tirsdag 21. april 2015

የወያኔው ካድሬ ሬድዋን ሁሴን በሊቢያ የታረዱ ወገኖቻችንን አስመልክቶ የሰጠው የንቀት አስተያየት!!

ዲቦራ ለማ/ ኖርዌ

በሀገራችን ኢትዮጵያ ላለፉት 24 አመታት የህዝብን ጫንቃ አጉብጦ ህዝብን በዘርና በጎሳ ከፋፍሎ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለወገኖቻቸው ብቻ በማቀራመት ሀገሪቷን የጥቂት ጎጠኛ ወንበደዎች አድርገው እንደ ግል ንብረታቸው ሲቆጣጠሩዋትና ሲገዝዋት እንደነበሩ ለሁላችንም ግልፅ ነው። የሆነው ሆኖ ይሄ ሳያንሳቸው በዛው ልክ እነርሱ ወደ ላይ ኢኮኖሚያቸው እያደገ የሌላ የተማረው ህብረተሰብ ልጆቹን እንኳን በትክክል መመገብ የማይችልበት ደረጃ ደርሶ ዜጎች በፓለቲካ አመለካከታቸው በገዛ ሀገራቸው እንዳይኖሩ ለስደት መዳረግ ከጀመሩ አራት አስርተ አመታት ተቆጥረዋል።

ኢትዮጵያዊያኖች ከሀገራችን ተሰደን በተለያየ አለም ውስጥ የምንገኝ ቢሆንም የሚደርስብን ችግር እንደያለንበት አካባቢ መልኩን ይቀያይር እንጂ ችግሩ እንዳለ ቢሆንም በተይ በየመን፣ በሊቢያ፣ በሱዳ በአጠቃላይ በየአረብ ሀገራቱ እየደረሰ ያለውን ግፍ ግን በምንም አይነት ሚዛን ብናስቀምጠው የሚወዳደረው አይገኝም። አሁን ግን ይህንን ላወራ ሳይሆን በቅርቡ በደቡብ አፍሪካ በወገኖቻችን ላይ የደረሰው አደጋ እጅግ አስደንጋጭና አሳዛኝ ነበር። ይህንን አይነቱ የጭካኔ ስራ ከሰው የተፈጠረ ሰው በእውነት ይህንን ያደርገዋል ብሎ ለማሰብ ከባድ ቢሆንም በወገኖቻችን ላይ ግን ተፈፅሞ አይተናል። 

ይህኛውን አዝነን ሳንጨርስ ISIS የተባለው የአሸባሪ ድርጅት ወደ 28 የሚሆኑ ወገኖቻችንን በሊቢያ በሚዘገንን ሁኔታ መግደሉን የውጪ ሚዲያዎች በፎቶ የተደገፉ ዘገባዎችን አድርሰውን ልባችን ተሰብርዋል። የበለጠ የሚያሳዝነው ዜጎቻችን መሞታቸው እየታወቀ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን አላረጋገጥንም በማለት የሟቾች ቤተሰብ ሀዘናቸውን ተቀምጠው የብሄራዊ ሀዘን ቀን ማወጁ ቀርቶ ቢያንስ እግዜር ያፅናችሁ ብሎ በሚዲያ ለመናገር እኳን ጊዜ ፈጀቶባቸው ምንም አይነት የተቃውሞ መግለጫ እንኳን ሳያወጡ ሌሎች ሀገራት የሃዘን መግለጫዎቻቸውን ሲያቀርቡ ሰማን።

ከሁሉ የገረመኝ ግን አቶ ሬዲዋን ሁሴን በዚህ ጉዳይ ላይ ተጠይቀው ሌሎች ለሚሰደደዱ ሰዎች ትምህርት ይሆናል ብለው አረፉት አሁን ይሄ ሊያሳዝናቸውና ሊያስቆጫቸው ሲገባ እንደመቀጣጫ ይሆን ዘንድ ብለው የሰጡት አስተያየት እጅግ በጣም ውስጤን አስቆጣው እንደው ለመሆኑ እነኚህ የወያኔ ካድሬዎች ከሰው አልተፈጠሩም  ነግ በኔ ነው ለራሳቸው ቢያስቡ ጥሩ ነው። የካድሬው ሬድዋን  አስተያየት ይህን ይመስላል። ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ከታች ይጫኑ።

In Ethiopia, government spokesman Redwan Hussein said officials were in contact with its embassy in Cairo to verify the video's authenticity. Hussein said he believed those killed likely were Ethiopian migrants hoping to reach Europe. Libya has become a hub for migrants across Africa hoping to cross the Mediterranean to enter Europe for work and better lives.
"If this is confirmed, it will be a warning to people who wish to risk and travel to Europe though the dangerous route," Hussein said.

እግዚአብሄር ለሟች ቤተሰቦች መፅናናቱን ይስጥልን ሀገራችንንም ከጨካኝ የወያኔዎች እጅ ፈንቅሎ ያውጣልን። ወገን ሀገራችን ከፍተኛ የብሄራዊ ውርደት በየአቅጣጫ እየደረሰባት ነው የህዝባችንን እምባ ማበስ የምንችለው እኛው እራሳችን አንድ በመሆንና በመተባበር እንዲሁም ህይወታቸውን ሰጥተው ሀገራቸውን ነፃ ለማውጣት በሁለገብ ትግል በረሃ የወረዱ ወገኖቻችንን በማገዝ ትግሉን እናግዝ እያልኩ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።

ድል ለጭቁኑ ኢትዮጵያ ህዝብ!!

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar