lørdag 19. oktober 2013

ከድጡ ወደ ማጡ

ኦክቶበር 18.2013
ዲቦራ ለማ/ ከኖርዌ

ለ 22 አመታት በሐገራችን ኢትዮጵያ ላይ የሥልጣን ጥማት ያሰከረው የወያኔ መንግሥት ፕሬዘዳንት በመለዋወጥ ዛሬም እራሱን ህዝብ እንደመረጠውና ህዝቡ በስርዓቱ ደስተኛ እንደ ሆነ በማስመሰል የሚያደርገው ጥረት በጣም የሚያሳፍር ነው።

የወያኔ መንግስት ለራሱ እንደሚመችና እንደሚፈልገው የሚያሽከረክረውን አሻንጉሊት መሪ ማስቀመጡ ማናለብኝነቱን የሚያሣይ ነው። በዚህ በተንኮታኮተ ሥርዓት ውስጥ ዶ.ር ሙላቱ ተሾመ ለፕሬዜዳንትነት ሲመርጧቸው አሜን ብለው መቀበላቸው ምን ያህል የስልጣን ጥማት እንዳላቸውና ሆድ አደር መሆናቸውን እንዲሁም ለህሊናቸው የማይገዙ የወንበዴ ተባባሪ መሆናቸውን የሚያሳይ እውነታ ነው ።

ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ የቸገረው የገዢዎች  መለዋወጥ ሳይሆን  ከደረሰበት እረገጣና ጭቆና ቀንበር  ሥርዓት መላቀቅ ነው። ወያኔ እንደ መንግስት የዜጎችን ጥያቄ በአግባቡ መመለስ ሲገባው የህዝቡን ጥያቄ ውድቅ ለማድረግ በአለም ላይ አሉ ከሚባሉ ሽብርተኞች ጋር በማመሳሰል የተቃዋሚ ድርጅቶችን አመራሮችና አባላትን ሽብርተኞችና  የሽብርተኞች ተባባሪ ብሎ በመወንጀል ጥያቄያቸውን ውድቅ ለማድረግ ይሯሯጣል አድርጓቸዋልም;;


ገዢው መንግስት እንደሚያወራውና እንደሚሰብከው በህገ መንግስቱ ላይ እንዳሰፈረው አንቀጽ  ሕዝቡ በዲሞክራሲ መብቱ ተጠቅሞ በምርጫና በሰላማዊ ሰልፎች የሚጠይቁትን የፍትህ፤የነጻነት የእኩልነት  ጥያቄ አክብረው ስልጣናቸውን ለህዝብ ማስረከብ ሲኖርባቸው። ሆኖም ገዢው የወያኔ መንግስት በሀገሪቷ ላይ እያደረሰ ያለው ውንብድና ኢሰብአዊ  ድርጊቶች የሙስና መስፋፋት  ህዝቡን በዘርና በሐይማኖት መከፋፈልና ማጋጨት  ሃገሪቷን ከድጡ ወደማጡ እንደሚባለው ከማትወጣበት አዝቅት ውስጥ ጥለዋታል ።

ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለ ማሪያም ደሳለኝ በቅርቡ ለሐገር ውስጥ ጋዜጠኞች እንደተናገረው ከሆነ የተቃዋሚ  ፓርቲዎች ያደረጓቸውን ሰላማዊ ሰልፎች ሲተነትኑ በሐገሪቷ ላይ 99 ፓርቲዎች አሉ እነሱም በየሳምንቱ እሁድ ተቃውሞአቸውን ያሰማሉ እኛም ለጥያቄዎቻቸው ከአንዴ አራት ጊዜ መልስ ሰጥተናቸዋል እንዲሁም ተቃውሟቸውን ለህዝቡ ማሰማት ነበር የሚፈልጉት አሰምተዋል ከአሁን በኋላ በየሳምንቱ እሁድ ለዘጠና ዘጠኙ ፓርቲዎች ጥበቃ ልናካሂድ አንችልም በማለት የህዝቡን ጥያቄ በንቀት ተዘባብተውበታል።

ወያኔ ለህዝቡም ሆነ ለሐገሪቷ ካለው ጥላቻና ንቀት የተነሳ ሐገሪቷን በአለማችን ላይ አሉ ከሚባሉት እንደ አገር መቀጠል ከማይችሉት ሐገሮች እንድትመደብና በድህነትም ቀዳሚ  ከሆኑ አገሮች ተርታ እንድትገኝ አድርገዋታል ።

ወገን ይህ ሁሎ በደልና ጭቆና የበረታው ወያኔ ከፋፍለህ ግዛው በሚለው መርሆው እኛም ተቀብለነው ስለተመቻቸንለት ነው ከአሁን በኋላ መከፋፈልን ትተን አንድ ሆነን እጅ ለእጅ ተያይዘን የወያኔን አገዛዝ በቃ ማለት ይገባናል።

ይህ ትውልድ ደግሞ ለነጻነቱ ለመብቱ ብሎም ለሐገሩ እድገት ዋስትና ለመሆን ቆርጦ መነሳቱን የሚያመለክቱ ሁኔታዎች እየታዩ ነው ስለዚህም ህገመንግስቱ በሚፈቅድላቸው መሰረት በሰላማዊ ትግል ወያኔን ማስወረድ ወይም በትጥቅ ትግል ወያኔ በሚገባው ቋንቋ እንፋለመዋለው ከሚሉት ከግንቦት ሰባት ህዝባዊ ሃይል ጋር በመቀላቀል ወያኔን ከምድረ ኢትዮጵያ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማስወገድ ይኖርብናል በመጨረሻ ለመላው ኢትዮጵያዊ የማስገነዝበው ነገር ቢኖር እያንዳንዱ የዜግነት ድርሻውን እንደየ አቅሙ በመወጣት ሐገራዊ ግዳጁን ይወጣ እላለሁ።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሞት ለወያኔ     

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar