søndag 18. mai 2014

የአሶሳው ግድያ የታቀደ ስለመሆኑ ተረጋገጠ


አብርሃ ደስታ እንደዘገበው:- ባለፈው ሳምንት 9 የትግራይ ተወላጆች በቤኑሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ታርደው መገደላቸው ይታወሳል። አንድ ሌላ የታክሲ ሹፌርን በጥይት
ተገድሏል (ከትግራይ)። በአንድ የዕጣን ድርጅት ይሰሩ የነበሩ ሦስት የአማራና ኦሮምያ ክልል ተወላጆችን ተገድለዋል። ትናንት ሐሙስ ግንቦት 7ም አንድ መኪና በታጣቂዎች ተይዞ በእሳት
ጋይቷል። በተሳፋሪዎቹ የደረሰ ጉዳት በትክክል ባይታወቅም አንዲት ተሳፋሪ ግን ቆስላ ተገኝታለች።
በ9ኙ የትግራይ ተወላጆች ላይ የደረሰውን ግድያ ለማጣራት በመኮርኩት መሰረት ግድያው ሆን ተብሎ ታቅዶ የፈፀመ ስለ መሆኑ አረጋግጫለሁ። ሙሉ መረጃ ያላቸው አሶሳ የሚኖሩ
የትግራይ ተወላጆች እንዳረጋገጥሉኝ ከሆነ ዓማፂ ቡድኑ የትግራይ ሰዎችን አርዶ ለመግደል ማቀዱ ይታወቅ ነበር። የወረዳው አስተዳዳሪ ይህን መረጃ ከግድያው በፊት ደርሶታል።
ባከባቢው የሚገኘው የመከላከልያ ሰራዊት አዛዥም ግድያ እንደሚፈፀም ተነግሮታል። ባጠቃላይ መንግስት ግድያው በተመለከተ ሙሉ ቅድመ መረጃ ነበረው። መንግስት
መረጃ እያለው ግድያው መከላከል አለመቻሉ ኗሪዎችን አሳዝኗል። በአሶሳ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች መንግስት ተገቢውን ፀጥታ
የማስከበር ተግባር አለመፈፀሙ አስገርሟቸዋል። መንግስት ለስልጣኑ እንጂ ለህዝብ ደህንነት እንደማይተጋም አስረግጠዋል።
አሁንም አሶሳ አከባቢ የሚኖሩ የሌላ ክልል ተወላጆች ስጋት ዉስጥ ናቸው።
መንግስት በትግራይ ልጆች ላይ ግድያ እንደሚፈፀም እያወቀ ለምን መከላከል እንዳልቻለ ለህዝብ መግለፅ ይኖርበታል። የሰለማዊ
ሰዎች ደህንነት መጠበቅ ባለመቻሉም ይቅርታ ይጠይቅ፣ ተገቢውም ካሳ ይክፈል።

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar