July 27,2015
ኢ/ር ይልቃል መንግስት ለፕሬዝደንት ኦባማ ያዘጋጀው የእራት ግብዣ ላይ እንደማይገኙ አስታወቁ
• ‹‹ኦባማ ኢህአዴግን በዴሞክራሲያዊ ምርጫ የተመረጠ ነው ማለታቸው የኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ግንባታ ላይ ውሃ የሚቸልስ ነው››
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የኢትዮጵያ መንግስት ዛሬ ሀምሌ 20/2007 ዓ.ም ምሽት 1፡00 ሰዓት ላይ ቤተ መንግስት ውስጥ ለአሜሪካው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ የሚያደረገው የእራት ግብዣ ላይ እንደማይገኙ ለነገረ ኢትየጵያ ገልጸዋል፡፡ የራት ግብዣው ላይ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ጥሪ የተደረገላቸው ኢ/ር ይልቃል ‹‹ አሸባሪ አድርጎ የሚቆጥረን ኢህአዴግ ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ ሲመጡ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ለማስመሰልና ዕውቅና ለማግኘት ያደረገው በመሆኑ አልገኝም›› ብለዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል አክለውም ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ ጭቆና እና ስቃይ ውስጥ ባለበት በአሁኑ ወቅት ኢህአዴግ የጠራው የቅንጦት ግብዣ ላይ መገኘት የህዝቡን ሰቆቃ እንደመርሳት እቆጥረዋለሁ›› ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል የአሜሪካው ፕሬዝደንት ባራክ ኦባማ መግለጫ በሚሰጡበት ወቅት ኢህአዴግ በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነው ማለታቸው ቅር እንዳሰኛቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ኢህአዴግን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠ ነው ማለት የሰላማዊ ታጋዮችን ስቃይ የሚክድና ለአምባገነኖች ይሁንታ የሚሰጥ ነው›› ሲሉ የፕሬዝደንት ኦባማን ንግግር ነቅፈውታል፡፡ ፕሬዝደንት ኦባማ የጠበንጃ ትግልን አለመደገፍን ለመግለፅ የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንትን ጨምሮ ሌሎች የአሜሪካ ተቋማት ኢ-ዴሞክራሲያዊ መሆኑን አረጋግጠውት፣ መቶ ፐርሰንት ምርጫ አሸንፌያለሁ የሚልን ፓርቲ በዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንደተመረጠ መግለፃቸው እንዳሳዘናቸው ኢ/ር ይልቃል ገልጸዋል፡፡ በሌላ በኩል ኢ/ር ይልቃል በነገው ዕለት የአሜሪካ ኤምባሲና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በጋራ ያዘጋጁት ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar