torsdag 20. mars 2014

በኩዌት ኢትዮጵያውያንን በተለየ ማፈስ ሊጀመር ነው፤

በምሽት ፍተሻ ኢትዮጵያውያንን ማደን ተጀምሯል፤ መኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ናቸው።
በኩዌት የኢትዮጵያውያንን ስጋት እና ወከባ የተከታተሉ የወያኔ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች እና ተባባሪዎቻቸው የመኖሪያ ፍቃድ እናሰራለን አናሳድሳለን በማለት ከኢትዮጵያውያን ላይ ገነብ በማጭበርበር እየተቀበሉ መሆኑ ተደርሶበታል። እነኢህ አጭበርባሪዎች የወቅቱን ጉዳይ ተገን በማድረግ የኢትዮጵያውያንን ገንዘብ በማታለል ከተቀበሉ በኋላ ተበዳዮች ሂደው የሚከሱበት ቦታ የለም ስጋት ውስጥ መሆናቸውን እሳቤ በማድረግ በደላሎቻቸው አማካኝነት እያዋከቡ ይገኛሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በየኩዌታውያን መኖሪያ ቤት የቤት ሰራተኞች እና ሌሎች ወንጀሎችን ሊከታተል የሚችል ካሜራ እንዲገጠም መመሪያ በተዋረድ ከመንግስት መተላለፉ ታውቋል። እንዲሁም ኩዌታውያን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽሙት ወንጀል በስፋት እየተነገረ ሲሆን ኩዌት ለኢትዮጵያውያን ሌላኛዋ ሳኡድ አረቢያ ልትሆን አፋፍ ላይ ደርሳለች ሲሉ በኢህ ሰሞን ከባለፈው በበለጠ ሁኔታ በምሽት ኢትዮጵያውያንን ኢላማ ያደረገ የምሽት ፍተሻ መቷቷፉን ምንጮች ተናግረዋል።
ከሶስት ቀናት በኋላ ይጀመራል ተብሎ የሚጠበቀው ሁሉን አቀፍ አፈሳ እና አደና የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው እና የሌላቸው ሳይል የተገኘው ሁሉ እንደሚታፈስ ከፖሊስ አገኘነው ያሉትን መረጃ ኢትዮጵያውያኑ ያደረሱን ሲሆን እያንዳንዱ በኩዌት የሚኖር ኢትዮጵያዊ በተጠንቀቅ ለሚመጣው ነገር በንቃት መጠበቅ እንዳለበት አሳስበዋል። 
~~ምንሊክ ሳልሳዊ~~

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar