከተመለሱት የመጀመሪያው ዙር የአፍሪካ ወጣቶች መካከል ነበሩ፡፡
ለከፍተኛ ትምህርቴም የፖለቲካ ሳይንስ እና ሕግን ለማጥናት መረጥኩ፡፡ በተለይም ደግሞ በአሜሪካ የሕገ መንግስታዊ ሕግን ህልዮት፣ ተግባር እና መንግስት ላይ ልዩ ፍላጎት አደረብኝ፡፡
የእርስዎ አባት ኢኮኖሚክስ ካጠኑ በኋላ ወደ ኬንያ ተለመሱ፡፡
የመጨረሻ ዲግሪዎቼን ከተቀበልኩ በኋላ እዚያው አሜሪካ ለመቅረት መረጥኩ፡፡
ከዚያ በኋላ መንግስት የእራሱን ሕዝብን በሚፈራበት ሀገር እንጅ ህዝብ የእራሱን መንግስት በሚፈራበት ሀገር መኖር እንደማልችል አስቀድሜ ተገነዘብኩ፡፡
እንግዲህ ያ ዓይነቱ ሁኔታ እንደ ጀፈርሰን ዓይነት ዴሞክራት ሙስናን፣ ተከታታይነት ባለው ሁኔታ ክብርን መጠየቅን፣ ለሁሉም ዜጎች እኩል መብቶችን ማጎናጸፍን እና ሌሎችንም በማካተት ጽናት ያለው ተቃውሞዬን ማቅረብ ጀመርኩ፡፡
እ.ኤ.አ ግንቦት 2009 እንዲህ ብለው ነበር፡
እንደተማሪ ሕገ መንግስትን አጥንቻለሁ፣ እንደ መምህር አስተምረዋለሁ፣ እንደ ሕግ ባለሙያ እና ሕግ አውጭ አካል በዚሁ ሙያ እገዛለሁ፡፡ እንደ ዋና የጦር አዛዥ እና እንደ ዜጋ ሕገ መንግስቱን ለመንከባከብ፣ ለመጠበቅ እና ለመከላክል ቃል ገብቻለሁ፡፡ ምንም ይሁን ምን ለሕገ መንግስቱ መርሆዎች መከበር ፍጹም በሆነ መልኩ ጀርባችንን ሳናዞር በጽናት እና በአይበገሬነት እንጠብቀዋለን፣ እንንከባከበዋለን፡፡
ይህንን ስናገር እንዲሁ በዘፈቀደ እንደ ሀሳባዊ በመሆን አይደለም፡፡ የተከበሩ እሴቶቻችንን እንደ ዓይናችን ብሌን የምንከባበከባቸው ጥሩ ነገር በመሆናቸው ምክንያት ብቻ አይደለም፣ ሆኖም ግን ሀገራችንን ጠንካራ ሆና እንድትቀጥል ስለሚያግዙ እና እኛም ደህንነታችን ተጠብቆ እንድንኖር ስለሚያስችሉን ነው፡፡ የእኛ እሴቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ- በጦርነት እና በሰላሙ ጊዜ፣ ደስታ በተንሰራፋበት እና ብጥብጥ እና ሀዘን በገሰበት ዘመን ሁሉ ብሄራዊ ሀብቶቻችን እና የኩራት ምንጮቻችን እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ለእሴቶቻችን ታማኝ መሆን አሜሪክ ከትንሽ እና ከተበጣጣሰች ቅኝ ተገዥ ሀገር ወደ ጠንካራ እና የዓለም ልዕለ ኃያል የተባበረች ሀገርነት እንድትሸጋገር አስችሏታል፡፡
እኔም እንደዚሁ የሕገ መንግስትን ሕግ አጥንቻለሁ፣ እያስተማርኩትም፣ እየተገበርኩትም ነው፡፡ ለእርሱ መርሆዎች ተግባራዊነት በምንም ዓይነት መንገድ አላጎበድድም፣ ግንባሬንም አላጥፍም፡፡
ለእኔ ሕገ መንግስቱን መያዝ ቀላል የሆነ ሀሳባዊ ነገር ነው፡፡ ጠለቅ ተብሎ ሲታይ የማይበገር ጽናትን የተላበስኩ ሀሳባዊ ኢትዮ- አሜሪካዊ ነኝ፡፡
ስለሆነም ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በየሳምንቱ አንድም ሳምንት ሳላጓድል በአሜሪካ የሰብአዊ መብቶች ጥበቃ ሰነዱ ላይ የሰፈሩትን የአሜሪካንን እሴቶች እያስተማርኩ፣ እየሰበኩ እና እተገበርኩ ለመዝለቅ ችያለሁ፡፡
እ.ኤ.አ በ2009 ባደረጉት መሳጭ ንግግርዎ ላይ እንዲህ ብለው ነበር፣ “ልንዋጋላቸው እና ልንጠብቃቸው በተቀመጡት ምርጥ ሀሳቦች ላይ መደራደር ስንጀምር ያን ጊዜ እራሳችንን እናጣለን፡፡ እናም እነዚያን ሀሳቦች ልናከብራቸው፣ ልንጠብቃቸው እና ልንዋጋላቸው የሚገባን ደህና ጊዜ በገጠመን ወቅት ብቻ ሳይሆን ፈታኝ እና አስቸጋሪ በሆነበት ጊዜ ጭምር መሆን አለበት፡፡“
የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይን አመራሮች በአዲስ አበባ በሚገናኙበት ጊዜ የአሜሪካንን ምርጥ ሀሳቦች ለድርድር ማቅረብ የለብዎትም፣ እናም ለሁሉም ነገር ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው በኢትዮጵያ በይፋ በሚታወቀው እና በስውር እስር ቤቶች ታስረው በሚማቅቁ በሺዎች የሚቆጠሩ የፖቲካ እስረኞች ጉዳይ ላይ ኬረዳሽ ብለው ወደ አሜሪካ እንዳይመለሱ፡፡
አይበገሬዎቹ ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ አብርሃ ደስታ፣ በእስር ላይ የሚገኙትን የዞን 9 ጦማሪያን እና በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን ከእስር ቤት ለማስፈታት ጥረት እንደሚያደርጉ ተስፋ አለኝ፡፡
ከጥቂት ቀናት በፊት በ6 የኢትዮጵያ የሙስሊም እርቅ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ በስምንት ምሁራን፣ በሁለት ጋዜጠኞች፣ በአንድ የኪነ ጥበብ ባለሙያ እና በአንድ ተማሪ የአሸባሪነት ድርጊት በመጸም፣ ደባ በመሸረብ እና በማነሳሳት የሚል ክስ የመሰረተባቸው መሆኑ ተዘግቧል፡፡ እነዚህ ዜጎች ያለምን ፍትህ በአምባገነኖች የዘፈቀደ እስራት እ.ኤ.አ ከ2012 ጀምሮ በእስር ቤት ውስጥ በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
እነዚህ መንግስት ከአምላክ ስራ እራሱን አስወጥቶ በሌላው ስራው እንዲሰማራ በማለት ሕገ መግስታዊ መብታቸውን በመጠቀማቸው ብቻ ሰብስቦ ወስዶ በእስር ቤት በማጨቅ መከራ እና ስቃይ እየፈጸመባቸው ያሉት ወጣት የኢትዮጵያ ሙስሊም የእርቅ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እንዲፈታ ግፊት እንደሚያደርጉ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
እ.ኤ.አ ከየካቲት 2007 ጀምሮ እርስዎ ዕጩ ፕሬዚዳንት ሆነው የምረጡኝ ቅስቀሳዎን ሲያካሂዱ በነበረበት ጊዜ እኔ የእርስዎ ቁጥር 1 ደጋፊ ነበርኩ፡፡
ላለፉት በርካታ ዓመታት የእርስዎን መመረጥ በማጉላት በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮ-አሜሪካውያን ሁሉ ድምጻቸውን ለእርስዎ እንዲሰጡ በርካታ ትችቶችን በመጻፍ የገንዘብ ማሰባሰብ እና የድምጽ ድጋፍ ሳሰባስብ ቆይቻለሁ፡፡
የእርስዎን ፖሊሲዎች ጠንካራ በሆነ መልኩ ስከላከል ቆይቻለሁ፣ እንዲሁም በእርስዎ ላይ በመገናኛ ብዙሁን የሚሰነዘሩትን ጎጂ የሆኑ ትችቶች የተከታተልኩ ሳመከን ቆይቻለሁ፡፡
ባለፈው ዓመት በኢትዮጵያ ላይ እየተከተሏቸው ያሉትን ፖሊሲዎች በማየት በጣም እንቆቅልሽ ስለሆኑብኝ “በፕሬዚዳንት ኦባማ ላይ ኩራት ማሳደሬ ለምን እንዳሳፈረኝ/Why I am Ashamed to be Proud of President Obama“ በሚል ርዕስ ትችት ጽፌ ነበር፡፡
በእርስዎ የመጨረሻዎቹ ሁለት የፕሬዚዳንትነት ስልጣን ዓመታት ጊዜ ውስጥ እንደገና በእርስዎ ላይ ኩራት ይሰማኝ እንደነበረ ከመግለጽ ውጭ ሌላ ፍላጎት አልነበረኝም፡፡
በእርስዎ አድራሻ የተጻፉ እና ያልተፈተሹ 10 ቁርጥራጭ የግንኙነት ወረቀቶችን በየቀኑ የማንበብ ልምዱ እንደነበርዎት ከሆነ ምንጭ ማነበቤን እያስታወስኩ ያ ልምድ ለእርስዎ በጣም ጠቃሚ የሆነ የየዕለት ንባብዎ አድርገው እንደያዙት ተገንዝቢያለሁ፡፡
ከእነዚህ ደብዳቤዎች ውስጥ የእኔ ደብዳቤ 10ኛው ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ፡፡
ይህ አሁን የጻፍኩልዎ ደብዳቤ በብዙ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ድምጽ የሌላቸው እና ድምጾቻቸው ጸጥ እንዲሉ በኃይል ታፍነው የሚገኙትን ኢትዮጵያውያን ጥልቅ ስሜት ያካተተ መበመሆኑ እንድሚያነቡት ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
በየዕለቱ በአድራሻ ለእርስዎ በቀጥታ የሚጎርፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ደብዳቤዎችን እያጣሩ ወደ እርስዎ የሚመሩት ሰዎች የእኔን ደብዳቤ ድምጽን ከፍ አድርጎ የተጻፈ እና አስፈሪ የሆነ፣ በሰፊው የተዘጋጀ፣ ለእራስ ክብር የሰጠ፣ በእራስ ክብር መስጠት ላይ ትኩረት ያደረገ፣ በእራስ ተነሳሽነት እራስን ሰይሞ የተጻፈ፣ በስህተት ላይ የሚጓዝ የሕገ መንግስት የህግ ፕሮፌሰር እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋች በማለት ለእርስዎ እንዳይደረስ ሊያደርጉ ይችላሉ ብዬ አስባለሁ፡፡
ለእርስዎ የጻፍኩት ጽሁፍ ይዘት ብዙም ትርጉም ላይሰጥዎ ይችል ይሆናል ምክንያቱም የሸክስፒርን አባባል ልዋስና በአንድ ነገሮች ሁሉ እንቆቅልሽ እና እጅግ አስቸጋሪ በሆኑበት ሰው የተጻፈ ስለሆነ በተወለደባት ሀገር እና በወገኖቹ ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ በማየት ከቀናት በኋላ ያመነዥከዋል ሊሉ ይችሉ ይሆናል፡፡
ምናልባትም የእኔ ደብዳቤ እጅግ በጣም እረዥም እና በቀጥታ ጣቶችን በግልጽ ወደ ጥፋተኛው የሚሰነዝር ነው፡፡
ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ እንዳሉት በገሀነም በጣም ከፍተኛው የሆነው አኮማታሪ ሙቀት የሚቀመጥላቸው “ከፍተኛ የሆነ የሞራል ኪሳራ በተከሰተበት ጊዜ ገለልተኛ ሆነው በተቀመጡት ሰዎች ላይ ነው” በሚለው የክርክር አመክንዮ በመገፋፋት ነው፡፡
ባለፉት ዘጠኝ ዓመታት ኢትዮጵያን በገጠማት የሞራል ኪሳራ ላይ ገለልተኛ ሆኘ አልተቀመጥኩም፡፡
እ.ኤ.አ ከ2006 ጀምሮ በየሳምንቱ ሰኞ ከትክክለኛ የታሪክ ጎን በኩራት በመቆም ትግሌን ቀጥዬ እገኛለሁ፡፡
ባልሳሳት “የተስፋ ጥንካሬ” በሚለው በእርስዎ መጽሐፍ ላይ ይመስለኛል የተመለከትኩት እንዲህ ይላል፣ “ለእሴቶቻችን ዋጋ የማንከፍል ከሆነ በእርግጥ በእነዚህ እሴቶች ላይ እምነት አለን ወይ በማለት እራሳችንን መጠየቅ“ ይኖርብናል፡፡
የእኔ ጓደኞች እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ፣ ውብሸት ታዬ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ የዞን 9 ጦማሪያን፣ ወጣት የሙስሊሞች እና ሌሎችም በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ለመርሆዎቻቸው ሲሉ ከፍተኛ የሆኑ ዋጋዎችን በመክፈል ላይ ይገኛሉ፡፡
እ.ኤ.አ መስከረም 2014 በኢትዮጵያ ላለው ገዥ አካል የልዑካን ቡድን እንዲህ ብለው ነግረዋቸው ነበር፡
ስለሆነም ስለሲቪል ማህበረሰቡ እና ስለመንግስት የመነጋገር ዕድል ይኖረናል፣ እናም ኢትዮጵያ እያስመዘገበችው ያለውን ዕድገት ምሳሌነት እንዴት በማድረግ ወደ ሲቪል ማህበረሰቡ ማስተላለፍ እንደምንችል እና በአፍሪካ አህጉር በአጠቃላይ ጥረቶቻችንን በማስፋት እና በማጠናከር ዴሞክራሲን ማጎልበት እና ሁሉንም ለፖለቲካው ጥሩ ያልሆኑትን ነገሮች ሁሉ ለኢኮኖሚው ጥሩ ሊሆኑ እንደሚችሉ ማሰብ መቻል ነው፡፡
እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015 የሲቪል ማህረሰብ ድርጅቶች በነጻ መንቀሳቀስ እንዲችሉ እና በኢትዮጵያ የዴሞክራ ስርዓት ግንባታው እንዲሰፋ ለማድረግ ከህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ አመራሮች ጋር ተገናኝቶ የመወያየት ዕድል ይግጥመዎታል ብዬ አስባለሁ፡፡
እ.ኤ.አ ሀምሌ 2009 እንዲህ ብለው ነበር፣ “ታሪክ ከእነዚህ ከአፍሪካ ጀግኖች ጎን እንጅ መፈንቅለ መንግስት አድርገው ወይም ደግሞ በስልጣን ላይ ለመቆየት ሲሉ ሕገ መንግስትን ለውጠው ከሚቀርቡት አምባገነኖች ጎን አይደለም፡፡ አፍሪካ ጠንካራ ሰዎችን አትፈልግም፣ የምትፈልገው ጠንካራ ተቋማትን ነው፡፡“
በመጀመሪያው የመክፈቻ ንግግርዎ ላይ እንዲህ ብለው ነበር፣ “በሙስና እና በመታለል ስልጣንን የተቆጣጠሩ እና ሰላማዊ አመጸኞችን ጸጥ ለማድረግ ጥረት የሚያደርጉ ሁሉ ትክክለኛ ባልሆነው ታሪክ ጎን የተሰለፋችሁ መሆናችሁን ማወቅ አለባችሁ፣ ሆኖም ግን የጨባጣችሁትን ቡጢ ለሰላም ስትሉ ከዘረጋችሁ እጆቻችንን ዘርግተን እንቀበላችኋለን፡፡“
እ.ኤ.አ ሀምሌ 2015 ኢትዮጵያን በሚጎበኙበት ጊዜ ሀገሪቱን እ.ኤ.አ በ2009 ባደረጉት ማስጠንቀቂያ መሰረት በመግዛት ላይ ያለው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ሀገሪቱን በማን አለብኝነት በማተራመስ ላይ የሚገኝ የወሮበሎች ስብስብ እርስዎ ጠንካራ የአፍሪካ ሰዎች አያስፈልጉም ያሉትን ሆኖ ያገኙታል፡፡ እርስዎ እንደሰጡት ማስጠንቀቂያ ሁሉ እነዚህ የወሮበላ ስብስቦች ስልጣንን የያዙት በነጻ እና በዴሞክራሲያዊ ምርጫ ሳይሆን በሙስና እና በማታለል ሰላማዊውን ህዝብ ጸጥ በማድረግ እና በጠብመንጃ ኃይል በመፈንቅለ መንግስት ነው፡፡
ላለፉት ስድስት ዓመታት ከወያኔው ቡድን ጋር በመደራደር ላይ እያሉ የጨበጡትን ቡጢ ፈትተዉት ነበር ፡፡ ምናልባትም በአሁኑ ጊዜ የተጨበጠውን ቡጢ በመግዛት ላይ ያለው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ማሳየት ያስፈልጋል።
በአዲስ አበባ ከህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ጠንካራ ሰዎች ጎን ቆመው መታየትዎ ለእኔ እና አኔን ለመሳሰሉት በርካታዎቼ ዜጎች የሚያደናግር እና በከፍተኛ ደረጃ የሚሰማ ቁስል ነው፡፡
በአዲስ አበባ ከሚገኙት ጠንካራ ሰዎች ጋር የእርስዎን ፍቶግራፎች ስመለከት በከፍተኛ ሀዘን በመዋጥ ዓይኖቼ የቅበዘበዛሉ፣ የፊቶቼ ገጽታም ይለዋወጣሉ፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ሁኔታ እኔም እንዳለየ አይቸ ጆሮ ዳባ ልበስ እለዋለሁ፡፡
ከህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ዘራፊ አምባገነኖች ጎን በአዲስ አበባ ቆመው ሲታዩ በታሪክ ጥላ ላይ ቆመው እንደሚታዩ ይቁጠሩት፡፡
አንድ ሰው በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ጥላዎች በጸሐይ መስታወት እራሳቸውን ሊያዩ አይችሉም“ ወይም ደግሞ በታሪክ መስታወት ልበለው?
የታሪክ ተመራማሪዎች እርስዎ በአፍሪካ እያወጧቸው ስላሉት ፖሊሲዎች እና እያደረጓቸው ስላሏቸው ጥረቶች አንድ ቀን ይጽፉት ይሆናል፡፡ ሰለእርስዎ ትሩፋት እና ምን እንደሰሩ እና ምን እንዳልሰሩ ይጽፉታል፡፡
ሁሉም ስለዚያ የሚደረገው ነገር ብዙ ፋይዳ ያለው ነገር ይኖረዋል ብዬ አልጠብቅም፡፡
ፋይዳ የሚኖረው ነገር ቢኖር እ.ኤ.አ በ2009 አክራ ላይ በትልቅ የመቆሚያ መድረክ ላይ ሆነው አንስተውት ለነበረው የታሪክ ጥያቄ እንዴት አድርገው ከህሊናዎ ጋር በማስታረቅ መመለስ እንዳለብዎት ከማሰቡ ላይ ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ በአፍሪካ በተለይም በኢትዮጵያ በሚያራምዱት ፖሊሲ ላይ ከትክክለኛው ታሪክ ጎን ቆመዋልን?
ጳጳስ ዴስሞንድ ቱቱ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ኢፍትሀዊነት ሲፈጸም ዝም ብለህ በገለልተኝነት የምትመለከት ከሆነ ከጨቋኙ ጎን መሰለፍን መርጠሀል ማለት ነው፡፡
የዝሆን እግር ባይጧ ጅራት ላይ ረግጦ ቆሞ ከሆነ እና ያንን እየተመለከትክ በገለልተኝነት ዝም የምትል እና በእግሯ ላይ መቆሙን የማትናገር ከሆነ አይጧ የአንተን ገለልተኝነት የምታደንቀው አይሆንም፡፡“
እንደዚሁም ሁሉ ኢትዮጵያውያንን አንገታቸውን በቦት ጫማ ረግጠው ለጣረሞት ዳርገዋቸው ካሉት ጨቋኝ አምባገነኖች ጋር ጥቂት ፎቶግራፎችን ተነስተው ሆኖም ግን ምንም ነገር ሳይናገሩ ዝም ብለው በገለልተኝነት ወደመጡበት የሚመለሱ ከሆነ ኢትዮጵያውያን የእርስዎን ገለልተኝነት እንደማያደንቁልዎት በድፍረት ልነግርዎት እወዳለሁ፡፡
እ.ኤ.አ ጥቅምት 2011 ታላቁ ወግ አጥባቂ እና የብሔራዊ ጉዳዮች ተንታኝ ሴናተር ቴድ ክሩዝ እንዲህ ብለው ነበር፣ “የፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጠንካራ ትሩፋት ለነጻነት ከቆመው ከአዲሱ ትውልድ የመጡ መሪ መሆናቸው ነው፡፡“ ሴናተር ክሩዝ ይህንን ሲሉ መሰረት እንዳላቸው ተስፋ አለኝ፡፡
በአፍሪካ የእርስዎ ብቸኛው ትሩፋት ለነጻነት ከቆመው ከአዲሱ ትውልድ የመጡ የመሆንዎ ጉዳይ ብቻ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
የአፍሪካን ወጣት እና የአዲሱን ትውልድ አመራሮች ባሰቡ ቁጥር አሮጌዎቹን የአፍሪካ መሪዎች ትውልድ እንደማይረሷቸው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡
እርስዎም እንደሚያውቁት ሁሉ ታላላቆቹ የኢትዮጵያ መሪዎች ባለፉት ጥቂት ምዕተ ዓመታት የአውሮፓን ተስፋፊ ቅኝ ገዥዎች ተደጋጋሚ ወረራ በመመከት የኢትዮጵያን ነጻነት ሳያስደፍሩ ጠብቀው ከሶስት ሺ ዓመታት በላይ ነጻነቷን ጠብቃ እንድትቆይ አድርገዋል፡፡
የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን እንደ ቅርጫ ስጋ ለመቀራመት በማሰብ አድርገውት ከነበረው የበርሊን ጉባኤ ከተካሄደ ሁለት ዓመታት በኋላ እ.ኤ.አ በ1896 በአድዋ ጦርነት ዳግማዊ ምኒልክ እስካፍንጨው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ ታጥቆ የመጣውን የሰለጠነ የጣሊያንን ወራሪ ኃይል ጋሻ እና ጦር እንዲሁም ቀስት እና ኋላቀር መሳሪያዎችን በመጠቀም አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ወራሪውን ጦር አሳፍረው በመመለስ የአፍሪካ ኩራት ሆነዋል፡፡
ንጉስ ምኒልክ ግዙፍ የሆነን እና በዘመናዊ የጦር መሳሪያ የተደራጀን የአውሮፓን ቅኝ ገዥ ሰራዊት ድል አድርገው ያንበረከኩ በአፍሪካ ታሪክ የመጀመሪያው አፍሪካዊ መሪ ናቸው፡፡
በታሪካዊ መሪዎቿ ብርታት እና ጀግንነት ምክንያት አንድም የአውሮፓ ኃያል ኢትዮጵያን ቅኝ ግዛት ማድረግ ሳይቻለው ቀርቷል፡፡
ዳግማዊ ምኒልክ በቅኝ ግዛት ወራሪው የኢጣሊያ ሰራዊት ላይ አንጸባራቂ የሆነ ድል ካስመዘገቡበት ጊዜ ጀምሮ ኢትዮጵያ የተስፋ ቀንዲል እና የክብር ምልክት እንዲሁም ለመላ የአፍሪካ እና ለዲያስፖራ አፍሪካውያን ህዝቦች የክብር እና የኩራት ምንጭ ሆና ትገኛለች፡፡
አሁን ለጉብኝት አዲስ አበባ በሚገቡበት ጊዜ ከዳግማዊ ምኒልክ ሐውልት በመሄድ ለክብራቸው ሲሉ በሐውልቱ ስር እቅፍ አበባ ሊያሰቀምጡ ይችላሉን?
ኢትዮጵያ 13 ወራት ሙሉ የጸሐይ ብርሀን ያላት ሀገር ሆና እንደሚያገኟት እርግጠኛ ነኝ፡፡
ኢትዮጵያውያን እንግዳ ተቀባዮች፣ ሰው አክባሪዎች፣ ትሁቶች፣ ስህተቶቻቸውን አምነው የሚቀበሉ ጨዋዎች ሆነው ያገኟቸዋል፡፡
ሚስተር ኦባማ ታላቅ የኢትዮጵያ ጉዞ ይሁንልዎ፡፡
የሰው ዘር መገኛ ወደሆነችዋ ሀገር የሚያደርጉት ጉዜ የደስታ እና የተቃና ይሁልንዎ እላለሁ፡፡
ለመዘመር ስነሳ ሁሉም ትናንሾቹ ወፎች በለሆሳስ ዘመሩና በፍጥነት ተነስተው ከከተማው እንደበረሩ ተነግሮኛል፡፡
ሆኖም ግን ያ ድርጊት እንዲህ የሚለውን ጥንት የባርነት ስቃይ በነበረበት ዘመን በሚዘመረው መዝሙር “እንደ ሙሴ ተጓዝ፣” በሚለው መልካም ጉዞ እመኝልሀለሁ፡፡“
በሙሴ አኳኋን ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀህ ግባ፡፡
የእኔ ህዝቦች ይለቀቁ በማለት ለሁሉም ፈርኦኖች ንገር፡፡
እንደዚህ ተጨቁነው እስከመቸም አይቆዩ፡፡
ህዝቦቸን ልቀቅ እና ይሂዱ፡፡
አምላክም ፈቀደ፣ ሂዱ ሙሴን ተከትላችሁ ወደ ኢትዮጵያ ሂዱ አለ፡፡
ህዝቦቼ እንዲለቀቁ ለሁሉም ፈርኦኖች ንገሯቸው፡፡
እነሆ ሙሴም ወደ ኢትዮጵያ ምድር ሄደ፡፡
ህዝቦቸ እንዲሄዱ ለቀቋቸው፡፡
ሁሉም ፈርኦኖች እንዲያውቁት አደረገ፡፡
ህዝቦቸ እንዲሄዱ ልቀቋቸው፡፡
አዎ አምላክ እንዲህ አለ፣ ዘምሩ ከሙሴ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ምድር ሂዱ፡፡
ህዝቦቸ እንዲሄዱ ልቀቋቸው፡፡
ህዝቦቼ እንዲሄዱ ለሁሉም ፈርኦኖች ንገሯቸው፡፡
ፕሬዚዳንት ኦባማ ህዝቦቼን እንዲለቋቸው ለህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ፈርኦኖች ይንገሩ፡፡
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!
ሀምሌ 14 ቀን 2007 ዓ.ም
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8920#sthash.OcmM5n2X.dpuf