torsdag 31. oktober 2013

በወያኔ ሎሌነት ከመማቀቅ አንድ ቀን ነፃ ሆኖ መኖር ይሻላል

በወያኔ ግፈኛ ስርአት መከራቸውን ከሚያዩ ዜጎች ውስጥ ራሱ ሥርአቱ ለራሱ መገልገያ የሰበሰባቸውና ያሰማራቸው ዜጎች ይገኙበታል። ከእጅ ወደ አፍ እንኳን ለማትሆን ደመዎዝ በሰራዊቱ ውስጥ በተራ ወታደርነትና በበታች ሹማምንት የሲኦልና የጉስቅልና ኖሮ እንደሚኖሩ እናውቃለን።
በየዞኑና በየወረዳው በካድሬነት ወያኔ ለገላጋይነት ያሰማራቸው ሰራተኞችና የድርጅቱ አባሎች ከህዝቡ የጥላቻ ሰለባነት ባልተናነሰ በኑሮአቸው ለራሳቸውም ለቤተሰቦቻቸውም ሳያልፍላቸው እንደሚኖሩ እናውቃለን።
ይልቁንስ የወያኔው የአመራር ጉጅሌ ነገ የት እንደሚያደርሳቸው በማያውቁት ጨለማ ውስጥ ነው የሚዳክሩት ሚስጥርና የዳጎሰ ጥቅም ከነሱ ዘንድ አይደርስም። በቀድሞ ጊዜ የነበሩት የባላባት ሎሌዎች እንኳን ክብር አላቸው።
በዚህ ላይ ሁሉም አስተማማኝ ሎሌ መሆኑን ወያኔ ለማረጋገጫ የሚጠቀምበት ግምገማ አለ። የወያኔ ግምገማ የበታች አባላትና ደጋፊዎቹን በማስፈራራት ያላቋረጠ ድጋፍ እንዲሰጡት የሚያደርግበት በመሰረቱ ከውሻ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የማይለይ ተቋም ነው። የትምህርት እድል የስራ እድገትና የደመወዝ ጭማሪ የወያኔው ጉጅሌ የባርነት መደለያዎች ናቸው።
ግንቦት 7 ከጥቂት ከመንገዳቸው እያወጡ ህዝብ ከሚያሰቃዩት የወያኔ ታዛዥ ሎሌዎች በቀር የሀገርና የወገን ጠላት ናቸው ብሎ አያምንም። ትግላችን ለነሱም ነጻነት ነው። እነዚህ ወገኖቻችን ባገኙት አጋጣሚና እድል ሁሉ ትግሉን ያግዛሉ ብሎም ያምናል። የሚያግዙም አሉ። እርግጥ ነው ባሽከርነት ኑሮ የተንገፈገፉ የሰራዊቱ አባላትና ለህሊናቸው ክብር ያላቸው በርካታ የስርአቱ አገልጋዮች ትግላችንን እየተቀላቀሉ ነው።
ግንቦት 7 ንቅናቄ ዛሬም እንደሁሌው ለነዚህ ወገኖች ኑ ተቀላቀሉን የሚል ጥሪውን ያቀርባል። ሁላችንም ከነክብራችን ሆነን ሰዎችን ሳይሆን ውዲቱን ሀገራችንና ህዝባችንን በፈቃደኝነት በነጻነት የምናገለግልበት ጊዜ እየቀረበ ነው፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ፊን ፊሸር የተባለ የስለላ የኮምፕዩተር ፕሮግራም ኢትዮጵያ ዉስጥም በሠፊዉ ሥራ ላይ እየዋለ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ።


October 30/2013
ፊን ፊሸር ሰላዩ ቫይረስ
ፊን ፊሸር የተባለ የስለላ የኮምፕዩተር ፕሮግራም በዓለም 25 ሀገሮች ዉስጥ መሠራጨቱንና መንግስታቱም የገዛ ዜጎቻቸዉን ለመሠለል እንደሚጠቀሙበት አንድ ጥናት አመለከተ። ኢትዮጵያ ዉስጥም በሠፊዉ ሥራ ላይ እየዋለ መሆኑን ጥናቱ ይፋ አድርጓል።

የኢንተርኔት ቫይረሱ ኮምፕዩተር ዉስጥ ከገባ ግለሰቦች በኮምፕዩተራቸዉ ላይ የሚያደርጉትን የፅሁፍ የድምፅና የምስል የመልዕክት ልዉዉጦች ወደዋና መረጃ ማሰባሰቢያዉ ማዕከል ይልካል። ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች RSF ኢትዮጵያ ዉስጥ ኢንተርኔት ላይ የሚደረገዉን ቁጥጥር አስመልክቶ የተጠቀሰዉ የስለላ የኮምፕዩተር ፕሮግራም ሥራ ላይ መዋሉን ጥናቱን ጠቅሶ ለዶቼ ቬለ መግለፁን ዘግበናል። ዶቼቬለ ስለጉዳዩ የጠየቃቸው የኢትዮ ቴሌኮም የኮምንኬሽን ኦፊሰር አቶ አብዱራሂም አህመድ ኢትዮ ቴሌኮም በተጠቀሰው ፕሮግራም እንደማይገለገል በስልክ ተናግረዋል። አቶ አብዱራሂም ስለጥናቱ ውጤት እንደማያውቁ ገልፀው ሆኖም ፊን ፊሸር የተባለው የስለላ የኮምፕዩተር ፕሮግራም ኢትዮጵያ ውስጥ ሥራ ላይ ውሏል መባሉን ከዕውነት የራቀ ሲሉ አጣጥለውታል።

ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት RSF በያዝነዉ ሳምንትባወጣዉ የኢንተርኔት ቁጥጥርን የሚመለከት ዘገባ አምስት ሀገሮችን የኢንተርኔት ጠላት ሲል ፈርጇል። የሶርያ፤ ቻይና፤ ኢራን፤ ባህሬን እንዲሁም የቬትናም መንግስታት የኢንተርኔት መረጃዎችን ለመቆጣጠር ከሚሰነዝሩት የድረገፅ ጥቃት በተጨማሪ ዜጎችን ለመሰለል የግለሰቦችን የኢሜል መረጃ የሚያጠምዱ ፕሮግራሞችን በመጠቀም ግንባር ቀደም ተብለዋል። ከበርካታ ሀገሮች እነዚህ አምስቱ የተመረጡትም ለኢንተርኔት ቁጥጥሩ የሚጠቀሙበት ቴክኒዎሊጂ መራቀቅና በዚህ ስለላ መሠረትም ጋዜጠኞችና ዜጎቻቸዉን በማሰራቸዉ እንደሆነ የRSF የዘመናዊ መገናኛ ብዙሃን ዘርፍ ተመራማሪ ግሬግዋ ፑዤ ገልፀዋል። በተለይም ቻይና የኤሌክትሮኒክ መከላከያዋ ከዓለም ምናልባትም የረቀቀ ተብሎ ሲገመት ይህንኑ ቁጥጥሯን ለማጠናከር የግል ኢንተርኔት ኩባንያዎች ዜጎቿን ለመሰለል የሚረዱ ስልቶችን እንዲያቀርቡላት ማድረጓም ተገልጿል።

 ኢራን በበኩሏ የራሷን «ሃላል ኢንተርኔት» በሚል አቋቁማ የኢንተርኔት መረጃ ቁጥጥሯን አጠናክራለች። RSF የተራቀቀ ቴክኒዎሎጂን ሳይኖራቸዉ አምባገነን መንግስታት ዜጎቻቸዉን ለመሰለል እንደማይችሉ በማመልከት ለመጀመሪያ ጊዜ ተባባሪ የኢንተርኔት ጠላቶች ሲል የመሰለያ ፕሮግራሞችን የሚሰሩና ለሀገራቱ የሚያቀርቡ ድርጅቶችንም ስም አጋልጧል። ፈላጭ ቆራጭ መንግስታት ዜጎቻቸዉን በኢንተርኔት መረጃ ልዉዉጥ ሳይቀር እንዲቆጣጠሩና እንዲሰልሉ ስልቱን እያስተካከሉ የሚያቀርቡትን አምስት የግል ኩባንያዎችም የዘመኑ «ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች» ሲል RSF ወቅሷል።

ኢትዮጵያ ዉስጥ በርከት ያሉ ድረ ገፆች መነበብ እንደማይችሉ ተደጋግሞ የተገለፀ ጉዳይ ነዉ፤ መንግስት በበኩሉ ወቀሳዉን ቢያስተባብልም። የጥናቱ ተባባሪ ፀሐፊ ግሬግዋ ፑዤ ከአምስቱ ሀገሮች ተርታ በዘገባዉ ኢትዮጵያ ያልተጠቀሰችዉ የኢንተርኔት አገልግሎቱ እንደአምስቱ ሀገሮች የተስፋፋ ባለመሆኑ እንደሆነ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል። ያ ማለት ግን ድርጅታቸዉ ክትትል አላደረገም ማለት አይደለም፤

«ባለፈዉ ዓመት ኢትዮጵያ ዉስጥ ምን እንደተደረገ እየተካተልን ቆይተናል። ማለትም TOR የተሰኘዉ ስልት ተዘግቷል፤ የሰዎች ኢሜይል ልዉዉጥ እየሰበረ የሚበረብረዉ DPI የተሰኘዉ ፕሮግራምም ስራ ላይ መዋሉን እናዉቃለን፤ ዛሬ ደግሞ ሲቲዝን ላብ የተሰኘዉ ተቋም ከቶሮንቶ አንድ ዘገባ አዉጥቷል፤ ያም ኢትዮጵያ ዉስጥም አንድ የግለሰቦችን የኮምፕዩተር መረጃ የሚያጠምድ ፕሮግራም መጠቀም መጀመሩን ይገልፃል። ተቋሙ ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ዘገባ ፕሮግራሙ ኢትዮጵያ ዉስጥ ኢንተርኔት ላይ የሚካሄደዉን ቁጥጥር የሚያረጋግጥ መረጃ አካቷል።»

ግሬግዋ ፑዤ የጠቀሱት ሲቲዝን ላብ የተሰኘዉ ተቋም ይፋ ያደረገዉ ዘገባ የግለሰቦችን መረጃ የሚያጠምደዉ የኢንተርኔት ፕሮግራም ፊን ፊሸርስ እንደሚባል ይገልፃል። እንደዘገባዉም ኢትዮጵያ በተለይም ከተቃዉሞ ፖለቲካ ቡድኖች ጋ ግንኙነት ያላቸዉ ግለሰቦችን ለመከታተል ትጠቀምበታለች።



ኩባንያዉ ይህን የግለሰቦችን የኢንተርኔት መረጃ የሚያጠምድ ፕሮግራም ለኢትዮጵያ ያዘጋጀዉ የግንቦት ሰባት አባላትን ፎቶዎች በመጠቀም እንደሆነም ዘገባዉ በመዘርዘር ምስሎቹን ያሳያል። ግሬግዋ ፑዤ፤
«ባለፈዉ የበጋ ወቅት ሲቲዚን ላብ ፊን ፊሸር የተሰኘዉ ፕሮግራም ኢትዮጵያ ዉስጥ ሥራ ላይ መዋሉን ደረሰበት። የግንቦት ሰባትን «ስሙን በትክክል ብየዉ እንደሁ አላዉቅም» ምስል የያዘዉ ይህ ህገወጥ ፕሮግራም በርካታ የተቃዉሞ ፓርቲ አባላት በኢሜል አድራሻቸዉ እንዲደርሳቸዉ ተደረገ። እናም ይህ ምስል ትክክለኛ መልዕክት የያዘ ሳይሆን ያ መረጃ የሚያጠምደዉ ፕሮግራም ነዉ። ይህን ፕሮግራም አንዴ ኮምፕዩተርሽ ዉስጥ ከገባ ወደማዘዣዉ ኮምፕዩተር መረጃዎችን በሙሉ እየቀዳ ይልካል። ይህ ነገር ኮፕዩተርሽ ዉስጥ ካለ እያንዳንዷ የምትፅፊያት ነገር ፕሮግራሙን ወደላከዉ አካል ይሸጋገራል።» እሳቸዉ እንደሚሉትም ሲቲዚን ላብ ባደረገዉ ክትትል የግለሰቦችን መረጃ እየቀዳ የሚልከዉ ህገወጥ ፕሮግራም ትዕዛዝ አስተላላፊ የኮምፕዩተር መረጃ ማከማቻ የሚገኘዉ እዚያዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ መሆኑን ደርሶበታል። ኢትዮጵያ ዉስጥ በኢንተርኔት ላይ የሚከናወነዉን ጥብቅ ቁጥጥር እና ስለላ አስመልክቶችም ሲቲዚን ላብ ይፋ ያደረገዉን አዲስ መረጃ በማካተት ድንበር የለሽ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅት ዘገባ ይፋ እንደሚያደርግም ከወዲሁ ጠቁመዋል። 

“ሰማያዊ ፓርቲ” የአመራር ሽግሽግ አደረገ፤

“ሰማያዊ ፓርቲ” የአመራር ሽግሽግ አደረገ፤ ሰማያዊ ፓርቲ በተጓደሉ የፓርቲዎች አመራሮች ምትክና በአሁኑ ወቅት አመራር ላይ የሚገኙ አመራሮች መካከል ሽግሽግ አደረገ። የፓርቲው ብሔራዊ ም/ቤት አባላት ሰሞኑን ባካሄዱት ስብሰባ ላይ ሁለት አዳዲስ የፓርቲው አመራሮች ኃላፊነት እንደተሰጣቸው አዲስ የተሾሙት የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አስታውቀዋል። አዲሱ የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፀው በፓርቲው ፕሬዝዳንት አቅራቢነት ለብሔራዊ ም/ቤቱ ቀርበው የተሾሙት የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊ የነበሩት ወጣት ኃይለገብርኤል አያሌው ለስራ ጉዳይ ደቡብ ሱዳን በመሄዳቸው እንዲሁም ቀደም ሲል የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረውና በአሁኑ ወቅት በስደት ላይ ባለው በወጣት አርአያ ጌታቸው ምትክ ወጣት ብርሃኑ ተክለያሬድ እንዲሁም በወጣት ኃይለገብርኤል ምትክ ወጣት ዮናታን ተርሣ መተካታቸውን ሕዝብ ግንኙነቱ ገልፀዋል። ከዚህ በተጨማሪ አቶ ወረታው ዋሴ ቀደም ሲል ከነበሩበት የፓርቲው ጥናትና ስትራቴጂ ጉዳይ ኃላፊነት ወደ ፋይናንስ ጉዳይ የተዛወሩ ሲሆን በእሳቸው ምትክ ደግሞ ወጣት ደሳለኝ ነጋ እንዲተካቸው ተደርጓል ብለዋል። ቀደም ሲል ምክትል የሕዝብ ግንኙት ኃላፊ የነበረው ወጣት አሮን በስራ መደራረብ ሳቢያ ወደ ጥናት ምርምር መቀየሩንም አያይዘው ገልፀዋል። የፖለቲካ ሽግሽጉ ከፖለቲካ ልዩነት ጋር የተያያዘ አለመሆኑንና በቀጣይ ፓርቲውን ይበልጥ ወደፊት ከማራመድ ጋር የተያያዘ መሆኑንም ኃላፊው ገልፀዋል። በተያያዘም ባለፈው ቅዳሜ «ወጣቶችና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ይዞታ» በሚል በአዲስ አበባ የታሪክ መምህር በሆኑት በአቶ ሰለሞን ተሰማ የቀረበው ውይይት በመጪውም ቅዳሜ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። ~~ከሰብአዊ~~

የተበተኑ የኢትዮጲያ ፍርስራሾች

ዳኛቸው ቢያድግልኝ 
አገር ማለት ሕዝብ ነው ሕዝብም የሰዎች ስብስብ፡፡ መልክዐምድሩና የተፈጥሮ ሀብት ደግሞ የሰዎችን አኗኗርና አስተሳሰብ 
የሚቀርጽና ማንነትንም የሚያላብስ ነው። በየመንደሩና አካባቢው ያለው የተለያየ የአኗኗር ሁኔታ የቋንቋና የባህል 
መስተጋብር ደግሞ ትብብርንና አንድነትን የሚያወርስ እኔነትንና የእኔነትን የሚሰጥ ይሆናል። ኢትዮጵያዊነትም እንደዚያ 
ነው። 
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ግን በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት ተሰንዝሮባቸው ያቺ የሰውን ዘር ትልቅ የመሆን ተስፋን የሰነቀች 
ምንጭ ትደርቅ ዘንድ የራስዋ ልጆች እኔ እበልጥ እኔ እበልጥ እያሉ በፉክክር ሊያጠፏት ይሽቀዳደማሉ። የቀጨጨ 
ትውልድና የጫጨ አእምሮ ያለው ዘር ይጠፋ ዘንድ እውነት ነውና ኩራታችንን ተቀምተን አናሳና ሁዋላ ቀርነታችንን 
ተቀብለን እንድንጠፋ ተፈርዶብን መጥፋትንም ተለማምደን በዚህም ዳር እንቁም በዚያኛው እግር በእግር እየተጠላለፍን 
እንዘጭ እንዘጭ የምንልም በርካቶች ሆነናል። ከትናነንት በመማር ፈንታ በትናንቱ እያማረርን ቂም አርግዘን ሞት የምናምጥ 
በየጎጡ የሰፈርንም ብዙ ነን። “ለመጥፋት መጋፋታችን መቆም አለበት! መኖር ይገባናል! እኛ እኮ ምንጮች፤ የሰው ዘር፣ 
የእህል ዘርና የስልጣኔ ፈር ቀዳጆች ነን!” ብለን በነበረን ላይ ያለችንን አክለን “የነገን ተስፋ ብሩህ አድርገን ማለፍ የሚገባንና 
ጮክ ብለን የማሰብ ሃላፊነት ያለብን የኢትዮጵያ ልጆች ነን” የሚል መነሳሳት ያስፈልገናል። ኮሎኒያሊስቶች ባሻቸው 
ቀጣጥፈው የሰሯቸው አገሮች እንኳን አገር ነን ብለው በሚኮሩበት በዚህ ዘመን የፈረንጅ የእውቀት ቃርሚያ የቀመሱቱ 
የኛው ልጆች ኢትዮጵያ የምትባል አገር እኮ አልነበረቺም እያሉን መቃብራችንን ሊያስቆፍሩን ይውተረተራሉ። ለመሆኑ 
ኢትዮጵያዊነት ምን ማለት ይሆን? ኢትዮጵያዊነት ለኔ እንዲህ ይገለፃል ወይም እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ስል የሚሰማኝ ስሜት 
እንዲህ ነው። 
ግን በዚህም አላበቃም ከዚህ በላይ የማንነቴ መገለጫ ትልቅ እውነትም አለና። ኢትዮጵያዊ ነኝ እንድል የሚያደርገኝ ሌላው 
እውነት ከውልደቴ በሁዋላ የተማርኩት ብቻ ሳይሆን በውርስ የተቀበልኩትምእኔነት ነው እላለሁ። ይህም ውርስ….

ስለዚህ እያንዳንዳችን የተሸከምነው ጓዝ ብዛቱ የትየለሌ በመሆኑ ግለሰብም ሕዝብን (ያሉትንና የነበሩትን) ይወክል ዘንድ 
እውነት ነው። ዘር ከልጓም ሲሉ፣ የእናት ሆድ ዥጉርጉር ሲሉም ያንን ትልቅ እውነት በሀገራዊ ብሂል የሚገልጹበትና 
ሳይንሱም ይህንን እውነት የሚመሰክርበት ነው። ለዚህም ነው በሌላ ሀገር ተወልደው፣ የሌላ አገር ማንነትን ይዘው ነገር ግን 
ምንነታቸውን በሰጣቸው የጂን አሻራ ምክንያት ኢትዮጵያዊ የሚያስብሉ ባህርያትን የሚያንጸባርቁ ወገኖችን 
የምንመለከተው። 
እንዲያም ሆኖ ግን እኔ የተሰራሁበት አፈር፣ ወሀና አየር የኢትዮጵያው ስለሆነ ዛሬ በዐለም ዙርያ በመዞሬ ያካበትኩት 
እውቀትና ልምድም ተጨምሮበት እንኳን ኢትዮጵያ ከውስጤ ከወጣች ባዶዬን የምቀር ነኝ። መሰረቴ ሀገሬ በመሆንዋ 
“ከኢትዮጵያ አፈር ውሀና አየር የተሰራሁ፣ ማለትም የበላሁት የጠጣሁት፣ የተነፈስኩት አየርና የሞቅሁት ፀሀይ ያለኝን ተክለ 
ሰውነት እውነት ያደረገ፤ አስተሳሰቤን፣ ወግና ልማዴን ስነልቦናዬን ጭምር ያወረሰኝ፣ ሀሳቤን እግለጽበት ዘንድም አፍ 
የፈታሁበትን ቋንቋ የሰጠኝ የምንነቴ መገለጫ ነው” 
“…ከእናቴና አባቴ እኩል በእኩል በተቀበልኩት ክሮሞዞም ይሉት ድርና ማግ የተሸመንኩ ‘ጂን’ በሚሉት ዝንጉርጉር የዘርማንዘሮቼ አሻራ 
ጥበብ የደመቅሁ አንድም ብዙም ሰው መሆኔም ጭምር ነው። አያቶቼን፣ ቅም አያቶቼን ከዚያም በፊት የነበሩትና የመጀመርያው ለተከታዩ 
ሲያወርሱት የቆዩት አሻራቸውን ሁሉ መረከቤና የዚያም ነጸብራቅ መሆኔ ነው ኢትዮጵያዊነቴ። ከኔ ጋር በአካል ምንም ግንኙነት 
ሳይኖራቸው ሳላያቸው ሳያዩኝ ግን እነሱን እንድመስል የሚያደርጉኝን መሰረታዊ የሆኑ ባህርያት የተረከብኩበት መገለጫዬ ነው 
ኢትዮጵያዊነቴ።” የተበተኑ የኢትዮጵያ ፍርስራሾች Page 2

ያለሀገሬ ባዶ ነኝ። ብዙዎች ላይ የሚነበበውና ምትሀታዊ ሀይል የሚመስለው እውነትም ይኸው ነው። ስለዚህ ሀገራችን 
ከሌለች ሀገርም ከሌለን የኛ መኖር ካለመኖራችን ጋር አንድ ነው። ጎዶሎ ስሜት ያልተሟላ ማንነት ይዞ መንገታገት! በስደት 
አካላዊ ምቾት እንኳን ቢኖር የተሰበረ ቅስም የመያዛችን ትልቁ ምክንያትም ይኸው ይመስለኛል። ለዚህ ነው አገር 
አልፈረሰችም ሲሉኝ ስብርባሪዎችዋን ተበታትነው እያየሁ እንደምን አልተነካችም ልበል? አገር ሕዝብ ከሆነ ሕዝብ ሲበተን 
አገር እየፈረሰ ነው ማለት ምን ውሸት አለው? የሚያሰኘኝ። 
የኢትዮጵያ ጠላት ኢትዮጵያን ካስተዳደረ፣ የኢትዮጵያ ምሁራን ለሕዝባቸውና ለወገናቸው ማገልገል ተስኗቸው በስደት 
ለአፍሪካ ሀገሮች፣ አውሮፓና አሜሪካ እውቀታቸውን የሚሰጡ ከሆነ፣ የነገ ሀገር ተረካቢዎች የሆኑ ወጣቶች በተገኘው ቀዳዳ 
ሁሉ “በሀገር ተዋርዶ ከመኖር እየሄዱ መሞት” ብለው የሚሰደዱ ከሆነ፤ ወይዛዝርቶች ወደ አረብ ሀገር ለባርነትና፣ ለግርድና 
ሲያቀኑ ባዕድ ሀገራት ለም መሬታችን እየተሰጣቸው ሕዝባቸውን ሲመግቡ እንደሞኝ እየተመለከትን እድሜ የምንገፋ ከሆነ 
አገር ምንም አልሆነች ማለት እንደምን ይቻለናል? እንደ መለስ ዜናዊ “መሬቱ እኮ እዚያው ነው ሱዳኖች መጥተው አረሱት 
እንጂ” አይነት አባባል እኛም “ኢትዮጵያ እኮ አለች ሕዝብዋ እየተሰደደና እየተፈናቀለ ነው እንጂ …” ብለን በራሳችን 
ካልቀለድን በቀር እየፈረሰች ያለች አገር ናት። 
ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ስንደረደር የካፒቴን ተሾመ ተንኮሉን ቃለመጠይቅ ኢሳት ላይ እየተመለከትኩ ነበር። የደረሰበት በደል 
በጫካ ሕግ ላይ የተመሰረተ የጠላትነትና የማንአለብኝነት ተግባር ነበር። ለማመንም ለመቀበልም እጅግ የሚያዳግት ነው። 
እስከዛሬው ቀን ድረስ ለተቀበለው ስቃይ ምክንያት ምን እንደሆነ አልተነገረውም። ሀገሩን ማፍቀሩና ማገልገሉ በወያኔ ዘንድ 
እንደ ከባድ ጥፋት ከመቆጠሩ በስተቀር። ከዚያ በደል ሁሉ በሁዋላ ደግሞ አገርህ ትፈልግሀለች መባሉ ይበልጥ የሚያቆስል 
ነው። እንደ ካፒቴን ተሾመ ተንኮሉ አይነት ኢትዮጵያ በከፍተኛ ወጪ ያስተማረቻቸውና የሀገር መከታ የሆኑት ሁሉ ተሰደው 
የእለት ጉርሳቸውን ለማግኘት የተገኘውን ስራ እየሰሩ ተበትነው ይኖራሉ። በሙያቸው እየሰሩ ያሉትም ቢሆኑ ለመኖር እንጂ 
ሀሴትን ለማግኘት እንዳልታደሉ ይታወቃል። በ42 ፕሮፌሰሮች መባረር የተጀመረው ዘመቻ ዛሬ ከየተቋማቱ አገር ጥለው 
የሚኮበልሉ ምሁራን ቁጥር ከግምትም በላይ ነው። የመውጫ ቀዳዳ አበጅተው አገሬን የሚለውን በርካታ ወገን ከሀገሩ 
አስጨንቀው አስወጥተውታል እያስወጡም ነው የምንል ከሆነ በዚያች አገር መኖር የሚችለው መከራን ለመቀበልና 
ለመጋፈጥም ዝግጁ የሆነና ባርነትን በግዱና ምርጫ በማጣት የተቀበለው ነው ማለት ነው። ባለሀገር ነን ባዮቹና የሀገሪቱን 
ጸጋ እየተቀራመቱ ያሉት ጥቂት የወያኔ አባላትና ተላላኪዎቻቸው ብቻ ናቸው። እነርሱም የቆቅ እንቅልፍ የሚተኙና ሀብት 
የሚያሸሹቱ ይበዙባቸዋል። 
ትውልድን የሚያንጽና የሚቀርጽ አካል ከሌለ የሚጠብቀን ለባርነትና ለውርደት የተመቸ ዜጋን መተካት ግድ ይሆናል።
ሀገረገዢዎቹ ደግሞ ከነርሱ የተሻለ የሚያስብ እንዲኖር አይሹም እንዲሁ እየተንገታገቱ ልጆቻቸውና የልጅ ልጆቻቸው 
ለዘመኑ የሚመጥን እውቀትና ሀብት ይዘው የሚፈነጩበትን አገር እየሰሩ ነው። በቁም መፍረስና መሞት ማለትም ይኸው 
ነው። በተለያየ የሙያ ዘርፍ በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠኑ ወገኖች በውጭው አለም ከእውቀታቸውና ከልምዳቸው ጋር 
የማይመጣጠን ስራ ሲሰሩ ማየት ትልቅ የሀገር ሀብት ከንቱ መቅረቱን መመስከር ስለሆነ ያማል። በሙያቸው የሚሰሩትም 
ቢሆኑ ለሀገርና ለወገን የሚገባውን ማድረግ ካልቻሉ በደሉ ያው ነው። በጥቂት የወያኔ ባለስልጣኖች ባለንብረትነት 
የሚገነባው ሕንጻ ሽቅብ ሲወጣና ወደ ጎን ሲሰፋ ኢትዮጵያዊነት ግን ቁልቁል ሲሄድና የሃገሪቱም ጠረፍ ወደጎን ሲጠብ 
ማየትስ ምንኛ አሳዛኝ ነው? 
ያለው መንግስት ባመነው መሰረት ብቻ እንኳን በሁለት አመት ውስጥ አራት መቶ ሺህ ዜጎች በሕገወጥ መንገድ ተሰደዋል 
የሚል ዜና ሰምተናል። ምናልባትም ተመሳሳይ ቁጥር በህጋዊ መንገድ ከሀገር ለቀው ወጥተዋል ይህ ከቶ ምንን ያመለክታል? 
የኢትዮጵያ ወጣቶች ደም የሰሃራ በረሃን እያጠጣው ነው፣ የውቅያኖስ አሳዎችን እየቀለበ ነው። በየመን ሞት ነው፣ በሊቢያም 
ሞት ነው። በኬንያ፣ ታንዛንያ፣ ማላዊ፣ ዚምባብዌ፣ ሞዛምቢክ የኢትዮጵያ ወጣቶች እስርቤቶችን አጨናንቀውታል። የአለም 
ደቻሳ የጣር ድምጽ ዛሬን ድረስ ይሰማል። በፈላ ውሃ የተቃጠለችው ሸዋዬ ሞላ ምስል አሁንም አለ፤ የሚደርስላት ጠፍቶ 
አስፋልት ላይ ደሟ የተነዠቀዠቀው ወጣት ምስል በሃሳባችን ወስጥ ትኩስ ሀዘን አስፍሯል። ኤምባሲዎቻችን ሱቅ 
በደረቴዎችና ሰላዮችን እንጂ ኢትዮጵያን ጉዳዬ የሚሉ ሰዎችን አልያዘም። ወደ ሞታቸው እየተጋፉ መርከብ ወይም ጀልባ 
የተሳፈሩ ወጣቶች በላምባዱዛ መርገፋቸው አንገት ያስደፋል። በአንድ ዘመን አረቦች በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ተሰደው 
እየኖሩ የእለት ጉርሳቸውን ያገኙ እንዳልነበር ዛሬ አረቦች በጋጠወጥ ድርጊት ልጆቻቸንን እህቶቻቸንን ሚስቶችንም ጨምሮ 
እንደ አሻንጉሊት እየተጫወቱባቸው ነው። ቀኑን በስራና በችጋር ለሊቱን በመደፈር እያሳለፉት መጨረሻቸው እብደትና ሞት የተበተኑ የኢትዮጵያ ፍርስራሾች Page 3

ሆኗል። በዚህ አይነት መከራ የሚመጣ ገንዘብን የሚጠብቁ ተጧሪዎች ደግሞ ልጆቻቸውንህቶቻቸውን ወንደሞቻቸውን እና 
ሚስቶቻቸውን ለዚህ መከራ አሳልፈው ከሰጡ በርህራሄና በመተሳሰብ የሚታወቀው ኢትዮጵያዊነት አብቅቶለታል። 
መከታነት አጋርነትም በችጋር ምክንያት ተሟጥጦ ሄዷል፣ ክብርም እንዲሁ። ወጣቶቻችን እንደ ባርያ እየተሸጡ ነው፣ የኛው 
ጉዶችም ባርያ ፈንጋይና ደላሎች ሆነው ወገኖቻቸውን ያሻሽጣሉ። እንዲህ ከዘቀጥን እውነት ኢተዮጵያ የምንላት ሀገር 
አልፈረሰችምን? በትክክል እየፈረሰች ነው የሚያሰኘኝ የተበታተኑ የኢትዮጵያ ፍርስራሾች በመላው አለም መበተናቸውን 
መመስከሬና አንዱም እኔው መሆኔ ነው። 
ወድቀናል መነሳት ግን ይቻለናል። ፈርሰናል መልሰን የመጠገን አቅም ግን አለን። ስለዚህ በዚህች በምንወዳት አገራችን ተስፋ 
ልንቆርጥ አይገባም። ከየተበተንበት ጉድባ ከየወዳደቅንበት ቀዬ ደልቶን ከምንኖርበት የሰው አገርም ቢሆን ቀና ብለን 
ተስፋችንን ልናለመልም ቃልኪዳናችን ልናድስ ይገባል። ሀገር የሌለው፣ መሸሻ፣ ማኩረፊያና ማረፊያ የሌለው ሰው ያበቃለት 
ነው። የተቀበልነው ፓስፖርትና የያዝነው ዜግነት አገሮች በመልካም ፈቃድ የሰጡንን ባልፈቀዱ ጊዜም የሚነጥቁን መሆኑን 
ልናስተውል ይገባል። ባይነጥቁንም ሁለተኛ ዜጎች ጥገኞችም ነን። 
በኢትዮጵያ ተስፋ እንዳንቆርጥ ማንነታችንን አሽቀንጥረን እንዳንጥል የሚያደርጉ ክስተቶች ስንመለከት ደግሞ ታላቅ ብርሃን 
ይሆንልናል። ኢትዮጵያችንን በዚያም በዚህም ቢቀጠቅጧትና እያንዳንዱ ሰው ሀገሩን እንዲጠላ የሚያደርጉ ሁኔታዎች በቀን 
በቀን ቢገጥሙት፣ ምርር ብሎት በሰሃራ በረሃም ቢያቋርጥ፣ በኬንያ ቢፈተለክ በሱዳን ቢያቀጥን በቦሌም ቢከንፍ ሃሳቡ 
አረፍ ሲልለት ኢትዮጵያዊነቱ ይነግስበታል፤ በረሃውን ሲያቋርጥ ድህነት ቢያሸማቅቀውም እንኳን ኢትዮጵያዊ ኩራቱን ይዞ 
ቀን እስኪያልፍ እያለ የጭለማውን ጊዜ ይገፋዋል። ሰው እንጂ ሀገር አይሞትም የሚል የተስፋ ደወል አድማስ እየሰነጠቀ 
ግም ድው ኳ ሲል ይሰማዋል። ሰለዚህም ነው ባንዲራውን ሲያሳንሱበት ለብሶት፣ ቆብ አድርጎት፣ የአንገት ልብስ አሰርቶት 
ጉንጭና ሌላም የሰውነት ክፍሉን አረንጓዴ ቢጫና ቀይ ቀብቶት አደባባዩን የሚያደምቀው። ሀውልቱን ሲያፈርሱበት ታሪኩን 
አስውቦ ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ መጽሃፍ አድርጎ ያወጣዋል። በሃይማኖቱ ሊያናክሱት ሲፈልጉ ተቃቅፎ 
ይሳሳማል። ይህን ስሜት እንደ ምርኩዝ ይዞ ኢትዮጵያን ማዳን ይቻለናል። መንደርደርያና ማኮብኮብያውን ግብ አድርገው 
ነገር የሚወናጨፉቱ ይህንን ታላቅ ነገርም ሊገነዘቡ ይገባል። የምቾት ፖለቲካ ለማሻመድ ጊዜው የለንም፣ አገር የማዳን 
ጥድፊያ እንጂ የምርጫና የድምጽ ብልጫ ጊዜ ላይ አይደለንምና ቀዳሚውን ቀዳማይ ዓላማ አድርገን እንጀግን። ወደ ድል 
ለሚወስደው ጎዳና መንገድ ጠራጊ እንሁን ያም ቢያቅተን እንቅፋት መሆናችን ይብቃ በማለት ኢትዮጵያችን በነጻነት 
ለዘለዐለም ትኖርልን ዘንድ ጀግነው የተነሱትን እናበረታታ። 
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁን! 
biyadegelgne@hotmail.com 

onsdag 30. oktober 2013

International Commission of Jurists (ICJ): Ethiopian Leaders to Face a Trial for Genocide

October 30, 2013
by Betre Yacob
The International Commission of Jurists (ICJ) reported to have begun to work to bring Ethiopian authorities to justice for having committed a genocide in the Ogaden region. The International Commission of Jurists is a known international human rights organization composed of jurists (including senior judges, attorneys, and lawyers). The commission is known for its dedication to ensuring respect for international human rights standards through the law.Swedish TV channels showed a movie smuggled out from Ogaden by an Ethiopian refugee
The report came right after different Swedish TV channels showed a movie smuggled out from Ogaden by an Ethiopian refugee, who had been a government official in the region. The 100 hours long movie is said to have many evidences of genocide committed by the Ethiopian government in the region.
Speaking to journalists, Stellan Diaphragm, the commissioner of the Commission, said that he would do everything necessary to bring the case to the International Criminal Court (ICC).
Reports indicate that although Ethiopia is not a member of the ICC, the country can possibly face trial for crimes under international law.
The Ogaden region is a territory in Eastern part of Ethiopia, and populated mainly by ethnic Somalis. Since 2007, the region has been a site of brutal struggle between the government troops and the Ogaden National Liberation Front (ONLF), a rebel group seeking for more autonomy for the region.
Different human right organizations accuse the Ethiopian government of committing grave human right violation (including genocide) against the civilians in attempt to control the ONLF’s public support.
According to the Genocide Wach, the crimes committed in the region include extrajudicial killings, arbitrary detention, rape, torture, disappearances, the destruction of livelihood, the burning of villages and the destroying of life stock.

ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚሄዱ የአማራ ተወላጆች ኩላሊት ለሱዳንኞች እየተሸጠ ነው

ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚሄዱ የአማራ ተወላጆች ኩላሊት ለሱዳንኞች እየተሸጠ ነው
ከደቡብ ጎንደር : ከምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም : ከሴሜን ወሎ ለጉልበት ሥራ ወደ ሁመራ የሚመጡ ወገኖቻችን ባሰሪወቻቸው አና ባካባቢው በዚህ ሥራ በተሰማሩ ( የትግራይ ተወላጆች ) ግፍ እየተሰራባቸው ነው :: ባለፉት 2 ወራት ብቻ የ16 ሰወች አስከሬን በተለያየ አካባቢ ወድቆ የተገኘ ሲሆን ጎዳዩን ቀለል በማድረግ እና እውነቱን ሰው እንዳይገነዘብ ሲባል የተለያዩ መላምቶች በመንግስት ሆን ተብሎ ተሰጦታል ::
ለምሳሌ በአንድ ሳምንት ዉስጥ በተደጋጋሚ የተፈፀመውን እሄን ድርጊት በቀጥታ በብሔሮች መካከል በተነሳ ግጭህት ( የወሎ እና የጎጃም በሚል ) እርስ በርስ በጩቤ እየተዋጉ ነው በማለት ጉዳዩን አድበስብሶት የቀረ ሲሆን ሌሎች ገለልተኛ ሚዲአወችም እሄንኑ በማስተጋባት እውነቱ ተደብቆ ወንጀሉ ግን ቀጥሏል ::
በሁመራ ከተማ ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ የህገወጥ መሳሪያ ዝውውር በስፋት የሚፈፀም ሲሆን በዚህ ሥራ የተሰማሩት ሁሉም የትግራይ ተወላጆች ከሱዳኖች ለሚቀበሉት መሳሪያ ክፍያ እንዲሆን የሚሰጠው የገበሬወችን ኩላሊት ነው ::
እንዲህ አይነት ሥራ በሱዳን በኩል ወደ እስራኤለ በህገወጥ መልኩ የሚጉዓዙ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወገኖቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለ እንደሆነና አልፎ አልፎም በሱዳን በገድሃሪት እና አጎራባች አካባቢወች ድረስ በመምጣት ካምፕ ዉስጥ በመግባት ኢትዮጵያውያኑን ስደተኞች አፍኖ በመያዝ ብዙ እሺ ዶላር በማስከፈል ይለቁአቸዋል መክፈል ያልቻሉትን ግን ኩላልታቸውን በማውጣት ለእልፈተሞት ይዳረጋሉ ::
ለወገኖቻችን እንድረስላቸው !!
የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ
ሰሜን ጎንደር

ኢትዮጵያ- የፖሊስ መንግስት ያንሰራፋባት ሀገር



ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረ ማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሀገሬ
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ህገመንግስት በህግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የሚውሉ ዜጎችን አስመልክቶ የሚከተሉትን መብቶች ያጎናጽፋል፡፡“በህግ ከለላ ጥላ በቁጥጥር ስር የዋለ ማንኛውም ሰው በህግ አግባብ መብቱ ተጠብቆ ይያዛል፡፡ ማንኛውም ሰው በሀሰት ለመረጃ ጠቀሜታ ተብሎ በማስገደድ እንዲያምን ወይም የተባለውን እንዲቀበል አይገደድም፡፡ ማንኛውም በማስገደድ የተገኘ መረጃ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡“ ይላል አንቀጽ 19(2)(5)፡፡ እውነታው ሲታይ ግን ይህ የይስሙላ ሙበት የተጻፈበትን ወረቀት ዋጋ ያህል የለዉም፡፡

ባለፈው ሳምንት ሂዩማን ራይትስ ዎች “HRW“ የተባለው ዓለም ዓቀፋዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በኢትዮጵያ መንግስት “የፌዴራል ፖሊስ ማዕከላዊ ምርመራ” እየተባለ በሚጠራው የፖሊስ ጣቢያ የሚፈጸሙትን አስደንጋጭና አስከፊ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ዘገባ ሪፖርት አቅርቧል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው ይህ የፖሊስ ምርመራ ማዕከል በጥርጣሬ የተያዙ ዜጎችን በማሰቃየት ይታወቃል፡፡

እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ “በቁጥጥር ስር ባሉ እስረኞች ላይ በተለይም ያለው መንግስት ይቃወሙኛል በሚላቸው የፖለቲካ እስረኞች ላይ ማዕከላዊ ምርመራ እየተባለ የሚጠራው የምርመራ ተቋም እልህ አስጨራሽ የምርመራ ሂደት በማድረግ እስረኞችን በግድ ወንጀል ሰራን ብለው አንዲአምኑ በማስገድድ፣ እንደሚያሰቃይና ህገወጥ የእስረኞች አያያዝ“ እየፈጸመ እንደሆነ በማረጋገጥ በዘገባው ይፋ አድርጓል፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ በማያያዝም “ማዕከላዊ ምርመራ እየተባለ የሚጠራው ተቋም ብዙ የተቃዋሚ የፖለቲካ እስረኞች፣ ሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪዎች፣ መንግስት የብሄር ግጭት ተንኳሾች ናቸው በሚላቸውና ሌሎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በጅምላ ተይዘው የሚሰቃዩበት የምርመራ ማዕከል” ነው ብሎታል፡፡
ገጣሚው ዊሊያም ኤርነስትን አባባል በመዋስ “ማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል” የሰቆቃ መደብር በለቅሶና በሰቃይ የታጠረ የጭለማ ቤት ነው :: የገዥው መንግስት ተቃዋሚዎች፣ አመጸኞች፣ የሚላቸዉን የነጻው ፕሬስ ጋዜጠኞች እና ሌሎች እስረኞች በሙሉ በምርመራ ጊዜ ሰቆቃ ተጠቅሞ አራሳቸዉን አንዲወነጅሉ ያስገደዳቸዋል:: እንዲሁም ብዙዎቹ ማሰቃየትን ጨምሮ የተለያዩ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ይፈጸሙባቸዋል፡፡

እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች አባባል ማዕከላዊ እየተባለ የሚጠራው የምርመራ ተቋም “አስቀያሚው የአካልና የስነ ልቦና ማሰቃያ እንዲሁም አስገድዶ የማሰመኛ ምሽግ” መሆኑን በመጠቆም በማዕከሉ ከሚፈጸሙ የማሰቃየት ወንጀሎች እነዚህ ከብዙ ጥቂቶቹ መሆናቸውን በአጽንኦት ገልጿል፡፡ አኔም በግሌ ከአስፈሪው ማአከላዊ ምርመራ መዳፍ የተረፉ የቀድሞ እስረኞችን አነጋገሬ አውቃለሁ::

እ.ኤ.አ. በ2011 የአሜሪካ መንግስት መምሪያ በዓመታዊ የሰብአዊ መብት አያያዝ ዘገባው በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ለማሳየት የሚከተለውን ማጠቃለያ አስፍሯል፡፡
  • ብዙ ተጨባጭ መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት እ.ኤ.አ. በ2009 በአዲስ አበባ የሚገኘው ማዕከላዊ እየተባለ የሚጠራው የፖሊስ ምርመራ ማዕከል ፖሊስ ኃይልን በመጠቀም አስረኞችን አስገድዶ ለማሳመን የአካል ማሰቃየት ሰቆቃ ድርጊት ሲፈጽም ነበር፡፡ ይህ ዓይነት የማሰቃየት ዘዴ በአሁኑ ጊዜም በተግባር ላይ እየዋለ ያለ መሆኑን ዜጎች ያላቸውን ሰፊ እምነት አጽንኦት በመስጠት እየገለጹ ነው፡፡ ባለስልጣናቱ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ማዕከላዊ ምርመራን ለመጎብኘት የሚያቀርቡት ጥያቄ አሁንም በመንግስት በኩል አዎንታዊ ምላሽ እንዳላገኘ ይታወቃል፡፡“ በማለት ድርጅቱ ያለውን ሀሳብ ቋጭቷል፡፡


የ15ኛው ክፍለ ዘመን የሰቆቃ ስልት በ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ!
በአዲስ አበባ እምብርት ላይ የሚገኘው ማዕከላዊ እየተባለ የሚጠራው የማሰቃያ ምርመራ ተቋም በመካከለኛው (15ኛው) ዘመን በአውሮፓ የሰብአዊ መብት ረጋጮች በንጹሀን ዜጎች ላይ ይደረግ የነበረውን አስፈሪ፣ አስደንጋጭና ተስፋቢስ የማሰቃየት ስልት ገጽታ መለስ ብለን እንድናስታውስ ያስገድደናል፡፡ እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች መግለጫ “የማዕከላዊ ምርመራ ፖሊሶች በህግ ጥላ ስር የተያዙ የህግ አስረኞችን እነርሱ በሚፈልጉት መልኩ በግድ ለማሳመን፣ መግለጫ እንዲሰጡና ሌሎች መረጃዎችን ለማግኘት ሲሉ በእስረኞች ላይ ማሰቃየትን ጨምሮ የተለያዩ የማስገደጃ ዘዴዎችን እና ልዩ ልዩ ኢሰብአዊ ድርጊቶቸን ይፈጽማሉ፡፡ እንደ መካከለኛው የአውሮፓ ዘመን መብት ረጋጭ ተቋሞች ሁሉ የኢትዮጵያው የምርመራ ማዕከልም እንደመርማሪዎቹ ፍላጎትና አመችነት ሁኔታ እስረኞችን በአራት ዋና ዋና ክፍሎች መድቧቸዋል፡፡ የማዕከላዊ ምርመራ ማዕከል በተለያዩ የእስረኞች አያያዝና እያንዳንዳቸው ባላቸው ቅጽል ስም የሚታወቁ አራት አይነት የማጎሪያ እስር ቤቶች አሏቸው፡፡ እነርሱም፣ 1ኛ) ጨለማ ቤት፣ ይህ እስር ቤት በጣም አስቸጋሪና ብርሀን የማይገኝበት የማጎሪያ ክፍል ነው፡፡ በዚህ እስር ቤት እስረኞቹ የፀሐይ ብርሀን እና የመጸዳጃ ቤት የማግኘት ዕድላቸው በጣም ጠባብ ሲሆን አንዳንድ ጊዜም ለብቻ የመታሰር ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል፣ 2ኛ) ጣውላ ቤት፣ ይህ እስር ቤት በክፍል ውስጥ እንደልብ መዘዋወር የማያስችል ሲሆን ክፍሎቹም በቁንጫ ተባይ የተወረሩ ናቸው፡፡ 3ኛ) ሸራተን፣ በቅርብ ጊዜ ከእስር ቤት የማይለቀቁ ብዙዎቹ እስረኞች ወደዚህ የማጎሪያ ቤት እንዲዛወሩ ይፈልጋሉ፡፡ ይህ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ባለው ሆቴል ስም የተሰየመው እስር ቤት እስረኞቹ የተሻለ የአካል እንቅስቃሴ የማድረግና በህግ አማካሪዎቻቸውና በዘመዶቻቸውም መጎብኘት እንዲችሉ የእስር ቤቱ ኃላፊዎች ፈቃድ የላላበት ነው፡፡ 4ኛ) የተፋፈገው የሴት እስረኞች ማጎሪያ፣ ይህ እስር ቤት በገፍ ሴት እስረኞችን አጭቆ የያዘ ነው፡፡”

ገዥው የኢትዮጵያ አስተዳደር ከተቃዋሚ የፖለቲካ እስረኞች መረጃዎችን፣ መግለጫዎችን እና ተገደው የእምነት ቃል እንዲሰጡ ለማድረግ የተለያዩ የማሰቃያ ዘዴዎችን ይጠቀማል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዎች አንደጠቀሰው: “እስረኞች በተደጋጋሚ በጥፊ ይጠናገራሉ፣ በእርግጫ ይመታሉ፣ በቦክስ ይደለቃሉ፣ በዱላና በጠብመንጃ ሰደፍ ይደበደባሉ፡፡ አንዳንዶች እንደተናገሩት በሚያስጨንቅ ሁኔታ [በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ይደረግ እንደነበረው ‘እጅን በገመድ አስሮ ገልብጦ ከጣራ ወደ ታች በማንጠልጠል እንዲወድቁ በማድረግ የማሰቃየት’] ወይም ሁለት እጆችን ወደ ላይ ከእራስ በላይ ከፍ አድርጎ በገመድ አስሮ በማቆም ለበርካታ ሰዓታት በማቆየት በተደጋጋሚ ያሰቃዩ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ አሁንም [በመካከለኛው ዘመን ይደረግ እንደነበረው ሁሉ] በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ምርመራ ማዕከልም የእስረኞችን እጆች በካቴና በማስገባት ለበርካታ ጊዜ ታስረው እንደሚቆዩ እንዲያውም አንድ እስረኛ ከአምስት ተከታታይ ወራት በላይ እጁ በካቴና ታስሮ እንደቆየ እና ማቋረጫ በሌለው የቃል ጥያቄ ምርመራ በታሳሪዎቹ ዘንድ ፖሊስ ተደጋጋሚ ዛቻ እንደሚያደርግ ተረጋግጧል፡፡” በጥንት ጊዜ ‘በእስፓኞች ይደረግ እንደነበረው አሰቃቂ የምርመራ ሂደት‘ አንዳንዶቹ እስረኞች ለበርካታ ጊዜ ተገልለው ለብቻቸው እስራታቸውን እንዲገፉ ተበይኖባቸዋል፡፡ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን የእስር ቤት ማጎሪያዎች ይደረግ እንደነበረው ሁሉ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ እስረኞቹ የፀሐይ ብርሃን የማግኘት መብታቸውን ይከለከላሉ፣ በደካማ የንጽህና አያያዝና በውሱን የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ይሰቃያሉ፡፡ እነዚህ ሁኔታዎች በተለይም በመጀመሪያ ለምርመራ የቀርቡትን ተጠርጣሪዎች ላይ የበለጠ አሰቃቂ ይሆናሉ፡፡”

የእነዚህ ሁሉ የማሰቃየት ተግባራት ዋና ዓላማው በእስረኞች ላይ ታላቅ ጫና በመፍጠር ትክክል ይሁንም አይሁን ለቀረበባቸው የወንጀል ክስ ፈጻሚ መሆናቸውን እንዲያምኑ በማስገደድ መግለጫ፣ የእምነት ቃልና መረጃ እንዲሰጡ ለማድረግ ነው፡፡ እነዚህን በማስገደድ የተሰጡ መግለጫዎችና በግዳጅ የተገኙ የእምነት ቃሎችን አንዳንድ ጊዜ ተወንጃዮቹ ከእስር ቤት ከተለቀቁ በኋላ ወደ ህብረተሰቡ ሲቀላቀሉ ያለውን መንግስት ተገደው እንዲደግፉና ጉዳያቸው በፍርድ ቤቶች በሚታይበት ጊዜም መንግስት እንደ ማስረጃ ለመጠቀም ስለሚፈልጋቸው ነው፡፡

በማዕከላዊ እስር ቤት እስረኞች ለደረሱባቸው የአለአግባብ መታሰርና መንገላታት የሚጠየቅም ሆነ የሚገኝ ካሳ የለም፡፡ ፍርድ ቤቶች ከፖለቲካ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን የማየት ነጻነት የላቸውም፡፡ ፍርድ ቤቶች የማዕካላዊ ምርመራ ፖሊስ በምርመራ ጊዜ በእስረኞች ላይ የማሰቃየትና ህገወጥ ድርጊቶችን ፈጽሟል የሚል ውንጀላ ለፍርድ ቤቶች ቢቀርብ ተገቢውን የማጣራት ሂደት በማከናውን እርምጃ ለመውሰድ አይችሉም፡፡ በሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ መሰረት የቀድሞ እስረኞች የማዕከላዊ ምርመራን የበቀል እርምጃ በመፍራት በምርመራ ወቅት የደረሱባቸውን በደሎች ለፍርድ ቤቶች ለማቅርብ ስለሚፈሩ ዝምታን እንደሚመርጡ ጠቁሟል፡፡ አንዳንዶቹም ከፍርድ ቤቶች ችሎት በፍጹም ደርሰው እንደማያውቁ ይናገራሉ፡፡

እ.ኤ.አ. በጁላይ 2008 በዓለም በደህንነት ሙያ ታዋቂ የሆኑት እንግሊዛዊው ጡረተኛ ኮሎኔል ሚካኤል ዴዋርስ የኢትዮጵያን የእስር ቤቶች አያያዝ ሁኔታ አጥንተው የመፍትሄ ሀሳቦችን እንዲያቀርቡ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተዋውለው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ እስር ቤቶችን ከጎበኙ በኋላ በተጨባጭ የተመለከቱትን የእስር ቤቶችን ሁኔታ እንደሚከተለው አቅርበዋል፡፡ እንደዚህም ይተርኩታል፡፡
  • “እስረኞቹ ወዳሉበት ግቢ ውስጥ እንድገባ ጥያቄ አቀረብኩ፣ ይህ ግቢ ረዥም የሆነ በአንድ ጎኑ በኩል መጠለያ ሊሆን የሚችል ዳስ ይዟል፣ ግቢው በግንብ አጥር የታጠረ ሲሆን ለአካባቢው ጥበቃ እንዲያመች ሆኖ የተሰራ የጥበቃ ማማና ጥበቃዎች አሉት፡፡ በግቢው ውስጥ ከ70 እስከ 80 የሚሆኑ እስረኞች በተጎሳቆለ ሁኔታ ይታያሉ፡፡ ለሁሉም እስረኞች በምንጣፍ ለመጋደም የሚያስችል በቂ ክፍል የለም፣ መብራት የሚባል ነገር የለም፣ ቦታው በአይነምድርና በሽንት በሚሰነፍጥ ሽታ ታውዷል፣ በግቢው ውስጥ ምንም ዓይነት ውኃም ሆነ የመጸዳጃ ፋሲሊቲ የለም፣ በግቢው ውስጥ ለሴት እስረኞች ተብሎ ትንሽ የሳር ጎጆ ተቀልሳ በቅርብ እርቀት ትታያለች፣ ሆኖም ግን ግቢውን ለማሻሻል ተብሎ በግቢው ውስጥ የተሰራ ምንም ነገር የለም፣ አብዛኞቹ እስረኞች በትናንሽ ወንጀሎች በተለይም በሌብነት ወንጀል እየተያዙ ወደ እስር ቤቱ በተደጋጋሚ የሚመጡ ናቸው፡፡ ጥቂቶቹ ለወራት በዚሁ እስር ቤት የቆዩ ናቸው…፡፡”

ኮሎኔል ዴዋርስ በእስር ቤቱ የተመለከቱትን በሚከተለው መልክ አጠቃለዋል፣ “የእስረኞቹ አያያዝ በሚያሳፍር ሁኔታ ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህም ሁኔታ ፌዴራል ፖሊስን ለሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ትችት እንዲጋለጥ አድርጎታል፣ ማንም ቢሆን እስር ቤቶች እንደ ሂልተን ሆቴል መሆን አለባቸው ብሎ ሀሳብ የሚያቀርብ የለም ነገር ግን ማንም የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በኢትዮጵያ እስር ቤቶች ላይ ተገኝቶ ቅኝት ቢያደርግ እኛ ያደረግነውን ጥረት የሚደግፉ መረጃዎችን ማውጣት ይችላል… የዚህ ሁሉ የመጨረሻ ውጤቱ ሁከት፣ የእስረኞች ፍትህ አልባነትና በዓለም አቀፉ ማህበረሰብና በሰብአዊ መብት ተሟጋች ደርጅቶች መወገዝ ነው፡፡”

እ.ኤ.አ. ኦክቶበር 2013 ሂዩማን ራይትስ ዎች ባቀረበው ዘገባ መሰረት “ባለፉት አስር ዓመታት ሂዩማን ራይትስ ዎች እና ሌሎች ዓለም አቀፋዊና የአገር ውስጥ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች ማለትም በዘፈቀደ ማሰርና ማጋዝ፣ ህገወጥ የእስረኞች አያያዝ ድርጊት እና ማሰቃየት በተለያዩ ህጋዊና ህጋዊ ባልሆኑ እስር ቤቶች ውስጥ መፈጸማቸውን በተጨባጭ ማስረጃ አረጋግጠው ለህዝብ ይፋ አድርገዋል፡፡

ማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል ቤት: ኢትዮጵያ እስር ቤት መሆኗን ይመሰላል
ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ የእስር ቤቶችን አያያዝ ሁኔታዎች በተመለከተ ገንቢ ትችት ማቅረቤ ይታወሳል፡፡ እ.ኤ.አ. ፌብሯሪ 2012 ባቀረብኩት ትችት የኢትዮጵያ መንግስት በየፖለቲካ እስረኞች ማጎሪያዎች ላይ በዘፈቀደ የሚፈጽማቸውን የሰብአዊ መብት ረገጣዎችና ህገወጥ የእስረኞች አያያዝ ሁኔታ ለማጋለጥ ሞክሪያለሁ፡፡ እ.ኤ.አ. ፌብሯሪ 2013 ኢትዮጵያን “በአፍሪካ የፖሊስ ረጋጭ መንግሥት ተምሳሌትነት በመፈረጅ ጠንካራ ትችት አቅርቢያለሁ፡፡ የክርክር ጭብጤንም እንደሚከተለው አቅርቢያለሁ፡፡
  •  “የሌባ ፖሊስ መንግስት ብቸኛ መለያው -- ልዩ መታወቂያው -- በማያቋርጥና በየቦታው የሚፈጽማቸው የዘፈቀደ እስሮች፣ ዜጎችን ማደንና ወደ እስር ቤት ማጋዝ ናቸው፡፡ ማንም ሰው በከፍተኛም ሆነ በዝቅተኛ የመንግስት ባለስልጣን ስሜታዊ ትዕዛዝ በቀጥጥር ስር ውሎ የሚታሰር ከሆነ ይኸ የፖሊስ መንግስት መገለጫ ነው፡፡ ከህግ አግባብ ውጭ የዜጎች መብት የሚጣስ ወይም የሚረገጥ ከሆነ ያ በጣም አስቀያሚ የፖሊስ መንግስት መገለጫ ነው፡፡ የህግ የበላይነት ከህግ በላይ በሆነ ፖሊስ አዛዥ የሚተካ ከሆነ ያ የሌባ ፖሊስ መንግስት ተምሳሌት ነው፡፡”

በዚያ ባቀረብኩት ትችት በአዲስ አበባ ከተማ በሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ ከህግ አግባብ ውጭ የፍተሻ ወረቀት ሳይዙ በሌሊት በግልሰቦች ቤት በመሄድ በሚያካሂዱት ህገወጥ ፍተሻ ላይ ያተኮረ ነበር፡፡ በአንዱ ህገወጥ የቤት ፍተሻ ላይ የተደረገው የሚቆጠቁጥ ድርጊት ግን የፌዴራል ፖሊስ ኃላፊዎች በሙስሊም ዜጎች ቤቶች በመግባት የፈጸሙት የገንዘብ፣ የወርቅ ጌጣጌጥ፣ የተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች፣ የሃይማኖት መጻህፍትና ሌሎች የግል ቁሳቁሶች ላይ የተደረገው ዝርፊያ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ ክፍለ ከተማ የፖሊስ አዛዥ ለሆነ ሰው የአሜሪካ ድምፅ የአማርኛው ፕሮግራም ጋዜጠኛ ጠንካራ ጥያቄዎችን በማንሳት ቃለመጠይቅ ሲያቀርብለት እንዲህ የሚል አሳፋሪ ማስፈራሪያ ሰጥቷል፣ “ዋሽንግተንም ሆነ በሰማይ ቤት ብትኖር ደንታዬ አይደለም፣ ከቁብ አልቆጥረውም፣ነገር ግን አዚያው ድረስ መጥቼ አንጠልጥልዬ አመጣሀለሁ፣ ይህን ልታውቅ ይገባል” ብሎ ዛተበት፡፡

እ.ኤ.አ. ጁላይ 2012 ኤርን በርኔት የተባለቸው የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ኢትዮጵያን ከጎበኘች በኋላ የሚከተለውን ምስክርነት ሰጥታለች፡፡
“ባለፈው ወር ኢትዮጵያ በነበርኩበት ጊዜ የፖሊስ መንግስት ምን እንደሚመስል ለመመልከት ችያለሁ… አውሮፕላን ማረፊያው በቆየሁበት ጊዜ የጉምሩክ የስራ ሂደቱን ለማጠናቀቅ አንድ ሰዓት ወስዶብኛል፣ ይህም በሰልፉ መብዛት ምክንያት አይደለም ነገር ግን በፍተሻና በሚቀርቡት ጥያቄዎች መንዛዛት ምክንያት ነው፡፡ የመንግስት ባለስልጣኖች ብዙ ጊዜ በመንግስት መኪናዎች እንድንንቀሳቀስ ይፈልጋሉ፣ ይህም ወዴት እንደምንሄድ ለማወቅ ስለሚፈልጉ ነው፡፡ በመቶሺዎች የሚቆጠር ዶላር ዋጋ ያላቸው የቴሌቪዥን መሣሪያዎች በአውሮፕላን ማሪፊያው ከተውን በኋላ ብቻ ነው ቁጥጥራቸው በመጠኑም ቢሆን መላላት የቻለው፡፡”

የፖሊስ መንግስት ቃለመጠይቅ አንዴት አይነት አንደሆነ በቪደኦ ማየት ይቻላል!?
ሂዩማን ራይትስ ዎች በተቃዋሚ ፖለቲካ እስረኞች ወይም መብታቸውን ለማስከበር በሚጠይቁ ዜጎች ላይ በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ ዘገባ በማረጋገጥ በየጊዜው ዘገባዎችን እያዘጋጀ ያስቀምጣል፡፡ በዚህ ዓመት መጀመሪያ አካባቢ በአዲስ አበባ ከተማ የሙስሊሙን አመጽ መርቷል በሚል ውንጀላ ተከሶ የተያዘ ወጣት ግለሰብ ቃለ መጠይቅና የእምነት ቃሉን በቪዲዮ በመቅረጽ ህዝብ እንዲያየው ተደርጓል፡፡ በኢትዮጵያ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ከሁለት ዓመት በላይ ጀምሮ መንግስት በኃይማኖታችን ጣልቃ መግባቱን ያቁም በማለት ተቃውሞውን ሲያሰማ ቆይቷል፡፡

ከታወቁ የዜና ምንጮች መረዳት እንደተቻለው በቪዲዮ የተቀረጸው ቃለ መጠይቅ በማዕከላዊ ምርመራ በአንደ ፖሊስ ወይም ደህንነት ባለስልጣን ቢሮ ውስጥ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በቃለመጠይቅ መስጫው ክፍል ውስጥ ሌሎች ሰዎች የነበሩ ሲሆን የሚሰማው የዋናው ቃል ጠያቂ ድምጽ ነበር፣ (የሌላ ሰው ድምጽ መስማማቱን ለመግለጽ ዋናውን ቃለ መጠይቅ አድራጊ ሲያቋርጠው ለተወሰነ ጊዜ ይሰማ ነበር፡፡)

የቃለ መጠይቅ ማድረጊያው ክፍል ባለመስታወትና ባለፋሽን በር ያለው ነው፡፡ በመሰረቱ ላይ ባለ ነጭ ቀለም መጋረጃ ይታያል፡፡ በጣም ውድ የሆኑ ከውጭ ኢምፖርት ተደርገው የገቡ ባለ ረዥም መደገፊያ በቆዳ የተለበዱ የባለስልጣን ወንበሮች እና ግማሹ የቃለ መጠይቅ ማድረጊያ ክፍል በሶፋዎች ተሞልቶ በካሜራ ሌንሱ ይታያል፡፡ ከተጠርጣሪው ጎን የኢትዮጵያ ካርታ ተሰቅሎ ይታያል፡፡ ቃለ መጠይቁ በጨለማው የማዕከላዊ ምርመራ ክፍል ውስጥ አለመደረጉን ያሳያል፡፡ እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ከሆነ ቃለ መጠይቁ የተካሄደው በማዕከላዊ ፖሊስ ኮሚሽነሩ ቢሮ ውሰጥ እንደሆነ ይገመታል፡፡

በቪዲዮ ቴፑ እንደሚታየው ተጠርጣሪው ሰው ሁለት እጆቹን በካቴና ታስሮ ለጸሎት እንደሚተጋ ሰው መዳፎቹን ከወዲያ ወዲህ ሲያወራጭ ይታያል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ለወጣቱ ተጠርጣሪ ዝርዝር ቃለመጠይቅ ሰጠ፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው የሚያስጠላ አዛዣዊ ድምጽ የሚያስተላልፍ መሆኑን ያሳብቅበታል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው በመካከለኛው ክፍለ ዘመን ይደረግ እንደነበረው የማስገደድ ዝርዝር ቃለ መጠይቅ ሁኔታ ይታይበት ነበር፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው በፍርሀትና በለሆሳስ ድምጽ የሚናገረውን ተጠርጣሪ ስለእምነቱና ሌሎችም ጉዳዮች በጥያቄ ያዋክበው ነበር፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው በሚያስፈራ መልክ ስለሰለፊያ እምነት ምንነትና ስለእስላም አክራሪነት እንዲሁም በሌሎች ላይ ሰለሚኖረው መልካም አስተሳሰብ አደገኛነት ሲጠይቀው ተስተውሏል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ተጠርጣሪውን በአሽሙር በመሸንቆጥ ሲያስጨንቀው ታይቷል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ተጠርጣሪውን የሙስሊም ትምህርት ቤቶችን ሽፋን በማድረግእሱ እና መሰሎቹ በኢትዮጵያ የእስላም መንግስት ለማቋቋም ጥረት እንደሚያደርጉ ወንጅሎታል፡፡ የተጠርጣሪው ድርጀት የገንዘብ ምንጩ ከየት እንደሆነ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ደጋግሞ በመጠየቅ ሲያባሳጨው ታይቷል፡፡ በቃለ መጠይቅ ሂደቱ ሁሉ ቃለ መጠይቅ አድራጊው በተጠርጣሪው ላይ ሲያፌዝ፣ ንቀት ሲያሳይ፣ ሲቀልድና በንቀት ሲሳለቅ ታይቷል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ተጠርጣሪው እንዲናገር ዕድሉን ከሰጠ በኋላ ተጠርጣሪው በማስተባበል መናገር ሲጀምር ቃለ መጠይቅ አድራጊው ወዲያውኑ በማቋረጥ ያስቆመዋል፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ወጣቱ ተጠርጣሪ በተስፋቢስነት በረዥም የባለስልጣን ወንበር ላይ ተቀምጦ ሁለት እጆቹን በካቴና ታስሮ ቃለ መጠይቅ አድራጊውን በአክብሮት ዓይን እያየ በለሆሳስ ቅላጼና በጉልህ በማይሰማ ድምጽ በሚናገርበት ጊዜ የበላይነት ስሜት ያንጸባርቅበታል፣ ይረብሸዋል፣ እንዲሁም በተለየ መልኩ ያንቋሽሸዋል፡፡

እንደ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ከሆነ በቪዲዮው ላይ የተደበቀ ብዙ ነገር አለ፡፡ ለምሳሌ ያህል የተቀረጸው የቪዲዮ ቃለ መጠይቅ ከመደረጉ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ ለመደብደብ ወደ ኋላ በማይሉ ዝቅተኛ የፖሊስ ባለስልጣኖች በማለሳለስና ተገድዶ ላመነው የቪዲዮ ቀረጻ ተባባሪ እንዲሆን በማድረግ ሙሉ ቃለ መጠይቅ ተደርጎለት ነበር፡፡ የቪዲዮ ቀረጻ ቃለ መጠይቁ በሚደመጥበት ጊዜ ሌሎች የፖሊስ አባላትና የሲቪል ሰራተኞች እንዲገኙ ተደርጓል፡፡ እንዲገኙ የተደረገበት ዋና ዓላማም ጉዳዩ ለፍርድ ቤት በሚቀርብበት ጊዜ ተጠርጣሪው ግለሰብ ያለምንም ተጽዕኖ በእራሱ ፈቃድ አምኖ የተናገረው መሆኑን መመስከር እንዲችሉ ለማመቻቸት ነው፡፡ (በቪዲዮ የተቀረጸውን ቃለ መጠይቅ ቅጅ ለተከላካይ ጠበቆችም ሆነ ለፍርድ ቤቱ የተሰጠ ነገር የለም፡፡) ቃለ መጠይቁ የተቀረጸው የፖሊስ ማስፈራሪያነት በሌለበትና ከጣልገብነት ነጻ በሆነ መልኩ በተረጋጋና በጥሩ የንግግር ቅላጼ መሰረት ተደርጎ ነው፡፡ ጥያቄዎቹ በመስክ ላይ እንደሚፈነዳ ደማሚት ተደርገው በዘዴ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ ጥያቄ አቅራቢው ተጠርጣሪው የየትኛው ድርጅት አባል እንደሆነ፣ ምን ፍልስፍና እንደሚከተል፣ እነማን ደጋፊዎቹ እንደሆኑ፣ የገንዝብ ምንጫቸው ከየት እንደሆነ፣ የተከሰሰበት ወንጀል ምን እንደሆነና የመሳሰሉት አጠቃላይ ጥያቄዎች ይቀርቡለታል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ተጠርጣሪው ድርጊቱን ለመፈጸሙ ሊያሳምን በሚችል መልኩ ተያያዥነት ያላቸው በሚመስል መልኩ ሌሎች ሁለተኛ ዙር ጥያቄዎች ይከተላሉ፡፡ ለምሳሌም ተጠርጣሪውን ለምንድን ነው የዚህ ድርጅት አባል የሆንከው? አባል ሆኖ ምን ሚና እንደተጫወተ እንዲሁም እነዚህን የተወነጀለባቸውን ድርጊቶች ለምን ሪፖርት እንዳላደረገና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ይጠየቃል፡፡ የቪዲዮ ቃለ መጠይቁ ተጠርጣሪው የወንጀል ድርጊቱን መፈጸሙን ለማመኑ ትክክለኛ መረጃና ለእራሱ መስቀያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

ዋና የፖሊስ መርማሪዎች ጭካኔና አስገዳጅነት የተሞላበትን በቪዲዮ የተቀረጸ ቃለ መጠይቅ ያለበት የምርመራ ውጤት ማስቀረት አይፈልጉም፡፡ የውስጥ አዋቂ ምንጭች ተጠርጣሪው ወጣት እጆቹን በካቴና ታስሮ በሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ መደነቃቸውን ይገልጻሉ፡፡ እጁን በካቴና ታስሮ ለአንድ ከፍተኛ የፖሊስ ባለስልጣን ቃለመጠይቅ የሚሰጥ ተጠርጣሪ የጥያቄና መልስ ሂደት በቪዲዮ ቴፕ ተቀርጾ ማየት በጣም አስደንጋጭ ከመሆኑም በላይ እንደ አንዳንድ የውስጥ ምንጮች ተጠርጣሪውን ወጣት በካቴና አስሮ ቃለ መጠየቅ ማድረጉ ለምን እንዳስፈለገ ግልጽ እንዳልሆነ ይናገራሉ፡፡ እንዲሁም የቪዲዮ ቀረጻ ቃለ መጠይቁ መንግስት በተቃዋሚ የፖለቲካ ደርጅቶች ላይ የስነ ልቦና ጦርነት በማካሄድና በማስፈራራት ረገድ ጠቀሜታ ያስገኝለታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ይህ ሁኔታ ተጠርጣሪዎችን በማስፈራራትና በማሸማቀቅ ለተቃዋሚ ኃይሎችና ለአመጸኞች ማዳከሚያ እንዲሆን ታስቦ የተሰራ ነው፡፡ በጥንካሬና በጽናት የተሞሉ ወጣት የተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች በማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል መዳፍ ስር ወይም መንጋጋ ከገቡ ፍርሀትና መደናገጥ አንደሚታይባቸው ለሕዝብ ለማሳየት ነው፡፡ ይህ ሁኔታ የተቃዋሚ ድርጀት መሪዎች ማዕከላዊ የምርመራ ማዕከል ከደረሱ እንደሚሰባበሩ፣ እንደሚደቆሱ፣ እንደሚታኘኩና እንደሚበጣጠሱ የማያዳግም መልዕክት ማስተላለፊያ ዘዴ ነው፡፡ እንደ ሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ ከሆነ ተገዶ ማመን አንዳንድ ጊዜ ግለሰቦች ከእስር ቤት ከወጡ በኋላ ሳይወዱ በግድ መንግስትን እንዲደግፉ የሚደረጉበት ዘዴ ነው፡፡

ይህም ሆኖ በቪዲዮ የተቀረጸውን የቃለ መጠይቅ አድራጊውን ሙሉና የተጠርጣሪውን መብት በመጣስ ለእይታ የበቃውን ድራማ መመልከት “በህግ ከለላ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎች በፍርድ ቤት ወንጀለኛነታቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ ነጻ ናቸው፣ እንዲሁም ተገደው በእራሳቸው ላይ ምስክርነት አይሰጡም“ የሚለውን ህገመንግስታዊ መብት የጣሰ የማይታመንና አስደንጋጭ ሁኔታ ነው (አንቀጽ 20(3) ፡፡ ቃለ መጠይቅ አድራጊው የወጣቱን ተጠርጣሪ ህገመንግስታዊ መብት በኮርማ እንደተናደ የሴራሚክ ቁልል ደፍጥጦታል፡፡ ወጣቱ ተጠርጣሪ “ያለመናገር መብት“ እንዳለው በግልጽ የተቀመጠውን ህገመንግስታዊ መብት ቃለ መጠይቅ አድራጊው ከቁብ የቆጠረው አይመስልም (አንቀጽ 19(2)(5) ፡፡ “በህግ ከለላ በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ያለመናገር መብት አላቸው፡፡ በህግ ከለላ በቁጥጥር ስር የዋሉ ዜጎች ተገደው የእምነት ቃል እንዲሰጡ አይደረግም ተገደው የሰጡትም ቃል ለማስረጃነት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ በማስገደድ የተገኘ ማንኛውም ማስረጃ በህግ ፊት ተቀባይነት አይኖረውም፡፡” ቃለ መጠይቁ በሚደረግበት ጊዜ የተጠርጣሪው የህግ ጠበቃ እንዲገኝ አለመደረጉ ቃለ መጠይቅ አድራጊውን የሚያሳስበው አይመስልም (አንቀጽ 20(5)፣ አንቀጽ 21(2) ፡፡ “የተከሰሱ ሰዎች የህግ ጠበቃቸው የመጎብኘትና… ከህግ ጠበቃቸው ጋር የመመካከር መብት አላቸው፡፡“ “ተጠርጥሮ በህግ ከለላ ጥላ ስር የዋለው ተጠርጣሪ ስለቀረበበት ክስ አስቀድሞ በቃለ መጠይቅ አድራጊው አልተገለጸለትም፡፡“ አንቀጽ 20(2) “የተከሰሱ ሰዎች ስለቀረበባቸው ክስ ዝርዝር መረጃ የማግኘት መብታቸው የተጠበቀና ይህም በጽሁፍ ሊደርሳቸው ይገባል፡፡“

ቃለ መጠይቅ አድራጊው ተጠርጣሪውን ከየትኛው የእስልምና እምነት ክፍል እንደሆነ በማስፈራራት መረጃ ለማግኘት ሞክሯል፣ ለማስረዳትም ጥረት አድርጓል፣ አክራሪነት የየትኛው የእስልምና አስተምህሮ እንደሆነና ተጠርጣሪው ይህንን አውግዞ መንግስት የሚፈልገውን እንዲመርጥ በመጠየቅ የተጠርጣሪውን መብት ደፍጥጦታል፡፡ አንቀጽ 27(1)(3) “እያንዳንዱ ሰው የራሱ የእምነት ነጻነት አለው… ይህ መብት ግለሰቡ የመረጠውን ኃይማኖት በግሉ ወይም ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ የመከተልና የማራመድ መብትን ጭምር ያጠቃልላል… (3) ማንም የመረጠውን የራሱን እምነት ለማራመድ የሚያግደው ወይም የሚከለክለው የለም፡፡“ ቃለ መጠይቅ አድራጊው ለተጠርጣሪው ስለኃይማኖት እንቅስቃሴውና ስለእምነት ምርጫው ሲጠይቅ “ተጠርጣሪው በግል ወይም ከሌሎች ጋር በጋራ በመሆን የመሰብሰብ፣ የጦር መሳሪያ ሳይዙ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግና አቤቱታ የማቅረብ መብት” (አንቀጽ 30(1) እንዳለው የተረዳ አይመስልም፡፡ በአጭሩ ቃለ መጠይቅ አድራጊው የተጠርጣሪውን መብት የደፈጠጠው ህገመንግስቱ ያጎናጸፈውን የኢትዮጵያን ህገመንገስት በመጣስ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ፈርማ የተቀበለቻቸውን ልዩ ልዩ ዓለም አቀፍ ደንቦችን በመናድ ጭምር ነው፡፡

ጥፋተኝነትን ለመከላከል የአሜሪካ ህገመንግስት 5ኛ ማሻሻያ
ጥፋተኝነትን መከላከል ወይም ያለመናገር መብት የአሜሪካ ህገ መንግስት ለዜጎቹ ያጎናጸፋቸው ዋነኛ የመብት ስብስቦች ናቸው፡፡ ማንም ሰው “በማንኛውም የወንጀል ጉዳይ ተገዶ ምስክርነት እንዲሰጥ አይደረግም“ በማለት አምስተኛው የአሜሪካ ህገ መንግስት ማሻሻያ ይደነግጋል፡፡ ከእንግሊዝ ተሰደው አሜሪካንን በቅኝ ግዛትነት የያዟት የስነምግባር ሰዎች ናቸው ይህንን የተገበሩት፡፡ ምክንያቱም በእምነታቸው ሰዎች ሲጠየቁ ዝም የማለት ወይም በጌቶቻቸው ስቃይ ተገድደው መልስ ያለመስጠት መብት እንዳላቸው የጸና እምነት ስለነበራቸው ነው፡፡ የበላይ ጠያቂ ጌቶች ብዙውን ጊዜ ደጋጎቹን የእምነት ሰዎች የያዙት እምነት ምን እንደሆነ እንዲያምኑ ያስገድዷቸውና ያሰቃዩአቸው ነበር፡፡ ዝም ካሉና ካልተናገሩ ጥፋተኛ ብለው ይፈርጇቸው ነበር፡፡ የእንግሊዝ ህግ በ1600ዎቹ አጋማሽ ጥፋተኝነትን የመከላከል መብት ለዜጎቹ አጎናጽፏል፡፡

ይህ እራስን ከጥፋተኝነት የመከላከል የተቀደሰ መብት የአሜሪካ የወንጀል መከላከል ህግ መሰረት ነው - ማንም የተከሰሰ ሰው ጥፋተኝነቱ ባስተማማኝ ሁኔታ ከጥርጣሬ ባለፈ መልኩ በመንግስት እስካልተረጋገጠ ድረስ ነጻ ነው፡፡ ጥፋተኛ መሆን አለመሆኑን የማረጋገጡ ተግባር ደግሞ የመንግስት፣ የአቃቢያን ህግና የፖሊስ ነው፡፡ የተከሰሰን ሰው ጥፋተኝነት ለማረጋጥ የተከሰሰው ግለሰብ ምንም ነገር ማድረግ የለበትም፣ በተለይም ከፖሊስ ወይም ከአቃቤ ህግ ጋር መነጋገር ወይም መተባበር ግዴታ የለበትም፡፡ የአሜሪካ ኮንግረስ፣ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የአሜሪካ ፕሬዚዳንትም ሆነ የአካባቢ ፖሊስ የአሜሪካንን ዜጋ በማስገደድ ለጥፋተኝነታቸው ማስረጃ የሚሆኑ መግለጫዎችን እንዲሰጥ/እንዳይሰጥ ወይም እንዲያምን/እንዳያምን ማድረግ አይችሉም፡፡

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርደ ቤት የፖሊስን አስገዳጂ የምርመራ ቃለ መጠይቅ ተግባር ያቆመው እ.ኤ.አ. በ1966 ነው፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ “በፖሊስ ምርመራ ጊዜ የህግ መብት ማስጠንቀቂያ“ ለተባለ ቀላል የአሰራር ሂደት ኃላፊነት ሰጥቷል፡፡ በተግባር ሲታይ ይህ የፖሊስ ምርመራ የህግ መብት ፖሊስ ምርመራ ሊያደርግ በሚፈልግበት ጊዜ ተጠርጣሪውን/ዋን በቢሮው ወይም የተጠርጣሪውን/ዋን ነጻነት ሊያውክ በማይችል ሁኔታ መሆን እንዳለበት፣ ተከሳሹ/ሿ ዝም የማለት መብት እንዳላቸው፣ በተጠርጣሪው/ዋ የተሰጠው ምስክርነት ለተጠርጣሪው/ዋ ማስረጃነት ሊውል እንደሚችል፣ተጠርጣሪው/ዋ ከመጠየቁ/ቋ በፊት ከህግ አማካሪው/ዋ ጋር የመምከር መብት እንዳለው/ላት እና ተጠርጣሪው/ዋ የህግ ጠበቃ ለማቆም አቅም ከሌለው/ላት መንግስት ምርመራ ከመጀመሩ በፊት ጠበቃ እንደሚያቆም በግልጽ ያስቀምጣል፡፡ ሆኖም ግን ድርጊቱ ሆን ተብሎ በማወቅ የተፈጸመ ከሆነ፣ ወይም ከስለላ ስራ ጋር የተያያዘ ከሆነ፣ ወይም አንድን ዓላማ ለማሳካት መሰረት አድርጎ የተፈጸመ ከሆነ ወይም በፖሊስ ህገወጥ የምርመራ ዘዴ የተገኘ መረጃ ከሆነ እራስን ከጥፋተኝነት የመከላከል መብት ወይም የህግ የምክር አግልግሎት የማግኘት መብትን ያስነሳል፡፡ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይህን “ሚራንዳህ ወይም በፖሊስ ምርመራ ጊዜ የህግ መብት በቀን ተቀን የፖሊስ ምርመራ ተግባራት ሁሉ እንዲካተት አውጇል፣ ማስጠንቀቂያዎቹም አገር አቀፋዊ ባህል ሆነው እስኪሰርጹ ድረስ ይሰራል”፡፡

በአሜሪካ ህገ መንግስት አምስተኛ ማሻሻያ የተሰጠውን እራስን ከጥፋተኝነት የመከላከል መብት መከላከል እንድችል የህግ ባለሙያነቴ የሰጠኝ መብት በኩራት እንድሞላ አድል ደርሶኛል፡፡ እ.ኤ.አ. በ1998 በህዝብና በፒቪ መካከል በነበረው ጉዳይ የሚራንዳህ የህግ ስርዓት ታስቦበትና ሆን ተብሎ የምስክርነት ማስረጃው (ጥፋተኝነትን አስገደድዶ መቀበል፣ በግዳጅ ማሳመን) በመጣሱ በካሊፎርኒያ ግዛት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርቤ ሽንጤን ገትሬ በመከራከር ማስቀየር በመቻሌ ልዩ ክብርና ሞገስ ይሰማኛል፡፡ በዚያን ወቅት በካሊፎርኒያ ግዛት በሚገኙ የፖሊስ መምሪያዎች ተጠርጣሪዎች በምርመራ ጊዜ ያለመናገርና የህግ ባለሙያ የማናገር መብት እንዳላቸው እየታወቀ ፖሊስ አፋጥጦ በመጠየቅ መረጃን የማግኘት ጥረቱ በጊዜው በነበረው አሰራር ተቀባይነት ነበረው፡፡ ይህ በተወሰኑ የፖሊስና አቃብያነ ህጎች ክልል ወስጥ ይደረግ የነበረው ህገወጥ የአጠያየቅ ስርዓት “ከሚራንዳህ ህግ ውጭ” በመባል ይታወቅ ነበር፡፡

በካሊፎርኒያ ግዛት በፒቪ ፍርድ ቤት ውሳኔ መሰረት “ከሚራንዳህ ምርመራ ውጭ“ የሚደረግ የምርመራ አሰራር በፍፁም አንዲቆም ተደረገ፡፡ እ.ኤ.አ. በ2000 ዘጠነኛው የተዘዋዋሪ ችሎት በሲኤሲጀ እና በሳንታ ሞኒካ ከተማ ተካሂዶ ተጠርጣሪዎች በምርመራ ጊዜ ያለመናገር መብት እንዳላቸው እየታወቀ ይህንን ጥሰው ከሚራንዳህ የምርመራ ህግ ውጭ አስገድዶ ለማሳመን እና ጥፋተኝነትን እንዲቀበሉ ብለው የሚፈጽሙ ፖሊሶች በህገ መንግስቱና በሲቪል ህዝቡ ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት በግል ተጠያቂና ተከሳሽ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡

በማስገደድና በማሰቃየት የተገኘ የእምነት ቃል ፍትሀዊም ተዓማኒነትም የለውም
በወንጀል መከላከል ህግ ተጠርጣሪውን/ዋን አስገድዶ በማሳመን ጥፋተኛ በማድረግ የተገኘ መረጃን ያህል ትኩረትን የሚስብ ነገር የለም፡፡ ፖሊስ ምርመራ የሚያደርግበት ዋና ዓላማ እውነታው ላይ ለመድረስ ወይም ተጠርጣሪው ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ አይደለም፡፡ ብቸኛውና ዋናው ዓላማ የጥፋተኝነት መግለጫዎችን እና የእምነት ቃል ከተጠርጣሪው አንደበት ለመስማትና ይህንን መሰረት በማድረግ በተከሳሹ/ሿ ላይ ክስ ለመመስረት እንዲቻል ነው፡፡ በማስገደድ የፖሊስ ምርመራ ሂደት ጊዜ ተጠርጣሪው ከጥፋተኝነት ነጻ መሆኑን በራሱ አንደበት መግለጽ ይጠበቅበታል፣ ወይም ደግሞ ጥፋተኛ ተብሎ እንዲወሰንበት መንግስትን በማገዝመተባበር ይጠበቅበታል፡፡ “የፖሊስ የበላይነት” በተንሰራፋበት አካባቢ እራስን ጥፋተኛ አድርጎ ማቅረብ ሜዳውን ለእብሪተኛና ለመሰሪ ፖሊሶች ምርመራ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ዜጎችን ለፍትህ እጦት ሰለባ ያደርጋል፡፡

የተጠርጣሪው ወይም የተከሳሹ በፖሊስ ምርመራ ሂደት ዝም የማለት መብት የጥፋተኝነትና የቅጣት ሰለባ ለማድረግ ከሚደረገው ጥረት አንጻር ብዙ አሳማኝ ምክንያቶች አሉ፡፡ ዋናው ጠቃሚ ነገር ፍትሀዊነት ነው፡፡ በሙያው የሰለጠነ የምርመራ ፖሊስ የህግ ጥሰት ፈጽሟል ባለው ተጠርጣሪ ዜጋ ላይ ጥያቄዎችን እንዲያቀርብ በመፍቀድ የግዳጅ የእምነት ቃል ማግኘት በምንም መልኩ ፍተሀዊነትን አያሳይም፡፡ የማስገደድ የምርመራ ዘዴ ፍትሀዊነት በጎደለው መልኩ ሕገመንግስታዊ የማስረጃ ማቅረብን ግዴታ ከመንግስት ከሳሽ አጅ ወደ ተጠርጣሪው እንዲዞር ያደርጋል፡፡ ተጠርጣሪው ፍትህን በአግባቡ ማግኘት እንዲችል ከተፈለገ በፖሊስ የምርመራ ሂደት ጊዜ ተጠርጣሪው የምክር አግልግሎት እንዲያገኝ የህግ ባለሙያ እንዲያገኝ የማድረጉ ሂደት ጠቃሚነቱ የጎላ ነው፡፡ የተጠርጣሪውን የህግ ጉዳይ ፍሬ ነገሩን የተጠርጣሪው የህግ አማካሪ ሳያየው ተጠርጣሪውን ወይም ተከሳሹን በፖሊስ እንዲመረመር ማስገደድ ተገቢነት የለውም፡፡ ለማንኛውም የምርመራ ጥያቄ ተጠርጣሪው ምን መልስ መስጠት እንዳለበትና መልስ መስጠት የሌለባቸውን ጉዳዮች የህግ ባለሙያው ካጠናው በኋላ የተጠርጣሪው የህግ አማካሪ መንግስት ምን መረጃ እንደሚፈልግና ምን መከላከያ ማስረጃዎች እንዳሉ ማወቅ አለበት፡፡

በማሰቃየት ወይም ማንኛውንም የሰብአዊ መብት ረገጣ ዘዴዎች በመጠቀም የተገኘ የእምነት ቃል በምንም ዓይነት ሁኔታ አስተማማኝ መረጃ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ተጠርጣሪዎች በመርማሪ ፖሊሶች የሚደርስባቸውን የአካልና የአዕምሮ ስነ ልቦና ስቃይ ለማቆም ሲሉ ያልሰሩትን ነገር እንደሰሩ አድርገው የእምነት ቃል ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ምግብ፣ ውኃና የመኝታ አገልግሎት የተነፈጉ ተጠርጣሪዎች ግራ በመጋባትና ስቃዩን በማስቀረት መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት ሲሉ የእምነት ቃል ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ ነጻ የሆኑ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ምርመራ ጊዜ ሲጠየቁ ከክሱ ነጻ የሚያወጣቸው እየመሰላቸው ስለእውነት ብቻ ይናገራሉ፡፡ በመሰሪ ፖሊሶች የሚዘረጉላቸውን አሽክላዎች አይገነዘቡም፡፡ እውነቱን መናገር ነጻ የሚያደርጋቸው ይመስላቸዋል፣ ሆኖም ግን ብዙውን ጊዜ እውነታው በተቃራኒው በሰለጠኑ የፖሊስ መርማሪዎች ተጠምዝዞና ተፐውዞ ተጠርጣሪውን ለማዳካም ሲባል ፖሊስ አደናጋሪ ጥያቄዎችን በመጠየቅ፣ በማስፈራራት፣ በመዛትና በማታለል ዓላማውን ለማሳካት ጥረት ያደርጋል፡፡ ነጻ የሆኑ ሰዎች የማያቋርጥ ለሰዓታት የዘለቀ የፖሊስ ምርመራ ከተደረገ በኋላ ያልሰሩትን ወንጀል እንደሰሩ (የሀሰት የእምነት ቃል) የሚያያረጋግጡ ብዙ ማህበራዊና ሳይንሳዊ ጥናቶች አሉ፡፡ በፖሊስ ምርመራ ጊዜ የተጠርጣሪው ዝምታ በዓለም ላይ ከወርቅ፣ ፕላቲኒየም፣ የተከበረ ድንጋይ ወይም አልማዝ የበለጠ ዋጋ አለው፡፡

ማስመሰል ለምን? ጨካኔንና ተያቂ አልባነትን መፍጠር
በ15ኛው ክፍለ ዘመን በእንግሊዝ አገር በተራ ፍርድ ቤቶች ሊከሰሱ የማይችሉና በጣም ታዋቂ የሆኑ ሰዎችን ጉዳይ የሚያይ ተጠያቂነት የሌለው ፍርድ ቤት (በፍርድ ቤቱ ጣሪያ ላይ የኮከብ ምልክት ያለበት) ተመሰረተ፡፡ ይህ ፍርድ ቤት በሚስጥርና የህግ ሂደትን ሳይከተል ምስክሮቸን ሳይሰማ ብይን ይሰጥ ነበር፡፡ በመጨረሻም ንጉሱ ይህን ተጠያቂነት የሌለው ፍርድ ቤት ተፎካካሪያቸውን፣ ተቃዋሚዎቻቸውን እና ትችት የሚያቀርቡባቸውን አካላት ጸጥ ለማድረግና ለማስወገድ ሲሉ ወደ ማጥቂያ ህጋዊ መሳሪያነት አሸጋገሩት፡፡ ገዥው የኢትዮጵያ አስተዳደርም እንደዚሁ በተመሳሳይ መልኩ የራሱን ተጠያቂ አልባ የፔንታጎን ቅርጽ ያለው ፍርድ ቤት በማቋቋምና በጣራው ላይ የኮከብ ምልክት ያለበትን ባንዲራ በመስቀል ስራውን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ህግ የማያከብር መንግስት የማስገደድ እምነት፣ ለህግ ንቀትን የሚፈለፍል ገዥ
የራሱን ህገመንግስት መረን በለቀቀ አኳኋን የሚደፈጥጠውን አገዛዝ ሁኔታ ሁልጊዜ ባሰብኩ ቁጥር እንቆቅልሽ ይሆንብኛል፡፡ ሁልጊዜ ህገመንግስታችን እየተባለ በመንግስት መሪዎች የሚለፈፈው እርባናየለሽ ዲስኩር ከማሳቁም በላይ ምንም እውቀቱ ሳይኖረው ከቅዳሳን መጽሐፍት እየጠቀሰ የሚያነበንበውን የኃይማኖት ደቀመዝሙር እና ምን እንደሚልና ምን እንደሚያደርግ ትርጉም ያለው እውቀት ሳይኖረው በዘልማድ ባህላዊ ባላትን ለማክበር ሽርጉድ የሚለውን ባተሌ እንዳስታውስ ያደርገኛል፡፡ “ሰይጣን ለዓላማው ከመጽሐፍ ቅዱስ ይጠቅሳል“ የሚለውን የሸክስፒርን ስንኝ እንዳስታውስም ያደርገኛል፡፡ የስርዓቱ ገዥዎች ህገመንግስቱን ከአደጋና ከተቃዋሚዎች ጥቃት ለመጠበቅ ከነፋስ የፈጠኑ ናቸው፣ የራሳቸውን ህገመንግስት እራሳቸው በመጣስ ዋጋውን እንዲሚያሳንሱት በውል የተረዱት አይመስልም፡፡ ለዓመታት ደጋግሜ እንደተናገርኩት ለኢትዮጵያ መንግስት መሪዎች ስለህገ መንግስት ወይም የህግ የበላይነትን መስበክ ለተሰበሰቡ አረማውያን (አህዛብ) መጽሐፍ ቅዱስን እንደመስበክ ወይም በጥቁረር ባልጩት ድንጋይ ላይ ውኃ እንደማፍሰስ ይቆጠራል፡፡ በቅርቡ የወጣው የሂዩማን ራይትስ ዎች ዘገባ ገዥው ስርዓት ስለ የህግ የበላይነት ያለውን ጥልቅ ንቀት በጉልህ ያሳያል፡፡

በአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሚገኙ ታላላቅ የህግ ዳኞች አንዱ የሆኑት ሌውስ ብራንዴስ እንዳመለከቱት “ህግ ባለበት መንግስት አገር መንግስት ጥንቃቄ በተመላበት ሁኔታ የህግ ጥበቃ ካላደረግ የመንግስት ህልውና አደጋ ውስጥ ይወድቃል፡፡ መንግስታችን ጠንካራና በየትም ቦታ የሚገኝ መምህር ነው፡፡ ለጥሩም ሆነ ለመጥፎ ነገር እራሱን ምሳሌ አድርጎ ለህዝቡ ያስተምራል፡፡ ወንጅል ተላላፊ በሽታ ነው፡፡ መንግስት እራሱ ህግ የሚጥስ ከሆነ ለህግ ያለውን ንቀት ይፈለፍላል፣ እያንዳንዱ ዜጋ እስከ እራሱ ድረስ ህግ እንዲጥስ ይጋብዘዋል፣ ስርዓተ አልበኝነት እንዲነግስ ይገፋፋል፡፡ የወንጀል ህግን ከማስተዳደር አንጻር ዓላማው ፍጻሜውን ሊያሳምር ይገባል፡፡ የግል ወንጀለኛን ለመዳኘት ሲል መንግስት እራሱ ወንጀልን የሚፈጽም ከሆነ አደገኛ በቀልተኝነት ይሆናል፡፡“ ብራንዴስ “በመንግስት በኩልየግል የስልክ መስመሮችን በመጥለፍ የስለላ ስራ በማካሄድ የእራስን የጥፋተኝነት መረጃ ለማቅረብ የሚደረግ አሰራር ህገወጥ ነው“ በማለት ሀሳባቸውን ቋጭተዋል፡፡

ገዥው አስተዳደር ህግን የሚጥስ ከሆነ ምን መደረግ አለበት? ህገመንግስት ደፍጣጭ ሲሆን? ገዥው አስተዳደር ለህግ የማይገዛ ወንበዴ ከሆነ ምን መደረግ አለበት? ህግን የማያከብርና የሚደፈጥጥ ገዥ አስተዳደር ህግን በሚያከብር መንግስት መተካት አለበት፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ መንግስት ይቃወሙኛል የሚላቸውን ከህግ ውጭ እያስገደደና እያሰቃየ በማሳመን የሚያገኘው የእምነት ቃል ሳያውቀውና ሳይገነዘበው ቀስ በቀስ እራሱ ህግ አልባ ለመሆኑ የእምነት ቃል መስጠቱን ይመሰክርበታል፡፡

“ጤናማ ሰው ሌሎቹን አያሰቃይም- በአጠቃላይ ሲሰቃዩ የነበሩ ወደ አሰቃይነት ይቀየራሉ፡፡” ካርል ጁንግ

tirsdag 29. oktober 2013

የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ አስተዳደር ከተማሪዎች አመጽ ጀርባ ኢሳት እና ሌሎች ሀይሎች እንዳሉበት ገለጸ

ኢሳት ዜና :- ተማሪዎች የርሃብ አድማ በማድረግ ላይ ሲሆኑ ዩኒቨርስቲው ትክክለኛነቱን አረጋግጦዋል፡፡
የተማሪዎች አመጽ የተነሳው መንግስት ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አዲስ የአለባበስ ፤ የአመጋገብ እና የአምልኮ ስርዓት ህግ ማውጣቱን ተከትሎ ነው። ” ተማሪዎች እምነታችሁ ተው ፣ ማተባችሁን በጥሱ” ተብለናል ይላሉ።
በ2004 እና በ2005 ዓም ተማሪዎች ህጉን እንዲተገብሩ ሙከራ ቢደረግም ተማሪዎች ለመቀበል ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ህጉ ሳይተገበር ቀይቷል ሲሉ የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ ከክልል አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት ተናግረዋል።
ተማሪዎች ለዘጋቢያችን እንደነገሩት ቁርስ፣ ምሳ እና እራት ለመመገብ በሀገሪቱ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የተፈቀደው የቀን በጀት 12 ብር ብቻ ነው፡፡ በደብረ ማርቆስ ከተማ 12 ብር አንድ ሻይ እና ዳቦ የመግዛት አቅም የሚሉት ተማሪዎች፣ መንግስት እየመገበን ሳይሆን የርሃብ አድማ ውስጥ እያስገባን ነው ይላሉ።
የተማሪዎችን ጥያቄ ትክክለኛነት የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ ያረጋግጣሉ፡፡ ተማሪዎች የሚቀርብላቸው የምግብ አቅርቦት የበጀት አነስተኛነት ከፍተኛ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ ከመንግስት ፈቃድ ውጭ በሚልየን የሚቆጠር የበጀት ድጎማ እያደረግን ተማሪዎችን ለመመገብ ጥረት አድረገናል የሚሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ሁኖም ግን መንግስት በገመገመውና በተቸው መሰረት የዳቦ ግራማቸው ከ80 ወደ 45 ግራም ዝቅ እንዲል መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ተማሪዎች በ45 ግራም ዳቦ እና ከዚያ ባነሰ ሁኔታ ቁርሳቸውን እንዲመገቡ ተገደዋል፡፡ የዳቦው መጠን ግን ተማሪዎች አውጥተው ባስመዘኑት መሰረት ከ25- 30 ግራም የሚመዝን ሲሆን አንድ ጉራሻ የመሆን አቅም ብቻ ነው ያለው፡፡
በምግብ እጥረት ትምህርት በተጀመረ በወር ጊዜ ውስጥ 32 ተማሪዎች ታመው ወደ ህክምና ተቛማት መወሰዳቸውን ከጤና ጥበቃ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
የደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ንጉሴ ምትኩ የተማሪዎች አመጽ የአመጋገብ እና የአምልኮ ስርዓት የወጣውን ህግ ለማስተግበር በተካሄደው አሰገዳጅ ህግ እና በምግብ ማነስ ምክንያት በተነሳ ርሃብ ላይ ብቻ የተመሰረት ሳይሆን ኢሳት እና ሌሎች ሃይሎች ያደራጁት ሊሆን እንደሚችል፣ ኢሳት ዘገባውን ያቀረበበትን ሰአት አይቶ መናገር እንደሚቻል ገልጸዋል።
በአመጹ ሙሉ በሙሉ የስድስት ህንፃዎች መስታውቶች ወድመዋል፤ ሶስት የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አምቡላንሶችን ጨምሮ ከአገልግሎት ውጭ ሁነዋል፡፡
አመጹን የፌደራል ፖሊስ ለመቆጣጠር በወሰደው እርምጃ በተማሪዎች ላይ ድብደባ ፈጽሟል፡፡
የአካባቢው ነዋሪዎች ለአመጹ ድጋፍ በመስጠታቸው ዬዩኒቨርስቲው መሪዎች ወቀሳ ሰንዝረዋል፡፡ነዋሪዎች በበኩላቸው ተማሪዎች እየራባቸው ሲወድቁ መመልከታቸውን ለደብረ ማርቆሱ ወኪላችን ነግረውታል፡፡ ተማሪዎቹ በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርበው መልስ በማጣታቸው በአጸፋው የወሰዱት እርምጃ አስተማሪ መሆኑንም ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
ESAT

የኢትዮጲያ ወዳጆች በሙሉ እንዲገኙ የከበረ ጥሪ እናቀርባለን

በቅርቡ ከኢትዮጲያ ኦጋዴን/ሶማሌ ክልል በድብቅ ወጥቶ በስዊዲን ቴሌቪዥን የተላለፈው ዶክመንተሪ ፊልም የዓለም ህብረተሰብን ያስደነገጠና ያስቆጣ በመሆን የወያኔን አረመኔአዊ አገዛዝ በድጋሚ አጋልጧል ።
ይህ ሁኔታ በጉራፈርዳ ፣ በቤንሻንጉል ፣ በአሶሳ ፣ በወልቃይት ፣ በኦሮሞ ፣ በአማራ ህዝብ እንዲሁም በመላ ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን የጅምላ ጭፍጨፋ አጉልቶ አሳይቶል ።
በመሆኑም የዓለም አቀፍ ሕግ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የሕግ ጠበቃ Jurist Stellan Gärde ወያኔ በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ስለሚቀርብበት አግባቦችና ቅድመ ዝግጅቶች ላይ ለኢትዮጲያዊያን ማብራሪያ በመስጠት ተዛማጅ መረጃዎችንም ለማጠናቀር በስብሰባው ላይ ይገኛሉ ።
በተጨማሪም በወያኔ እስር ቤት የተሰቃዩት ማርቲን ሸቤ ስላሳለፉት መከራና በዚሁ ዙሪያ የፃፉትን መፀሃፍ ይዘው በመቅረብ ማብራሪያ ይሰጣሉ ።
ዶክተር ሙሉዓለም አዳም በኖርዌይ የፖለቲካ አክቲቪስት ፣ መቶ አለቃ አበረ አዳሙ በኢትዮጵያ ፖሊስ በኃላፊነቶች የሠሩና የኢ.ፒ.ፒ.ኤፍ (EPPF) መሥራችና የአመራር አባል የነበሩ፣ ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ የኢሳት የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አዘጋጅ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ በቪዲዮ የተደገፈ ማብራሪያ ያቀርባሉ ።
አዘጋጅ የኢትዮጲያ ዴሞክራሲያዊ መድረክ
በዚህ ውይይት የኢትዮጲያ ጉዳይ የሚያሳስበው ዜጋና የኢትዮጲያ ወዳጆች በሙሉ እንዲገኙ የከበረ ጥሪ እናቀርባለን ።
የሃገር በባህል ምግብ ቡናና ሻይ ተዘጋጅቷል ቀን ኖቬምበር 2- 2013 ዓ .ም ቦታ Stockholm, Hallunda Folketshus ሰዓት ከቀኑ 13.00 ጀምሮ .
Sweden
Image

በኬንያና በዚምባብዌ የታሠሩ ኢትዮጵያውያን ይከሰሳሉ ተባለ

በህገወጥ መንገድ ወደ ኬንያና ወደ ዚምባብዌ ድንበር ሲያቋርጡ ተይዘው የታሰሩ መቶ ያህል ኢትዮጵያውያን ክስ ይጠብቃቸዋል ተባለ፡፡
ሰሞኑን ወደ ናይሮቢ ሊገቡ ሲሉ በፖሊስ የተያዙት ሀምሳ ሶስት ወጣት ኢትዮጵያውያን ህጋዊ ፓስፖርት እንደሌላቸውና ከአማርኛ ውጪ በእንግሊዝኛ መግባባት እንደማይችሉ የሳምራ ፖሊስ ኮማንደር ኤል ሙታሚያ ተናግረዋል፡፡ ከስደተኞቹ ጋር፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር የሚያካሂዱ ደላሎች ናቸው የተባሉ ኬንያዊያንም ታስረዋል፡፡Ethiopia, Abudrafi, treating kala azar and HIV, November 2010.
በሌላ በኩል የዚምባቡዌን ድንበር አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊሄዱ የነበሩ ሰላሳ ስምንት ኢትዮጵያውያን በሃገሪቱ ፖሊስ ተይዘዋል፡፡ ወጣት ስደተኞቹ ወደ ዙምባብዌ የገቡት በህገወጥ መንገድ ስለሆነ ክስ ይመሰረትባቸዋል ሲል ፖሊስ ገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ በኬንያና በዙምባቡዌ ለታሰሩ ስደተኞች ከመንግስት እገዛ ይደረግላቸው እንደሆነ ከአዲስ አድማስ ተጠይቀው፣ “መንግስት ሁልጊዜም ዜጐቹን የመርዳት ፍላጐት አለው፤ በየአገሩ ያሉ ኤምባሲዎቻችንም በዚህ ፖሊሲ መሰረት እየሰሩ ነው” ብለዋል፡፡
በቅርቡ የወጣው የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት መረጃ እንደሚለው በየአመቱ ከሀያሺ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያዊያን በኬንያ በኩል ደቡብ አፍሪካ ይገባሉ፡፡ (አዲስ አድማስ)

ኢህአዴግ የዘራውን አጨደ፣ ተጠያቂው ማን ነው?

እሳት አስነሳችሁ በሚል እስሩ ቀጥሏል
fire
ሻይ ቅጠል ለማልማት የተፈጥሮ ጥብቅ ደን እንዲያወድም የተፈቀደለት ቬርዳንታ ሀርቨስት የተባለ ኩባንያ በከፍተኛ ወጪ ያለማውና ለመለቀም በደረሰ ምርት ላይ ማንነታቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች እሳት ለቀውበታል። ጥቅምት 12 ቀን 2006 ዓም ደረሰ በተባለው ቃጠሎ ኩባንያው የደረሰበት ሊሳራ እስከ 80 ሚሊዮን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ አስታውቀዋል።
አንጋፋ እድሜ ጠገብና ረዣዥም የተፈጥሮ ደን በመጨፍጨፍ ጣውላ እያመረተ ሲቸበችብ የነበረው ኩባንያ ሙሉ ንብረቱና ከፍተኛ መጠን ያለው የጣውላ ምርት ከተለያዩ ማሽኖች ጋር ወድሞበታል። የአካባቢው የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ኩባንያው ላይ የደረሰው የእሳት ቃጠሎ ለመሰብሰብ የደረሰውን የሻይ ቅጠል ማሳ አጋይቶታል።
በጋምቤላ ክልል በመዠንግር ዞን፣ በጎደሬ ወረዳ በጉማሬና በካቦ ቀበሌዎች የሚገኝ 5000 ሄክታር በደን የተሸፈነ መሬት በኢንቨስትመንት ስም እንዲሸጥ መወሰኑን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ተቃውሞ አሰምተው ነበር። በወቅቱ ውሳኔውን “በባዕድ ወራሪ ሃይል እንኳን የማይፈጸም” በማለት የተቹና ቅሬታቸውን የገለጹ ነበሩ።
ሙሉ በሙሉ በደን የተሸፈነ 3012 ሄክታር ድንግል ለም መሬት በሄክታር111 ብር ሂሳብ ለ50 ዓመት የሊዝ ኮንትራት የተሸጠለት ይህ ኩባንያ ጥብቅ ደኑን ከማውደሙ በፊት ውሳኔው እንዲጤን የአካባቢው ህዝብ በወኪሎቹ አማካይነት ለፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ ጥያቄ አቀርበው ነበር። በወቅቱ ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ድርጊቱን በመቃወም የሚከተለውን ጽሁፍ አትሞ ነበር። ሰሚ ባለመገኘቱ የተፈራው ደረሰ።
ጡረተኛው ፕሬዚዳንት ለአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የተፈጥሮ ደኑ ከመጨፍጨፉ በፊት ውሳኔው እንዲመረመርና እንዲጠና ሚያዚያ 28 ቀን 2002 ዓ ም ለክልሉ ደብዳቤ ልኮ ነበር። ሟቹ ጠ/ሚኒስትር በወቅቱ የአፍሪካ የተፈጥሮ ጥበቃና የአየር ንብረት ተሟጋች ነኝ ያሉበት ወቅት መሆኑንን በማስታወስ፣ የፕሬዚዳንቱን መመሪያ በመጠቆም ባለስልጣኑ የጻፈውን የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ የክልሉ ፕሬዚዳንት ህዳር 10 ቀን በተጻፈ ደብዳቤ ደመሰሱት። ከላይ የተጠቀሰው ኩባንያ የ50 ዓመቱን ውል ቅድሚያ ክፍያ የአንድ ዓመት 19 ሺህ ዶላር ስለከፈለ ቦታውን እንዲረከብ ዞኑንን አዘዙ።
የበላይና የበታቹ በማይታወቅበት የመለስ አወቃቀር ጥብቅ ደኑ ያለበት መሬት ለህንዱ ኩባንያ ተላለፈ። ህዝብ ያነሳውን ጥያቄ እስከ ፕሬዚዳንቱ ያደረሱት ሊቀመንበር እንደ ወንጀለኛ ተቆጥረው ከሃላፊነታቸው ተባረሩ። ህዝብ የኑሮው መሰረትና የህይወቱ ያህል የሚንከባከበው ደን ተጨፈጨፈ። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት ደኑ ሲጨፈጨፍ የነበረው ሃዘን በቃል የሚገለጽ አልነበረም።timber log
ባገኘው ከፍተኛ የደን ምርት ጣውላ ማምረት የጀመረው ኩባንያ መጋዘን ገንብቶ የጣውላ ንግድ ውስጥ ገባ። አሁን ድረስ ንዴቱና የበደል ስሜቱ ያለቀቀቃቸው የአካባቢው ነዋሪዎች የተካሄደባቸውን ግፍ “ዝርፊያ” እያሉ ነው የሚጠሩት።
ህግን ጠብቀው ኢህአዴግን ያሳሰቡት የአካባቢው ነዋሪዎች አሁንም ቢሆን በእስርና በድብደባ በማሰቃየት ኢንቨስትመንትን /ነዋሪዎቹ ዝርፊያ ነው የሚሉት/ በክልሉ ቀጣይ ማድረግ አይቻልም። አስቀድሞ ባቀረቡት አቤቱታ መሰረት ኢህአዴግና ኩባንያው ጆሮ ሰጥተዋቸው ቢሆን ኖሮ እንዲህ ያለ አደጋ ሊፈጠር እንደማይችል አስተያየት ሰጡ አሉ።
92 ሚሊዮን ብር በላይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ እዳ ያለበት የእርሻ ድርጅት፣ ንብረቱ በእሳት ከወደመ በኋላ የተሸከመው እዳ አጀንዳ ሆኗል። የደረሰበት ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ ክልሉንና ኢህአዴግን ካሳ እንደሚጠይቅም ከወዲሁ ተሰምቷል። ዜናውን ያቀበሉ ክፍሎች “ህዝብ ላልተቀበለው ኢንቨስትመንት ካሳና የልማት ባንክ ላይ ለደረሰው ኪሳራ ተጠያቂው ኢህአዴግ ነው” የሚል ጥያቄ መነሳቱን አመልክተዋል።
ለአበባ እርሻ ላስቲክና ኬሚካል በማስያዝ ልማት ባንክን እያለቡ የተሰወሩ በርካታ ድርጅቶችና ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው ሸሪኮቻቸው መኖራቸውን በማስታወስ በጋምቤላ ተመሳሳይ ድርጊት ሊፈጸም እንደሚችል የዜናው ምንጮች ጠቁመዋል። ካራቱሪ በኪሳራ መንገዳገዱን፣ ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በ”ውክልና” ለሳዑዲ አረቢያ ቀለብ እንዲያመርት የተከሉት ሳዑዲ ስታርና ሌሎች የህወሃት ሰዎች ከተለያዩ የአገር ውስጥ ባንኮች ከፍተኛ ገንዘብ መበደራቸውን ገልጸዋል።
“ህዝብን ያለፈቃዱ በማፈናቀልና መሬቱን በመቀማት የሚከናወን ኢንቨስትመንት ሁሌም አደጋ ላይ መሆኑ አያጠራጥርም” በማለት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አኢጋን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ለጎልጉል ገልጸዋል። “ኢንቨስትመንት እንኳን ደህና መጣህ በሚል ህዝብ ካልተቀበለው ዘረፋ ነው” ያሉት አቶ ኦባንግ “በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ ድምጹን ሲያሰማ ጆሮ ያጣ ህዝብ ተቃውሞውን ገለጸ” በማለት በደረሰው ውድመት ባይደሰቱም ለውድመቱ ተጠያቂው ኢህአዴግና ከኢህአዴግ ጋር ተሻርኮ ዝርፊያ ያከናወነው ድርጅት እንደሆነ አመልክተዋል።
ካሩቱሪና ሳዑዲ ስታርን ጨምሮ ህዝብ ላይ በተፈጸመ ግፍ ሃብት ለማፍራትና ለመበልጸግ የሚያስቡ ትልቅ ግንዛቤ ሊወስዱ እንደሚገባ ያሳሰቡት አቶ ኦባንግ “ኢህአዴግ ዝርፊያና ኢንቨስትመንትን ለይቶ መሔድ ካልቻለ ስጋቱ እየጨመረ ይሄዳልና ከስህተት በመመለስ ህዝብ በሚፈቅደው መልኩ ማስተናገድ ግድ ነው” ሲሉ አሁንም ጆሮ የለውም ለሚባለው ኢህአዴግ ማሳሰቢያ አዘል ምክር ለግሰዋል። ባለሃብት የሚባሉትም ከዚህ ታላቅና አሳዛኝ ውድመት ሊማሩና ህዝብ “እንኳን ደህና መጣችሁ እንዲላቸው ህዝብ ከሚቃወመው ዝርፊያና አሰራር ራሳቸውን ሊያገሉ ይገባል” ብለዋል።
የክልሉ ፕሬዚዳንት ቃጠሎውን ማመናቸውን ሪፖርተር በእሁድ እትሙ ያስታወቀ ሲሆን አጣሪ ኮሚቴ ተቃቁሞ አደጋውን ያደረሱት እነማን ናቸው የሚለው እየተመረመረ እንደሆነ ጠቁሟል። የክልሉ የጎልጉል ምንጮች በርካታ ሰዎች እሳት አስነስታችኋል በሚል መታሰራቸውና በፌዴራል አንጋቾች እየተመረመሩ መሆኑን አረጋግጠዋል። እሳት ያስነሱትን ለማጋለጥ በሚል በየመንደሩ በሚደረግ ማዋከብ ነዋሪዎቹ መማረራቸውን ተናግረዋል። ለጊዜው የእስረኞች ቁጥር ባይታወቅም ወደ ማዕከል የተላኩ በርካታ እንደሆኑም ገልጸዋል። በማያያዝም ሁኔታው በዚህ ከቀጠለ ኢህአዴግም ሆነ ማንም ተጠቃሚ ስለማይሆን ህዝብን ማዳመጥ ሊቀድም እንደሚገባው ጠቁመዋል። ምንጭ ጎልጉል

søndag 27. oktober 2013

የኢዴፓ ገበና ሲገለጥ (ሊነበብ የሚገባው ደባ) ዶክተር በየነ እና ሻለቃ አድማሴ በአቶ መለስ ትእዛዝ የወር ደምወዝ ነበራቸው::

                 MUST READ
             
                   
Imageዴፓ ገበና ሲገለጥ (ሊነበብ የሚገባው ደባ)የልደቱ አያሌው ኢዴፓ በየትኛው ሞራሉ ነው ተቃዋሚውንም ይሁን ገዢውን ፓርቲ የሚተቸው??

Ethiopia #EPRDF #UDJ #EDP #BLUEPARTY 

ምንሊክ ሳልሳዊ
የአቶ ልደቱ አያለውን መጽሃፍ የጻፈው በወያኔ ልዩ ትእዛዝ አቶ ገነነ አሰፋ ነው::
ዶክተር በየነ ጴጥሮስ እና ሻለቃ አድማሴ መላኩ በአቶ መለስ ትእዛዝ የወር ደምወዝ ነበራቸው::
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢዴፓ ህልውና አያምንም::ዘላለም ህዝቡ ኢዴፓን በበጎ መንፈስ አያየውም::
በአሁን ሰአት ለተፈጠረው ኢሕኣዴጋዊ አክራሪነት እና የፖለቲካ ጽንፈኝነት ተጠያቂው ኢዴፓ እና አመራሩ ናቸው::

ኢዴፓ ብሎ ራሱን የሚጠራው በኢሕኣዴግ የጎለበተው ድርጅት ባካሄደው ስብሰባ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እና ገዢውን ፓርቲ እንደተቸ እየሰማን ነው:: ኢዴፓ የ97 ምርጫ የህዝብን ድምጽ አፈር የከተተ እና ከገዢው ፓርቲ ጋር መሰሪ ተግባራትን በማከናወን የቅንጅት አመራርን ለእስር ቅንጅትን ደግሞአላማውን በማኮላሸት ድባቅ እንዲመታ ያደረገ ታማኝ ቅጥረኛ በራሱ አጠራር ተቃዋሚ ፓርቲ ነው::ኢዴፓ ለዚህ ላደረገው አፍራሽ ተልእኮ አመራሮቹን ሳይታሰሩበት የፓርላማ ወንበር እና ጉርሻ በማግኘት ተለጥጦ እስከዛሬ ድረስ በገዢው ፓርቲ አመራሮች እና ካድሬዎች የአንበሳነት ቡራኬ እየተሰጠው ይገኛል::

ኢዴፓ በተለያዩ ከገዢው ፓርቲ በተመደቡ የደህንነት ሴረኞች እና ከመንግስት ስልጣን ወደ ፓርቲ ስልጣን በተለወጡ ሰዎች እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች በኢንቨስትመት ስራ ለይ የተሰማረን ነን የሚሉ ከባለስልታናት ጋር በሙስና የተጨማለቁ ሰዎች የሞሉበት በተቃዋሚነት ስም የሚያላዝን የገዢው ፓርቲ አጋር የፖለቲካ አራጋቢ ነው::የገዢውን ፓርቲ ሁኔታ ገመገምኩ የሚለው ኢዴፓ ገዢው ፓርቲ ከፕሮፓጋንዳ ባለፈ ለዴሞክራሲ ሥርዓት መጠናከር ምንም ዓይነት ተጨባጭ ዕርምጃ እየወሰደ እንዳልሆነና ይህም በአገሪቱ የጽንፈኝነት ፖለቲካና አክራሪነት የበለጠ እየተጠናከረ እንዲመጣ አድርጓል ማለቱ ምን ለማለት እና ማንን ለማጭበርበር ፈልጎ አሊያም በየትኛው ሞራሉ ነው ይህንን ሊል የሚችለው ... በሃገሪቱ በ1997 እና ከዛ በኋላ የተገኙ የተቃዋሚ ድሎች እንዲኮላሹ ከማድረጋቸውን በላይ የድርጅቱ አመራሮች ሕወሓት ከመደበላቸው ከአቶ ስብሃት ነጋ በሚወርድ ትእዛዝ የዲሞክራሲ ጭላንጭሉ ከናካቴው እንዲጠፋ እና አሁን ላለንበት የጭለማ አፋኝ ስርኣት እንድንዳረግ አስታውጾ አበርክቷል::በአሁን ሰአት ለተፈጠረው ኢሕኣዴጋዊ አክራሪነት እና የፖለቲካ ጽንፈኝነት ተጠያቂው ኢዴፓ እና አመራሩ ናቸው::

አቶ ልደት አያሌው ኢዴፓን ይመራ በነበረበት ጊዜ በየወሩ 5000 ብር ይከፈለው ነበር እንዲሁም ሙሼ ሰሙ ዶክተር ሶፊያ እና አቶ አብዱ .. እንዲሁ ደሞወዝ ነበራቸው:: አቶ ልደቱ የደህንነት ሚኒስትሩ የነበሩት አቶ ገብረመድህን እስከ 1993 ድረስ ደሞዙን በመቀበል የቆየ ሲሆን ከዛ በኋላ ደሞዛቸውን በበላይነት የሚያገኙት አሁን በሙስና እስር ላይ ከሆነው የደህንነቱ አማካሪ አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ነበር::በ97 ላደረጉት ውለታ ከስድስት ሚሊዮን ብር ስጦታ አግኝተዋል::
ለኢዴፓ አመራሮች ያዘጋጁትን መጽሃፍ ; ንግግር ; ማንኛውንም አርቲክል የጻፈው የገነት ዘውዴ ውንድም አቶ ገነነ አሰፋ ነበር ለዚህም በአቶ መለስ ዜናዊ ትእዛዝ ትልቅ የገንዘብ ጉርሻ ተሰቶታል::ታሪካቸው የማያልቀው ተቃዋሚ ነን የሚሉት የፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ውስጥ ውስጡ እንዲያሽመደምዱ በወቅቱ የፓርላማ አባል የነበሩት ሻለቃ አድማሴ መላኩ እና ዶክተር በየነ ጴጥሮስ ከአቶ መለስ ዜናዊ በተሰጠ ልዩ ምስጢራዊ ትእዛዝ በየወሩ የደህንነቱ አማካሪ የአሁኑ እስረኛ ወልደስላሴ ደምወዝ ይከፍላቸው ነበር::

ኢዴፓ አሁንም በህዝብ ፊት ቆሞ የህዝብን ማንነት ለመካድ እና ራሱን እንደ ህዝብ ፓርቲ ለማሳየት የሚቧጥጠው ነገር እንደማይሳካለት ቢያውቅም ከወያኔ በሚወርድለት ትእዛዝ በሙስና የተዘፈቁ የኮሌጅ ባለቤት የሆኑ የአማራ ክልል ግለሰብ አምጥቶ ሾሟል::የጸረ ሽብር ህጉን እንደግፋለን የሚሉት ከአማራ ክልል ባለስልጣናት ጋር በእከክልህ እከክልኝ ኢንቨስተር የሆኑት የኢዴፓ አዲስ ሊቀመንበር ሙሰኛው አቶ ጫኔ ከበደ በኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካ መሪዎች ጋዜጠኞች እና የሃይማኖት ሰዎች አሸባሪ ናቸው ብለው የሚያምኑ ሰው ናቸው::

እንደ ኢዴፓ/ኢሕኣዴግ እምነት ተቃዋሚዎች የኢዴፓን የተቃዋሚነት ሚናና ህልውና የካዱና፣ በሕዝቡ ዘንድ በበጎ መንፈስ እንዳይታይ ሆን ብለው ሴረኛ አሉባልታዊ ዘመቻ የሚያካሂዱ መሆናቸውን መገንዘቡን ገልጿል፡፡ እነዚህ ፓርቲዎች የወቅቱ ትግል ተጠናክሮ ለድል እንዳይበቃ ዋነኛ እንቅፋት መሆናቸውን ገልጾ ሕዝቡ የእነዚህን ተቃዋሚ ኃይሎች ትክክለኛ ማንነት እንዲገነዘብ ጠይቋል፡፡...ኢዴፓ ለገዢው ፓርቲ ታማኝነቱን ያሳየበት ይህ አባባል አሁንም ቢሆን ኢዴፓ ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በኢዴፓ ህልውና አያምንም::ህዝቡ ኢዴፓን በበጎ መንፈስ አያየውም:: ኢዴፓ 200 አመት እንደ አዲስ እየተወለደ ቢሰራ ተቀባይነት አያገኝም::በሃገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ሳይሆኑ ትግሉን አፈር እያበሉት ያሉት እንደ ኢዴፓ ያሉ ቅጥረኞች መሆናቸውን በአደባባይ ያየነው ጉዳይ ነው::ማንኛውም ተቃዋሚ ፓርቲ ከኢዴፓ ጋር በትብብር እንደማይሰራ የታወቀ ሲሆን ኢዴፓ ራሱ ራሱን መርምሮ ከቅጥረኝነት ወደ ተቃዋሚነት መሸጋገር የራሱ ድርሻ እንጂ ለሌሎች የሚሰጠው መመሪያ አይደለም:: ሌሎች ተቃዋሚ እንደሆኑ ራሳቸውን ያውቃሉ::
የስልጣን ጥመኝነት ያለበት የኢዴፓ አመራር በየትኛው ሞራሉ ህዝብ ፊት እንደሚቀርብ ባይታወቅም በፖለቲካ እፍረት የማይሰማው ቅጥረኛ ፓርቲ መሆኑን ግን በይፋ ያስመሰከረ እና የሆዳሞች እና የሙሰኞች ስብስብ እንደሆነ ማናችንም የምንመሰክረው ሃቅ ነው::