mandag 21. juli 2014

ዛሬ ከወደ ሰሜን ሸዋ መርሃቤቴ የተሰማው ወሬ እንደሚያስረዳው የመሬ ታጣቂዎች በመንግስት ታጣቂዎች ላይ አፈ ሙዝ አዙረውባቸዋል ይላል።

አለ ነገር፤ መሬ አለ ነገር… (አሉ)

አለ ነገር፤ መሬ አለ ነገር… (አሉ)
ዛሬ ከወደ ሰሜን ሸዋ መርሃቤቴ የተሰማው ወሬ እንደሚያስረዳው የመሬ ታጣቂዎች በመንግስት ታጣቂዎች ላይ አፈ ሙዝ አዙረውባቸዋል ይላል።
እንደ መረጃው ከሆነ፤ ለመሬ አካባቢ መብራት አገልግሎት ይሆን ዘነድ የተላከ ትራንስፎርመር ከአሁን አሁን ተተክሎ ግልጋሎት ይሰጣል ተብሎ ሲጠበቅ ባልታወቀ ምክንያት ”መሬ መብራት ሲያምርሽ ይቅር” ያሉ ባለስልጣኖች ትራንስፎርመሩን ወደሌላ አካባቢ ሊወስዱት ሲቃጡ መሬዎች ”እምቢኝ…!” አሉ።
በዚህ መሃል ግጭት ተፈጥሮ መሬዎች ትራንስፎርመራቸውን በቁጥጥር ስር አደርገው መሳሪያቸውን ወደረው ከመንግስት ሃይሎች ጋር ተፋጠዋል፤ ተፋጠዋል ብቻም ሳይሆን ተኩስ እየተለዋወጡ ነው። ይላል የደረሰን መረጃ።
መሬ የምትገኙ ወዳጆች ነገሩን አጣርታችሁ እነደምትነገሩን ተስፋ እናደርጋለን።
ለማንኛውም ይቺን ዘንድሮ አለ ነገር የምትለውን የፋሲል ደሞዝን ዜማ እንስማት!

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar