fredag 29. august 2014

እስር ቤት የሚገኙት የሽዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሽ በጠበቃቸው እንዳይጎበኙ ተከለከሉ

Habtamu abrhayeshiwas danielእነ የሽዋስ በጠበቃቸው እንዳይጎበኙ ተከለከሉ በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙት የሽዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ አብርሃ ደስታና ዳንኤል ሺበሽ በጠበቃቸው እንዳይጎበኙ መከልከላቸውን የሰማያዊ ፓርቲ የህግ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ይድነቃቸው ከበደ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ የማዕከላዊ ምርመራ ታሳሪዎቹ በሳምንት ሁለት ቀን (ረዕቡና አርብ) በጠበቃቸው እንዲጎበኙ ፈቅዶ የነበር ቢሆንም ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ደንበኞቻቸውን ለማግኘት በተደጋጋሚ ወደ ማዕከላዊ አቅንተው ሳያገኟቸው ቀርተዋል ተብሏል፡፡ ተማም አባ ቡልጉ ወደ ማዕከላዊ ባቀኑባቸው ቀናት ‹‹ሌላ ቀን ታገኛቸዋለህ፣ ስብሰባ ላይ ነን›› እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች እያቀረቡ ቀኑን ሙሉ ሲያስጠብቋቸው እንደነበርና በተለይ በዛሬው ቀን ነሃሴ 23 ደንበኞቻቸውን ለማግኘት እየጠበቁ ከዋሉ በኋላ ‹‹ከፈለክ ችሎት ላይ ታገኛቸዋለህ፡፡ ከዚህ ማግኘት አትችልም›› ተብለው እንደተመለሱ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ‹‹ታሳሪዎች በጠበቃቸው፣ በኃይማኖት አባታቸው፣ በጓደኛና በዘመድ የመጎብኘት መብት አላቸው፡፡ በሳምንት ይህን ቀን ተብሎ በህግ አልተወሰነም፡፡›› በሚል በሳምንት ሁለት ቀን ብቻ ነው የሚጎበኙት መባሉም ስህተት ነበር ያሉት አቶ ይድነቃቸው ‹‹ጭራሹን እንዳይጎበኙ መደረጉ ደግሞ ሆን ተብሎ የተፈጸመ ህገ ወጥ ድርጊት ነው›› ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

13 የኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች እና የጦር መኮንኖች በስዊዲን አለም አቀፍ የጦር ፍርድ ቤት ክስ ተመሰረተባቸው

አስራ ሶስት የኢትዮጵያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኖች እና የጦር መኮንኖች በስዊዲን ሀገር በሚገኘው አለም አቀፍ የጦር ፍርድ ቤት በስዊዲን ከፍተኛ ጠበቆች ክስ ተመሰረተባቸው። እነዚህ ተከሳሾች በግድያ፣ አስገድዶ በመድፈር፣ በስቃይ እንዲሁም ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ማሰርና ማሰቃየት እና በሌሎች ተመሳሳይ ወንጀሎች ክስ ተመስርቶባቸዋል። ክሱንም አለም አቀፍ የወንጀል ምርመራ ፓሊስ መረከቡ ታውቋል። ጉዳት ለደረሰባቸው ኢትዮጵያውያንም የአንድ መቶ ሰላሳ ሚሊዮን የስዊዲን ክሮነት ካሳ ተጠይቆባቸዋል። ክስ የተመሰረተባቸው ተከሳሾች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ቀርቧል።
የክስ መዝገቡ ሲቀርብ

1    አቶ አርከበ እቁባይ
2    አቶ አባዱላ ገመዳ
3    አቶ በረከት ሰምኦን
4    አቶ ሳሞራ የኑስ
5    አቶ አባይ ፀሀዬ
6    አቶ ጌታቸው አሰፋ
7   ሌ/ጀነራል ታደሰ ወረደ
8   አቶ ሀሰን ሽፋ
9   አቶ ሙሉጌታ በርሄ
10 አቶ ነጋ በርሄ
11  አቶ ወርቅነህ ገበየሁ
12 ኮማንደር ሰመረ እና አንድ ስማቸው ያልተገለፀ ሰው ይገኙበታል። ዜናውን ለመስማት ሊንኩን ይጫኑ
http://ethsat.com/video/esat-breaking-news-charges-against-ethiopian-officials/

søndag 24. august 2014

አስራ አንድ ጋዜጠኞች ተሰደዱ


የገዥው ፓርቲ ቅድመ ምርጫ የጽዳት ዘመቻ 10524067_10205094117060836_1496251840_n በአምስት ሣምንታዊ መጽሔቶችና አንድ ጋዜጣ ላይ የተመሰረተውን ክስ ተከትሎ አስራ አንድ ጋዜጠኞች ለስደት ተዳረጉ። አስራ አንዱ ጋዜጠኞች የተሰደዱት በፍትህ ሚኒስቴር ሐምሌ 28 ቀን 2006 ዓ.ም. “የዐመጸ ቅስቀሳና የሐሰት ወሬዎችን በመንዛት ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን ለመናድ ጥረት አድርገዋል” በተመሰረተባቸው ክስ መሆኑን የደረሱን መረጃዎች ያስረዳሉ።
ፍትህ ሚኒስቴር ክስ የመሰረተባቸው ሎሚ፣ ዕንቁ፣ ፋክት፣ ጃኖ እና አዲስ ጉዳይ መጽሔቶች እና አፍሮ ታይምስ ጋዜጦች ሲሆኑ፤ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አስራ አንድ ጋዜጦች ለስደት መዳረጋቸውን ለማረጋገጥ ችለናል።

ተሰዳጆቹ ጋዜጠኞች
1፣ ቶማስ አያሌው (የአፍሮ ታይምስ ጋዜጣ ማኔጂንግ ዳይሬክተር)፣
2፣ ግዛው ታዬ (የሎሚ መጽሔት አሳታሚ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር)፣

3፣ ዳንኤል ድርሻ (የሎሚ መጽሔት ሚዲያ ዳይሬክተር)፣
4፣ ሰናይ አባተ ቸርነት (የሎሚ መጽሔት ዋና አዘጋጅ)፣
5፣ አቦነሽ አበራ (የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር)፣
6፣ ሰብለወንጌል መከተ (የሎሚ መጽሔት ከፍተኛ ሪፖርተር)፣
7፣ እንዳልካቸው ተስፋዬ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት አሳታሚ)፣
8፣ ኢብራሂም ሻፊ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ምክትል ዋና አዘጋጅ)፣
9፣ እንዳለ ተሼ (የአዲስ ጉዳይ መጽሔት ከፍተኛ አዘጋጅ)፣
10፣ ሃብታሙ ስዩም (የአዲስ ጉዳይ አዘጋጅና አምደኛ) እና
11፣ አስናቀ ልባዊ (የጃኖ መጽሔት አሳታሚ እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር) ናቸው።

ጋዜጠኞቹ የተሰደዱት በደረሰባቸው ወከባ፣ እንግልት፣ ማስፈራራት፣ የቢሮ መታሸግ እንዲሁም ፍትህ ሚኒስቴር በመሰረተባቸው የክስ እስከ አስራ ስድስት ዓመት በእስር ሊቆዩ እንደሚችሉ በመረዳታቸው መሆኑን ለመረዳት ችለናል።
በጋዜጠኞቹ እና በአሣታሚ ድርጅቶቹ  ሽብርተኝነት የተከሰሱትን ሦስት ጋዜጠኞችና ስድስት ብሎገሮችን ተከትሎ በስድስት የሕትመት ውጤቶች ላይ የተመሰረተውን ክስ መዝገቦች
በጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው ተካልኝ እና ለግዛውና ቶማስ ኢነተርቴይንመን የፕሬስ ሥራዎች ኃ/የተወ/የግል ማኅበር ላይ የተመሰረተባቸው ክስ
10638025_10205094117020835_1656867008_n10615664_10205094120900932_988603941_n











በጋዜጠኛ ግዛው ታዬ ሆረደፋ እና በዳዲሞስ ኢንተርቴይመንት እና የፕሬስ ሥራዎች ኃ/የተወ/የግል ማኅበር ላይ የተመሰረተባቸው ክስ 10582234_10205094121620950_1897194456_n10615672_10205094120020910_340447533_n10620975_10205094118980884_1720323987_n

















በጋዜጠኛ አስናቀ ልባዊ መሸሻ እና በአስናቀ ኢንተርቴይንመንትና ፕሬስ ሥራዎች ኃ/የተወ/የግል ማኅበር ላይ የተመሰረተባቸው ክስ
10613877_10205094119940908_760332787_n10581612_10205094117940858_695020210_n











በጋዜጠኛ አለማየሁ ማሕተመወርቅ ገብረአጋይስት እና በአለማየሁ ሕትመትና ማስታወቂያ ኃ/የተወ/የግል ማኅበር ላይ የተመሰረተባቸው ክስ 10638025_10205094117020835_1656867008_n 10622204_10205094114860781_1427162277_na

mandag 18. august 2014

የኢትዮጵያችን ችግር ገዢዎች እና አደርባዮቻቸው የሚፈጥሩት የፖለቲካ ካንሰር ነው::…. .. እየተገፋን እስከመቼ?? ተነስ እንጂ ወገን !!

 - ምንሊክሳልሳዊ

August18/2014
ሁኔታዎች ገዢው ፓርቲ ብቻ በሚፈልገው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ደጋግሜ ለመናገር የምንፈልገው ለሃገርም ለህዝብም ከባድ እና አደገና አደጋ እንዳለው ነው:: በፖለቲካ ታማኝነት ያልተማሩ እና ከካድሬ ትምህርት ቤት ተመርቀው የወጡ በፖለቲካ ጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የአገርን አመራር እና የህዝብን አንድነት ሊጠብቁ ስለማይችሉ በሃገሪቱ የፖለቲካ መስክ ትልቅ በሽታ ሆነዋል::

በሃገሪቱ የተከሰተውን ደዌ ከማዳመጥ ይልቅ በሽሙጥ አንዱ አንዱን እየወገረው በመብረር ላይ እንገኛለን :; እርስ በእርስ ከመወጋገር ያድነን እንዳንል እየተወጋገርን ጸሎት ለቅጽበት ነው::ማን ከማን ይማር ሎሌ ከንጉሱ ሆኖብን ሆነና የራሳችንንም ሆነ የሃገራችንን ህመም ተጋግዘን እንዳናድን ራሳችን በሽታ ሆነናል::ምን እንደተባልን እንኳን ማዳመጥ አለመቻላችን አንዱ ደንቃራችን ሲሆን የምንናገረውንም ከማንነገርው መራርጠን መተንፈስ እስኪያቅተን ድረስ እያቃተትን በሽታችንን እያባስን ብዙሃዊ ተላላፊ ህመም አድርገነዋል ከዚህ ይሰውረን እንዳንል ራሳችን አሁንም ደንቃራ ሆነናል::

የኢትዮጵያችን ችግር ገዢዎች የሚፈጥሩት የፖለቲካ ካንሰር ነው::ልዩነት እንዳለ ሆኖ በጋራ ሃገራዊ መርህ ላይ ያልተመሰረተ ፖለቲካ እንዴት ህዝባዊ መተሳሰብ ሊፈጥር እንደሚችል በሃገራችን የሚገኙ ፖለቲከኛ ነን የሚሉ አልተረዱትም ወይንም አውቀው እየተባሉ እያባሉን እያነካከሱን ነው:: በጋራ መተሳሰብ ላይ ያልተመሰረተው ፖለቲካችን እና በመጭበርበር የሚያጭበረብሩን ገዢዎቻችን ለነገ ሃገር ተረካቢ ትውልድ አደገኛ የሆነ የፖለቲካ በሽታ እያወረሱ ይገኛሉ፤ የፖለቲካ በሽታ ብቻ ሳይሆን በአንድ ወጥ መርህ ላይ የተመሰረተ እና የደቀቀ ኢኮኖሚ ጭምር:: ይህ በተጭበረበረ ፖለቲካ ላይ የተገነባ ኢኮኖሚ የህዝቦችን የጋራ መደጋገፍ በማስመጥ ገዢው መደብ በፍጹም ከኔ ውጪ የሚነካ ካለ እሳት እንደነካ ነው በማለት በፍራቻ ላይ የተመሰረተ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ዜጎች በሃገራቸው ብሄራዊ አጀንዳ ጉዳይ እንዳይሳተፉ እንዳይተሳሰቡ እንዳይደጋገፉ እንቅፋት ሆኖ ይገኛል::ከማህበረሰቡ ተገልሎ እየተሰራ ያለውን ውጤት እያየነው ነው::

በሃገራችን በመጀመሪያ ደረጃ ሁሌ ለገዢዎቹ የሚኒነግራቸው ቢኖር የህግ የበላይነት እንዲከበር ነው:: የስልጣን እድሜ ለማስረዘም ሲባል በሃገሪቱ ገንዘብ የተገዙ የፓርቲ ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ከህግ በላይ በመሆን አሳር እና አበሳ እያሳዩን ሲሆን ይህንንም ከተራ ዜጋ ጀምሮ እስከ ሃይማኖት መሪዎች ድረስ አበቱታ እያሰሙ የህግ ያለህ የመንግስት ያለህ እያሉ ነው::ሲታይ ግን ምንም መፍትሄ ያለው አይመስልም ይህ ደግሞ ገዢ ነኝ ባዩ አካል የስርኣት ለውጥ ማምጣት ስለማይችል በህዝቦች የጋራ ትግል ለውጡን ተከትሎ ህግና ደንብ ሊከበር እንደሚችል የሚታወቅ እና የተጠና ነው::በዚሁ ከቀጠለ ግን አገር ከገባችበት አደጋ ወደ ሌላ አደገኛ አደጋ እንደምትሸጋገር ለመናገር እወዳለሁ::

ሌላው የተንሰራፋው ሙስና የሃገር ሃብትን በተገቢው ቦታ ላይ እንዳናውል እንቅፋት ሆኗል:: ሁሉም በተደጋጋሚ ታግለው ስልጣን እንደያዙ የሚደነፉት የወያኔ ጁንታ አባላት በሙስና ውስጥ ተዘፍቀው አገሪቷን እርቃኗን አስቀርተዋታል:: ይህ አደገኛ የሙስና ሂደት ህዝብን ወደ ኑር ውድነት እና ድህነት እስር ውስጥ ከቶታል:: ተናግረን የማንጨርሳቸው እስር፣ ስደት ፣ስራ አጥነት ፣ግድያ ፣ክስራ መፈናቀል፣ ተመሳሳይ ምእንግስታዊ ውንብድናዎችቸና ሽብሮች በዜጎች ላይ እየተፈጸሙ በገሃድ እየታዩ እንዲሁም መንግስትዊ ቅጥፈት/ውሸቶች በአደባባይ እየተደሰኮሩ የትውልድን ሞራል ለመግደል ካለመታከት እየተውተረተሩ ነው። ራሳችንን ማንቃት ለለውጥ መነሳት ግድ ይለናል ፤ ደጋግመን እንናገራለን በሕዝብ ልጆች አፋጣኝ ትግል እጅግ ሊለወጥ የሚገባው ጉዳይ መሆኑን ለማሳወቅ እወዳለሁ :: በተጨማሪ በፖለቲካ ታማኝነት ያልተማሩ እና ከካድሬ ትምህርት ቤት ተመርቀው የወጡ በፖለቲካ ጥላቻ የተሞሉ ሰዎች የአገርን አመራር እና የህዝብን አንድነት ሊጠብቁ ስለማይችሉ በሃገሪቱ የፖለቲካ መስክ ትልቅ በሽታ ሆነዋል::

የፖለቲካ ካንሰራችንን ተነጋግረን እና በጋራ ሆነን ከማዳን በጉልበት በሽሙጥ እና እኔ አውቅልሃለሁ በሚል አባዜ እስከመቼ ድረስ እንደምንቀጥል አልታወቀም:: ሁኔታዎች ገዢው ፓርቲ ብቻ በሚፈልገው መንገድ የሚቀጥል ከሆነ ደጋግሜ ለመናገር የምንፈልገው ለሃገርም ለህዝብም ከባድ እና አደገና አደጋ እንዳለው ነው:: ሁላችንም ዜጋ እስከሆንን ድረስ ለሃገራችን እኩል አስታውጾ ማበርከት አለብን ።….እየተገፋን እስከመቼ?? ተነስ እንጂ ወገን !! #ምንሊክሳልሳዊ

søndag 17. august 2014

እንደገና ይድረስ ለሠራቱ


“የትግሬ” ነፃ አውጪ ነኝ ብሎ ራሱን የሠየመው የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን አገሪቷን እያጎሳቆለ ያለው ከሠራዊቱ ጀርባ ተንጠላጥሎ መሆኑ ይታወቃል። ይህ የዘረኞችና የዘራፊዎች ቡድን የተሸከመውን ሠራዊት ሳይቀር በጉስቁልናና በድንቁርና እንዲኖር ፈርዶበታል። ህወሃት ሠራዊቱ እንዲማር፤ ዘመኑ ከሚፈቅደው የቴክኖሎጂ እውቀት ጋር ራሱን እንዲያዋህድ እና በራሱ የሚተማመን የዘመነ ሠራዊት እንዲሆን ፍላጎት የለውም።አሜሪካን በአገሯ በሚገኙ የጦር ትምህርት ተቋማት ውስጥ ወታዶሮችን ለማሰልጠን ፍላጎት ብታሳይም ሳሞራ የኑስና መለስ ዜናዊ እምቢ ማለታቸውን አብዛኛው የሠራዊቱ አባላት የሰሙት አይመስልም። አሜሪካን በሁለት ዓመት ውስጥ ብቻ 42 ወታደሮችን አገሯ ወስዳ ለማስለጠን በጠየቀች ግዜ ሳሞራ የፈቀደው 13 ወታደሮች ብቻ ሂደው እንዲማሩ ነው። እነዚህም ከህወሃቶች መካከል ፊደል የቆጠሩ ተፈልገው በመገኘታቸው መሆኑም ታውቋል። በሠራዊቱ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች የትምህርት ዝግጅት ቢኖራቸውም የትምህርት እድሉን ተከልክለዋል።
ህወሃት ከራሱ ውጪ ያሉት ሌሎች ላይ ምንም ዕምነት እንደሌለው በተለያየ አጋጣሚ ተናግሮታል። የትምህርት ዕድሉን ለምን መጠቀም እንዳልፈለጉ ሲጠየቅ ሳሞራ የኑስ “ሌሎችን አናምናቸውም አሜሪካን ሂደው ይቀራሉ” ብሎ መልስ መስጠቱም ተመዝግቦ ይገኛል። 11ኛ ክፍልን ያልዘለለው የህወሃቱ ኢታማዦር ሹም ሳሞራ የኑስ ሠራዊቱን ታማኝና የማይታመኑ በሚል ይከፍላቸዋል። የህወሃት አባል የሆነ ወታደር ታማኝ ፤ ሌሎች የሠራዊቱ አባላት የማይታመኑ።
አሁንም የሠራዊቱ አባላት ስሙ !
እናንተ ምንም ያክል ጥሩ ዜጋ ለመሆን ብትጥሩ በህወሃቶች ዘንድ የምትታመኑ አይደላችሁም። ህወሃቶች ከእነርሱ ውጪ ባሉ ሌሎች ላይ ጥርሳቸውን እንደነከሱ እስከ ዛሬ አሉ። በሌሎች ዜጎች ላይ የመዘዙት የበቀል ሰይፍም ወደ ሰገባው የሚመለስ አልሆነም። በሁለት ዓመት ውስጥ 42 ወታደሮችን አሜሪካን ወደ አገሯ ወስዳ ለማስልጠን ብትጠይቅም 13ቱን ብቻ ተቀብለው 29ኙን አንፈልግም ማለታቸው የተመዘዘው የበቀል ሰይፋቸው አንዱ አንጓ መሆኑን የትምህርት ዕድሉን የተነፈገው የሠራዊቱ አባል ልብ ሊለው ይገባል። እነ ሳሞራ የኑስ ከእነርሱ ውጪ ያሉ ሌሎች ዜጎች በድንቁርናና በችጋር እየተሰቃዩ ይኖሩ ዘንድ ፈርደውበታል። በእንዲህ ሁኔታ እንዲኖር የተፈረደበት ሠራዊት፤ ውጪ አገር ሂዶ እንዳይማር የተከለከለ ሠራዊት፤ ዘር ሃረጉ እና ድርጅታዊ ታማኝነቱ እየታየ ለሹመት የሚበቃው የሠራዊት አባል ይህን ውስኔ ለወሰነበት ለመለስ ዜናዊ ፋውንዴሽን ከሚያገኛት ከወር ደመወዙ ላይ ቆርጦ እንዲከፍል ይደረጋል። እንዲህ ዓይነት በደል በየትኛውም አገር ታይቶ አይታወቅም።
በችጋር እንድትኖሩ ከምታገኟት ከወር ደመወዝችሁ ላይ ይወሰዳል፤ ተምራችሁ ራሳችሁን እንዳትቀይሩ በነፃ የሚገኘውን የትምህርት ዕድል እንኳ እንዳትጠቀሙ ተከልክላችኋል። በዚህ ሁኔታ እንድትኖሩ ከተፈረደባችሁ በኋላ የገዛ ወገኖቻችሁን ደም በከንቱ እንድታፈሱ ትደረጋላችሁ። የቀደመው ትውልድ በደሙ ያቆመው ድንበር ፈርሶ እና ዜጎች ተፈናቅለው መሬቱ ለባዕድ ሲሰጥ አናንተ ቁማችሁ ትመለከታላችሁ። ያ የሚፈሰው ደም የራሳችሁ ደም፤ ተፈናቅሎ ሜዳ ላይ የሚወድቀው የገዛ ወገናችሁ መሆኑን ለማሰብ እንኳ ነፃነት ያጣችሁ ትመስላላችሁ። የህፃን ደም በአዲስ አበባ ጎዳና ላይ ሲፈስ ለምን ስትሉ አልተሰማም፤ ጋምቤላዎች ለዘለዓለም ከኖሩበት መሬት ተፈናቅለው መሬታቸውን ሌሎች ሲቀራመቱት ይሄ አይሆንም ለማለት የያዛችሁት ነፍጥ የሸንበቆ ምርኩዝ ሁኖባችኋል። በኦጋዴን ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈፀም ተባባሪ ትሆናላችሁ። ህወሃቶች በዚያች አገር ለሚፈፅሙት ማንኛውም ወንጀል እናንተ የእነርሱ በትር ሁናችሁ ታገለግላላችሁ። ከዚያች አገር ከሚገኘው ሃብት ግን ተካፋይ አትሆኑም። እነርሱ ሚሊየነር ሁነው የሚያደርጉትን ሲያጡ፤ አናንተ የሠራዊቱ አባላት ግን በችጋር ከነ-ቤተሰቦቻችሁ ትሰቃያላችሁ። ይሄ ሁኔታ ማብቃት የኖርበታል።
የአገሪቷ መከላከያ ኃይል ራዕይ ተብሎ የተነገረህ እንዲህ ይላል “. . . ለህገ-መንግስቱ እና ለህዝቡ ፍፁም ታማኝ የሆነ . . . የሃገራችን ህዝቦች ተምሳሊት የሆነ . . . የእውቀት መፍለቂያ የሆነ ሠራዊት መገንባት “
ምንም እንኳ ጥሩ ራዕይ ተቀርፆ የተቀመጠ ቢሆንም አንተ የሠራዊቱ አባል ግን የዚህ ራዕይ ተካፋይ አይደለህም።አንተ የምትካፈልው መከራውን እንጂ መልካሙን ራዕይ አይደለም። ለህገ-መንግስቱ እና ለህዝቡ ፍፁም ታማኝ የሆነ ሠራዊት መገንባት የሚለውን ራዕይ መልሰህ መልሰህ እንድታስብ እንመክርሃለን። በእኛ በኩል ግን ህወሃት በአገሪቷ ጫንቃ ላይ ከተቆናጠጠ ዘመን ጀምሮ ህዝቡን ሲያዋርድ ኖረ እንጂ ለህዝብ ታማኝ ሲሆን አልታየም። ህገ-መንግስት ብሎ ራሱ እዚያ ጫካ ሁኖ የፃፈውን ራሱ ሲያፈርሰው ኖረ እንጂ ሲያከብረው አላየንም። ህወሃት ለህገ-ማንግስቱ እና ለህዝቡ ታማኝ ሁኖም አያውቅም። ወደ ፊትም ራሱን ከህዝብ እና ከህግ-በታች አድርጎ እንዳይኖር እሰከ ዛሬ ሲፈፅመው የኖረው ወንጀል የሚያስችለው አይሆንም። ህወሃቶች ከነ እድፋቸው ወደ ማይቀረው መቃብራቸው መሄድን የመረጡ ስለሆነ ሠራዊቱ ራሱን ከእነዚህ ነውረኞች ለይቶ ለህገ-መንግስቱና ለህዝቡ ፍፁም ታማኝ መሆኑን ማስመስከር ይጠበቅበታል።
ሌላው ከህወሃት ውጪ ያላችሁ የሠራዊቱ አባላት ልታስቡበት የሚገባው ዓቢይ ነገር ደግሞ ‘የሃገራችን ህዝቦች ተምሳሊት የሆነ ሠራዊት መገንባት ‘ የሚለውን ራዕይ ነው። ሃገራችን ከ80 በላይ ብሄሮች የሚኖሩባት መሆኑ ይታወቃል።ለዚህች አገር ምሳሌ ሊሆን የሚችል መከላከያ ኃይል መገንባት እንደ ራዕይ የተቀመጠ ቢሆንም በተግባር የሆነው ግን ሌላ ነው። አሁን ባለው የአገሪቷ መከላከያ ኃይል ውስጥ ያሉ የጦር አዛዦችን ቀና ብለህ አይተህ እውነት መከላከያ ሃይሉ የህዝቦቿ ተምሳሊት የሆነ ሠራዊት መሆኑን ራስህ እንድትመልስ እንጠይቅሃለን። በአገሪቷ የተሾሙ ጄኔራሎች ከአንድ ጎጥ እና መንደር የተሰባሰቡ መሆናቸው በምን መልኩ የሃገራችን ህዝቦች ተምሳሊት የሆነ ሠራዊት ሊሆን እንደሚችል ህወሃቶችን ደግሞ ደጋግሞ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል።
በመጨረሻም ‘የዕውቀት ምንጭ የሆነ ሠራዊት መገንባት’ የሚል ራዕይም በጉልህ ተፅፎ ተቀምጧል። የህወሃት የጦር አበጋዞች ከ7ኛ ክፍል ያልዘለሉ፤ካርታ ይዘው የቆሙበትን ሥፍራ እንኳ ለማሳየት የሚደናበሩ መሆናቸው የታወቀ ነው። እነዚህ ፊደል ቆጥረው ያልዘለቁ ቡድኖች የሚመሩት ተቋም እንደምን ሁኖ የዕውቀት ምንጭ ሊሆን እንደሚችል የሚያውቅ የለም። የህወሃቶች እውቀት የንፁሃን ደም ማፍሰስ፤ የድሃ ሃብት መዝረፍ፤ እኔ ብቻ ባይነት እንጂ ከዝህ የዘለለ ሌላ እውቀት ያላቸው አይደሉም። እነርሱ ባለመማራቸው የጎደለባቸው ነገር አለመኖሩን እያዩት ለትምህርትና ለተለየ ዕውቀት ዋጋ ይሰጣሉ ማለት አይቻልም። ሌሎቹም ተምረው እውቀት እንዲገበዩ ለማድረግ ስብዕናቸው አይፈቅድላቸውም። በዚህም ምክንያት ከውጭ አገራት በነፃ የሚገኘውን የትምህርት ዕድል እንኳ ወታደሩ ተጠቅሞ ራሱን በእውቀት እንዳያዳብር ይከለክላሉ። እንዳይማር የተከለከል የሠራዊት አባል እንደምን ሁኖ የዕውቀት መፍለቂያ ሊሆን እንደሚችል የሠራዊቱ አባላት የሽፍቶቹን ቡድኖች መጠየቅ ይኖርባችኋል።
የሠራዊቱ አባል የህዝብ አካል መሆንህን አትርሳው። ነገ ዞረህ የምትገባውም እዚያው ከወጣህበት ህዝብ መሆኑን እኛ ልናስታውስህ እንወዳለን። አሁን ባለው አካሄድህ የወጣህበትህን ድንኳን፤ በዚያች ድንኳን ውስጥ ሁነህ ያሳደጉህ ወገኖችህን እያሳደድክ መሆንህን አስታውስ። የወጣህበትንም ድንኳን እያፈረስክ ነው። ድንኳንህንም አፍርሰህ ከጨረስከው ነገ ዞሮ ማረፊያ እንደማይኖርህ ደግሞ እኛ ልናስታውሰህ እንፈልጋለን። ጥሪያችንን መስማት ከማንም በላይ ለራስህ ይበጅሃል። የወገኖችህን ጥሪ ሰምተህ በወገኖችህ ላይ የተመዘዘውን የበቀል ሰይፍ ለማቆም ከህዝብ ጎን መሆንን አልመርጥ ካልክ መጨረሻህ አያምርም። እነ ሳሞራ የኑስ ጠላቶችህ እንጂ ወገኖችህ አይደሉም። እነ ሳሞራ የኑስ አንተንና ልጅ ልጆችህን ጭምር በድንቁርና አዘቅት ውስጥ አኑረው ቀጥቅጠው ለመግዛት ያላቸው ፍላጎት ወሰን እንደሌለው ማወቅ ይኖርብሃል። የተሸከምከው መሣሪያ ለፍትህ ለእኩልነት፤ ለነፃነት እና ለእውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ እንቅፋት የሚሆኑትን የሚፋለም ሊሆን ይገባዋል እንጂ እነዚህን ጥያቄዎች ባነሱ ወገኖች ላይ የሚያነጣጥር መሆን አይኖርበትም።
እንግዲህ ምን እናድርግ እያላችሁ የምትጠይቁን አላችሁ። ለዚህ ጥያቄ መልሱ ያለው ከእናተው ደጅ ነው። እኛ ያነሳነውን ጥያቄ ባላችሁበት ሁናችሁ ማንሳት ትችላላችሁ። አብዛኛው ሠራዊት ጥቂት ዘረኞችንና ዘራፊዎችን ተሸክሞ የሚኖሩበት ሁኔታ ለመቀየር ሦስትም አራትም እየሆናችሁ እምቢ ማለት መጀመር አለባችሁ። ህወሃቶችን ተሸክማችሁ፤ የህዝባችሁ ጠላቶች ሁናችሁ፤ አገራችሁንና ህዝባችሁን አዋርዳችሁ የምትኖሩት ኑሮ ኑሮ አይደለምና እምቢ አይሆንም ማለት ጀምሩ። ለዘረኞቹና ለዘራፊዎቹ ህወሃቶች ከመሞት ይልቅ ለፍትህ፤ ለእኩልነት እና ለነፃነት ብላችሁ ብትሠው መሥዋእትነታችሁ ለዘላለም ሲዘከር ይኖራል፤ ስማችሁም ከመቃብር በላይ ይሆናል።ፍፃሜያችሁም የጀግና ፍፃሜ ይሆናል።
ፍፃሜያችሁ የጀግና ፍፃሜ እንዲሆን ለፍትህ፤ ለነፃነት እና ለእኩልነት ዘብ የምትቆሙ ሁኑ እንጂ የአንድን ዘረኛና ዘራፊ ቡድን እድሜ ለማራዘም የምትቆሙ አትሁኑ።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ !!!

lørdag 16. august 2014

በሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች የተጀመረው እስር ተጠናቅሮ ቀጥሏል


ሰማያዊ ፓርቲ እንደዘገበው፦
blue party
ከአሁን ቀደም አራት የሰማያዊ ፓርቲ የአርባ ምንጭ አስተባባሪዎች በሽብርተኝነት ስም መታሰራቸው ይታወቃል፡፡ እነዚህን እስረኞች ያሉበትን ሁኔታና የዞኑን አደረጃጀት ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ (ከማዕከል) የድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድና የድርጅት ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል የሆነው ዮናስ ከድር ለጉብኝት በሄዱበት ወቅት ሲያስተባብሩ የነበሩት አባላት ከማዕከል የሄዱት የፓርቲው አመራሮች ሲመለሱ ለእስር መዳረጋቸውን ከአካባቢው የደረሰን መረጃ ይጠቁማል፡፡
በመሆኑም አቶ ከሳሁን አየለ የተባለው የሰማያዊ ፓርቲ አርባምንጭ አስተባባሪ ከአዲስ አበባ የመጡትን የፓርቲው አመራሮች ጋር በመሆን የዞኑን አደረጃጀትና በእስር ላይ ያሉትን የፓርቲው አስተባባሪዎች አስጎብኝቷል በሚል መታሰራቸው ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ሻምበል ካሳ የታሰሩትን ጠይቀሃል በሚል ለእስር መዳረጋቸውንና ነፃነት የተባለው የፓርቲው አስተባባሪ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር እንዳይሰራና በታሰሩት ላይ እንዲመሰክር በማስፈራሪያ መለቀቁ ታውቋል፡፡
በዞኑ የሚገኙ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች እስራትና መከባ እየደረሰባቸው ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ሉሉ መሰለ፣ በፈቃዱ አበበ፣ ካሳሁን አየለ፣ ሻምበል ካሰና ኢ/ር ጌታሁን የተባሉት የፓርቲው አስተባባሪዎችና አባላት በእስር ላይ እንደሚገኙ ለመረዳት ተችሏል።

fredag 15. august 2014

ቴዲ አፍሮ ሌሎች ድምጻውያን ያልነኩትን አዲስ ሃሳብ ይዞ አዲስ ነጠላ ዘፈን ከክሊፕ ጋር ሊለቀቅ ነው


ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በሰሜን አሜሪካ ካሊፎርኒያ፣ ኒዮርክ፣ ሲያትል፣ ሚኒሶታና ቴክሳስ የሙዚቃ ኮንሰርቶቹን ካቀረበ በኋላ ወደ አዲስ አበባ የተመለሰ ሲሆን እዛም የተመለሰው የጀመራቸውን ነጠላ ዜማዎች ለማጠናቀቅ እንደሆነ የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል።
teddy afro
እንደምንጮቻችን ገለጻ ቴዎድሮስ ካሳሁን በቅርቡ የሚለቀው ነጠላ ዜማ ቪድዮ ክሊፕ የሚኖረው ሲሆን አብዛኛው ሥራም መጠናቀቁም ታውቋል። ዘፈኑም የሙዚቃው ክሊፕም አንድ ላይ እንደሚለቀቅ የጠቆሙት ምንጮቻችን ዘፈኑ እንደተለመደው እስካሁን ሌሎች ድምጻውያን ያልነኩትን ሃገራዊና አዲስ ሃሳብ ይዞ እንደሚወጣ አስታውቀዋል።
ቴዲ በሰሜን አሜሪካ ኒዮርክ እና ሚኒሶታ ላይ አዳዲስ ሁለት ነጠላ ዜማዎችን መድረክ ላይ የለቀቀ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን እነዚህን ዘፈኖች በስቱዲዮ ቀርጾ ይልቀቃቸው አይልቀቃቸው ምንጮቻችን የነገሩን ነገር የለም።
ድምጻዊው አዲሱን ነጠላ ዜማ ከክሊፕ ጋር ከለቀቀ በኋላ በላስቬጋስ፣ ዋሽንግተን ዲሲ ዳላስን ጨምሮ የተለያዩ ኮንሰርቶች እንደሚኖሩት ታውቋል።
(ዘ-ሐበሻ)

 

“አሸባሪነት” በወያኔ አገዛዝ ሥር ባለችው ኢትዮጵያ


በአገራችን፣ በወያኔ አገዛዝ መደበኛ ትርጉማቸውን ከሳቱ በርካታ ቃላት መካከል “የሽብር ድርጊት“ እና ”አሸባሪ“ የሚሉት ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። ሰፊ ተቀባይነት ያለው የአሸባሪ ትርጉም “የሽብር ድርጊቶችን የሚፈጽም ሰው ወይም ድርጅት” ማለት ነው። “የሽብር ድርጊቶች” የሚባሉት ደግሞ የተለመዱ ጥቃቶችን ሳይሆን የሀይማኖት፣ የፓለቲካ ወይም የርዕዮተዓለም ግብ ለማሳካት ሲባል በሰዎች ላይ ፍርሀትን ለማንገስ፤ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚደርሱ አስከፊ ጥቃቶችን ነው። የሽብር ድርጊቶችን ሰላማዊውን ሕዝብ ጭዳ የሚያደርጉ በመሆኑ በጥብቅ ሊወገዙ ይገባል። ዓላማን በሽብር ድርጊቶች ማስፈፀም ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።
በወያኔ መዝገበ ቃላት ግን “ሽብርተኛ” እና “የሽብር ድርጊቶች” በዘፈቀደ የሚነገሩ ተራ ቃላት ሆነዋል። ስለአገራቸው እና ስለትውልድ የሚጨነቁ፤ ሀሳባቸው በነፃነት የሚያራምዱ፤ የወያኔን ፕሮፖጋንዳ እንደ በቀቀን የማይደግሙ ዜጎች “አሸባሪዎች” እየተባሉ ወደ እስር ቤቶች እየተወረወሩ ነው። ጋዜጠኞች፣ ጦማርተኞች፣ ፍጹም ሰላምተኛ አማኞች እና ሰላማዊ ፓለቲከኞች በሽብርተኞች ዝርዝር ውስጥ ቀዳሚውን ሥፍራ የያዙ ናቸው።
በአንፃሩ ደግሞ እውነተኛው አሸባሪ ህወሓት፣ የመንግሥትን ሥልጣን ይዞ መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ማሸበሩን በስፋት ተያይዞታል። ህወሓት ዘረኛ ርዕዮተ ዓለሙን ለማስፈፀም ሲል ባለፉት ሠላሳ አምስት ዓመታት ውስጥ የፈፀማቸው የሽብር ድርጊቶች ተዘርዝረው አያልቁም። የህወሓት የሽብር ድርጊቶች ዓላማ የኢትዮጵያን ሕዝብ በፍርሀት አደንዝዞ መግዛት ነው። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ “አሸባሪ” የሚለውን ቃል ራሱ በማሸበሪያ መሣሪያነት እያዋለው ነው። ይህ የውስጥም የውጭም ታዛቢዎችን የሚያሳስት በመሆኑ ትኩረት የሚያሻው ጉዳይ ነው።
“የፀረ-ሽብር አዋጅ” የሚባለው ህገ-አልባነትን ህጋዊ ያደረገው ሰነድ የመንደር ካድሬዎች ሳይቀሩ አንድን ሰው በሽብርተኝነት “ጠርጥረው” ማሳሰርና ማስደብደብ አስችሏቸዋል። የአስተሳሰብ ድህነት ያጠቃቸው የህወሓት ካድሬዎች ብቻ ሳይሆኑ ኃላፊነት የጎደላቸው ፓሊሶችም የፀረ-ሽብር ህጉን ጉልበታቸውን ማሳያ እና ተፎካካሪዎቻቸውን ማጥቂያ አድርገውታል። በፀረ-ሽብር ህጉ ተከስሰው ወህኒ የወረዱ ዜጎችን ያጤነ ማንኛውም ሰው ኢትዮጵያ አገራችን በዚህ ህግ ሰበብ ምርጥ ዜጎቿን እያጣች እንደሆነ ይገነዘባል።
በሽብርተኝነት ለመጠርጠር የሚያበቁ ምክንያቶች እጅግ አሳዛኝ ናቸው። ለካድሬ ሰበካ እውነተኛነት ጥርጣሬውን የገለፀ አስተዋይ ሰው መሆን ብቻውን እንኳን በሽብርተነት ያስጠረጥራል። በዚህም ምክንያት ነው በእውቀትም በአስተሳሰብም የበሰሉ ዜጎቻን በአሸባሪነት የመፈረጅ እድላቸው ከፍተኛ የሆነው። የንቅናቄዓችን ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ጨምሮ በርካታ የሀገራችን ምርጥ ዜጎች የዚህ የተዛነፈ ትርጓሜ ሰለባ ሆነዋል። ተስፋ የሚጣልባቸው በርካታ ወጣቶች በዚህ ህገ-ወጥ ህግ እና የተሳሳተ ትርጓሜ ምክንያት የወጣትነት እድሜዓቸውን በእስር ቤት እንዲያሳፉ ተገደዋል። ከዚያ የበዙት ደግሞ በቃሉ ተሸማቀው፤ በሚያስከፍለው ዋጋ ተሸብረው ራሳቸውን እንዲደብቁ ተደርገዋል።
ለመሆኑ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ምርጥ ዜጓቿ በአሸባሪነት ስም ወህኒ እየተወረወሩ ሲሰቃዩ ምላሻችን ምን ሊሆን ይገባል? እስከመቼ አስተዋይ፣ አርቆ አሳቢና አመዛዛኝ የሆኑ መሪዎቻችንን ለወያኔ ፋሽቶች እየገበርን እንኖራለን? ሀገራችን ይህን ኪሳራ የመሸከም አቅም አላት?
ግንቦት 7: የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ወያኔን ለማስወገድ የተሻለ ነው ብሎ ያመነበት የትግል ስልት – ሁለገብ የትግል ስልት ነው። በዚህ የትግል ስልት መሠረት ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነት እና ሕዝባዊ አመጽ ተደጋግፈውና ተናበው መሄድ አለባቸው ብሎ ያምናል። ስለሆነም እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በአመቸውና በሚያምንበት መንገድ ለትግሉ አስተዋጽኦ የማበርከት እድል አለው።
በዚህም መሠረት ለሀገር፣ ለትውልድ ድህንነት ዋጋ ለመክፈል እና ለገዛ ራሳችን ህሊና ታማኝ ለመሆን በወያኔ “አሸባሪ” ለመባል መድፈር የትግላችን አንዱ አካል አድርገን መቁጠር ይኖርብናል። በወያኔ “አሸባሪ” መባል የሚያሸማቅቅ ሳይሆን የሚያኮራ፤ ለታላቅ ኃላፊነት እና ሕዝባዊ አደራ በእጩነት የሚያቀርብ መሆኑን በራሳችንም በማኅበረሰባችንም ውስጥ ማስረጽ ይኖርብናል። “አሸባሪ” የሚለው ቃል በወያኔ ተግባር መሠረት ሲተረጎም “ለሀገርና ለትውልድ ደህነት የሚጨነቅ ምርጥ ዜጋ“ ማለት እንደሆነ ማስተማር ይገባናል።
ወያኔ ወደ ሕዝብ የሚወረውረውን ጦር መልሰን ወደ ራሱ መወርወር ይኖርብናል። ወያኔ አሸባሪነት ዜጎችን ለማጥቂያ እያዋለው መሆኑ ተረድተን እኛ በዚህ ስያሜ መሸማቀቅ ሳይሆን፣ መኩራትና መልሰን ወያኔን ማሸማቀቅ ይኖርብናል። በውጭ አገራት እየተስፋፋ የመጣው የወያኔ ሹማምንትን የማሸማቀቅ ዘመቻ በኢትዮጵያ ውስጥም መጀመር ይኖርበታል።
ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽ ሲቀናጁ ድላችንን ያፈጥናሉ። በወያኔ “አሸባሪ” መባል የመልካም ዜግነት ምስክርነት እንደሆነ በሙሉ ልባችን እንቀበል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

torsdag 14. august 2014

ከትግሬ መልአክ የአማራ ሰይጣን ይሻላል የሚለው የወልቃይት ህዝብ በወያኔ ላይ እያመጸ መሆኑ ታውቋል::

ምንሊክ ሳልሳዊ
የወልቃይት ጠገዴ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ትግራይ ውስጥ አንሰበሰብም እያሉ ነው::

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ወረዳው ወደ ትግራይ መቀላቀሉን በመቃወም ላይ መሆኑን እና ከወያኔው ጦር ጋር ተፋጦ እንዳለ ከአከባቢው የመጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ:: በአከባቢው ከፍተኛ ጦር በማስፈር ሕዝቡን እያሸበሩ እና እያሳደዱ መሆኑ ታውቋል:: በአሁን ሰአት እንደ አዲስ ከአንገረብ ወንዝ ምላሽ በመውሰድ ለመከለል ሲሆን ወልቃይት ጠገዴ ግን እኛ አማሮች ነን ከጎንደር ነን እያለ ሲሆን ወያኔ ለመስማት ዝግጁ አይደለም ይህንን ተከትሎ የወልቃይት ህዝብ እየታሰረ ሲሆን እስካሁን ወልቃይት አማራ ነው ስላሉ ብቻ ወደ ወህኒ የተወረወሩት ታጋይ ሃጎስ ደሳለኝ ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት የህዝቡ ጥያቄ ትግሬዎች ተከዜን ይሻገሩልን ሲሆን የኛ የሚሉት የቦታ ስም ማይ አምባ ስላንዲ ገቸው ዳንሻ ዳራ ሻሃን ምድረገበታ አዲሳለም ናቸው ::

ወያኔ ቦታዉን ከ1984 ጀምሮ ከወልቃይት ህዝብ ላይ በመውሰድ አዘናግቶ ወደ ትግራይ የቀላቀሉት ሲሆን የትግራይ ሕወሓታዊ ካድሪእዎችን በማፍሰስ በወልቃይት ሕዝብ ላይ ከፍተኛ በደል እየፈጸመ ነው::ሕዝቡ ያኮረፈ ሲሆን የተወሰነው ወደ ኤርትራ ሱዳን እና አርማጮህ ተሰዷል ሸፍቷል:: የወልቃይትን ህዝብ አሳልፈው እያስገደሉ እያሳሰሩ ያሉ ግለሰቦች ለከፍተኛ ስልታን እና ለፓርላማ አባልነት እንዲያገለግሉ እየተደረገ ሲሆን ከነዚሁም ውስጥ አቶ ሹምዪእ ገብሬ አቶ መንግስቱ አቶ አዘነው ከነልጁ ባለስልጣን ሆኗል:; እንዲሁም ሕወሃት የትግራይ ክልል ውስጥ አትከልሉን ያሉትን እንዲያድኑ ለካድሬዎቹ መሳሪያ በነብስ ወከፍ አድሏል::በፊትለፊት ህዝቡ ላይ መሳሪያ በመደቀን ሕዝብን እያሸበሩ ይገኛሉ::

ወልቃይት ጠገዴ ወደ ትግራይ ክልል እንዲሆን የሚታገሉ
1 mengiste Alemu 2 shumye gebre 3 Desalegn G/R 4 Alemu tamalew 5 Andarge mekonen 6 sisay tela 7 ferede mola 8 melke tiruneh 9 Azanew gebrye 10 kes alemaw 11 Alemneh kide 12 Haile G/medhn 13 Tagey merzo 14 Tagay laqew ሲሆኑ

ወልቃይት ጠገዴ የትግራይ አካል አይደለም የሚሉእና የሚታገሉ 1 berihun wolde 2 kasahun sisay 3 Agerew Wasie 4 Asmamaw Tafere 5 Fitalew tafere 6 Kefyalew tilahun 7 Alemaw wagnew 8 zafie asefa 9 Alemu tizazu 10 desalegn warkaw 11 fiteray G.Maryam እና ሌሎችም በበላይነት እንቅስቃሴውን እየመሩት ነው::

በአሁን ወቅት የክረምቱን መግባት ተከትሎ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ዝምታን ቢላበስም የሚጠብቀው መስከረም እስኪጠባ በጋ እስኪሆን ድረስ ነው በአከባቢው ይህንን ያወቀው ወያኔ ሰራዊቱን እና ያስታጠቀውን ሚሊሻ በተጠንቀቅ አከባቢው ላይ አስፍሯል::እንዲሁም በህገወጥ መንገድ ከሱዳን ሰራዊት ገብቷል::ይህ ደሞ አማራ ነኝ የሚለው የወልቃይት ጠገዴን ህዝብ አስቆጥቷል::

በዚህ ወር ወያኔ እረፍት ላይ ያሉ ተማሪዎችን ለመሰብሰብ ዝግጅት እያደረገ ነው :: የወልቃይት ጠገዴ የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ትግራይ ውስጥ አንሰበሰብም እኛ አማሮች ነን በማለት ጎንደር ዩንቨርስቲ ነው የምንሰበሰበው ብለዋል:: ሆኖም የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ግደይ አዛናው ወደ ጎንደር ማንም ተማሪ መሄድ የለበትም ሲል አስጠንቅቋል:: ይህን ማስጠንቀቂያ ተከትሎ ወላጆች ቁጣቸውን እንደገለጹ ታውቋል::ተማሪዎቹም ትግራይን አናውቅም ጎንደር ነው የምንሄደው በማለት ለማስጠንቀቂያው ምላሽ ሰቷል:: ይህ በእንዲህ እንዳለ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ በወያኔ አገዛዝ የተማረረ ስለሆነ ወደ ጎንደር ;አርማቾህ ;ክራክራ;እርጎዬ;ሰሮቃ;ዳባት;ደባርቅ በመሄድ ላይ መሆኑ ታውቋል::

onsdag 13. august 2014

የአዲስ አበባ መስተዳድር በቤቶች ግንባታ ዙሪያ ለምርጫ እንዲደርስ በሚል አስቸኳይ ትእዛዝ ሰጠ

Auggest13/2014
ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ40 በ60 በሚባለው የቤቶች መርሃግብር የታቀፉ የዲያስፖራ አባላት ከቀጣዩዓመት ምርጫበፊት ቤት እንዲሰጣቸው የአዲስ አበባ መስተዳድር መመሪያመስጠቱ ታውቋል። ሆኖምየጠቅላላተመዝጋቢውንየቤትፍላጎትለመሸፈንበትንሹከ16 ዓመታትበላይጊዜን እንደሚወስድ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ኢንተር ፕራይዝ እስካሁን 13ሺህ 800 ቤቶችን በሰንጋተራ እና ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በመሳሰሉ አካባቢዎች ላይ እየገነባ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ፣ እነዚህን ቤቶች እስከሚቀጥለው ዓመት አጋማሽ ድረስ ለዕድለኞች ለማስተላለፍ ታቅዷል።

የአስተዳደሩ ምንጮች እንደገለጹት ቤቶቹ ከቀጣይ ዓመት ምርጫ በፊት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው እንዲተላለፉ ከአስተዳደሩ መመሪያ ተሰጥቷል። ሆኖም ለ40 በ60 የቤቶች ፕሮግራም የተመዘገበው ጠቅላላ ሕዝብ ቁጥር 164 ሺህ 779 ያህልሲሆንአስተዳደሩግን በዓመትከ10 ሺህቤቶችበላይቤቶችን
የመገንባት አቅም ባለመፍጠሩ የተመዘገቡትን ብቻ ለማዳረስከ16 ዓመታት በላይ ጊዜን እንደሚፈልግ የአስተዳደሩ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡ ይህ ደግሞ ከዛሬ ነገ የመኖሪያ ቤት ባለቤት አስቆራጭ ዜና ነው ብለዋል፡፡ በ20/80 በተለምዶኮንዶሚኒየምፕሮግራምየምርጫ 97ን መቃረብ ታሳቢ አድርጎ ሲጀመርከ 350ሺ በላይ የአዲስ አበባ ነዋሪ መኖሪያ ቤት እፈልጋለሁ ብሎ መመዝገቡን ያስታወሱትምንጮቹ ፣ ፕሮግራሙ 10 ዓመታት ያህል ቆይቶ መመለስ የቻለው ግን 100 ሺ በታች ቤት ፈላጊዎችን ጥያቄ ነው ብለዋል፡፡በዚህ መረጃ መሠረት የጠቅላላ ተመዝጋቢውን ፍላጎት ለሟሟላት ተጨማሪ ከ20 ዓመታት በላይ ጊዜ ንእንደሚወስድ አፈጻጸሙ በራሱ የሚናገርነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የአስተዳደሩ ምንጭ እንደሚሉት መንግሥት በአዲስ አበባበዓመት ለቤቶች ግንባታ ብቻ ከ2 እስከ 3 ቢሊየን ብር እያወጣ መሆኑን አስታውሰው ከዚህ በላይ ለማውጣት የፋይናንስ አቅም ችግር መኖሩን፣ገንዘቡ ቢገኝም በግንባታ አፈጻጸምበኩል የአቅም ችግር በመኖሩ በአጭር ጊዜ የመኖሪያ ቤት ፍላጎትን ለመመለስ የማይችልበት አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም እንደገለጹት ደግሞ ዲያስፖራው በፈለገበት አካባቢ ቤት ለመስራት ይችል ዘንድ ክልሎች መመሪያ እንዲያወጡ መታዘዙን ገልጸዋል። ሁሉም ክልሎች ተመሳሳይ የሆነ መመሪያ ባለማውጣታቸው ለዲያስፖራው ቤት ለማደል የታቀደው እቅድ የተፈለገውን ውጤት አለማምጣቱን ገልጸዋል። ይሁን እንጅ ኢሳት የአዲስ አበባን አዲሱን ካርታ ዝግጅት አስመልክቶ ከወራት በፊት በሰራው ዘገባ፣ የቤት ግንባታ መርሃግብሩ የተሰናከለው በአዲስ አበባ የቤት መስሪያ ባዶ ቦታ በመጥፋቱ ነው። ቀደም ብሎ የኦሮምያን ልዩ ዞኖች ወደ አዲስ አበባ በመጠቅለል የቤት መስሪያ ቦታዎችን ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ የኦሮምያ ክልል አንዳንድ ባለስልጣናትና አብዛኛው የኦሮሞ ተወላጅ በመቃወሙ እቅዱን በቀላሉ ተግባራዊ ማድረግ አልተቻለም። ዲያስፖራው ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ ቦታዎችን እንዲጠይቅ ለማግባባት ኢምባሲዎች የስራ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ለአባይ ግድብ በቦንድ ስም ገንዘብ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገንዘብ ለማሰባሰብ የታቀደው እቅድ አለመሳካቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አምነዋል። ከፍተኛ ገንዘብ ይገኝበታል የተባለው የአሜሪካ የቦንድ ሽያጭ አምና ጭራሽ አልተካሄደም ብሎ መናገር እንደሚቻል ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በሁሉም አገሮች ያለው የቦንድ ሽያጭ ደካማ መሆኑን የጠቀሱት ሚኒስትሩ ፣ ለድክምቱ ዝርዝር ምክንያቶችን አላቀረቡም።

የዶ/ር ቴዎድሮስ ገለጻ፣ ኢሳት ከዚህ ቀደም የቦንድ ሽያጩ በውጭ አገር አለመሳካቱን ሲዘግብ የቆየውን ያረጋገጠ ሆኗል። በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ገንዘብ ለመሰብሰብ በገዢው ፓርቲ በኩል የሚዘጋጁትን ዝግጅቶች አጥብቆ ሲቃወም እንደነበር ይታወቃል። አቶ መለስ የአባይን ግድብ እቅድ ይፋ ሲያደርጉ በውጭ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ 1 ቢሊዮን ዶላር ያዋጣል የሚል እምነት ነበራቸው፣ ይሁን እንጅ እስካሁን ባለው መረጃ በውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ ከ20 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሊያዋ

ኤርትራ የሩሲያን የጦር ልምምድ ልታስተናግድ ነው


በመላኩ ጸጋው
በቅርቡ በተለያዩ አካባቢዎች ተከታታይ የጋራና የተናጠል የጦር ልምምድ ያደረገችውን ሩሲያን በቀጣይ በኤርትራ በቀይ ባህር
አካባቢ ልታስተናግዳት መሆኑን “ጊሲካ አፍሪካ ኦንላይን” በአውሮፓ የሚገኙ የኤርትራ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ከሰሞኑ
ባሰራጨው ዘገባ ገልጿል። የልምምዱ ዋነኛ ዓለማ በአንድ መልኩ የሩሲያን ጦር ዝግጁነት ለማረጋገጥ እንዲሁም በኤርትራ
ወደቦች አቅራቢያ ሩሲያ ቋሚ የጦር ሰፈርን (Military base) ለማቋቋም መሆኑን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል። እንደ ዘገባው
ከሆነ የሩሲያ የጦር ልምምድ በሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።
ኤርትራ ከተወሰኑ ጊዜያት ወዲህ በሩስያ እንደ አንድ ስትራቴጂክ

አጋር ሀገር እየታየች መሆኗን ዘገባው አመለክቷል። እንደዘገባው
ከሆነ አሜሪካ በጅቡቲ ቋሚ የጦር ሰፈር ያላት ሲሆን በተለያዩ
ጊዜያትም ከጅቡቲ ወታደሮች ጋር የአየር ኃይልና የባህር ኃይልን
ባቀናጀ መልኩ የጦር ልምምድ ታደርጋች። ጅቡቲ የአሜሪካንን
ጦር ከማስተናገድ ባለፈ በዋነኝነትም የፈረንሳይ የጦር ሰፈር
በመሆን እያገለገለች ነው። ሱዳን በአንፃሩ ኢራን በቀይ ባህር
የሱዳን ምዕራባዊ ግዛት የባህር ኃይል ቤዝ እንድትመሰርት
ለማድረግ እንቅስቃሴ የጀመረች መሆኗን ቀደም ያሉ የዩናይት
ፕሬስ ኢንተርናሽናል UPI ዘገባዎች ያመለክታሉ። ይህ የሱዳን እንቅስቃሴ ግን በእስራኤል አልተወደደም።
ሩሲያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አቅጣጫዎች ተከታታይ የጦር ልምምዶችን በማድረግ ላይ ትገኛለች። እንደ ዘጋርድያን
ዘገባ ከቀናት በፊት ከሃያ ያላነሱ የጦር መርከቦችንና በርካታ ተዋጊ አውሮፕላኖችን ባሳተፈ መልኩ በደቡብ ምስራቅ አውሮፓ
በሚገኘው ጥቁር ባህር ሰፊ የጦር ልምምድ አድርጋለች። ኢተር ታሰ የዜና ወኪል ባሰራጨው ዘገባም ከዚህም በተጨማሪ ሩስያ
በተመሳሳይ መልኩ ከቻይና ጋር በጋራ በመሆን 18 የጦር መርከቦችን ባሳተፈ መልኩ በሻንጋይ አቅራቢያ በያዝነው አመት የጦር
ልምምድ አድርጋለች። በሌላ አቅጣጫ ሩስያ ከቀናት በፊት አንድ መቶ ተዋጊ አውሮፕላኖችን ባሳተፈ መልኩ በዩክሬን ድንበር
አቅራቢያ ጠንካራ የጦር ልምምድ ያደረገች መሆኑን ዘገባዎች ያመለክታል።
ኤርትራ አልሸባብን በሶማሊያ በማገዝ በሀገሪቱ የውስጥ ጉዳይ በመግባት አካባቢያዊ ሰላምን እያወከች ነው በሚል በተባበሩት
መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በኩል ተከታታይ ማዕቀቦች ጥለውበታል። የቀድሞው የቡሽ አስተዳደርም ሆነ የኦባማ
አስተዳደር ኤርትራን ሽብርን በሚደግፉ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ እንድትካተት ያደረጓት ሲሆን በቅርቡም በዋሽንግተን
በተካሄደው የአሜሪካ አፍሪካ መሪዎች ስብሰባ ከሮበርት ሙጋቤ እና ከአልበሽር ጋር ኢሳያስ አፈወርቂ በስብሰባው ላይ
የሚታደሙበት ጥሪ ሳይደርሳቸው ቀርቷል።ሩሲያ በአንጻሩ ከዩክሬን ጋር በተያያዘ ፖለቲካ ውዝግብ መግባቷን ተከትሎ በምዕራባውያኑ ሀገራት ተከታታይ ማዕቀብ የተጣለበት ሲሆን የሩሲያ መንግስት በአንፃሩ የአውሮፓና የአሜሪካ የግብርና ምርቶች ወደ ሀገሩ እንዳይገቡ እገዳን ጥሏል። የዩክሬኑን ውዝግብ ተከትሎ ሩሲያ ተከታታይ ወታደራዊ ልምምዶችን እያደረገች ሲሆን የቀይ ባህሩም የጦር ልምምድ የዚህአካል ነው ተብሎ ይገመታል። ዘገባውን ያሰራጨው ጊሲካ አፍሪካ ኦንላይን የመረጃ ስርጭቱን በዋንኛነት በኢትዮጵያ፣በኤርትራ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሌላድ፣ ኬኒያ እና ኡጋንዳ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሰራ የሚዲያ ተቋም ነው።በኢጋድ ዙሪያም ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ሰፋ ያሉ ዘገባዎችን ሲያሰራጭ ቆይቷል። ዜናው የተገኘው ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ ከወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ ነው።

mandag 11. august 2014

የከዱ የግንቦት 7 አባላት አቶ አንዳርጋቸውን እያሰቃዩ ነው ተባለ፤ * 2 መምህራንና 1 ዳኛ በአንዳርጋቸው ጉዳይ ታፍነዋል

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን መያዝ ተከትሎ ለወያኔዎች ከአዲስ አበባ እስከ ደብረዘይት ትልቁን የምርመራ ስራ እየሸፈኑ ያሉት ከግንቦት ሰባት ሕዝባዊ ሃይል ጋር በኤርትራ የነበሩ እና ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር የፖለቲካ ስራ ሲሰሩ የነበሩ በኋላም ከድተው የገቡ ቅጥረኞች መሆናቸው ታውቋል። እነዚህ ቅጥረኞች ከመጀመሪያው ሰርጎ ገቦች እንደሆኑ ሳይጠረጠር ወደ ግንቦት ሰባት ከገቡ በኋላ ከአቶ አንዳርጋቸው መያዝ ቀደም ብሎ በመክዳት ወደ ወያኔ የተቀላቀሉ ናቸው ሲል ጦማሪ ምኒልክ ሳልሳዊ ዘገበ።

እንደ ምኒልክ ዘገባ ከሆነ በአዲስ አበባ እና በደብረዘይት ትልልቅ ሆቴሎች ተይዞላቸው በምርጥ መኪኖች እየተንሸራሸሩ አቶ አንዳርጋቸውን በማሰቃያ ክፍል ውስጥ በማምጣት እውነቱን አውጣ አንተ እንደዚህ ብለኸን አልነበረም በማለት በተለያየ ጊዜ በስብሰባ እና በውይይት ወቅት የተነጋገሩትን የፖለቲካ ኦፕሬሽኖችን እና የትግል ስትራቴጂዎችን በመጥቀስ ከፍተኛ ስቃይ እና ድብደባ እያደረሱብት ነው።


ከሕወሃት ከአንድ ብሄር ከተመለመሉ መርማሪዎች ጋር በጋራ በምርመራ ላይ የተሰማሩት ሶስቱ የግንቦት ሰባት ከሃዲ አባላት አንዳርጋቸውን በማሰቃየት ላይ ያሉት -

1) ሽታው ሽፈራው ኤርትራ የነበረ የጎጃም ሰው
2) ቴዎድሮስ ስዩም ኤርትራ የነበረ ከአዲስ አበባ የሄደ
3) ኢልያስ ጥረት ጎንደር ውስጥ የነበረ እና ከአንዳርጋቸው ጋር ሲሰራ የነበረ ናቸው ሲል በዝርዝር የጠቆመው ጦማሪ ምኒልክ ሳልሳዊ በወያኔ ተንኮል ተተብትበው ግንቦት ሰባትን በመክዳት ለምቾታቸው የሕዝብን ትግል በጥቅም በመለወጥ በዘመናዊ መኪና እየተንፈላሰሱ በአዲስ አበባ እና ደብረዘይት ምርጥ ሆቴሎች ውስጥ እየተዝናኑ የነጻነት ታጋይ የሆነውን አንዳርጋቸውን በቶርች በማሰቃየት ላይ መሆናቸውን ዘግቧል።


ምርመርውን በመሪነት የሚያንቀሳቅሱት የሕወሓት ደህንነቶች የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ በአከባቤው አንዳርጋቸውን በተመለከተ ለብአዴን ይሁን ለ ኦሕዴድ ሰዎች ምንም አይነት መረጃ እንዳይሰጣቸውና ወደ ማሰቃያ ክፍሉ ምንም እንዳይቀርቡ ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገ እንደሆነ ለማረጋገጥ መቻሉን የገለጸው ጦማሪው ከአንዳርጋቸው ጋር የተያያዘውን የሃገር ውስጥ ኔትወርክ በማፈራረስ ረገድ ከላይ ስማቸው የተጠቀሰው ከሃዲዎች እስከ ክፍለሃገር ድረስ በስፋት እየሰሩ ሲሆን እስካሁን በማፈራረስ ሙከራው ምንም አይነት ውጤት እንዳልገኙ ታውቋል ብሏል።


ጦማሪው ዘገባውን ሲቋጭም “ከአንዳርጋቸው ጋር በተያያዘ ከየክልሉ የግንቦት ሰባት መዋቅር ውስጥ አሉ የተባሉ እየተለቀሙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከጎንደር ክፍለሃገር መምህር ተስፋዬ ተፈሪ እና መምህር ጌታቸው የተባሉ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እንዲሁም የጎንደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ እንደሆነ የሚነግረው አቶ አበራ በከሃዲዎች ጥቆማ ከሃምሌ አጋማሽ ጀምሮ ታፍነው ከተወሰዱ በኋላ የት እንደታሰሩ እንኳን እንደማይታወቅ ተገልጿል።” ብሏል።

fredag 8. august 2014

የመከላከያ ሰራዊት አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ መጠየቃቸውን ተቃወሙ

esat
ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢሳት የመከላከያ ምንጮች እንደገለጹት የሰራዊቱ አባላት ለመለስ ፋውንዴሽን ገንዘብ እንዲያዋጡ በተጠየቁበት ወቅት ተቃውሞ አሰምተዋል። በባድሜ አካባቢ የሰፈሩት የመከላከያ አባላት በደሞዝ ክፍያ ሳምንት መነሻው 200 ብር ሆኖ በየደረጃው ያሉ ወታደሮች እንደ ማእረጋቸውና ደሞዝ መጠናቸው እንዲከፍሉ ሲጠየቁ፣ የሰራዊቱ አባላት ደሞዛችን አይቆረጥም በማለት ተቃውሞ አሰምተዋል።
ደሞዝ ከፋዮቹ ከላይ የመጣ መመሪያ ነው በሚል ሊያግባቡዋቸው ቢሞክሩም የሰራዊቱ አባላት ፈቃደኞች ሳይሆኑ ቀርተዋል። አንድ የ3ኛ ሻለቃ አንደኛ ጋንታ አባል የሆነ ወታደር አመጹን መርተሃል ተብሎ ሊታሰር ሲል አምልጦ እስከነመሳሪያው ተከዜ ውስጥ ገብቶ መሞቱ ታውቋል። ይህንን ተከትሎ መጠናኛ ብጥብጥ መነሳቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።
በአሁኑ ሰአት ውጥረቱ እንዳለ ሲሆን፣ ከመከላከያ እየጠፉ የሚሄዱትም ቁጥራቸው እየጨመረ ነው።
ባለፉት 3 ቀናት መከላከያን ጥሎ የጠፋ አንድ ወታደር እንደገለጸው፣ ሰራዊቱ በከፍተኛ ምሬት ውስጥ እንደሚገኝና የሚከዳው ሰራዊት ቁጥርም ከፍተኛ መሆኑን ተናግሯል። በተከዜ አካባቢ በሚካሄደው የኮንትሮባንድ ንግድ የአንድ አካባቢ ሰዎች የሆኑ የመከላከያ አዛዦች እየተጠቀሙ ነውየሚለው አባሉ፣ ከእነሱ ውጭ ያለው የመከላከያ አባል በችጋር እየተጠበሰ ባለበት ወቅት ለመለስ ፋውንዴሽን በሚል እንደገና መዋጮ መጠየቁ ብዙዎችን ስሜት የረበሸ ሆኗል ብሎአል።
እነሱ ተጨማሪ ገቢ አላቸው፣ እኛ ግን የምትሰጠንን ደሞዝ እንኳ ቆጥበን ለቤተሰቦቻችን እንዳንረዳ በመዋጮ እና በሰበብ አስባብ ይወስዱብናል ሲል ተናግሯል።
በኢትዮጵያ በወታደራዊ አዛዦችና በተራው ሰራዊት መካከል ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ልዩነት አለ። አብዛኞቹ የመከላከያ መኮንኖች የህወሃት አባላት ሲሆኑ፣ በአዲስ አበባ እና በኢትዮጵያ ዋና ዋና ከተሞች ዘመናዊ ቪላዎችንና ፎቆችን ሰርተው በወር በመቶሺዎች የሚቆጠር የኪራይ ገቢ ያገኛሉ። በአገሪቱ ውስጥ የሚካሄደውን የኮንትሮባንድ ንግድ የሚያስፈጽሙት፣ በመከላከያ ስም ያለቀረጥ የሚያስገቡዋቸውን እቃዎች በርካሽ በመሸጥ ህጋዊዎቹን ነጋዴዎች እያከሰሩ ከስራ ውጭ እያደረጉዋቸው መሆኑን በርካታ ነጋዴዎች ለኢሳት ይናገራሉ።

tirsdag 5. august 2014

የብሪታንያ መንግስት የኢትዮጵያን ጉዳይ አስፈጻሚ አስጠርቶ በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ በጽህፈት ቤቱ አነጋገረ።



ሐምሌ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በየመን የጸጥታ ሃይሎች ከተያዙ በሁዋላ ሰቆቃ እየተፈጸመባቸው ያለፉት 44
ቀናትን በደብረዘይት አየር ሃይል እስር ቤት ውስጥ ካሳለፉ በሁዋላ የብሪታንያ መንግስት የኢትዮጵያን ጉዳይ አስፈጻሚ አስጠርቶ በጽህፈት ቤቱ አነጋግሯል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሲሞንድስ አቶ አንዳርጋቸው የኮንሱላር አገልግሎት በአፋጣኝ እንዳያገኙ መደረጉ እንዳሳሰባቸው ለኢትዮጵያው ዲፕሎማት ተናግረዋል። 

የኢትዮጵያ  መንግስት ከዚህ ቀደም ለአቶ አንዳርጋቸው የኮንሱላር አገልግሎት እንደሚፈቀድ ቃል ገብቶ የነበረ ቢሆንም፣ የገባውን ቃል አለማክበሩን የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ መግለጫ ያመለክታል።ሚ/ር ሲሞንድስ የኢትዮጵያ መንግስት በአፋጣኝ የኮንሱላር አገልገሎቱን እንደሚፈቅድ እንዲሁም አቶ አንዳርጋቸው በሌለበት የተላለፈው የሞት ፍርድ ተግባራዊ እንደማይሆን ማረጋገጫ እንዲሰጥ የኢትዮጵያው ዲፕሎማት መልእከቱን ለመንግስት እንዲያስተላለፍ አሳስበዋል።የብሪታንያ መንግስት ያወጣውን መግለጫ በተመለከተ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የአቶ አንዳርጋቸው ባለቤት ወ/ሮ የምስራች ሃይለማርያም ፣ ለህዝብ ይፋ የሆነው መግለጫ በዲፕሎማሲ ቋንቋ ጠንካራ የሚባል መሆኑን ገልጸው፣ የብሪታንያ መንግስት ተጨማሪ ግፊቶችን እያደረገ ነው ብለዋል።ከዲፕሎማቶች አካባቢ የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው የእንግሊዝ መንግስት የኢትዮጵያን ዲፕሎማቶች እየጠራ በተደጋጋሚ ያነጋገረ ሲሆን፣ ዲፕሎማቶችም አቶ አንዳርጋቸው የኮንሱላር አገልግሎት በአስቸኳይ እንደሚያገኙ ቃል ገብተው ነበር። ይሁን እንጅ ቃላቸውን ለመጠበቅ ያልቻሉት የኢትዮጵያ ዲፕሎማቶች፣ የብሪታንያ ባለስልጣናት ፊት ሲቀርቡ የሚናገሩት እንደሌላቸውና “መልእክት እናስተላልፋለን” የሚል ቃል ብቻ እንደሚናገሩ ለማወቅ ተችሎአል። በሌላ በኩል ግን አቶ አንድርጋቸው የመጎብኘት ፈቃድ እንዲያገኙ ፈቃድ የሚሰጠው አካል ማን እንደሆነ አለመታወቁ ለዲፐሎማቶች ራስ ምታት መሆኑ ታውቋል። አቶ ሃይለማርያም ደሳለን ቀደም ብለው ኢትዮጵያን ለጎበኙነት የእንግሊዝ ዲፕሎማቶች የገቡትን ቃል ማክበር የተሳናቸው ሲሆን፣ አንዳንድ ወገኖች እንደሚሉት ዋናው ፈቃጆች ምናልባትም ከጀርባ ያሉ ሌሎች ስውር ባለስልጣናት ሳይሆኑ አይቀሩም። በኢትዮጵያ ውስጥ ስላጣን ላይ ያለውና ውሳኔ የሚሰጠውን ሰው በትክክል ለማወቅ ባለመቻሉ በርካታ ዲፕሎማቶች ግራ እየተጋቡ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።