mandag 1. februar 2016

“ወታደሮቻችን ያሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፤ ትግላችንን ለመቀላቀል ካሁን በኋላ ለምትፈልጉ ወደ ሰሜን ብቻ መሄድ የለባችሁም” ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

“ወታደሮቻችን ያሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፤ ትግላችንን ለመቀላቀል ካሁን በኋላ ለምትፈልጉ ወደ ሰሜን ብቻ መሄድ የለባችሁም” ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

Share4  7797  13 
 Share8

Screen Shot 2016-01-31 at 4.01.56 PM

“የብሔር ጥያቄን የመለሰች፤ ከራሷ ጋር የታረቀች ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን እንገነባለን”

– ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

(ዘ-ሐበሻ) የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ባደረጉት ሕዝባዊ ስብሰባ በኢትዮጵያ በተከሰተው ረሃብ; በኦሮሞ ተማሪዎች አመጽ እና ትግሉ ስላለበት ሁኔታ እንዲሁም ስለተቃዋሚዎች ተናግረዋል::
በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ የስርዓቱ ችግር ነው ካሉ በኋላ እርሳቸው የሚመሩት ተቋም ከዚህ ቀደም የገመተው የተራቢዎች ቁጥር አሁን ተግባራዊ እየሆነ እንደሆነ እንዲሁም ይህ አስተዳደር ከቀጠለ ከዚህ ቀደም እንደገመቱት በ2050 ዓ.ም 50 ሚሊዮን ሕዝብ እንደሚራብ ገልጸዋል::
በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ዙሪያም እንዲሁ የተናገሩት ፕሮፌሰሩ በኦሮሚያ ክልል ህፃናት እና ነብሰጡርን ሳይቀር እየገደለ ያለውን ስርዓት ሕዝቡ እየሞተ ያለው ወገኔ ነው ብሎ ማውገዝ አለበት ብለዋል:: በተለይም በአሁኑ ወቅት ከኦሮሞ ድርጅቶች ጋር በህብረት ለመታገል ንግግሮች መጀመራቸውንም አስታውቀዋል::
ስለተቃዋሚዎችም የተናገሩት ፕሮፌሰሩ “የተቃዋሚዎች የምኞት ፖለቲካ ነው የሚከተሉት” ሲሉ ተችተው የምር መታገል እንዳለባቸው አስምረውበታል::
ወቅታዊውን የአርበኞች ግንቦት 7 ሁኔታ በተመለከተም “ወታደሮቻችን ያሉት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው… ትግላችንን ለመቀላቀል ካሁን በኋላ ለምትፈልጉ ወደ ሰሜን ብቻ መሄድ የለባችሁም” ብለዋል::
ሙሉ ንግግራቸው:-


Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar