torsdag 15. mai 2014

የወያኔ መንግስት የፕሬዚዳንት ሳልቫኪርን ንግግር ለማስተባበል ሞከረ

ኢሳት ዜና :-የደቡብ ሱዳን ፕሬዝደንት ሳልቫኪር ባለፈው አርብ አዲስአበባ ውስጥ ከተቀናቃኛቸው ዶ/ር ሪክማቻር ጋር የሰላም ስምምነቱን የፈረሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም “አስርሃለሁ” ብለው ስላስፈራሩኝ ነው ሲሉ የተናገሩት “ለቀልድነው” ሲል የኢትዮጵያ መንግስት መግለጹን ሰንደቅ ዘግቧል።
ሳልቫኪር ከተቀናቃኛቸው ዶር ሪክማቻር ጋር የሰላም ስምምነት ፈርመው ወደ ሀገራቸው እንደተመለሱ ጁባ የአየር ማረፊያ ተሰብስበው ለሚጠብቋቸው ሰዎች በሰጡት መግለጫ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እሳቸውንም ሆነ ተቀናቃኛቸውን የሰላም ስምምነቱን ሳይፈርሙ ከአዲስአበባ ንቅንቅ እንደማይሉ እንዳስጠነቀቋቸው ተናግረው ነበር።
አቶሀይለማርያም ዶ/ርማቻርን ባናገሩበት ዕለት ጠዋት እሳቸውንም፦ “ይሄንን ስምምነት ካልፈረምክ አስርሃለሁ” እንዳሏቸው የጠቀሱት ሳልቫኪር፤ እሳቸውም በምላሻቸው “በዚህች ጥሩ ሀገር እኔን ካሰርከኝ እርግጠኛ ነኝ ጥሩ ምግብ ይቀርብልኛል።  ስለዚህ ወደ ጁባ መመለስ አያስፈልገኝም። በነፃም ትመግበኛለህ” ብለው መመለሳቸውን ነው የገለጹት።
ይህየሳልቫኪርመግለጫብዙዎችንያስገረመሲሆን፤የኬንያውንደይሊኔሽንንጨምርበበርካታሚዲያዎችሽፋንአግኝቷል።ነገሩማነጋገሩንበቀጠለበትበአሁኑወቅትሰንደቅሳምንታዊጋዜጣስለጉዳዩጥያቄያቀረበላቸውየጠቅላይሚኒስትርሀይለማርያምደሳለኝቃልአቀባይአቶጌታቸውረዳ፤<< ፕሬዝዳንቱይሄንንቃልየተናገሩትየሰላምስምምነቱንበማስፈራራትናበጫናመፈረማቸውንለማመልከትሳይሆንለቀልድሲሉ ነው>> በማለት ምላሽሰጥተዋል።
<<የፕሬዝዳንቱ አነጋገር የሰላም ስምምነቱን አስፈላጊነት በተመለከተ ያላቸውን ቁርጠኝነት ለመግለፅ እንጂ ንግግራቸው ስምምነቱን በግዴታ የተፈፀመ ለማስመሰል አይደለም፤ሆኖም ሚዲያዎች ግ ሁኔታውን አሉታዊ በሆነ መንገድ ማራገባቸው የተለመደ ነው፤ ኢትዮጵያ ሁለቱን ተቀናቃኝ ወገኖች የሰላምን አቅጣጫ እንዲከተሉ ጥረቷን ትቀጥላለች።የእነሱ ሰላም የእኛም ሰላም መሆኑን በመረዳት በተሟላ መልኩ ተሳትፎአችንን እንቀጥላለን>> ሲሉም አቶጌታቸው አክለዋል።
ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር እስካሁን ድረስ “ለቀልድስልየተናገርኩትነው>> በማለት ማስተባበያ አልሰጡም።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar