torsdag 1. september 2016

የወያኔ እኩይ የዘረኝነት ተግባር ማብቂያው ደረሰ!!


ሴፕቴምበር 1, 2016
ከዲቦራ ለማ/ኖርዌይ

በመጀመሪያ እግዚአብሄር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ ለሰው ልጆች የሚያስፈልገውን ሁሉ ባህሩን የብሱን፣ ብቻ ምንአለፋችሁ ሁሉንም ሰርቶ፣ አበጃጅቶ ለመኖር ምቹ አድርጎ ከጨረሰ በኋላ አዳምን ፈጠረ፣ ለአዳምም ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም እልዳልሆነ አየና ረዳት እንድትሆነው ሄዋንን ከጎኑ አጥንት አበጀለት። ከዚያም ታሪኩ ብዙ ነው፣ እግዚአብሄር አዳምና ሄዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሏት ብሎ ባረካቸው። እንግዲህ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሰው በምድር ላይ እንደፈለገ እየተባዛ እንዲኖር ተፈቅዶለታል። መፅሀፍ ቅዱስ ላስተምራችሁ አይደለም! እንዲያው ለሰው ልጆች በሙሉ በነፃ የተሰጠውን ተፈጥሯዊ መብቶች  በመፃረር በሀገራችን ያለው የወያኔ ስርአት እየፈፀመ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል ለማውገዝ ያህል መንደርደሪያ እንዲሆነኝ ነው።

ዘረኝነት ከብዙ ዘመናት በፊት በተለያዩ አህጉራት እንደ አሜሪካና አውሮፓ በመሳሰሉት ሀገራት በጥቁሮችና በነጮች መካከል ጎልቶ ይታይ የነበረ ቢሆንም አሁን ባለንበት 21ኛ ክፍለ ዘመን ግን ዘረኝነት የኃላ ቀር አስተሳሰብ በመሆኑ አሁን ባለንበት ዘመን እንደቀድሞው ጎልቶ አይታይም። በዚያን ጊዜ የነበረው ዘረኝነት ነጮች በአፍሪካውያን ጥቁሮች ላይ ያሳዩት የነበረ የበላይነት እንጂ አሁን በሐገራችን ያለው አምባገነን ስርአት የራሱን ህዝብ በገዛ ሀገሩ ባሪያ አድርጎ  እንደሚያሳየን አይነት ዘረኝነት አልነበረም። በርግጥ ወያኔ ከአመሰራረቱ ገና ከደደቢት በረሀ ይዞት የተነሳው አላማ ኢትዮጵያ የምትባልን ሀገር አፈራርሶ ታላቋ ትግራይ የምትባል የኢንዱስትሪ ከተማ መስርቶ ትግራይን ከኢትዮጵያ የመገንጠል አላማ ይዞ የተነሳ የማፍያ ቡድን ነው። ይህንንም እኩይ የዘረኝነት አላማ ለማስፈፀም ይዞ የተነሳው እስትራቴጂ ህዝቡን በዘር፣ በጎሳ፣ በሀይማኖት በመከፋፈል ከፋፍለህ ግዛው በተሰኘ አጋንንታዊ አስተሳሰብ ነው። በተለይ ያሰጉኛል ያስፈሩኛል ያላቸውን የአማራንና የኦሮሞን ህዝብ በጠላትነት በመፈረጅና ሁለቱን ብሄሮች በማጋጨት ከፍተኛ ወንጀል በኦሮሚያና በአማራ ክልል ተወላጆች ላይ ሲፈፅም ቆይቷል። አሁንም እየፈፀመ ነው።

ወያኔ የአማራ ህዝብ በኢትዮጵያ አንድነት ድርድር የማያውቅ መሆኑን አስቀድሞ ያውቅ ስለነበረ
ይህንን ህዝብ ለማጥፋትና ቁጥሩን ለማመናመን እጅግ በርካታ እኩይ ተግባራትን እየፈፀመ ይገኛል። የአማራውን ህዝብ ከተወለደበትና ካደገበት፣ የእድሜውን እኩሌታ ከኖረበት፣ ሀብት ንብረት ካፈራበት አካባቢ በማፈናቀልና ሜዳ ላይ ተበትኖ በገዛ ሀገሩ እንደስደተኛ መፃተኛ ሆኖ እንዲኖር አድርጎታል። የአማራው ህዝብ በተለያዩ አካባቢዎች የጅምላ ግድያ ተፈፅሞበታል። ይህ አልበቃ ብሏቸው እህቶቻችንን ተፈጥሮ የለገሳቸውን የመውለድና የመባዛት መብት በመገደብ መካን አድርጎ የሚያስቀር ክትባት እየሰጡ እንዳይዋለዱና ዘራቸው እንዳይቀጥል በማድረግ እህቶቻችን ልጅ ፍለጋ በየፀበሉ እንዲንከራተቱ አድርገዋል። ይህ ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል በአማራ ተወላጆች ላይ በዘረኛው ወያኔ ተፈፅሟል። ይህ ወንጀል እግዚአብሄር የሚፈርድባቸው እንዳለ ሆኖ በአለም አቀፍ የዘር ማፅዳት ወንጀል የሚያስጠቅይ አደገኛ ወንጀል ነው። ይህንን አይነት ወንጀል ወያኔ በገዛ  ህዝቡ ላይ ሲፈፅም ምን ያህል ጥላቻ ለህዝቡ እንዳለውና በርግጥም ከደደቢት በረሃ ይዞ የመጣውን አማራን የማጥፋት ተልኮ በፍጥነት እየተገበረ መሆኑንም ያሳያል።

ከላይ እንደገለፅኩት በተፈጥሮ ከመባዛት በተጨማሪ በተፈጥሮ የተሰጠን ሌላ መብት አለን። ይህውም ማንም ሰው እዚህ ቦታ ከዚህ ብሄር መወለድ እፈልጋለሁ ብሎ የተወለደ የለም ሁላችንም ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልደናል በተወለድንበት ሀገር ውስጥ ደግሞ የትኛውንም አይነት ዘርና ቋንቋ ይዘን መወለዳችን በተፈጥሮ የተሰጠን መብታችን ነው። ማንም ሊከለክለን ወይም ሊሰጠን የማይችለው መብታች ነው። ሆኖም ግን ወያኔ ኢህአዴግ ይህንን ተፈጥሯዊ መብታችንን በመጋፋት በዘርና በቋንቋችን እያጥላላ ዘራችንን እየጠቀሰ አማራ፣ ኦሮሞ እያለ ሲሰድበን ኖሯል። ትግሬ ከመሆን ውጪ በተይ አማራ ሆኖ መገኘት ነፍጠኝነት ሆኗል። የፖለቱካ እስረኞች ሳይቀሩ አንተኮ አማራ ነህ ኦሮሞ ነህ እየተባሉ በዘራቸው እየተሰደቡ እንደሚደበደቡ ብዙዎች ተናግረዋል። ወያኔ ይህንን ጠባብ አስተሳሰቡን ወደሌላው ብሄር ለማጋባት ብዙ ቢሞክርም አልተሳካም ወደፊትም አይሳካም ህዝቡ አንድ ነው። ብሄር፣ ቋንቋ፣ ሀይማኖት ሳይለየው ለብዙ ዘመናት በመተሳሰብና በመከባበር አብሮ የኖረ ህዝብ ነው።

በአማራው ላይ የሚፈፀመው በደል ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። ያስገረመኝ! በቅርቡ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ’’ህዝበ አማራው’’ አማራ እንደሆነ እየታወቀ፣ ወያኔ ትግራይን ሲገነጥል ግዛቱን ለማስፋት ሲል ህዝቡን እናንተ አማራ አይደላችሁም ትግሬዎች ናችሁ ተብለው በግድ ትግራዊነት የተቸራቸው የወልቃይት ጠገዴ ህዝቦች ኧረ እኛ ትግሬ አይደለንም አማራ ነን ድንበራችንም ተከዜ ድረስ ነው ትግሬ እንጂ ተከዜ ድንበር ተሻግሮ አያውቅም ብለው የማንነት ጥያቄ አቀረቡ። መንግስት ያለ መስሏቸው ኮሚቴ አቋቁመው ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ጥያቄያቸውን እስከ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ ቢያቀርቡም፣ ኮሚቴዎቹ የገጠማቸው እስርና እንግልት ነበር። ህዝቡም ይህንንኑ አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ ቢያደርግም አይምሬው ወያኔ ያሰረውን አስሮ የገደለውን ገድሎ የተሰጣችሁን ትግራዊነት ተቀብላችሁ ተቀመጡ ብሎት እርፍ አለው። ሰው የማንነት ጥያቄ ይዞ እንዴት ዝም ይላል ዝም አይልም ትግሉም እንደቀጠለ ነው።

ወያኔ ብሄር የሚሰጠን እሱ የሚነጥቀን እሱ ሆኖ ሳለ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት ለማስከበር ነው የትግራይ ተወላጆች አጥንታችንን ከስክሰን ደማችንን አፍስሰን የታገልነው ምናምን እያሉ ይደሰኩሩናል እነሱ እንደሚያስቡን ደንቆሮ መስለናቸው። መልክት ለወያኔዎችና ተላላኪዎቻቸው ለማንኛውም ዘረኝነት ለማንም አይበጅም፣ አሁን ጊዜው በጣም እረፍዶባችኋል ሀገር ማስተዳደር ካቃታችሁ ቆይቷል። በአራተኛ ክፍል ተማሪ ጀነራሎች ሀገር ቀርቶ ቀበሌ አይመራም፣ የአንድ ብሄር የበላይነትም ሆዳምነት ነው፣ እንደምታስቡትም ኢትዮጵያ አትፈርስም ህዝቡ ነቅቷል፣ ይበቃናል ትላላችሁ ብለን ታግሰን ነበር አሁን ግን እኛ በቃ ብለናል ጊዜው ቀርቧል የሁላችን ቁጣ በያለንበት ገንፍሏል፣ ፅዋው ሞልቷል ሀገራችንን ነፃ የምትወጣበት ጊዜው እውን ሆኖ በቅርብ ታዩታላችሁ። እንደምንፋረዳችሁም ማወቅ አለባችሁ ወንጀል ሰርቶ የትም መሰወር አይቻልም አለም አንድ ናት። 

ዝምታ ወርቅ ነው ብሎ አንገቱን ደፍቶ ለ25 ዓመታት የተቀመጠውን ህዝብ ቆስቁሰው ቆስቁሰው የተዳፈነውን እሳት አነደዱት። የማያዳፍኑት እሳት  በየአቅጣጫው ሲነሳ ወያኔ ማጣፊያው አጥሯት ግራ ገብቷታል። አንዴ መግለጫ አንዴ ምናምን ብታንጋጋም ግርግር ብትፈጥሩም ጊዜው እረፍዷል። ለ25 አመት ታፍኖ ሲናቅና ሲሰደብ፣ ሲገዛ፣ ስትረግጡት የነበረው ህዝብ አሁን ባንድነት በቃ ብለን ተነስተናል መመለሻ የለንም ጉድ ፈላብሽ ወያኔ የዘመናት ብሶት የወለደው .............. ብላችሁ ነበር አይደል ያኔ ስትገቡ አሁን ደግሞ እኛ በተራችን  ‘’የዘመናት ብሶት የወለደው የህዝብ ድምፅ የትግራይ ነፃ አውጪ ድርጅት / ህወሀት/ ሲጠቀምበት የነበረውን የኢትዮጵያ ህዝብ ራዲዮ ተቆጣጥሮታል’’!!! ብለን ሀገራችንን ነፃ የምናወጣበት ቀኑ እሩቅ አይደለም።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ



onsdag 31. august 2016

በር ዜና: በመተማና አምባጊዮርጊስ ከፍተኛ ውጊያ እየተደረገ ነው | መተማ ቤቶች እየተቃጠሉ ነው | ጦሩ እየከዳ ሕዝብን እየተቀላቀለ ነው

(ዘ-ሐበሻ) በመተማና በአምባጊዮርጊስ ከተሞች ከፍተኛ የሆነ ውጊያ እየተደረገ መሆኑ ተሰማ:: የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት በአማራው ላይ የሞት ፍርድ ከፈረደና መከላከያ ሰራዊቱ በሕዝብ ላይ እርምጃ እንዲወስድ ከተፈረደ በኋላ የመንግስት ጦርም ሕዝብ ላይ መተኮስ ከጀመረ ወዲህ በመተማ ቤቶች በመቃጠል ላይ ናቸው::
ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በመተማና አምባጊዮርጊስ ሕዝብ ከትግራይ ነጻ አውጪ ወታደሮች ጋር እየተዋጋ ሲሆን አንድ ኦራል ወታደራዊ ተሽከርካሪ ላይ ጥቃት ከመፈጸሙም በላይ በርካታ የአጋዚ ጦር አባላት ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል::

በአምባጊዮርጊስ እስካሁን ታይተው የማይታወቁ ጸጉረ ልውጥ ሰራዊት ከሕዝብ ጋር እየተታኩሱ ሲሆን ከተማዋ የጦር አውድማ መምሰሏ ተሰምቷል::
በሌላ በኩል በአብራጅራር ከተማ በመቶዎች የሚቆጠሩ የመክላከያ ሰራዊት አባላት በሕዝባችን ላይ አንተኩስም በሚል ከነትጥቃቸው ከሕዝብ ጋር በመቀላቀል የትግራይ ነጻ አውጪ ሰራዊትን እየተዋጉት መሆኑም ተዘግቧል:: ለዘ-ሐበሻ ከየስፍራው የሚደርሱ የመከላከያ ሰራዊት ድምጾች እንደሚያስረዱት ከሆነ ከሰራዊቱ መካከል ሕዝቤ ላይ አልተኩስም በማለት በርካታ አባላቱ ዝህቡን እየተቀላቀለ ነው::
ከታች የባህርዳርን ውሎ የሚያሳየውን ቭድዮ ይመልከቱ



mandag 30. mai 2016

መንግስት የ12ኛ ክፍል ፈተናው መሰረቁን አምኖ ዛሬ ሊሰጥ የነበረው ብሔራዊ ፈተና እንዲቋረጥ አደረገ

      



fetena2
(ዘ-ሐበሻ) በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ከተሞች ባለፉት 4 ወራት በነበረው የሕዝብ ተቃውሞ ተማሪዎች በአግባቡ ትምህርታቸውን ሳይማሩ ቀርተዋል:: ይህን ተከትሎም ያልተምሩትን እንዳይፈተኑ; ለፈተናም በቂ ዝግጅት ባለማድረጋቸው እንዲራዘም ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ ቢያቀርቡም ጥያቄው ውድቅ በመደረጉ በስርዓቱ ውስጥ ያሉት የውስጥ አርበኞች ተቃውሟቸውን ለማሳየት ፈተናውን በኢንተርኔት ለቀውት ነበር::
shiferaw-shigute
ትናንት የትምህርት ሚኒስትሩ ሽፈራው ሽጉጤ “የተሰረቀ ፈተና የለም; ብሔራዊ ፈተናው በታሰበለት እና በታቀደለት ጊዜ ይካሄዳል” ቢሉም ፈተናው ግን በሶሻል ሚድያዎች መራባቱን ቀጥሎ ነበር:: ዛሬ ጠዋት እንደገና እኚሁ የትምህርት ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ “እንደማንኛውም ሰው ፈተናው በኢንተርኔት ቀድሞ መበተኑን አይቻለሁ” በሚል ፈተናው እንዲቋረጥ መታዘዙን አስታውቀዋል::
ፈተናው ከመቋረጡ በፊት ዛሬ ጠዋት የተወሰኑ የትምህርት ዓይነቶች ፈተና ተስጥቶ እንደነበርም ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል::
እንደ አቶ ሽፈራው ገለጻ በሃገሪቱ 800 የፈተና ጣቢያዎች እንዳሉና ከየትኛው ቦታ ተሰርቆ እንደወጣ መንግስት የሚጣራ ይሆናል::

One Response to መንግስት የ12ኛ ክፍል ፈተናው መሰረቁን አምኖ ዛሬ ሊሰጥ የነበረው ብሔራዊ ፈተና እንዲቋረጥ አደረገ

  1. በዚህ ምክንያት ብዙ ኪሳራ እንሚደርስ መንግስት ማስተዋል አለበት

tirsdag 17. mai 2016

አዲስ አጭር መረጃ ስለታላቁ የነጻነት ታጋይ አንዳርጋቸዉ ጽጌ!!

በመላዉ ኢትዮጵያዊያን ልቦና ዉስጥ ሰርጾ መግባት የቻለና የማይበርድ የትግል ምእራፍን በመንደፍ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ነጻነትን የቀለመ አባት ነዉ ! እ.ኤ.አ በግንቦት ወር /2014 የየመን ዋና ከተማ ሰናአ ላይ ተሰወረ! የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን ለወንበሬ ያሰጋኛል ብሎ በጠላትነት የተነሳበት የግንቦት 7 ዋና ጸሐፊ ክቡር አንዳርጋቸዉ ጽጌ በግፍ ለወንጀለኛዉ የወያኔ ቡድን ተላልፈዉ ተሰጡ!
andargachew new picture
ነጻነት ላያንቀላፋና ነጻነት ላይታሰር አንድነትና ኢትዮጵያዊነትን በጫንቃዉ ተሸክሞ በማረፊያዉ ወቅትና ሰአት የጎረመሰዉ አባት አንዳርጋቸዉ ጽጌ ብዙሃንን አፍርቷል!! ዛሬ የፍሬዉ ትሩፋቶች አደራቸዉን ተቀብለዉ ሐገራቸዉንና ትዉልዳቸዉን ለመታደግ ዳር በደረሱበት ወቅት ወያኔያዉያን ግን ታላቁን አባት ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ላይ ይገኛሉ! ከሰሞኑ በደረሰን መረጃ መሰረት የተከበሩት የነጻነት አባት ክቡር አቶ አንዳርጋቸዉ ጽጌ የፌደራል ፖሊስ ህንጻ ስር ምድር ቤት ዉስጥ ( underground ) ክፍል ዉስጥ መወሰዳቸዉን የሚያረጋግጡ ሲሆን የብሔራዊ መረጃ ምንጮቻችን በበኩላቸዉ ሌሎች ተጨማሪ ግለሰቦች በዚያዉ በፌደራል ፖሊስ የምድር ቤት ብቸኛ ክፍል ዉስጥ ከታላቁ የነጻነት አባት ጋር እንደሚገኙ ፍንጭ ሰጥተዋል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !

onsdag 11. mai 2016

ኖርዌይ ኢትዮጵያውያን የፓለቲካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በግዳጅ ወደ ሀገራቸው ለመመሰስ ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ያደረገችውን ስምምነት የሚቃወም ታላቅ ሰልፍ ተካሄደ!!


 ሜይ 11፣2016
ዲቦራ ለማ/ኖርዌይ
 
ኢትዮጵያውያን በስደት ከሚኖሩባቸው የተለያዩ የአውሮፓና ስካንዴኔቪያን ሀገሮች አንዷ የሆነችው ኖርዌይ ስትሆን በኖርዌይ ሃገር ቁጥራቸው አነስተኛ የማይባል ኢትዮጵያውያን የፓለቲካ ስደተኞች ይገኛሉ። እነዚህ ስደተኞች ከሌላው ሀገር ለየት የሚያደርግ ጠንካራ የፓለቲካ አቋም ያላቸው መሆኑም ይታወቃል። ስደተኞቹ በተለያየ ጊዜያት የገዢውን ፓርቲ ብልሹ አስተዳደር የሚያጋልጡ የፓለቲካ ስራዎችን ሲሰሩ መቆየታቸው ይታወሳል።

ሆኖም ግን የኖርዌይ መንግስት እ.ኤ.አ በ2012 ከቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊ ጋር በኖርዌይ የሚኖሩ ጥገኝነት ጠያቂዎችን አስገድዶ ወደ ሃገር ለመመለስ የሚያስችል ስምምነት መፈረሙ ይታወሳል። ሆኖም ግን ይህ ስምምነት በተለያዩ ምክንያቶች ተግባር ላይ ሳይውል ቀርቷል። ኖርዌይ በድጋሚ አሁን በያዝነው አመት በፌብርዋሪ ወር እንደገና ስደተኞችን አስገድዶ ወደ ሀገር የመመለሱ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ከውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ቴዎድሮስ አደሃኖም ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን በኖርዌይ የሚገኙ ታላላቅ የዜና አውታሮች ሲዘግቡ ሰንብተዋል። 

ይህንኑ ስምምነት አስመልክቶ በኖርዌይ የሚገኘው የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ማህበር ስምምነቱ ትክክል እንዳልሆነ ተቃውሞውን ለመግለፅ በሜይ 10፣ 2016 ታላቅ ሰልፍ አዘጋጅቷል። ይህ የተቃውሞ ሰልፍ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል። ስደተኞቹ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በተለይ በቅርቡ በሀገራችን በአደባባይ እየተገደሉ ያሉ ወገኖቻችንን የያዙ ምስሎችንና የኖርዌይ ዜግነት ያላቸውና ከደቡብ ሱዳን ታፍነው በኢትዮጵያ እስር ቤት እየማቀቁ ያሉንትና አሁን ለዘጠኝ አመት የተፈረደባቸው የአቶ ኦኬሎ አኳይ ፎቶግራፍ እንዲሁም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ፎቶግራፎች በመያዝ ስለነሱም አያይዞ ለኖርዌይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካይ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ እየታወቀ ሰዎች በየሰከንዱ እየተገደሉ ባለበት ወቅት ሀገሪቱ በብዙ አቅጣጫ የህዝብ አመፅ ባለበትና ገዢው ፓርቲም ከመቼውም ጊዜ በከፋ ሁኔታ ሰዎችን እየገደለና እያሰረ ባለበት ሁኔታ ስደተኞችን አስገድዶ ለመመሰል ስምምነት ማድረጉ ለምን እንዳስፈለገ፤ እንዲሁም የኖርዌይ መንግስት ለኖርዌጅያን ዜጎች በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች መዘዋወር አደገኛ መሆኑን መግለጫ እየሰጠ ባለበት ሁኔታ የፓለቲካ ስደተኞችን አሳልፎ መስጠት ሰብአዊነት የጎደለውና የስደተኛ መብት ህግን የሚጥስ መሆኑን ኢትዮጵያውያኑ በሰልፉ ላይ ተናግረዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የስደተኞቹን ጉዳይ የሚከታተሉ የግብረ ሃይሉ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አያሌው ይመር ንግግር ያደረጉ ሲሆን ዝግጅቱም በተያዘለት ሰአት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

ኢትጵያ ለዘላለም ትኑር!!


    

onsdag 24. februar 2016

የህወሃት ልዩ ነፍሰ ገዳይ ሠራዊት አመሰራረት። አጋዚ!!!


የእግሊዝኛው ጽሁፍ አዘጋጅ ፡ዓለም ማሞ
የአማርኛው ተርጓሚ፡ቢላል አበጋዝ
 “ፔንታጎን ያሰለጠናቸው የኢትዮጵያ ሠራዊት ፤ክፉውን አጋዚ የተሰኘውን ልዩ ኅይልም ይጨምራል።”
–ጄረሚ ስከሂል
ኢንተር- ሴፕት ኤንድ ናሽናል ሴኩሪቲ ለተባለው ጋዜጣ መስራችና ቃል አቀባይ ከአሜሪካ መንግስት ክፍተኛ ምክር ቤት የፍርድ ኮሚቴ ዘንድ ቀርቦ ከሰጠው የምስክርነት ቃል የተወሰደ ጥቅስ። ዲሴምበር 9 ፣2010
ታሪኩ እነሆ
ከእድሜዋ በላይ የጠናች መስላ ትታያለች።በአካል ያያት ስድሳ ዓመት ሞልቷታል ብሎ መገመት ይችላል።እውነቱ ግን አርባ ዓመትዋ ብቻ ነው።
“ወታደራዊው መንግስት ስልጣን ከመያዙ ሁለት ዓመት በፊት ነው የተወለድኩት” ትላለች ታሪክ እየጠቀሰች።የተጨማደደው ቆዳዋ፤ማዲያቷ እና ሽበትዋ መከራን ያሳለፈችን እናት ታሪክ ይናገራሉ።ያለፉት አስር ዓመታት በችግር የተሰቃየችባቸው ናቸው። “የበኩር ልጄን ከአስር ዓመት በፊት ቀበርኩ፤እኛ ተቃዋሚዎች አቸንፈን ድምጣችንን በቀሙን ጊዜ” አለች ወደ አድማሱ ቃኝታ ከተራሮቹ ሰው ብቅ የሚል እንደሁ ትጠብቅ ይመስል።
“እንዴት ሞተ?” ብዬ ጠየቅኋት ላለፉት አስራ አምስት ደቂቃዎች ከማታው ውርጭ ላይ ከቆየንበት ውጭ ወደቤት እየተከተልኳት።
“በጠራራ ጸሃይ ከሚወደው ጓደኛው ጋር ነው የገደሉት።አንዲት ቦታ፤ በአንዲት ቀን ነው አዲስ አበባ ላይ የተገደሉት።” አለች በተጎሳቀለው ፊትዋ ላይ እምባዋ እየወረደ።ምሬትዋንና ያለችበተን የከፋ ሃዘን ጥልቀት በቃላት ለመግለጥ ይከብዳል። ከተቀመጥኩበት ብድግ ብዬ እጆችዋን ይዤ ካጠገብዋ ቁጢጥ አልኩ። “ማን ገደላቸው ?” ብዬ ጠየቅኋት።ትክዝ ብላ ቆይታ ወደበሩ ራመድ፡ ራመድ ብላ በሩን ከዘጋችው በኋላ ሚስጥር እንደምትነግረኝ ሁሉ ዝቅ ባለ ድምጥ “አጋዚ። ጋዚ። ነው የገደላቸው” እያለች የሟች ልጆችዋን ፎቶግራፎች ሳም ሳም አድርጋ እንዳያቸው ሰጠችኝ።ለትምህርት ምረቃ ቀን የተነሷቸው ነበሩ።ምስላቸው በፈገግታ ተሞልቷል።ምኞትና ተሰፋ ይታይባቸዋል።ፎቶግራፎቹ በእምባዋ ርሰዋል የንባዋ ዘለላ በፎቶ የሚታየውን የልጆችዋን ፈገግታ ሲሸፍነው ሀዘንዋን የሚጋሯት መስሎ ታየኝ። ሙታንና ቁዋሚዎች አብረው የሚያለቅሱበት አገር። በምናቤ ልጆቹ ቤቱ ውስጥ ያሉ መሰለኝ።በናትና ልጅ መሃል ሞትም የማያስቀረው ውህደት በማህፅንና በእትበት መሃከል ያለው ቁርኝት ይሆን ? እንጃ። ብቻ የልጆቹ ውቃቢና የዓፍላ መንፈሳቸው ክቤቱ ውስጥ አለ።ካደጉበት።ከምዬ ቤት።ገና ባጭር ሳይቀጩ ከነበሩበት።ከኪሴ መሃረብ አውጥቼ እንባውን ከፎተግራፎቹ በዝግታ ጠረግሁ።በጥልቅ አዘኔታ ሳያቸው ወንድሞቼ፤የወንድሜ ልጆች፤ያጎት ያክስቶቸ እንዲያው የናቴ ልጆች መስለው ታዩኝ።በህይወት ባሉበት ጊዘ አግኝቻቸው ባላውቅም የማውቃቸው መሰሉኝ።የኔ የራሴን ያለፈ የልጅነቴንና የወጣትነት ዘመን ከፊቴ ደቀኑብኝ።ወጣትነቴን፤ፍርሃት አልባነቱን፤ለፍትህ፤ለነጻነት፤በቁርጠኝነት ተከራካሪነት መቆሙን።
ዲሞክራሲ! ለምእተ አመታት እውን ያልሆን ስንቀርበው የሚርቀን  የኔ ትውልድ ህልም፤ያለፈው ትውልድም ህልም፤የዛሬው ትውልድም። “አዬ እርግማን” ብዬ ለራሴ አጉተመተምኩ።
ለመሄድ ስነሳ አዘንተኛዋ  እናት እቅፍ አረገችኝና  እባክህ ደግመህ መጥተህ ጠይቀኝ አለችኝ።እምባ እየተናነቀኝ ይሁን መጣለሁ። እጠይቅሻለሁ አልኳት።ስለያት ብቸኝነትዋን አሰብኩት።የሞቀ የደመቀ ሁለት ልጆችዋ ይቦረቁና ይጫወቱ የነበረበትን የዛሬውን ኦና ቤትዋን አሰብኩት።የናትን ሃዘን ጥልቀቱን እንድረዳው፤እንዲሰማኝ ሞከርኩ። የእናትን ሃዘን ፤የዘጠኝ ወር ቤትን ህመም ፤ ክናት ሌላ ማን ሊረዳው? አልኩ ለራሴ።
አጋዚ የሚለውን ስም በተደጋጋሚ ሰምቸዋለሁ።ኢትዮጵያ ውስጥ ሰዎች ስለ አጋዚ የሚናገሩት ልክ እንደ ውጭ ወራሪ ሀይል አድርገው ነው።የዚህ ቡድን ሰለቦችና ተግባሩን ያዩት እንደሚናገሩት “ግኡዝ ገዳይ ሮቦቶች፤ ምንም ልዩነት የማያደርጉ ትንሽ ከትልቁ መለየት ህጻናት ከአዋቂ፤ወጣት ሽማግሌ፤ ሴት፤ ወንድ፤ የታጠቀ ወይ ጀሌ አንዱንም የማይመርጡ።ጨፍጫፊ።ግፍ መስራቱን ይወዱታል ቢባል ከውነት የራቀ አይሆንም።
አንድ የፋሺት ጣሊያ ወረራ ጊዜ የነበሩ አርበኛ አጋዚን ከጣሊያኑ ጊዜ ካራብኘሪ ጋር ያመሳስሉታል።
“ቋንቋቸው ግራ ነው።ባህልና ወግ ግዳቸውም አይደል።ባሻቸው ጊዜ መጥተው ወንዶችን፤ልጆችን መንጭቀው ይሄዳሉ።ሲሻቸው እዚው ረሽነው ይሄዳሉ። መንደር ቀበሌ ከተማ ይወርራሉ።አየህ አጋዚ ልክ እንደ ጣልያን ካራብኘሪዎች ነው።” የአረጋዊው የነጣው ረጅም ጢም፤የተሸበሸበው ግንባራቸው ብሩህ አይኖቻቸው ምስክርነት የቆሙ ይመስላሉ።
“ታውቃለህ እንዲህ ያለ በገዛ ህዝቡ ላይ የሚጨክን መንግስት ኖሮን በታሪካችን አያውቅም። ካራብኘሪዎችን ምን እንዳደረግናቸው ልንገርህ።” አሉ በኮራ ድምጻቸው “የእግዜርን እርዳታ ይዘን ከአርበኞች ጋር ሁነን ነቅለን ጣልናቸው።” የሚነደው ያገር ፍቅራቸው እንደ እሳት  ወላፈን ሙቀቱ እየተሰማኝ። “አጋዚዎችንም ዋጋቸውን እንሰጣቸዋለን።አዲሱ ትውልድ የኛን አርበኝነት ተዋርሷል።የጊዜ ጉዳይ ነው።አገራችን ነጻ ትወጣለች።” አሉ ምርኩዛቸውን ጠበቅ አድርገው እየጨበጡ።የታሪክ ምጸት ቢሆንም የአጋዚን ከጣሊያን ካራብኘሪዎች ማነጻጸር አሁን ብቻ አይደለም የሰማሁት።በስልጣን ላለው መንግስት ተወዳዳሪ ለሌለው ጭካኔ ማመሳከሪያ በመሻት ነው።
ባገሪቱ የትኛውም ክፍል ህዝባዊ እምቢተኝነት ወይም አመጽ ሲነሳሳ ከየት መጣ ሳይባል አጋዚ ከቸች ብሎ የአፈናና የግድያ ተግባሩን ያከናውናል።ብዙ ተመሳሳይ የአጋዚን ዘግናኝ ተግባራት፤ኢሰባዊ ድርጊቶችም  የሚገልጡ በርካታ ምስክርነቶች ሰምቻለሁ።ሁለት ወንዶች ልጆችዋን ለአጋዚ የገበረችውን እናት ካነጋገርኩ ወዲህ ግን አስተሳሰቤ ተለወጠ።ሀዘንም ዋጠኝ።ከዚህ ሌላስ ምን ግፍ ተሰርቷል?ምን ግፍስ ይሰራ ይሆን? እያለ አእምሮዬ ወተወተ።የዚህን የገዳይ፤አፋኝ ቡድን አሳዛኝ ድርጊት በሚቻለኝ መጠን ለማጋለጥ ቁርጠኛ አደረገኝ።
አጋዚ የሚለው ስም በኢትዮጵያ ፍራትና ሽብርን ይፈጥራል።ልክ ካራቫን ዴላ ሙኤርቴ (የሞት ቅፍለት) ተብሎ በቺሌ ላቲን አሜሪካ ይታወቅ እንደነበረው አይነት ነው።ይህ ቡድን አውጉስቶ ፒኖቼ የተባለው ወታደራዊ አምባ ገነን በ1973 ዓም መፈንቅለ መንግስት እንዳካሄደ ያቋቋመው ነው።ሌላው ተመሳሳይ ደግሞ ጄኔራል ሆዜ አልቤርቶ ሜድራኖ ያቋቋመው ኦርጋኒዛሲኦን ዴሞክራሲያ ናሺናሊስታ[1] የተባለው የኤል ሳልቫዶር (ላቲን አሜሪካ) ገዳይ ሰራዊት ነው። ይህ ሰራዊት በስውር የሚያግት፤በህይወት ፈራጅ፤ሰቆቃ ፈጻሚ ነበር። ለማንም መንግስትን ለተቃወመ ወይንም ተቃውሙዋል ተብሎ ለሚጠረጠር ቡድን ወይም ግለ ሰብ ያለ ምህረትና ሰባዊነት የግፍ ቀንበሩን ያሰፈረ ቡድን ነበር።
አጋዚ ምስጢራዊ  ራስ ገዝ ተጠያቂነቱ ቱባ ለሆኑት እፍኝ የማይሞሉ የህወሃት አመራሮች ነው።አጋዚ የተሰየመው ከህወሃት መስራቾች አንዱ በነበረው ዘሩ ገሰሰ የትግል ስሙ አጋዚ ነበርና።በውነተኛ ወታደራዊ አደረጃጀት ሲመዘን አጋዚ የግል ጦር፤ቅጥረኛ በጦር ቱጃሮች (war lordes) የግል ጥቅማቸውን ለመጠበቅ የሚቆሙትን ዓይነት ነው።የእዝ ሰንሰለቱ ከቋሚው ዘረኛና በዘር ከተዋቀረው የህወሃት መደበኛ መከላከያ መዋቅር ውጭ ነው።የአጋዚ መኖር ዋነኛ ምክንያት ወያኔ ኢሃዴግን በስልጣን ማሰንበት ነው።መንደርም በእሳት ተለኩሶ ይውደም፤ንጹሃን በጥይት ይፈጁ፤ ቀዬዎች የሽብር አምባ ይሆኑ፤ወያኔ ብቻ ይሰንብት። የአጋዚ መኖር ለዚህ ነው።አጋዚ ቀድሞ ሲመሰረት “ጸረ ዓለማቀፍ ሽብርተኛ” የሚል ጭንብል ነበረው። ይህ የሆነው የምእራብ አገር መንግስታትን ለማማለልና ደስ ለማሰኝት አልፎም ድጋፍ፤ስልጠና እና ትጥቅም ለማግኘት ነበር።ቍም ነገሩ ግን አገር በቀል የሆኑትንና ለዲሞክራሲ ፤ ለፍትህና ለነጻነት ራእይ የሚደረጉ ትግሎችንና እቢተኝነትን መደምሰስ ነው።
በዚህ ጉዳይ ላይ ጥቂት መርማሪ ጋዜጠኞች ስለ አጋዚና የውጭ ድጋፉ ጠይቀዋል።ይህን ግፈኛ ቡድን ማነው የሚያስታጥቀው ማንስ አሰለጠነው እያሉ።ከኒህ ጋዜጠኞች መካከል ጄረሚ ስከሂል ተቀዳሚው ነው።የዩ ኤስ አማሪካን ተመሳሳይ ሚና በአፍጋኒስታን፤ በማሊ፤ በሶማሊያ፤በየመን መርምሯል። በዲሴምበር 9 ቀን 2010 ዓም ለአሜሪካ ምክር ቤት በዝርዝር ምስክርነት ሰጥቷል።ምስክርነቱ ሰው አልባ የሚበር አውሮፕላንን  እቅስቃሴ፤የዩ ኤስ አሜሪካንና የሶማሊያ ጎሳ ጦር አበጋዞች ጋር ግንኙነት አካትዋል። “ሽብርተኝነትን መዋጋት” በሚል ሰበብ እንዴት አሜሪካ እንደ አጋዚ ያሉ የገዛ አገራቸውን ዜጎቸ የሚያሸብሩ ወታደራዊ ተቋሞችን መደራጀት ልታግዝ እንዴት እንደቻለች ጠይቋል። እንደ ሚስተር ሺል ጥናት “የዩ ኤስ አሜሪካን ልዩ ወታደራዊ ቡድን ለረጅም ጊዜ የአጋዚን ሰራዊት ሲያሰለጥን ኖርዋል”[2] የስከሂል የጥናት ጭብጥ እንደ ህውሃት ካሉት ጋር መቧደን የዘለቄታው ጉዳቱን  ለአሜሪካና ለአገራችንም የሚያስከትለውን ጉዳት ማመላከት ነው።
ቃሌን ጠብቄ የሁለቱ ልጆች እናት የወላድ መሃንዋን ልጠይቃት ተመለስኩ።ጭጋጋማ ቀዝቃዛ ምሽት ነበር።ከጓሮዋ  ካለችው ትንሽ ያትክልት ስፍራ እየቆፋፈረች ነበረ።”በልጆቼ ሃሳብ የተጨናነቀውን አእምሮየን ቢያስታግስልኝ ብዬ እማስናለሁ።” አለች እጅዋን እየጠራረገች። ክበሩ መግብያ ስደርስ ጠበቅ አድርጋ አቀፈችኝ። የናት ፍቅር ሙቀቱ እየተሰማኝ ወደቤቱ ውስጥ ተከተልኳት።
“እግዜር ይባርክህ ልትጠይቀኝ በመምጣትህ።” አለች ወደ ማድቤቱ እያመራች። “ሻይ አፈላልሃለሁ” አለች።
“አመሰግናለሁ” ብዬ መለስኩ።
ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በእጅ በተሰራ ቅርጫት ብስኩት፤ ሻይ በፊንጃል ይዛልኝ መጣች።ስለ ብዙ ነገሮች አወራን።”ዛሬማ ብዙ እናቶች ለሞቱ ልጆቻችው ጥቁር ይለብሳሉ” አለችኝ አንዳንዶቹን በስም እየጠራች።
“ዛሬ እኮ ጨለማ ዘመን ነው።ጓደኞቸ፤መንደርተኞቸ፤የከተማውም ሰው አንድ ሰው ቢያንስ ተገሎባቸዋል” አለችኝ።
ደግሜ ልጠይቃት የመጣሁት ስለሟች ልጆችዋ ለመጠየቅ የሷንም መጽናናት ላውቅ ብዬ ነው።እንቅልፍ አጥታ እንደሰነበተች እንዲያው ድክም ብሏታል።ትንሽ ተኝታ ታድር እንደሁ ጠየቅኋት። “ሽለብ ሲያገኝ ልጆቼ ከፊቴ ድቅን ይላሉ።ከትምርት ቤት ሲመጡ፤ያዘዝኳቸውን ሲከውኑ፤የትምህርት ቤት የቤት ስራቸውን ሲሰሩ።እንቅልፍ የለኝም።ደህና እንቅልፍ የተኛሁበት ምሽት ይናፍቀኛል።”  ጥልቁ ሃዘንዋ፤አንዱ በሌላው ላይ የተደራረበው መከራዋ ህወሃት የፈጸመውን በደሎች ያመለክታሉ።ፈተናዋ አድክሟታል።
“የት ነው ልጆችሽ የተቀበሩት ?” አልኳት
“ተዚህ ግድም።ሩቅ አይደለም። በግር ያስኬዳል።በሰንበት ሁሌ ልጆቼን ላጫውት እሄዳለሁ” አለች።
“ዛሬ ትወስጅኛለሽ?” አልኳት
“አዎ! እወስድሃለሁ” እያለች ጥቁር ጥለት ነጠላዋን ተከናንባ “ተከትለኝ” አለችኝ። “በዚህ ጋ” ስትል ተከትያት ለአስራ አምስት ደቂቃ በደረቀው ሳራማ ሜዳ ላይ የግር መንገዱን ተከትለን ተጓዝን።ከሩቁ የሚግጡ ከብቶች ይታዩኛል።ጥቂት ሄደን ቤተ ክርስቲያኑ ቅጥር ደረስን።ጥቂት ጸሎት አድራጊዎች ተውጭው ይታያሉ ሌሎችም እየመጡ ነበር።ተገረገራው ስትደርስ አማተበችና እየሰገደች ጸለየች። እኔም እንደስዋ አደረግሁ። ጥቂት ራመድ እንዳለች ከበተ- ክርስትያኑ ደቡባዊ ጠርዝ ልጆችዋ ካረፉበት ደረስን። ጠጋ ስንል ንግግርና ልቅሶ ተደባልቀው እንሰማለን።
“እዚህ ነው ትኝት ያሉት።ልክ ከቤታቸው አብረው በልጅነታቸው ተቃቅፈው ይተኙ እንደነበረው፤አበቦቼ፤ልጆቼ” እያለች ፊትዋ ላይ ያለውን እንባ ጠረገችው።የራሴን እንባ እየታገልኩ እሷን ላጽናናት ሞከርኩ።ትንሹ ሲገደል ገና አስራ ስድስት ዓመት እንደነበረና ሰላማዊ ሰልፍ ሲካፈል እንደተገደለ ነገረችኝ። “ልክ እንደኔው ልጆቻችው በአጋዚ ጥይት የረገፉባቸው እናቶች እጅግ ብዙ ናቸው።” አለች ጉዞአችንን ወደ መጣንበተ ማምራት ስንጀምር።
“እንደምሰማው አጋዚዎች የሰለጠኑት በአሜሪካኖች ነው።ይህ እውነት ነው?” ብላ ጠየቀችኝ።አጥብቃ ነው የጠየቀችው ድምጽዋ ንንዴትም ብሶትም የተቀላቀለበት ይመስላል።
“አዎን ተመሳሳይ ዜና ሰምቻለሁ” ብዬ መለስኩላት።
“ለምን ልጆቻችንን የሚገድል ታጣቂ ቡድን ያሰለጥናሉ? ሳስብ የነበረው አሜሪካኖች ደግ ሰዎች ናቸው ብዬ ነበር። አዛኞችም ናቸው ብዬ ነው።”
“የአሜሪካ ህዝብ አይደለም።ይህ የፖለቲከኞች ውሳኔ ነው።” ብዬ ተገቢውን መለስኩላት። ትንሽ ቢያጥናናት ብዬ።
“ምን አልባት እንዳንተ የተማሩ ሰዎች የኛን በደል ለአሜሪካ ፖለቲከኞች ማድረስ አለባቸው። አጋዚ የሚባለው ልጆቻችንን መግደል እንዲያቆም።” አለች።
ለአሜሪካ ፖለቲከኞች ፤ለአሜሪካም ህዝብ ለዓለምም ሁሉ መልክትዋን ለማድረስ ቃል ገባሁላት።
ለመሄድ ስነሳ እንደምትማጠነኝ ሁና ወዳይኔ ብረቱ እያየች፤
“እባክህ በደላችንን ዓለም እንዲያውቀው አድርግ።አጋዚን አሰልጥነው ማስታጠቃቸው፤ በጅምላ ገዳዮችን ማሰልጠናቸው መሆኑን ይወቁት።አንድ ብቻ ሳይሆን ሁለት ልጆችዋን የተቀማችዋን እናት ታሪክን ንገራቸው።የወላድ መካንን እናት ምን ይሏታል? መካን የሆንኩት ሁለቱን ባንዴ አጋዚ ሲቀማኝ ነው።” አለች።
እኔ ለዚህ ሁሉ ጥያቄዎችዋ መልስ የለኝም።መልስም የምትጠብቅ አይመስለኝም።እንደው ሀዘንዋ ይውጣላት ብላ እንጂ።ምናልባት ሁለቱንም።እኒህ እለት ተእለት የማብሰለስላቸው ጥያቄዋች ናቸው።እስተማውቀው ድረስ ጥያቄዎቹ በሺ የሚቆጠሩ እናቶች ባገሩ በሞላ የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ናቸው።
ምስኪንዋን እናት ተሰናብተን መንደሩን ለቀን ስንጓዝ አይኖቼ አካባቢውን አማተሩ።የሚጫወቱ ልጆች አይታዩም።በማሳው ላይም ገበሬዎች የሉም ።መንገደኛም አይታይም።ህይወት እርጭ ብሎ፤ታግቷል።ተሩቅ የተኩስ ድምጥ ይሰማኛል።ማን ይሆን ባለሳምንት? ሌላ ወጣት? ወንድ ?ሌላ ወጣት ሴት?ሽማግሌ ማን ይሆን? ማነው ባለተራ ? ማን ይሆን የአጋዚ እራት ብዬ ተከዝኩ።
ባልጋዬ ጋደም ብዬ ያን ማታ የዚህን ጭካኔ መነሻ ልደርስበት አሰብኩ።ዘመናዊ ስልጣኔና ተቋም አቀድ የሆነ አረመኔያዊ ጥፋት በንጹሀንና ባልታጠቁ ህዝቦች ላይ! ሃሳቤ ከቦታ ቦታ ተንክራተተ፤ከአንድዋ እናት እምባ ወደ ሌላዋ። ከአንዱ አባት ምሬት ወደ ሌላው።ሸለብ ያረገኝ ብዬ ባስብ አእምሮዬ እምቢ አለ።“ሽለብ ሲያደርገኝ ልጆቼ ድቅን ይላሉ” ብላ ያለችው ደግሞ ደጋግሞ ባሳቤ ይመጣል።ልጠይቃት መሄዴ ሃዘንዋን አባብሶት ይሆን? ብዙ ተገላብጨ እንቅልፍ እምቢ ሲለኝ ተስፋ ቆረጥሁ።አጣጥፌ ከደብተሬ ያኖርኩትን የተጣጠፈ ወረቀት ሳብ አደረግሁት።የጥንቱ ሮማዊ ገጣሚ ጋየስ ቫሌሪየስ ከታለስ (84᎔54 ከክርስቶስ ልደት በፊት)ግጥም ነበር። ለሟች ወንድሙ የገጠመው፤
“በባእድ ባህሮች ቀዘፋ፤ ባልታወቁ ወደቦች ለቀናት በባህር ስጓዝልህ
ከዚህ የመጣሁት ለሽኝት ነው የናቴ ልጅ ላንተው ስንብት፤
ለሞትከው የቋሚን የመጨረሻ ስጦታ ይዥልህ
ቃሌ ከንቱ ነው ትቢያ ለሆነው ሰው።
አይ ወንድምየ ይኸው አንተን ነጠቁኝ
አንተን አብሮ አደግ ወንድሚን ቀሙኝ!
በጨካኝ እጃቸው ቀጠፉህ እኔንም በሀዘን ወጉኝ።
ይሄው ተዝካርህ ድሮም ለሄደ ድንግጉ
ትዝካርህን እነሆ በማእርጉ
የወንድምህ እምባ ያራሰውን
ውሰድ አድናቆቴን በሞቴ የእምባየን ንዳድ ስንብቴን”
ግጥሙን በህወሃቱ አጋዚ ለተገደሉት ሁሉ ደጋግሜ አነበብኩት።ደጋግሜ ባነበብሁት ቁጥር  አገሩን ማሰስ አማረኝ። እያንዳንድዋን አጋዚ ልጇን የቀማትን እናት ላናግር።ላዳምጣቸው፤ ሀዘናቸውን እካፈል ብዬ።ስሜቴና ፍላጎቴ ቢገፋፉኝም በተግባር ማዋሉ አቀበት መሆኑ አልጠፋኝም።የአጋዚ ግድያ ከመብዛቱ የተነሳ ቁጥሩ አያሌ ነውና በጥቂት ዓመታት ላዳርስ የምችለው ጥቂቶችን ብቻ ነው።ጥቂቶችን ብቻ።ጠዋት ሲነሱ ባዶ ወንበሮችን የሚያዩትን እናቶች። ከትምሀርት ቤት የቀሩባቸውን፤ለሰርጋቸው ያልበቁላቸውን፤አያቶች ያደርጉናል ብለው ይጓጉላቸው የነበሩትን።
ቆይቶ አእምሮዬ ተረጋግቶ አሰበ።አገሩን አስሼ የእናቶችን የሃዘን ህመም ሁሉ ማዳመጥ ወሰንኩ።የግል የምስጢር ፍላጎቴም ይሆናል የአባቴን አገር፤ውቡን አገር ያያት የቅማያቴን አገር ላይ።ቀኑ፤ቦታው፡ሰአቱ፡ምክኛቱ ወይ ሰውዬው የተለየ ይሆናል ወይ ጠመንጃውን የተኮሰው ሰውዬ አንድ አይሆን ይሆናል። የናቶች መሪር ሀዘን ግን ከሰሜን ተራሮች ይሁን ከምዕራብ ጥቅጥቅ ጫካ ፤ከሜዳማው አገር ይሁን ከደቡቡ ሳራማ መሬት፤ክምስራቅ፤ከከተማ ይሁን ባላገር የትም ቢሆን የእምዬ ሀዘን ያው ነው።እርር፤ድብን ነው።የዘጠኝ ወር ቤት ንዳድ።
ላሁኑ ስለማውቃት እናት መናገር መርጫለሁ።ስለተዋወቅኋት ደስታና ክብር ስለሚሰማኝ እናት።በስም ልጠራት የማልችለው እናት።የሁለት ልጆችዋ ምስል በአእምሮዬ ታትሞ የቀረው።ጀምበር በወጣች ቁጥር እኔን ወጥረው ይይዙኛል።ሁሌም ለፍትህ ቁም።ለስልጣን ለሹመት ሳይሆን እያሉ። ይህ ደግሞ ላደርግ ከምችለው ትንሹ ነገር ነው።

ደራሲውን ለማግኘት