የኢትዮጵያ ህዝብ ማናቸውም መብቶቹ ተነፍጎ የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ ላይ እንገኛለን:: የህዝቡ የሰብዓዊ መብቶችበየትኛውምዓለም በማይገኝ መልኩ ይጨፈለቃል ለዚህ ያበቃን ደግሞ ትልቁ ምክንያት የህወሓት/ወያኔን የወንበዴነት ጭካኔ ለመጋፈጥ ያለመፈለጋችንወይም የጭካኔያቸውን መጠን የሚቋቋም ትግል ባለመኖሩና መስዋዕትነትን ለመክፈል ባለመቁረጣችን የመጣብን መከራ እንጂ ህወሓት/ወያኔምንም ስለሆነ አይደለም:: የተቃራነውን ጎራ የልብ ትርታ የተረዳው ህወሓት/ወያኔ ሲፈልገው ይገድላል፣ያስራል፣ ያዋክባል፣መሬትንናንብረትን በሠበብ አስባቡ ይነጥቃል፣ ከስራ ያባርራል፣ የትምህርትና ሌሎች መብቶችን ገፎ ለመከራ ይዳርጋል ካልሆነም ከአገር ማሳደድንእንደትልቅ አማራጭ ተያይዞታል::
በኢትዮጵያ የመኖር መብት እንዳለንና አገራችን መሆኑን እያወቀ መብቶቻ ችንን የነፈገን ህወሓት/ወያኔ በማን አለብኝነት መቀጠላቸውን ይሁንብለን ተቀብለን እኛም መስማማታችን ለዛሬው የባሰበት ችግር አድርጎናል:: እነሱ አገራችን አይደለችም ብለው በሚበዘብዟት አገር ላይተንደላቀው እየኖሩ ኢትዮጵያ አገሬ የሚሏት እየተዋከቡ ለችግርና ለመከራ መዳረጋችን እጅግ ያሳዝናል:: አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያለውጥ ልታመጣ የምትችለው ህወሓት/ወያኔ ይዞት ከተነሳው አገርን የማጥፋት እኩይ ተግባሩና አስተሳሰቦቹ ጋር ወደመቃብርሲወርድ ብቻ ነው :: ህዝቡም ጨክኖ ለዚህ እውነት ሲነሳ ብቻ ነው::
ከመቼውም ጊዜያት በላይ ህዝባችንና አገራችን ለከፍተኛ ውርደት የተጋለጥንበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል:: በሃገራችን መኖር አልቻልንም፣በሃገራችን ጉዳይ ላይ መወሰን አልቻልንም ፣በሃገራችን ላይ የበይ ተመልካች ሆነን እንገኛለን፣ በህወሓት/ወያኔ ቀኝ ገዥነት ህዝባችንናአገራችን ለከፍተኛ ብዝበዛ ተጋልጠናል፣ በከፍተኛ ሁኔታ በታጠቁ የህወሓት/ወያኔ በዝባዞች ቁጥጥር ውስጥ ወድቀናል፣ ከፍተኛ ህዝብከረሃብ አልፎ ለከፍተኛ ጠኔ ተጋልጦ ይገኛል፣ ይህ አልበቃ ብሎ የአገሪቷ ህዝብ ወደ ውጭ ወጥቶ እንኳን እንዳይሰራ ለከፍተኛ ውርደትተዳርጎ ማንም እንደፈለገው የሚያደርገውና ተከላካይ የሌለው በዓለማችን ላይ የሚገኝ ህዝብ ለመሆን በቅተናል::
ህዝቡ በአገር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጦ ማንም እንደፈለግ የሚጫወትበት ህዝብ ከመሆኑም በላይ በየትኛውም ነገሩ ላይ ሃይማኖታዊጉዳዮቹን ጨምሮ በፈለገው መልኩ እንዳያከናውን መደረጉ ይታወቃል:: ከዚህም አልፎ ደግሞ የአገሪቷ መሬት በተለያዩ ጊዜያት ለተለይዩጎረቤት አገራትና ሃይሎች በመስጠትና በማካለል ትልቅ የታሪክ ውርደት ገጥሞናል:: ኢትዮጵያ መቼም ባልታየ መልኩ ለትልቅ ችግርተጋልጣለች:: ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ትልቅ መስዋእትነትን የሚጠይቅ ትግል ከፊታችን ተጋርጦብናል ይኸውም በህወሓት መቃብር ላይአገራችንን እንደገና ለማከም የሚያስገድድ ሁኔታ ገጥሞናል:: የህዝብ መብት ጉዳይ ሲነሳ ግድያ፣እስራትና ሞት ሆኗል እጣችን የአገሪቷን ወሰንለማስጠበቅ የተወሰደው እርምጃም ምንም ባለመሆኑ ዛሬ ኢትዮጵያ መሬቷንና የግዛት ክልሎቿን እየተነተቀጭ ትገናለች::በአባቶቻችን ተከብረው የነበሩ ድንበሮችን አሳልፎ ለመስጠት ዛሬ ለሱዳንና ለኤርትራም ጭምር እንደፈለገ የሚደራደረው ህወሓት/ወያኔ ገናያልጨረሳቸው ኢትዮጵያን የማጥፋት አላማዎቹ አላለቁም እና እንዲሁም ቀደምት ወራሪዎቻችን የፈለጉትን መሬት አባቶቻችን በትግላቸውያቆዩትን አገር በባንዳዎች በእጅ አዙር ለማግኘት እየጣሩ መሆኑና ለዚህም ተፈጻሚነት ደግሞ የህወሓት/ወያኔ የባንዳ ቡድን ሃላፊነት ወስዶእየሰራ መሆኑን ስንመለከት ያሳዝናል::
የእነዚህ ባንዳዎች አስተሳሰባቸው እና ድርጊታቸው በኢትዮጵያ ላይ መቀጠሉ እንዲያበቃ ዛሬ በህብረት ሆ ብለን መነሳት ካልቻልንተግባራቸውም ከመፈጸም ሊያቆሙ የሚችሉ አይደሉም :: ህወሓት/ወያኔን ለማሸነፍ ሰዎች የተለያዩ የትግል አማራጮች አዋጭ ናቸውብለው ባሰቡበት መንገድ ሊሄዱ ይችላሉ፣ ይሁንና አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ግን ህወሓት/ወያኔን በሰላማዊ ትግል እናሸንፋለንለሚሉ ትግሉ ተገቢ ውጤት እንዲያመጣ ከተፈለገ ትግሉን ማቀጣጠልና በአጭር ጊዜ ወደውጤት እንዲመጣ ማድረግ ወይም ትግሉን ትቶመውጣት ሌላኛው አማራጭ ይሆናል :: ምክንያቱም ህወሓት/ወያኔ በናንተ ስም የኢትዮጵያን ህዝብ እያታለለና ብልጭ ድርግም በሚለውየሰላማዊ ትግል ውስጥ አማራጭ እየመሰላችሁ እየገባችሁ የህዝቡን ተስፋ ሟሟጠጥና ከትግል ማራቅ በፍጹም አዋጭ የትግል ሥልትእንዳልሆነ ሁላችንንም እንረዳለን ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ ህወሓት/ወያኔ በአገሪቷ ታሪክ ውስጥ የፈጠራቸው ዘርን ከማጥፋት ጀምሮእስከግለሰቦችና ቡድኖች ጭምር ለወሰዳቸው ግፎች የሚፈለግ ቡድን ከመሆኑም በላይ በትግራይ ህዝብ ሳይቀር በተለያዩ ቡድኖችና ግለሰቦችየሚፈለጉ ሰዎች ስብስብ በመሆኑ ሰላማዊ ሽግግርን ይፈልጋሉ ብሎ ማሰብ በፍጹም የሚታሰብ አይደለምና ነው::ለዚህም ምስክር ይሆን ዘንድ በቅርቡ በራያ በተደረገው ስብሰባ ለአቶ አብርሃ አንድ ተሰብሳቢ ያቀረቡላቸውን ጥያቄ መስማት ብቻ ይበቃልእሱም ህወሃት የሽፍታ ቡድን መሆኑን እና ከእነሱ የሚያላቅቋቸው መሆኑን በጥያቄ መልክ ማቅረባቸውን “ሽፍታ” ማለት ደግሞ ምን ማለትእንደሆነ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ የሚታወቅ በመሆኑ ነው::ይህ ብቻ አይደለም በተለያዩ ጊዜያት አገርን በመክዳትና የአገሪቷንና የህዝቦቿን ጥቅሞች አሳልፎ በመስጠትም የሚፈለጉ ከመሆናቸውም በላይበሠብዓዊ መብት ረገጣ በኩል አሁን ህወሓት/ወያኔን የሚመሩ ሃይሎች በአገራችን ውስጥ የተፈጸሙ የጅምላ ጭፍጨፋዎችን በማቀድ፣በመተግበርና በማስተግበር በከፍተኛ ሁኔታ በአገር ውስጥና በውጭ ሃገራት የህግ አካላት እንደሚፈለጉ ጠንቅቀው የሚያውቁ መሆናቸውምጭምር ነው::ስለሆነም ይህ ችግራቸው ሊያመጣባቸው የሚችለውን አደጋ በማየት አገሪቷን ለመከላከል ሳይሆን ይህንን የራሳቸውን ችግር ለመቅረፍየሚያስችላቸውን ሁሉ ለማድረግ እንደቆረጡና ይህንን ችግራቸውን ሊያቃልልላቸው የሚችልን ካልሆነም ጊዜ ሊያራዝምላቸው የሚችልንሁኔታን ለመፍጠር ሲባል ማናቸውንም የአገሪቷን ጥቅሞች አሳልፈው ለመስጠት መቁረጣቸውን በቀላሉ መረዳት እንችላለን፣ በምንምመለኪያ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆኑ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ከሚወስዱት አረመኔያዊ እርምጃ ልንመለከታቸው እንችላለን::ከሁሉም በላይ ህወሓት/ወያኔ በተለያዩ ሰዓት የሚቀብራቸው በአንድ ወቅትና ወይም በተለያዩ ጊዜያት ሊፈነዱ የሚችሉ እምቅ ችግሮችበአገራችን ህዝቦች መካከል የፈጠራቸው እንዳሉ ሆነው አሁን ደግሞ ከጎረቤት አገራት በተለይም ከሱዳን ጋር ድንበር ለማካለል በሚል በሟቹጠቅላይ ሚኒስቴር ተጠንሥሶ የነበረውና አብሮት ያልተቀበረው አስተሳሰቡ ዛሬ በቀሪዎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሊተገበር ከፍ ዝቅ እያሉያሉበት ጊዜ በመሆኑና በሌላ በኩል ከህወሓት/ወያኔ ማንነትና ይዞት ከተነሳው ዓላማው አንጻር ህወሓት/ወያኔ ሲፈልግ ኢትዮጵያዊ ይሆናልሳይፈልግ ደግሞ ታላቋ ትግራይ ይሆናል ስለሆነም ለመሆኑ የማንን መሬት ነው ህወሓት/ወያኔ የሚደራደርበት ? ህዝቦች ለተወሰነ ጊዜሊጨቆኑ ይችሉ ይሆናል ሁል ግዜ ግን እየተጨቆኑ ይኖራሉ ማለት ግን እንዳልሆነ አውቆ መረዳት ያልፈለገው ህወሓት/ወያኔ እራሱ ላይትልቅ ችግርን ሊያመጣ መቃረቡን በትክክል መገመት ይቻላል::ህወሓት/ወያኔ በምንም መለኪያ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆነና ኢትዮጵያዊነት ምኑም እንዳልሆነ የራሱ ታሪክ ያሳየናል:: ለዚህም ማስረጃ ለታላቋትግራይ ሲሆን አሰብ ይካለላል ለኢትዮጵያ ሲሆን አሰብ የኤርትራ ይሆናል ፣ ለህወሓት/ወያኔ ሲሆን ህገመንግስት ይጣሳል ለህዝብ ጥቅምሲሆን ይኸው ህገመንግስት እንደፈለገ ይተረጎማል፣ የኢትዮጵያውያን ደም በሳውዲ ሲፈስ ህገወጥ ያሰኛል ለዚሁ ሰብዓዊ ግፍ ካሳን ከሳውዲመጥየቅ ሲግባ 360 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት እቅዶች ለሳውዲዎች ያሸልማል፣ በኢትዮጵያ ላይ የመበታተን አደጋ ስትፈጥር የነበረችውሱዳን በአምላክ እጅ መልሷን አግኝታ ስትበታተንና ደረቅ መሬቷን ስትታቀፍ ለህወሓት በታታኝ ቡድን ላደረገችው አስተዋጾ ከ1200 ኪ. ሜበላይ በሚሸፍን መሬት ላይ እስከ 50 ኪ.ሜ ወደ ውስጥ የሚገባን መሬት ለመስጠት ሲሆን ሽንጡን ገትሮ ህወሓት/ወያኔ ሲንቀሳቀስ ምንይባላል ? ህዝብን የሚያሸብርና ሽብርተኛ እራሱ ህወሓት/ወያኔ ሆኖ ሳለ የህዝብ ወገኖች የሆኑ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ታጋዮች ምንም ትጥቅሳይኖራቸው በሽብርተኝነት እየተፈረጁ በየዕስር ቤቶች የሚንገላቱ ለመሆን በቅተዋል::በአጠቃላይ ህወሓት/ወያኔ የኢትዮጵያዊነት መለኪያም ሆነ ተግባር የሌላቸው ህይሎች ስብስብ የሆነና በኢትዮጵያውያን ደምና ላብየራሳቸውን የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነት ጥማት ለማርካት በቋመጡ ሃይሎች የተዋቀረ ቡድን በመሆኑና ይህንን የማፍያ ቡድንን እኩይተግባርን ለማገዝ በነዚሁ ዘረኞች በተዋቀረ ሠራዊት እየታገዙ አገራችንን ይዘው ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናልና አገራችንን ለማዳን መቁረጥይኖርብናል:: ማንም ሊረዳን አይችልም ትግላችን ወደፊት ሲገፋ ግን ብዙዎች አቋማቸውን አስተካከለው ከኢትዮጵያውያን ጋር ይወግናሉ::ምክንያቱም አገራችን በህወሓት/ወያኔዎች የባንዳ ሃይሎች ብቻ ሳይሆን በታሪካዊ ጠላቶችችንም እጅ ስር በመውደቃችንም ጭምር ነውና ::ህወሓት/ወያኔ በወልቃይት ጥገዴ ህዝብ ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በሰላም የተጠናቀቀ መስሎት ከሆነ ተሳስቷል:: የወልቃይትጠግዴ ህዝብ፣ የሲዳሞ ህዝብ፣ የጋምቤላ ህዝብም ሆነ ሌሎች የህወሓት/ወያኔ የጅምላ ጭፍጨፋ ተጠቂዎች ሁሉ እንዳልተሸነፉ መታወቅይኖርበታል በእርግጥ መከራቸው ሁሌም የሚያደማ ቢሆንም :: ይልቁንም ህወሓት/ወያኔ አሁንም ሆነ ለወደፊትም ቢሆን በህዝብና በታሪክፊት በፍርድ ፊት ሊሆን የቀረበበት ጊዜ ነው:: ህወሓት/ወያኔ የሚቀብራቸው ፈንጂዎች ምን አልባትም በመጀመሪያ የሚያጠፉት እራሱንህወሓትን/ወያኔን እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ:: ምክንያቱም ለህዝቦች መከፋፈልና እልቂት የቀበራቸው ፈንጂዎች አቅጣጫቸውን ወደ እራሱ ወደ ህወሓት/ወያኔ እያደረጉ በመሆኑም ጭምር ነው:: ህወሓት/ወያኔና ባለሟሎቹ የኢህአዴግን ስም ተከናንበውና ተሸፋፍነው በህዝብ ላይየሚፈጽሙትን ደባ ለማስቆም በሚደረገው ትግል ውስጥ ተሳትፎአችንን እናጠናክር በህወሓት/ወያኔ መቃብርም ላይ አዲሲቷን ኢትዮጵያበጋራ እንመስርት:: ካልሆነ ህወሓት/ወያኔ አገሪቷን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊበታትናት መቁረጡን ከድርጊቱ መመልከት እንችላለን:: ቸርይግጠመን::እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar