mandag 30. desember 2013

ይድረስ ለብአዴን አባላት



በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ ወደ ባህር ዳር አቅንተው ነበር። መቸስ በረከት ስምዖን አማራ ካልሆንኩ ሞቼ እገኛለሁ ብሎ አለመንደሩ የአማራ ህዝብ መሪ እኔ ነኝ ብሎ ከአማራ ህዝብ ፊት ሲቆም አለማፈሩ ያስገርማል። አዲሱ ለገሰም እንደ በረከት ራሱን የአማራ ህዝብ ወኪል እኔ ነኝ ይላል።እነዚህ ሁሉት ህወሃት የሠራቸው ፍጡራን ባህር ዳር እንዲወርዱ ያደረጋቸው ብአዴን ተዳክሟል ተብሎ መታሠቡ ነበር።
እንግዲህ በእንበረከት የአስተሳሰብ ደረጃ ብአዴን ተዳከመ ሲባል ምን ማለት ይሆን?
ከጥቂት ደካማ ካድሬዎች በቀር ሌሎች እንደ ሰው ማሰብ የሚችሉ የብአዴን አባላት አገሪቷ እየሄደች ያለችበት መንገድ ያሳስባቸዋል። ህወሃት በአማራ ህዝብ ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ የሚያንገበግባቸው በርካታ ናቸው። ጉርፋርዳ እና ቤንሻንጉል አገራችሁ አይደለም ተብለው አማሮች ከኖሩበት ቀየ ተፈናቀለው ሜዳ ላይ የመውደቃቸው ድርጊት የእግር እሳት ሁኖ የሚለበልባቸው ብዙዎች አሉ። በዚህ ሁኔታ ያዘኑና የተቆጡ የብአዴን ካድሬዎች ድርጅቱ ቆሜለታለው የሚለው ፍትህ የት አለ፤ እኩልነትስ ከወዴት አለ፤ ኢትዮጵያስ የሁላችን አገር ነች የምትባለው መገለጫው ምንድ ነው እያሉ ይጠይቃሉ። እነዚህ ጥያቄዎች በካድሬዎች መካከል መመላለስ ሲጀምሩ ድርጅቱ ተዳክሟል ተብሎ ግምገማ ይካሄዳል።
በረከት እና አዲሱ ነፃነትን ሳያውቁ ራሳቸውን ነፃ አውጪ አድርገው የሚቆጥሩ የህወሃትን ዙፋን ከመጠበቅ የዘለለ ምንም ሚና የሌላቸው ያልሆኑትን ለመሆን የሚውተረተሩ ደካሞች መሆናቸውን እናውቃለን። እነዚህ ግለሰቦች ስለ አማራ ህዝብ ነፃነትና ክብር ይሠራሉ ብሎ ማሰብ የሚቻልበት ሁኔታ የለም። በረከትና አዲሱ በህዝብ መካከል እየኖሩ የህዝብ ፍቅር የሌላቸው፤ ከህዝቡ ጋር መኖርንም የማያውቁ፤ እለት ዕለት በሚፈጥሩት የፍርሃት አረንቋ ውስጥ የሚኖሩ እና ሠላም የራቃቸው ግለሰቦች ናቸው። ከእነዚህ ግለሰቦች እውነትን ፈልጎ ማግኘት፤ ነፃነትን ጠይቆ መቀዳጀት፤ ለፍትህ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የሚቻል አይደለም። የአማራ ህዝብ ከጉራፋርዳ እንዲወጣ የተደረገበት ምክንያት ምንድ ነው ተብለው ሲጠየቁ የጠባቦች ጥያቄ ብለው ይሳደባሉ። አያቶቻችን በደምና አጥንታቸው ያቆዩልንን ድንበር አፍርሳችሁ ለባእዳን ለምን ትሰጣላችሁ ሲባሉ የጦርነት ናፋቂ ጥያቄ እያሉ ይዘባበታሉ። እንደምን ሁኖ ከሁለት ሚሊዮን በላይ አማራ ከቁጥሩ ጎድሎ ተገኘ ሲባሉ የትምክህተኞች ወሬ እያሉ ይሳለቃሉ። አዎን እነበረከት ስምዖን የሚፈልጉት ዜጎች ስድባቸውን ተሸከመው እንዲኖሩላቸው እንጂ እውነትን፤ ፍትህን እና እኩልነትን እንዲጠይቁ አይደለም።
የሰሞኑ የባህር ዳር አስቸኳይ ስብሰባ ምክንያትም በብአዴን ካድሬዎች መካከል የፍትህ፤ የነፃነት እና የእኩልነት ጥያቄዎች ሥር እየሰደዱ መምጣታችው ነው። በካድሬዎቹ መካከል እንደ እሳት ሰደደ እየተሰራጩ ላሉ የፍትህ፤ የነፃነት እና የእኩልነት እጦት ጥያቄዎች ከህወሃት መራሹ “መንግስት መሰል” አካል በቀላሉ መልስ ማግኘት የሚቻል አይደለም። ይሄ ቡድን ነፃነትን ሳያውቅ ነፃ አወጣኋችሁ ማለትን ብቻ የሚያውቅ፤ራሱ ለሠራው ህግ መገዛትን ሳይወድ ስለ ህገ-መንግስት የበላይነት የሚሰብክ፤ ራሱ ከሁሉ በላይ እኔ ነኝ ብሎ ሲያበቃ ስለ እኩልነት ለመስበክ የማያቅማማ የነውረኞች ስብሰብ ነው። በረከትና አዲሱም የዚህ ነውረኛ ቡድን አካል እንጂ የአማራ ህዝብ አካል ናቸው ለማለት ለአማራ ህዝብ የሠሩት በጎ ነገርን ፈልጎ ማግኘት አይቻልም።
የብአዴን ካድሬዎች ሆይ !
ብአዴን ከተመሠረተ በኋላ ከሁለት ሚሊዮን በላይ አማራ መጥፋቱን በፓርላማ ሪፖርት መደረጉን ሰምተችኋል።ለመሆኑ ከሁለት ሚሊዮን በላይ አማራ የት ጠፋ? በአገሪቷ ካሉ ብሄረ ብሄረሰቦች መካከል እንደምን ሁኖ የአማራ ቁጥር ብቻ ሊቀንስ ቻለ? ከአማራ ክልል ወጥተው በሌላ ክልል የሚኖሩ አማሮች ይሄ አገራችሁ አይደለም፤ ወደ አገራችሁ ሂዱ ተብለው የሚባረሩት ለምንድ ነው? ኢትዮጵያ አገራቸው ካልሆነች የእነዚህ አማሮች አገር ወደየት አለች? ከጉራፈርዳ እና ከቤንሻንጉል ተነቅለው ሜዳ ላይ እንዲወድቁ የተደረጉ አማሮች በደላቸው ምንድ ነው? ለነዚህ ጥያቄዎች አማራ ካልሆንን ሞተን እንገኛለን የሚሉት በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ መልስ አይሰጡም። እነርሱ የቆሙት በህወሃት “የትግራይ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት አማራ ነው” ተብሎ የተያዘውን እምነት በተግባር ለማስፈፀም እንጂ ለአማራ ህዝብ ደህንነት እንዳለሆነ ምግባራቸው ህያው ምስክር ነው።
ብአዴን ከተመሠረተ ዘመን ጀምሮ በአማራ ህዝብ ላይ የደረሰውን ግፍ እናውቃለን። የአማራን ቅስም መሰበር፤ ትምክህቱን ማስተንፈስ፤ ኢትዮጵያዊ ማንነቱን ማዋረድ የሚሉት የእነበረከት ስምዖን ዋነኛው መፈክሮቻቸው ናቸው።በዚህ መፈክር መሪነት ከሁለት ሚሊዮን በላይ አማሮች ጠፍተዋል፤ኢትዮጵያ አገራችሁ አይደለችም ተብለው ከጉራፈርዳ እና ከቤንሻንጉል ውጡ ተብለው ሜዳ ላይ ተጥለዋል። ከንግዱ አምባም ሳይቀር ቀስ በቀስ አማሮች እንዲጠፉ ተደርገው ሥፍራቸውን ለሌላ እንዲለቁ ሁነዋል። ከፕሮፌሰር አሥራት ጀምሮ ለአማራ ህዝብ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምልክት እና ጥሩ ምሳሌ ሊሆኑ የሚችሉ አማሮች ቀስ በቀስ እንዲጠፉ መደረጋቸውን በአይናችን አይተናል በጆሮአችንም ሰምተናል። ብአዴን የተባለው ድርጅት በአማራ ስም ቢቋቋምም አማሮችን ከውርደትና ከሚደርስባቸው በደል ሊታደጋቸው አልቻለም።እንዲያውም ግፉንና በደሉን ለማስፈፀም የተወከለ ድርጅት ሁኗል።
እንግዲህ የብአዴን ካድሬዎች ሆይ እናንተም ከበረክተ ስምዖንና ከአዲሱ ለገሰ ጋር ተሰልፋችሁ ህዝባችሁን ትወጉ ዘንድ አይገባም። ዙሮ መግቢያችሁ ዛሬ እንወክለዋለን ያላችሁት ግን ደግሞ በአሣር በመከራ ውስጥ ያለው ህዝብ እንጂ ሌላ ዙሮ መግቢያ እንደሌላችሁ እወቁ። የወከላችሁት ህዝብ ሲረገጥ የለም ህዝቤን አትበድሉ ማለት ይጠበቅባችኋል። አማራ ከቁጥሩ ጎደለ ሲባል ምን ሆኖ እንደጎደለ በመጠየቅ የችግሩን ምንጭ ማወቅ ሥራችሁ ነው። አማራ ወደ “አገርህ” ሂድ ተብሎ ከኖረበት ሲነቀል ኢትዮጵያ አገሩ ካልሆነች የአማራ አገሩ የት ነው ብላችሁ መጠይቅ አለባችሁ።
ዛሬ እናንተን ትምክህተኞች እያለ የሚገመግማችሁ በረከት ስምዖን አያሌው ጎበዜን አስነስቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንዲተካ አድርጓል። የአያሌው መሄድና የገዱ መምጣት ለአማራ ህዝብ ነፃነት እና ክብር የሚፈይደው አንዳችም ቁም ነገር የለም። አያሌውም ሆነ ገዱ ለቆሙለት ህዝብ ይቅርና ለራሳቸውም ክብር የሌላቸው ደካሞች መሆናቸው የታወቀ ነው። ለራሱ ክብር ያለው የህዝብ ወኪል እወክለዋለው የሚለው ህዝብ ከኖረበት ቀየ እየተነቀለ ሜዳ ላይ ሲጣል አይቶ ዝምታን አይመርጥም። አያሌውና ገዱ ከአማራ ህዝብ አብራክ ወጥተው ደሃውን አማራ በሙሉ ነፍጠኛ፤ ትምክህተኛ፤ ሌላም ሌላም እያሉ እየሰደቡ ለሳዳቢ አሳላፈው የሰጡ ደካሞች ናቸው። ካድሬ ሆይ ስማን! የገዱ በአያሌው መተካት የተዋረደውን ክብርህን አይመልሰውም። ያጣኸውን ነፃነት መልሶ አያቀዳጅህም። ለሱዳን ተቆርሶ የተሰጠውን በአያቶችህ ደምና አጥንት የቆየውን መሬትም አይመልስልህም። የብአዴን ካድሬዎች ሆይ ስሙ ለክብራችሁ፤ ለማንነታችሁ፤ ለነፃነታችሁ ቀናዒ እንድትሆኑ ሁኑ እንጂ የህወሃትን ትርፍራፊ የምትለቃቅሙ አትሁኑ።
በብአዴን ውስጥ ያላችሁ የንቅናቄያችን አባሎች ሆይ !!
የህወሃት ስንቅና ትጥቁ ጥላቻ መሆኑን ታውቃላችሁ። ህወሃት “አማራ የትግራይ ህዝብ ቀንደኛ ጠላት ነው” ብሎ የሚያምን ቡድን ነው። ከዚህ ቡድን ፍትህ፣ እኩልነትና ነፃነት ያለመስዋእትነት እንደማይገኝ መዘንጋት አያስፈልግም። እስከ አሁን የንቅናቄያችንን መሠረት ለማሲያዝ ያደረጋችሁት አስተዋፅኦ በቀላሉ የሚታይ አይደለም። በህወሃት የተነጠቀው ነፃነታችን፤ የተዋረደው ክብራችንና ማንነታችን በቀላሉ እንደማይመለስ መገንዘብ ይኖርብናል። ትግሉ መራራ የሚሆንበት ግዜ መጥቷል። ለነፃነትና ለማንነት የሚከፈል መሥዋእትነት ደግሞ አስፈላጊ መሥዋዕትነት ነው።ጥቂት ዘረኞች አንገታችንን አስደፍተው በማንነታችን ላይ ተሳልቀው፤ ህዝባችንን አጎሳቁለውና ረግጠው ሲገዙ በአይናችን እያየንና በጆሮአችን እየሰማን ተንጋለን ለመተኛት አልተፈጠርንም። እንዲህ ዓይነቱን ሥንፍና ከቀደሙት ከኩሮዎቹ አያቶቻችንና አባቶቻችን አልተማርንም።
በአውሬው መረብ ውስጥ ሁናችሁ የለውጥ ኃዋሪያ ለመሆን መነሳታችሁ የሚደነቅ ነው።የለውጥ ኃዋሪያነት ትልቅ ሸከም ያለው ነው።ጥላቻን ወደ ፍቅር የሚቀይር፤ ለይቅርታ ራስን ማዘጋጀት፤ ከግዜያዊ ጥቅም ይልቅ ትውልድን አሻግሮ የማየት ራዕይን የሚጠይቅ ነው። ህወሃት አገሪቷን እያፈረሰ ያለው ከፍቅር ይልቅ በጥላቻ ስለተሞላ፤ ከይቅርታ ይልቅ በበቀል ልቦና የሚመላለስ በመሆኑን፤ ትውልድን አሻግሮ ከማየት ይልቅ የስግብግብነት ስሜቱ ያየለበት ሆኖ በመገኘቱ ነው። ንቅናቄያችን ይህን ከመሰለ አገር አጥፊ አስተሳሰብ በላይ ነው። ንቅናቄያችን ሁል ግዜ ለይቅርታ የተዘጋጀ ልቦና አለው። ይሄ ሲባል ግን የበቀለኞችን ሠይፍ ለመመከት ራሱን አያዘጋጅም ማለት አይደለም። እንዲያውም ሰይፋችን ከእነርሱ ሠይፍ በላይ የሳለ መሆኑን ያውቁት ዘንድ እንወዳለን። ንቅናቄያችን ትውልድን አሻግሮ የሚያይ ባለ ረዥም ራዕይ ነው። እንደ ህወሃት ለዘረፋ የተሠለፈ፤ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል የሚል አይደለም። ዘራፊውንና እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይበቀል የሚለውን ሁሉ ነቅሎ ሥፍራውን ለማስለቀቅ ሳያቅማማ በፅናት የሚሠራ ነው።
በብአዴን ውስጥ ያላችሁ የንቅናቄው አባላት ሆይ!!
የገዱ በአያሌው መተካት የሚያመጣው ለውጥ የለም።አያሌው ሄደ ገዱ መጣ ሁለቱም ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ደካሞች ናቸው። ገዱ የነፃነትን፤የፍትህንና የእኩልነትን ዋጋ የሚያውቅ አይደለም። ገዱ ሲሊኩት ወደየት፤ ሲጠሩት አቤት ከማለት የዘለለ ለዚያች አገር ለውጥ የሚፈይደው አንዳችም ነገር እንደማይኖር እወቁ። ስለሆነም የተጀመረውን ትግል ከዳር ለማድረስ ሳታቅማሙ በፅናት ቁሙ። ፍርሃትን ግደሉት። ከፍርሃት አርነት የሚያወጣን ነፃነት፤ ፍትህና እኩልነት ብቻ ነው። እነዚህ ለሰው ልጆች መሠረታዊ ቁም ነገሮች በአገሪቷ ሰፍነው ዜጎች ሁሉ እፎይ እሰከሚሉ ድረስ የሚከፈለውን መሥዋ ዕትነት ለመክፈል ወደ ኋላ እንዳትሉ። በእኛም በኩል አስፈላጊውን መሥዋዕትነት ለመክፈል የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን። የጀመርነውንም ትግል ሳናቅማማ እና ሳናፈገፍግ እንቀጥላለን።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

lørdag 28. desember 2013

Esat special Public meeting in Bergen Norway part 1 and 2 Dec14 2013



በኖርዌ በርገን ከተማ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ  በርገን ቅርንጫፍ አዘጋጅነት በዴሴምበር 14, 2013 ዶ/ር ታደሰ ብሩ የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ስራ አስፈጻሚ አባል በተገኙበት ታላቅ ህዝባዊ  ስብሰባ ከኢሳት ቁጥር 1 እና 2 ይመልከቱ


fredag 27. desember 2013

በሳውድ አረቢያ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ውስጥ ዘረኝነትና ሙስና ተስፋፍቷል ተባለ


ኢሳት ከቆንስላው ባገኘው የውስጥ መረጃ በሃላፊነት ላይ የተመደቡት አምስቱ ዲፕሎማቶች በዘረኝነትና በሙስና ከመዘፈቃቸው ም በተጨማሪ ሊሴ ፓሴ ለማውጣት ወደ ቆንስላው የሚደውሉትን ስደተኞች በስብሰባ ሰበብ የሉም በማስባል ጉዳያቸውን እያስፈጸሙ እንደልሆነ ተመልክቷል። ከአንድ ወር በፊት ከ160 ሺ በላይ ህዝብ የተፈናቀለበትን ችግር ለማወቅ በቆንስላው የተገኙትና ከዲፕሎማቶች ውጭ ያሉ ሰራተኞችን ብቻ በመሰብሰብ ” የችግሩ ምንጭ ምንድነው በማለት?” የተወያዩት የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ ለዚህ ሁሉ ችግር መፈጠር መንስኤ በሆኑት ዲፕሎማቶች ላይ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረው የነበረ ቢሆንም እስካሁን የወሰዱት እርምጃ አለመኖሩ ታውቋል።

“የመኖሪያ ፈቃድ የላችሁም” በሚል ምክንያት ኢትዮጵያውያን ከሳውድ አረቢያ እንዲወጡ ሲታዘዙ፣ ከዚህ ቀደም በቋሚነት ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩ 24 የቆንስላው ሰራተኞችን የሚያግዙ በአገሪቱ የሚኖሩ 40 ድጋፍ ሰጪ ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ህዳር 12 ቀን 2006 ዓም ለ3 ወራት በሚቆይ የኮንትራት ጊዜ ተቀጥረዋል። ከተቀጠሩት 40 ሰራተኞች መካከል 30 ዎቹ  ሰራተኞች የተቀጠሩት የዲፕሎማቶች የቅርብ ቤተሰቦችና ዘመዶች ናቸው። አብዛኞቹ ሰራተኞችም የተቀጠሩት የዘር ማንነታቸው እየታየ ሲሆን ከተቀጣሪዎቹ መካከል እንግሊዝኛ፣ አማርኛና አርበኛ ከማይናገሩት ጀምሮ ማስተርስ እና የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ይገኙበታል።
ከተቀጣሪዎቹ መካከል የተሻለ የትምህርት ደረጃና ብቃት ያላቸው 10 ሰዎች ከአንድ ወር በሁዋላ ታህሳስ 14 ቀን  ተመርጠው እንዲባረሩ ሲደረግ 30 ዎቹ የዲፕሎማቶች ቤተሰቦች እንዲቆዩ ተደርጓል። አስሩ ሰዎች እንዲባረሩ የተደረጉት ከመባረራቸው ከአንድ ሳምንት በፊት  ከውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሰባቱበቋሚነት እንዲቀጠሩ ደብዳቤ መላኩን ተከትሎ ፣ በትምህርት ደረጃና በችሎታቸው የተቀጠሩትን አስቀድሞ በማባረር እና ውድድር ውስጥ እንዳይገቡ በማድረግ የዲፕሎማቶችን ቤተሰቦች  እድሉን እንዲያገኙ ለማድረግ መሆኑ ታውቋል። በቆንስላው ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ከ1 ሺ 300 እስከ 1 ሺ 500 ሪያድ የሚከፈላቸው ሲሆን፣ ለአዲሶቹ የሚከፈላቸው 2000 ሪያድ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ የቆንስላውን ዲፕሎማቶች በማግለል ሰራተኞችን በዝግ ስብሰባ ያነጋገሩ ሲሆን፣ ሰራተኞችም የሳውድ አረቢያ ችግር ከመፈጠሩ በፊት የነበረውን ችግር አንድ ባንድ ዘርዝረው በድፍረት ተናግረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አፋጣኝ እርምጃ እንደሚወስዱ ለሰራተኞች ቃል ገብተው የሄዱ ቢሆንም እስካሁን ምንም እርምጃ ባለመውሰዳቸው ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉ ታውቋል።
አንደኛው ዲፕሎማት 9 ዘመዶቹን ሲያስቀጥር፣ ሌላዋ ደግሞ 8 ቤተሰቦቿንና የብሄሩዋን ልጆች ብቻ በመምረጥ አስቀጥራለች። ቀሪዎቹ 13 ሰዎች ደግሞ የሌሎች ዲፕሎማቶች ዘመዶችና ወዳጆች ናቸው።
ዲፕሎማቶቹ በሳውድ አረቢያ የሚኖራቸው ቆይታ ከ4 አመት የማይዘል በመሆኑንም ጊዜያቸውን ሀብት በማከማቸት እንደሚያጠፉ ታውቋል። ምንም እንኳ መንግስት ወደ ሳውድ አረቢያ የሚደረገው ህገወጥ ጉዞ እንዲቆም ቀደም ብሎ መመሪያ ቢያስተላልፍም፣ በሳውዲ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አማካኝነት የህገወጥ የሰዎች ዝውውር በዲፐሎማቶች አማካኝነት ሲካሄድ መቆየቱን መረጃው ያሳያል።
በእስር ቤት ውስጥ የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሊሴ ፓሴ እንዲሰራላቸው በተደጋጋሚ ሲጠይቁ፣ ዲፕሎማቶቹ ” ስብሰባ ላይ ናቸው” በሚል ለጥያቄያቸው መልስ እንደማይሰጡ መረጃው ያመለክታል።  የሳውዲው ችግር እንደተፈጠረ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ለዲፕሎማቶቹ በሰጡት ጥብቅ ትእዛዝ ለአንድ ወር ያክል ፈጣን አገልግሎት በመስጠት ከ130 ሺ በላይ ሰዎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ቢችሉም፣ በአሁኑ ጊዜ ወደ ቀድሞ ሁኔታቸው መመለሳቸው ታውቋል። በእስር ቤቶች ውስጥ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን አሁንም ሊሴ ፓሴ እንዲሰራላቸው በተደጋጋሚ ወደ ቆንስላው ስልክ እንደሚደውሉ ቢታወቅም፣ አገልግሎት እያገኙ አለመሆኑ ግን ታውቋል።

ታህሳስ 15 ኢሳት ዜና 



torsdag 26. desember 2013

ሰበር ዜና ሪያድ መንፉሃ ውስጥ፡ ማምሻውን ውጥረት ነግሷል ! በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ኢትዮጵያውያኑ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ወረቀት በትኗል!








ሰበር ዜና ሪያድ መንፉሃ ውስጥ፡ ማምሻውን ውጥረት ነግሷል ! በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ኢትዮጵያውያኑ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ወረቀት በትኗል! 
=====================================================
ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቋጣጠር ከቀትር 6 ሰዓት ጀምሮ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው የሃበሾች መንደር ከ 15 ሺህ በሚበልጡ ቆመጥ፡ እና አሜሪካ ሰራሽ ኦዚ በታጠቁ የሳውዲ ኮማንዶዎች መከበቡን የሚናገሩ የአካባቢው ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መታፈሳቸውን ይገልጻሉ ፡፤ በአካባቢው ውጥረት መስፈኑንን የሚገልጹ የአይን ምስክሮች ማንኛውም ሰው ወደተጠቀሰው መንደር መግባት እንጂ መወጣት እንዳማይችል ይገልጻሉ። 

ይህን ተከትሎ ማምሻውን አያሌ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል የተፈጸመው አይነት ጭፍጨፋ ይፈጸምብን ይሆን የሚል ስጋት ውስጥ እንደሆኑ የሚናገሩ ምንጮች ዛሬ አመሻሹ ላይ መንፉሃ ዳግም ወደ ጦር ቀጠናነት መለወጡ ያስደነገጣቸው የሃበሻ ሱቆች እና ምግቤቶች በግዜ ለመዝጋት መገደዳቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያኑን ነዋሪ ለበለጠ ጭንቀት እንደዳረጋቸው ይናገራሉ። የፀጥታ እስከባሪዎቹ ማመዘኛ ህጋዊ መሆን ያለመሆን ነው የሚሉ ምንጮች የሌላ ሃገር ዜጎች መንፉሃ ውስጥ፡በነጻነት ሲንቀሳቀሱ መታየታቸውን ጠቅሰው በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ይህ ሁለተኛ ዙር የሳውዲ መንግስት እርምጃ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውንም ጭምር ፈቃዶቻቸውን እይቀደዱ ከሃገር ለማባረር እቀድ መኖሩን ማሳያ ነው ብለዋል ። 

በተለይ ታህሳስ 7 ቀን 2006 ዓም በተሰጠው የምህረት ግዜ ውስጥ፡የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ ለማስተካከል ጀምራችህ ላልጨረሳችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በሚል ረዕስ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ባወጣው ማስታወቂያ ተጭበርብረናል የሚሉ ወገኖች « የጀመራችሁትን የማስተካከል ሂደት ማጠናቀቅ እንድትችሉ ሚሲዮኑ ለሳውዲ አረቢያ መንግስት ጥያቄ ለማቅረብ እንዲቻል ከታትህሳስ 9 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተገኝታችሁ እንድተመዘገቡ እናስታውቃለን » በሚል አያሌ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፈቃድ እና የፓስፖርት ቁጥሮቻቸውን የሪስፖንሰር « የከፊል » ቴልፎን ቁጥሮቻቸውን እና ኢትዮጵያውያኑ ሪያድ መንፉሃ ነሲም ነስሪያ ኡመልሃማም እና አካባቢዎ የሚኖሩበትን የመኖሪያ አድራሻ ዲፕሎማቱ እንደመዘገቡ የሚናገሩ ታዛቢዎች ጉዳያችን በኤንባሲ በኩል ታይቶ እልባት ያገኛል ብለው የተስፋ የጣሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በህገወጥነት ተፈርጀው ስም ዝርዝር እና የመኖሪያ አድራሻዎቻቸው ለሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች መተላለፉ ዲፕሎማቱ ከህዝብ ያልተፈጠሩ እርጉም አረመኔ መሆናቸውን ማስያ ነው ብለዋል። 

በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ሰሞኑንን በልማት ማህበራት በኩል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሶስት ወር ግዜ ውስጥ የሳውዲን ምድር ለቆ እንዲወጣ በተላላኪዎቻችቸው አማካኝነት መለዕክት ሲያስተላለፉ በነበሩበት ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠማቸው የሚናገሩ ምንጮች እንደማንኛውም የወጭ፡ሃገር ዜጋ ህጋዊ ለመሆን የሚያስችሉን ነገሮች አሞልተን እያለን በኢትዮጵያዊነታችን ብቻ ሳውዲ ውስጥ የመኖር መብታችን መታገዱ ከጀርባው ድብቅ አጀንዳ እንዳለው ይገልጻሉ ። በተለይ ኢትዮጵያውያኑ ቀደም ብለው ህጋዊ ለመሆን የሚያስችላቸውን ጉዳዮቻቸውን ለማስፈጸም በሳውዲ ኢሜግሬሽን ስደተኞች ጉዳይ መ/ቤት ተጸኖ እይተደረገባቸው መሆኑንን በማውሳት በተደጋጋሚ ብሷታቸውን በጽሑፍ እና በአካል ለኢትዮጵያ ኤንባሲ ቢያቀርቡም ጆሮ ዳባ ተብለው ከርመው ዛሬ በኤንባሲው አንደበት ህግወጥ ትብለው በመፈረጅ ለባዕዳን ተላልፈው መሰጠታቸው በህዝብ ዘንድ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ቁጣን ይቀሰቅሳል ተብሎ ይሰጋል። 
በኢንባሲው ህግወጥ ትብለው የተፈረጁት ኢትዮጵያውያን ጥያቂያቻቸውን በማጠናከር 
1/ነፃ የሙያ ቅየራ /profishinal change/ ይፈቀድልን ።
2/ የመኖሪያ ፈቃዶቻችንን ከግለሰብ ወደ ተለያዩ መ/ቤቶች እንድናደርግ ይፈቅድልን ።
3/ ያለ ምክንያት ሚደረግ የመኖሪያ ፈቃድ በላግ ይቁምልን ።
4/ፖሊሲ ባልተፈፀመ ወንጀል ይዞ ማሰር ያቁምልን ።
5/ለዕድሳት የሚሰጡ የመኖሪያ ፈቃዶቻችን በጊዜ ታድሰው ይመለሱልን ።

ይህ ሁሉ የማይቻል ከሆነ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን የተከበረው ኤምባሲ መሉ የኢቃማ ወጪያችውን ከነ ሞራል ካሳ የሳውዲ መንግስትን ጠይቆ በሰላማዊ መንገድ ወደ ሐገራቸው የሚመለሱበትን ሆነታ ሊያመቻችላቸው ይገባል የሚሉ ወገኖች የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ካርታ አሲዘው አሊያም ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቻቸውን ሸጠው ሳውዲ አረቢያ ሰርቼ እለወጣለሁ በሚል ተስፋ ከ 1 መቶ ሺህ እስከ 2 መቶ ሺህ ብር አውጥተው የገዙትን መኖሪያ ፈቃዶቻቸውን ሰርዘው ሃገር እንዲገቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ እያሰማ ያለው ጩኽት ወገናዊነት የጎደለው በመሆኑ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ከፍተኛ ተቋውሞ መቀስቀሱን አክለው ገልጸዋል።




Thursday, December 26, 2013
ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቋጣጠር ከቀትር 6 ሰዓት ጀምሮ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው የሃበሾች መንደር ከ 15 ሺህ በሚበልጡ ቆመጥ፡ እና አሜሪካ ሰራሽ ኦዚ በታጠቁ የሳውዲ ኮማንዶዎች መከበቡን የሚናገሩ የአካባቢው ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መታፈሳቸውን ይገልጻሉ ፡፤ በአካባቢው ውጥረት መስፈኑንን የሚገልጹ የአይን ምስክሮች ማንኛውም ሰው ወደተጠቀሰው መንደር መግባት እንጂ መወጣት እንዳማይችል ይገልጻሉ። 

ይህን ተከትሎ ማምሻውን አያሌ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል የተፈጸመው አይነት ጭፍጨፋ ይፈጸምብን ይሆን የሚል ስጋት ውስጥ እንደሆኑ የሚናገሩ ምንጮች ዛሬ አመሻሹ ላይ መንፉሃ ዳግም ወደ ጦር ቀጠናነት መለወጡ ያስደነገጣቸው የሃበሻ ሱቆች እና ምግቤቶች በግዜ ለመዝጋት መገደዳቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያኑን ነዋሪ ለበለጠ ጭንቀት እንደዳረጋቸው ይናገራሉ። የፀጥታ እስከባሪዎቹ ማመዘኛ ህጋዊ መሆን ያለመሆን ነው የሚሉ ምንጮች የሌላ ሃገር ዜጎች መንፉሃ ውስጥ፡በነጻነት ሲንቀሳቀሱ መታየታቸውን ጠቅሰው በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ይህ ሁለተኛ ዙር የሳውዲ መንግስት እርምጃ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውንም ጭምር ፈቃዶቻቸውን እይቀደዱ ከሃገር ለማባረር እቀድ መኖሩን ማሳያ ነው ብለዋል ። 

በተለይ ታህሳስ 7 ቀን 2006 ዓም በተሰጠው የምህረት ግዜ ውስጥ፡የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ ለማስተካከል ጀምራችህ ላልጨረሳችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በሚል ረዕስ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ባወጣው ማስታወቂያ ተጭበርብረናል የሚሉ ወገኖች « የጀመራችሁትን የማስተካከል ሂደት ማጠናቀቅ እንድትችሉ ሚሲዮኑ ለሳውዲ አረቢያ መንግስት ጥያቄ ለማቅረብ እንዲቻል ከታትህሳስ 9 ቀን 2006 ዓም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ተገኝታችሁ እንድተመዘገቡ እናስታውቃለን » በሚል አያሌ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፈቃድ እና የፓስፖርት ቁጥሮቻቸውን የሪስፖንሰር « የከፊል » ቴልፎን ቁጥሮቻቸውን እና ኢትዮጵያውያኑ ሪያድ መንፉሃ ነሲም ነስሪያ ኡመልሃማም እና አካባቢዎ የሚኖሩበትን የመኖሪያ አድራሻ ዲፕሎማቱ እንደመዘገቡ የሚናገሩ ታዛቢዎች ጉዳያችን በኤንባሲ በኩል ታይቶ እልባት ያገኛል ብለው የተስፋ የጣሉ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በህገወጥነት ተፈርጀው ስም ዝርዝር እና የመኖሪያ አድራሻዎቻቸው ለሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች መተላለፉ ዲፕሎማቱ ከህዝብ ያልተፈጠሩ እርጉም አረመኔ መሆናቸውን ማስያ ነው ብለዋል። 

በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ሰሞኑንን በልማት ማህበራት በኩል ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በሶስት ወር ግዜ ውስጥ የሳውዲን ምድር ለቆ እንዲወጣ በተላላኪዎቻችቸው አማካኝነት መለዕክት ሲያስተላለፉ በነበሩበት ወቅት ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠማቸው የሚናገሩ ምንጮች እንደማንኛውም የወጭ፡ሃገር ዜጋ ህጋዊ ለመሆን የሚያስችሉን ነገሮች አሞልተን እያለን በኢትዮጵያዊነታችን ብቻ ሳውዲ ውስጥ የመኖር መብታችን መታገዱ ከጀርባው ድብቅ አጀንዳ እንዳለው ይገልጻሉ ። በተለይ ኢትዮጵያውያኑ ቀደም ብለው ህጋዊ ለመሆን የሚያስችላቸውን ጉዳዮቻቸውን ለማስፈጸም በሳውዲ ኢሜግሬሽን ስደተኞች ጉዳይ መ/ቤት ተጸኖ እይተደረገባቸው መሆኑንን በማውሳት በተደጋጋሚ ብሷታቸውን በጽሑፍ እና በአካል ለኢትዮጵያ ኤንባሲ ቢያቀርቡም ጆሮ ዳባ ተብለው ከርመው ዛሬ በኤንባሲው አንደበት ህግወጥ ትብለው በመፈረጅ ለባዕዳን ተላልፈው መሰጠታቸው በህዝብ ዘንድ የመነጋገሪያ አጀንዳ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ቁጣን ይቀሰቅሳል ተብሎ ይሰጋል። በኢንባሲው ህግወጥ ትብለው የተፈረጁት ኢትዮጵያውያን ጥያቂያቻቸውን በማጠናከር 
1/ነፃ የሙያ ቅየራ /profishinal change/ ይፈቀድልን ።
2/ የመኖሪያ ፈቃዶቻችንን ከግለሰብ ወደ ተለያዩ መ/ቤቶች እንድናደርግ ይፈቅድልን ።
3/ ያለ ምክንያት ሚደረግ የመኖሪያ ፈቃድ በላግ ይቁምልን ።
4/ፖሊሲ ባልተፈፀመ ወንጀል ይዞ ማሰር ያቁምልን ።
5/ለዕድሳት የሚሰጡ የመኖሪያ ፈቃዶቻችን በጊዜ ታድሰው ይመለሱልን ።
ይህ ሁሉ የማይቻል ከሆነ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን የተከበረው ኤምባሲ መሉ የኢቃማ ወጪያችውን ከነ ሞራል ካሳ የሳውዲ መንግስትን ጠይቆ በሰላማዊ መንገድ ወደ ሐገራቸው የሚመለሱበትን ሆነታ ሊያመቻችላቸው ይገባል የሚሉ ወገኖች የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ካርታ አሲዘው አሊያም ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቻቸውን ሸጠው ሳውዲ አረቢያ ሰርቼ እለወጣለሁ በሚል ተስፋ ከ 1 መቶ ሺህ እስከ 2 መቶ ሺህ ብር አውጥተው የገዙትን መኖሪያ ፈቃዶቻቸውን ሰርዘው ሃገር እንዲገቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ እያሰማ ያለው ጩኽት ወገናዊነት የጎደለው በመሆኑ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ከፍተኛ ተቋውሞ መቀስቀሱን አክለው ገልጸዋል።

ትግሉ የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅበት ወሳኝ ምእራፍ ላይ ደርሷል

ራሱን የብሄረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ብሎ የሚጠራው ድርጅት በከፍተኛ የፖለቲካ ኪሳራ ውስጥ ገብቷል። የህወሃትን ዙፋን ከመጠበቅ ባለፈ ምንም ሚና የሌላቸው የብአዴን አመራሮች ያለፉትን ሶስት ወራት በተለያዩ መንገዶች የድርጅቱን አባሎች ሲገመግም ከርመዋል። በግምገማዎች ላይ እንደተረጋገጠው ብአዴን የህወሀትን ዙፋን ሊሸከሙ የሚችሉ ወጣቶችን ኮትኩቶ ለማሳደግ አለመቻሉ ነው። በብአዴን ውስጥ ለሚታየው የውስጥ ትርምስ በድርጅቱ ውስጥ የሚገኙ የግንቦት7 አባላትና ደጋፊዎች እየተጫወቱት ያለው ሚና በሌሎች ድርጅቶች ውስጥ ላሉ የንቅናቄው አባላት ጥሩ ትምህርት የሚሰጥ ነው። የንቅናቄው አባሎችና ደጋፊዎች በድርጅቱ ውስጥ የታቀፉ ወጣቶችን የፖለቲካ ግንዛቤ ከማሳደግ ጀምሮ ፣ የንቅናቄውን መረብ እስከ ወረዳዎች በመዘርጋት ከፍተኛ ሚና በመጫወት ላይ ናቸው። ሰሞኑን በገሀድ በየግምገማዎች ላይ ሲነገር እንደነበረው ብአዴን እወክለዋለሁ ከሚለው የአማራ ህዝብ ሙሉ በሙሉ ተነጥሎ በአየር ላይ የተነሳፈፈ ድርጅት ሆኗል።
ይህን እውነታ ዘግይተው የተረዱት የብአዴን ዙፋን ጠባቂ አመራሮች የሚይዙትን የሚጨብጡትን በማጣት የተለያዩ ውሳኔዎችን እያሳለፉ ነው። ታማኝ የሚሉዋቸውን ካድሬዎች በየወረዳዎች በመላክ በግንቦት7 የሚጠረጠሩትን ወይም የግንቦት7 አባሎች ናቸው ተብለው ከሚገመቱ ሰዎች ጋር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት አላቸው ተብሎ የሚታሰቡትን ሰዎች በመያዝና በማሰቃየት ሌላው ወጣት ንቅናቄውን እንዳይቀላቀል ለማድረግ እቅድ ነድፈው ለመንቀሳቀስ አስበዋል። እንዲሁም አንድ ለአምስት የተባለውን አደረጃጀት በመስሪያ ቤቶች፣ በቤተሰብ፣ በትምህርት ቤቶችና በተለያዩ ተቋማት ላይ በስፋት በማውረድ፣ የሰውን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር አልመዋል። ወጣቱ አካባቢውን እየለቀቀ ግንቦት7ን ለመቀላቀል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የአካባቢ ፖሊሶችንና የድንበር ጠባቂዎችን በማጠናከር ለመቆጣጠር ውሳኔ አሳልፈዋል።
በድርጅቱ ውስጥ የግንቦት7 ደጋፊዎች ናቸው ተብለው የሚጠረጠሩትን ወይም ዝንባሌ አላቸው የሚባሉትን ሁሉ ነቅሶ በማውጣት ለብአዴን ነፍስ ለመዝራት ሙከራ እየተደረገ ነው። እነዚህን ውሳኔዎች ያስፈጽማሉ የተባሉ በጭካኔያቸው ፣ በጎጠኝነታቸውና በንቅዘታቸው የሚታወቁትን የእነሱ ታማኝ ካድሬዎችን ወደ ፊት ለማምጣት በማሰብ ሰሞኑን ሹም ሽር አድርገዋል። ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም እንደሚባለው የሰዎች መለዋወጥ የብአዴንን ህልውና ከክስመት የሚታደገው አይሆንም።
ለመሆኑ ብአዴን የህወሀትን ዙፋን ከመጠበቅ በስተቀር ባለፉት 22 አመታት እወክለዋለሁ ለሚለው ህዝብ ምን ሰራ? ብአዴን ባለፉት 22 ዓመታት ከሰራቸው አሳፋሪ ስራዎች መካከል ሰፊው የአገራችን መሬት ለሱዳን ተላልፎ ሲሰጥ የስምምነት ፊርማውን ማስቀመጡ ነው። ከዚህ በተጨማሪ እወክለዋለሁ የሚለው የአማራ ህዝብ ከቦታ ቦታ ሲፈናቀል፣ ለአመታት ህዝቡ በኤድስና በወባ እንደቅጠል ሲረግፍ ፣ ወጣቱ ስራ አጥቶ በአደገኛ እጾች ደንዝዞና ተስፋ ቆርጦ የወጣትነት እድሜውን በከንቱ ሲያሳልፍ ብአዴን ዞር ብሎ ለማየት ፈቃደኛ አልሆነም።
የብአዴን ዙፋን ጠባቂነት የሰለቻቸው የድርጅቱ አባላት በተለያዩ ጊዜያት የውስጥ ትግል ሲያደርጉ ቆይተዋል። ብዙዎች በህወሀትና በተላለኪው ብአዴን የጸጥታ ሀይሎች ተገድለዋል፣ አንዳንዶች ድርጀቱን ለቀው ወጥተዋል፣ አንዳንዶች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብአዴን ውስጥ ብቻ ሳይሆን በመላ አገራችን ስር ነቀል ለውጥ ለማምጣት ፈቃደኝነታቸውን አሳይተው በግንቦት7 ስር ታቅፈው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉት ወጣት አባላት የቀድሞ አባሎች የጀመሩትን ትግል በተደራጀና ስርአት ባለው መልኩ ለማስኬድ የጀመሩት ትግል ንቅናቄው በትኩረት የሚከታተለው ነው። ይህ ትግል ተጠናክሮ በሌሎች ድርጅቶችም ተግባራዊ እንዲሆን ግንቦት7 በተለያዩ የኢህአዴግ ድርጅቶች ውስጥ ላሉ አባሎቹ ጥሪውን ያስተላልፋል።
ግንቦት7 መላውን የኢትዮጵያ ህዝብ ከዘረኛው፣ ዘራፊውና ራዕይ አልባው የህወሀት ጎጠኛ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመገላገል እና በምትኩ የሁሉም የምትሆን ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት የጀመረውን ትግል ከመቼውም ጊዜ በላይ አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህ ወሳኝ የትግል ምእራፍ ወቅት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ አስፈላጊ ነው ብሎ ንቅናቄው እንደሚያምን በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። በተለይም በኢህአዴግ ድርጅቶች ውስጥ ታቅፈው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉ እውነተኛ የስርአት ለውጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ ሀይሎች የብአዴን ወጣት የግንቦት7 አባላት እያሳዩት ካሉት እንቅስቃሴ ልምድ በመውሰድ በውስጥ የሚያደርጉትን ትግል አጠንክረው እንዲገፉበት ንቅናቄያችን ጥሪውን ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

onsdag 25. desember 2013

የጥራት እና ደረጃ መዳቢ ባለስልጣን መ/ቤት እና ሕ.ወ.ሓ.ት (ልዩ ትንታኔ)

ነጻነት ይበልጣል (ከጀርመን)

ዛሬ ላስነብባችሁ ያሰብኩት  ቀደም ሲል የጥራት እና ደረጃዎች መዳቢ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ተብሎ ይጠራ ስለነበረው  አሁን ለአራትተከፋፍሎ እንዲጠፋ ስለተደረገ ተቋም ነው፡፡ መስሪያቤቱ ምርት እና አገልግሎችን  በመቆጣጠር የሸማቹን ደህንነት እና ጤንነነት ማስጠበቅ የገቢና ወጪ ምርቶችን  ጥራት በመከታተል ጉልህ ድርሻ እንዲያበረክት ታስቦ የተቋቋመ ነው፡፡ መስሪያቤቱን ለረጅም ዓመታት በበላይነትይመሩ የነበሩት አቶ መሳይ ግርማ ሲባሉ በውስጡ የፍተሻ እና ካሊብሬሽን አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የሰርተፊኬሽ አገልግሎትዳይሬክትሬት፣የኢንስፔክሽን አገልግሎት ዳይሬክትሬት፣የደረጃዎች ዝግጅት ዳይሬክትሬት፣ የስልጠናአገልግሎት  ዳይሬክትሬት እና የፋይናንስዳይሬክትሬት እና ሌሎች የአገልግጎች ዘርፎች ነበሩት፡፡አቶ መሳይ መስሪያቤቱን 16 ዓመት በላይ አስተዳድረዋል፡፡ ድንገት ባልተጠበቀሰዓት ከአቶ መሳይ እውቅና ውጭ 3 ሰዎች  አቶ ተክኤ ብርሀኔ ከመቀሌ፣አቶ ደቻሳ ጉሩሙ ከጅማ እና አቶ ዳንኤል ዘነበ ከሀረርጌተመልምለው  ወደ መስሪያቤቱ ተመደቡ፡፡
ሰዎች ሳይፈለጉ መመደባቸው ብቻ ሳይሆን በወቅቱ እንዲከፈላቸው የተፃፈላቸው የደመወዝ መጠንም በመስሪያቤቱ የደመወዝ ስኬል የሌለ፤ካላቸው የትምህርት እና የስራ ልምድ ጋር ምንም አይነት ዝምድና ስለሌለው አቶ መሳይ መክፈል አልችልም በማለት አንገራገሩ፡፡ እነሱ መችየዋዛ ቢሆኑ እና እስከ ጠቅላይ /ቤት የተዘረጋ ሰንሰለት ስለነበራቸው በስልክ ተደውሎላቸው ሳይወዱ በግድ መክፈል ጀመሩ፡፡ እነዚህ ሰዎች2002 . ለሚካሄደው  ምርጫ ቅድመ ዝግጅት እንዲረዳ ከየክልሉ ተፈልገው የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሀዋርያ ሁነው ወደ ፌዴራልመንግስት የመጡ ናቸው፡፡ተክኤ በስፓርት ፣ደቻሳ በሂሳብ እና ዳንኤል በማኔጅሜንት ተመርቀዋል፡፡ ሲመጡ የሚያርፉበት የኪራይቤቶችየሚያስተዳድረው ሰፋፊ ግቢ የተዘጋጀላቸው ሲሆን ዳንኤል ከአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን /ቤት አጠገብ፤ተክኤ እና ደቻሳ ደግሞ 22አካባቢ ባለ ሰፋፊ ግቢ እንዲኖሩ ተመቻችቶላቸዋል፡፡
ዋናው  የቅርብ ጊዜ አላማቸውም 2002 ለሚደረገው ምርጫ የመንግስት ሰራተኛውን ከኢህአዴግ ጎን ማሰለፍ እና ቀጣይ አመራሮችንማዘጋጀት ነው፡፡ በዚህም መሰረት ባሉበት ቀበሌ በምርጫ ጣቢያ ሀላፊነት ተመድበው ይሰራሉ፡፡በተጨማሪም መንግስት በቢ..አር.(business process re engineering) ብሎ ወደፊት ሊዘረጋ ላቀደው የሰራተኞች ማፈኛ መንገድ የራሱን  ታማኝ  የስለላ ሰዎች ወደመሲሪያቤቱ ያስገባል፡፡ የአዲሶቹን ተመዳቢዎች አመጣጥ ተከተሎ በመስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የፍረሃት  ድባብ ተፈጠረ፡፡እነሱ ሰራተኞችንወደሚጭነው ሰርቪስ ሲገቡ አንድም ሰው ትንፍሽ አይልም፡፡የአውቶቡሱ ሰው ሁሉ በጸጥታ ይዋጣል፡፡ጆሮ ጆሮ እያሉ ያንሾካሽካሉ፡፡በእረፍት ሰሀት እነሱ በተቀመጡበት አካባቢ አብሮ ተቀምጦ ሻይ ቡና የሚል የለም፡፡ሲመደቡ የኮሙኒኬሽን ሰራተኞች ተብለው ሲሆንከመስሪያቤቱ እውቅና ውጭ ከነአቶበረከት ሰምኦን ጋር በየሳምንቱ ስብሰባ እና የመረጃ ልውውጥ ያደርጋሉ፡፡ከሳይንስና ቶክኖሎጂ ሚኒስትሩአቶ ጁነዲን ሳዶ ጋር ከፈለጉ በአካል መኪና አዝዘው ካልፈለጉ በስልክ በቀጥታ መገናኘት ይችላሉ፡፡
አቶ መሳይ እና ሌሎች የመስሪያቤቱ ከፍተኛ አመራሮች የማያውቁት መረጃ ከነሱ  ይገኛል፡፡በዚህ የአንድ አመት ቆያታቸው በመስሪቤቱደጋፊዎችን ማፍራት አልቻሉም፡፡
2003. የቢ..አር ጥናት ሲጀመር አዲስ የመጡት ካድሬዎች  የጥናት ቡድን መሪ እየተባሉ ተመደቡ፡፡ ..አር ለመስራት ቀርቶስለመስሪቤቱ አሰራር በቂ እውቀት የሌላቸው ሰዎች መስሪያቤቱን አፍርሶ እንደ አዲስ የማደራጀት ስራ በእነዚህ ሰዎች ስር ወደቀ፡፡በዚህምተቀራራቢ ስራዎችን በጋራ ማደራጀት በሚል ሰበብ ከብሄራዊ የጨረር መከላከያ አንዱን መምሪያ በማፍረስ፤የክሊነር ፐሮደክሽንመስሪያቤትን ሙሉ በሙሉ፤የሳይንስ መሳሪያዎች መስሪያቤትን ሙሉ በሙሉ አፈራርሰው አነዚህን መስሪያቤቶች ከደረጃ መዳቢ ባለስልጣንመስሪያቤት ጋር በማዋሀድ አራት የተለያዩ መስሪያቤቶችን ለመፍጠር ጥናቱ ተጀመረ፡፡ አዲስ የተጠኑት መስሪያቤቶች
1.Meterology institute,
2.Accreditation biro, 
3 .Standards agency 
4. Conformity assessment enterprise ይባላሉ፡፡
እነዚህ መስሪያቤቶች በተጠኑበት ወቅት ለጥናት ቡድኑ በየሳምንቱ በጣም ውድ በሆኑ ሆቴሎች የእራት ግብዣ  እየተዘጋጀ ወር ያክልተደከመበት፡፡ወደ መጨረሻው ምእራፍ ሲቃረብ  የጥናት ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ናዝሬት ውስጥ 10 ቀን በላይ ሆቴል ውስጥ ተቀምጠውእንዲሰሩ ተደረገ፡፡በመጨረሻም የጥናቱን መጠናቀቅ አስመልክቶ  በአቶ ጁነዲን ሳዶ አማካነት አርባምንጭ ለሶስት ቀናት ድል ያለ ግብዣተደረገ፡፡ከአርባምንጭ መልስ ሁሉም በሳይንስ እና ቴክኔሎጂ / ስር የሚገኙ ሰራተኛ  ለገሀር በሚገኘው የመንገድ እና  ትራንስፖርትመሰብሰቢያ አዳራሽ ጠቅላላ ስብሰባ ተካሄደ፡፡በስብሰባው የየጥንት ቡድኑ ሀላፊዎች የጥናታቸውን ውጤት ይፋ አደረጉ፡፡የሀገራችን ችግሮችተዳሰሱ፡፡ለችግሮች መፍትሄ ይሆናሉ የተባሉ አማራጮች ከየአቅጣጫው ጎረፉ፡፡
አብዛኞች ወጣቶች ተስፋ ያደረጉትን በየመስሪያቤቱ ያለውን ብልሹ አሰራር እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል አስተያየታቸውን ሰጡ፡፡በዚህውይይት ከተነሱት ውስጥ እስካሁን የማሰታውሳቸው አቶ ገብረጊዳን ገብረመስቀል በቅጽል ስሙ(GG) “በየመስሪያቤቱ ያለውን የተማረየሰው ሀይል  እጥረት ለመቅረፍ መንግስት በውጪ የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ገብተው እንዲሰሩ ቢደረግ መልካም ነው፡፡ለምሳሌ እንደ ኢንጅነር ቅጣው እጅጉ አይነት ሰዎች ነበሩዋት ሌሎችም እንዲህ አይነቶች ይኖራሉ ብሎ ተናገረ፡፡በእረፍት የንግድ ሚኒስትሩየአቶ ታደሰ ሐይሌ ባለቤት / አልማዝ ካህሳይ ይህን የተናገረውን ልጅ ጠራቸው እና ስሙን ጠይቃ “አንተማ የእኛው ነህ እየውልህ /ቅጣው በመንግስታችን ላይ ሊሰራ አቅዶት የነበረውን ስለማታውቅ ነው እንዲህ ያልከው፡፡በቶሎ ቀጨው እንጂ ቢቆይ በጣም አደገኛ ነበር፡፡እንዲህ አይነቱን ሰው ስሙን መጥራት የለብህም” አለችው፡፡
ይቅርታ / አልማዝ እኔ እሱን አላውቅም ነበር ሲል መለሰላት፡፡ሌላው ከጠቅላይ / /ቤት የመጣ  አቶ ጸጋዬ የሚባል አንድ ተናጋሪበንግግራቸው መሀል ጣል ያደረጉዋት ቀልድ መሰል መልክት ሁሌም ትከነክነኛለች፡፡አቶ ጸጋዬ “አማርኛ እጅዋን አገኘች በግል ትምህርት ቤትውስጥ አማርኛ መናገር እና ድንጋይ መወርወር ያስቀጣል ተብሎ በጉልህ ተጽፎ አንድ ትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ አንብቤያለሁ” ብለውአረፉ፡፡ ሌላው ጠያቂ አብዲ ዱጋ ይባላል፡፡አብዲ ጥያቄውን ያቀረበው ለሚኒስትር ጁነዲን ሳዶ ነው፡፡ጥያቄው “ኦሮሚያ ክልል ውስጥአየተካሄደ ያለው የአበባ እርሻ ልማት የአካባቢውን አፈር እና ውሃ እየበከለው ነው፡፡በዚህም የተነሳ እንስሳት ይሞታሉ ሰዎች ይታመማሉ፡፡የሰራተኞችም ህይወት አደጋ  ውስጥ ነው  የሚከፈላቸውም ገንዘብ እዚህ ግባ የሚባል አደለም፡፡እንዲያውም  ባለ ሀብቶች ከሌሎች ሀገሮችሲባረሩ ነው ወደዚህ ሀገር የመጡት ይባላል እና ይህን እንዴት ያዩታልሲል ጠየቀ፡፡አብዲን የገጠመው ከፍተኛ ውግዘት ነው፡፡ለውግዘቱመነሻም በወቅቱ የአበባ እርሻ ልማት ሲጀመር አቶ ጁነዲን የኦሮሚያ ርእሰ መስተዳድር ስለነበሩ እሳቸውን እንደተቃወመ ተቆጠረ፡፡አብዲምያጠናው ባዮሎጂ ስለነበር ሙያዊ ትንታኔ መስጠቱን ቀጠለ፡፡ክርክሩ እየከረረ ሲሄድ ጓደኞቹ ዝም እንዲል አደረጉት፡፡ስልጠናው ቀናትበፍረሃት እንደተዋጠ ተጠናቀቀ፡፡ከዚህ ሰብሰባ መልስ በቀጥታ ሁሉም መስሪያቤት ወደ ሰው ኃይል ምደባ እንዲገባ መመሪያ ተላላፈ፡፡

ስብሰባው አርብ ተጠናቆ ሰኞ ጠዋት አቶ መሳይ ከመስሪያቤቱ በፍቃዳቸው እንዲለቁ  ትእዛዝ እንደተሰጣቸው  ለሚቀርቡዋቸው ሰዎች ሲናገሩ የኮሚኒኬሽን ሰራተኞቹ እነ ተክኤ ደግሞ  ምደባውን እንዳያስተጉዋጉል በማሰብ አስቀድሞ መባረሩን በየቢሮው እየዞሩ ያውጃሉ፡ይህን ተከትሎ መስሪያቤቱ ሰው የሞተ ያክል በኡኡታ በልቅሶ ታመሰ፡፡አብዛኖች መልካም ተግባሩን ለሰራተኛ አዛኝነቱን እያሰቡ አባታቸውንበሞት የተነጠቁ ያክል ከልብ አዘኑ፡፡በዚሁ እለት የንግድ ሚኒስትሩ የአቶ ታደሰ ሀይሌ ባለቤት / አልማዝ ካህሣዬ መስሪያቤቱንእንዲያስተዳድሩ ተሾሙ ፡፡የተለያዬ ዳይሬክተሮችን ሹመት ሰጡ፡፡በዚህ ወቅት ቀደም ሲል ወያኔን እንደሚቃወሙ የሚታወቁት እና ከአቶመሳይ ጋር ቀረቤታ አላቸው የተባሉ ነባር ዳይሬክተሮች ተነስተው በምትካቸው የኢህአዲግ አባላትን መመደብ ተጀመረ፡፡ ምደባውምየሚካሄደው እያንዳንዱ ሰራተኛ እየተገመገመባለው ችሎታ ነው ይባል እንጅ ነገር ግን አስገራሚው እና ያን ያክል የተደከመበት ጥናትየግምገማውን 75% የሚይዘው  ከስራው ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው አመለካካት የሚባል ነገር ነው፡፡ሰራተኞች በወቅቱ ያነሱት የነበረውጥያቄ አመለካከት በምን ሊለካ ይችላል የእኔን አመለካካት ምን እንደሆነ ማን ያውቀዋል የሚል ነበር፡፡
ግምገማውን የሚሞሉት ቀደም ብየ የጠቀስኳቸው እነ ተክኤ፣ደቻሳ እና ዳናኤል ናቸው፡፡እነዚህ ሰዎች እንደመሰላቸው የግምገማ ነጥቡንመስጠታቸው ሳያንስ ምደባውን በዋናነት የሚመሩት እነሱ ናቸው፡፡ወደ ደረጃ መዳቢ መስሪያቤት የመጡትን የሌላ አዳዲስ  መስሪያቤትሰራተኞች መልካቸውን ሳይቀር የማያውቁዋቸውን ሰዎች ግምገማ በድፍረት ይሞሉ ነበር፡፡በመሀል በተቃዋሚነት ያልተፈረጁትን እና አባልመሆን የሚፈልጉ ካሉ በምደባ እና በእድገት አያባበሉ ወደ ድርጅቱ የማግባባት ስራ ተከናወነ፡እኔ ስራየን እንጂ የፓርቲ አባል መሆን ፍላጎትየለኝም ያሉት ደግሞ ቀደም ሲል በተለያዩ የውጭ ሀገራት ሳይቀር ከፍተኛ ስልጠናዎችን ተከታትለው ስራቸውን በብቃት ሲወጡ የነበሩበርካታ ባለሙያዎች አብዮታዊ ዲሞክራሲን ባለመቀበላቸው ብቻ  ዘራቸው እየታየ ከስራቸው ከተባረሩት መካከል ከዚህ  በታች የተዘረዘሩትለማሳያ ያክል የቀረቡ ሲሆኑ አንድም የትግራይ ብሄር  ተወላጅ አለመባረሩን አንባቢያን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ሌላው እና አስገራሚው ነገርበወቅቱ  የኦሮሞ ብሄር ተወላጆችን እያገለለ እየተካሄደ ያለው ምደባ ያሳሰባቸው የኢህዴድ አባላት ጥያቄያቸውን ለሚኒስትር ጁነዲን ሳዶቢያቀርቡም / አላማዝ ካህሳይ እያንዳንዱን ኦሮሞ እቢሮአቸው ጠርተው አርፈው እንዲቀመጡ አለዚያ እንደሚባረሩ በዛቻገልጸውላቸዋል፡፡በወቅቱም ከፍተኛ ተቃውሞ ያሰማው አቶ ሙሉጌታ መኮነን ያለስራ ለአንድ ዓመት ደመወዝ ብቻ እየተከፈለው ሊሰራበማይችል ዘርፍ የቡድን መሪ ሁኖ ሲመደብ በስሩ ግን ምንም ሰው አልነበረም፡፡
.
           ስም
    የነበራቸው ሀላፊነት
ብሄር
1
አቶ መሳይ ግርማ
የጥራት እና ደረጃ /ቤት ዋና ዳይሬክተር
ኦሮሞ
2
አቶ ጋሻው ወርቅነህ
የጥራት እና ደረጃ /ቤት ምክትል ዳይሬክተር
አማራ
3
አቶ ተፈራ ማሞ
የኤሌክትሪክል ላብራቶር  ሃላፊ
ኦሮሞ
4
አቶ ሀይሉ
የመሳሪያ ጥገኛ አገልግሎት ሃላፊ
ኦሮሞ
5
አቶ ደሬሳ ፉፋ
የሰርተፊኬሽን አገልግሎት ዳይሬክተር
ኦሮሞ
6
አቶ መስፍን
የስልጠና አገልግሎት ዳይሬክተር
አማራ
7
አቶ አዱኛው መስፍን
የጥራት ማኔጅሜንት አሰልጣኝ
አማራ
8
አቶ እንዳ
የኢንፎርሜሽን አገልግሎት ሀላፊ
አማራ
9
አቶ አመሃ በቀለ
የጥራት ማኔጅሜነት አሰልጣኝ
አማራ
10
አቶ ሂርጳ
የጥራት ማኔጅሜነት አሰልጣኝ
ኦሮሞ
11
አቶ መረሳ
የሰርትፊኬሽን ኤክስፐርት
ኦሮሞ
12
አቶ ቴወድሮስ ዘካሪያስ
የፍተሻ ላብራቶር ኤክስፐርት
አማራ
13
አቶ  ልኡል
የባህርዳር ቅርንጫፍ  ሀላፊ
አማራ
14
የሰርትፊኬሽን ሲስተም ኦዲተር የነበሩት
ኦሮሞ
15
የድሬደዋ ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩት
አማራ
16
የናዝሬት ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩት
ኦሮሞ
17
የሀዋሳ  ቅርንጫፍ ሀላፊ የነበሩት
ደቡብ
ታማኝ የህወአት አባላት  በባትሪ  ከሌላ ቦታ ተፈልገው ያለ ልምድ  እና ችሌታቸው  በከፍተኛ አመራርነት ሲመደቡ የተለሳለሰ አቋምያላቸውን እና የአባልነት ጥያቄ ሲቀርብላቸው ጥያቄውን የተቀበሉ ነባር የመስሪያቤቱ ሰራተኞች የፍርፍሪው  ተቋዳሽ ሁነዋል፡፡በዚህ ምደባእስከቡድን መሪ ያለው ሀላፊነት ያለ ፓርቲ አባልነት ወይም ያለ ትግራይ ተወላጅነት በምንም መልኩ ለተራው ሰራተኛ አይሰጥም፡፡
.
 ስም
  ቀደም የነበራቸው ሀላፊነት
አሁን የተሰጣቸው ሀላፊነት
ብሄር
1
/ አልማዝ ካህሳየ
የኢንስፔክሽን አገልግሎት ዳይሬክተር
የደረዳዎች ዋና ዳይሬክተር
ትግሬ
2
አቶ ወንዶሰን ፍስሃ
የካሊብሬሽን አገልግሎት ሀላፊ
 የሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር
ትግሬ
3
አቶ አርአያ
መከላከያ ኢንጅነሪንግ
የአክረዲቴሽን /ቤት ዋና ዳይሬክተር
ትግሬ
4
አቶ ጋሻው ተስፋዬ
የፍተሻ ላብራቶር ኤክስፐርት
የተስማሚነት ምዘና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር
ትግሬ
አቶ ገብሬ
ኝግድ እና ኢንዱስትሪ ኤክስፐርት
በደረጃዎች ኢጀንሲ ዳይሬክተር
ትግሬ
6
አቶ ብርሀኑ ተካ ረዳ
የፋይንነስ አስተዳደር ዳይሬክተር
የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የፋይናንስ ዳይሬክተር
ጉራጌ
7
/ ገነት /መድህን
የፍተሻ እና ካሊብሬሽን  አገልግሎት ዳይሬክተር
የአክረዲቴሽን /ቤት ዳይሬክተር
ትግሬ
8
/ ብርሀን ብሂል
የአዋሳ ቅርንጫፍ /ቤት ጸሀፊ
የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የሰው ሀብት እስተዳደር ሀላፊ
ትግሬ
9
አቶ ብርሀኑ ተካ
የሰርቪስ ሹፌር
የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የተራንስፖርት መምሪያ ሀላፊ
ትግሬ
10
አቶ ተክኤ ብርሀኔ
የኮሙኒክሽን ሰራተኛ
የተስማሚነት ምዘና ድርጅት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር
ትግሬ
11
አቶ ዳዊት
 የሰርቪስ ሹፌር
የሜትሮሎጂ ኢንስቲቲዩት የትራንትፖርትመምሪያ ሀላፊ
ትግሬ
12
አቶ ጸጋዬ
ኢንስፔክተር
የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ሀላፊ
ትግሬ
13
አቶ ዘነበ
ኢንስፔክተር
የገበያ ጥናት ሀላፊ
ትግሬ

ቀደም ሲል እንደማናኛውም ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳሉ የመንግስት መስሪያቤቶች የሚታዩ ችግሮች ቢኖሩም የተወሰደው እርምጃ ግን የወቅቱንየትግሬዎች የንግድ እንቅስቃሴ ያላንዳች ተቆጣጣሪ እንደፈለጉት ለማሽከርከር ታስቦ አንደሆነ ይታወቃል፡፡ለዚህም መነሻ የሚሆነው በተለያዩጊዜያት በቆርቆሮ፣በብረታብረት፣በማዳበሪያ፣በሳሙና፣በከብሪት፣በሲሚንቶ ፣በዘይት፤በጨርቃ ጨርቅ  በባትሪ ድንጋይ፣በኤሌክትሪክገመዶች የመሳሰሉት ምርቶች ላይ ተደጋጋሚ ችግር ተከስቶ በበላይ አካል የስልክ ትእዛዝ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ምርቶች ለህብረተሰቡእንዲሰራጩ ተደርጉዋል፡፡ለአብነት ያክል የአቢሲኒያ ሲሚንቶ ፋብሪካ በጥራት ጉድለት ምክንያት እንዳያመርት አገዳ መስሪያቤቱሲያስተላልፍ በወቅቱ የከተማ ሚኒስትር የነበሩት / ካሱ ኢላላ  ፍተሻውን ያከናወኑ ባለሙያዎችን በግላቸው ቢሮ ድረስ በማስጠራትትክክል አደላችሁም፤ልማታችንን እያደናቀፋችሁ ነው፤ኢንቬስተሮች ወደ ሀገራችን እየመጡ እንዳይሰሩ መሰናክል እየፈጠራችሁ ስለሆነአቁሙ ሲባሉ የመስሪያቤቱ ሀላፊዎች እገዳውን ባስቸኩዋይ አንዲያነሱ ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፈዋል፡፡መስሪያቤቱም እንዲፈርስ የተደረገውባለሞያዎችም የተፈናቀሉት ሆን ተብሎ ያለ አግባብ  መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲረዳው ያስፈልጋል፡፡

 http://www.zehabesha.com/amharic/archives/11179