አንድ ለጊዜዉ ማንነታቸዉ እንዲገለጽ ያልተፈለገ ከፍተኛ ወታደራዊ የወያኔ ባለስልጣን መሰወራቸዉና ወደ አርበኞች ግንቦት 7 መቀላቀላቸዉ በወያኔ በኩል ከባድ እራስ ምታት ፈጥሯል። የእኚሁን ባለስልጣን ጉዳይ በተመለከተ አርበኞች ግንቦት 7 ምንም የሰጠዉ መግለጫ ባይኖርም በወያኔ በኩል ግን ያለዉ የደህንነት ክንፍ አጣርቻለዉ ብሎ መረጃዉን ማሳለፉን ለመረዳት ተችሏል።
በተያያዘ ዜና ከአርበኞች ግንቦት 7 የጥቃት ማግስት ጀምሮ የተለያዩ የነጻነት ሐይሎች ጦርነት እያካሄዱ እንደሚገኙ ከወያኔ ወታደራዊ ግንኙነት ክፍል የወጣ መረጃ አመለከተ። መረጃዉ እንደሚጠቁመዉ ኦነግና የኦጋዴን ነጻ አዉጪ ሀይሎችም ተመሳሳይ የሆነ ሽምቅ ዉጊያ ተያይዘዉታል። የአሜሪካዉ ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማን መምጣት ምክንያት ባደረገ መልኩ ኢትዮጵያ ምንም አይነት የጦርነት አዋጅ እንደማታዉጅ ወታደራዊ ደህንነቱ ለየ እዝ ባለስልጣናቱ ሚስጢራዊ ትዕዛዝ በማሳለፉ የእዝ አመራሮችን ያበሳጨ ነዉ ተብሏል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የወያኔ ንብረት የሆነዉን በጎንደርና በተለይም አዘዞ ላይ የሚገኘዉን ሱር ኮንስትራክሽን የደመሰሰና ያቃጠለ ሲሆን በቅርበት የሚገኙ ወታደራዊ ተቋማት የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸው ይታወሳል
አሰግድ ታመነ
- See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8977#sthash.82Vx139t.dpuf
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar