mandag 14. oktober 2013

መብቱን ለማስከበር ታስሮም እንደማያጎበድድ በእስር ላይ የሚገኘው አንዷለም አራጌ አረጋገጠ

ፋሽስት ወያኔ ባቀነባበረው የውሸት ክስ በሽብርተኝነት ተከሶና በወያኔ አሻንጉሊት ዳኞች እድሜ ልክ ተፈርዶበት ቃሊቲ ወህኒ ቤት የሚገኘው የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አንዳለም አራጌ ዛሬም በእስር ቤት ለመብቱ እየታገለ እንደሆነ ተገለጸ። በውጭ ያሉት የተቃውሞ ሃይሎች መሰባሰብና እየተጠናከሩ መምጣት ሰላም የነሳው ፋሽስት ወያኔ በሀገር ውስጥ በቁጥጥሩ ስር ባለው የፓርቲዎች ሰላማዊ ሰልፍ እንቅስቃሴ ላይ ዛቻ እንዲያሰማ እንዳደረገው ይታወሳል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ነው እንግዲህ ፋሽስት ወያኔ ለአቶ አንዷለም አራጌ ሰላም በማሰብ በሚል በእስር ቤት የሚጠይቁትን ሰዎች ቁጥር ለመወሰን የፈለገው።

ፋሽስት ወያኔ ከሌሎች የቆዩ እስረኛ ጓደኞቹ ጋር እንዳይገናኝ በማሰብ እስካሁን ድረስ አቶ አንዷለም አራጌን በጊዜያዊ ማቆያ ውስጥ ማሰሩ ሳያንስ ይህን የነጻነት ታጋይ የሚጎበኙ ሰዎች ቁጥር ለመገደብ በመወሰን እነማን እንዲጎበኙት እንደሚፈልግ ስም ዝርዝር እንዲያቀርብ ጥያቄ ማቅረቡ አንዷለምን አበሳጭቷል ተብሏል። በማንኛውም ጊዜና ቦታ ለመብቱ እንደቆመ አስረግጦ በማሳየት ላይ ያለው አንዷለም ግን “መጎብኘት ሕገመንግስታዊ መብቴ ነው ። የስም ዝርዝርም አልሰጥም” በማለቱ የተነሳ ከመስከረም 29 2006 ዓ/ም ጀምሮ ማንም ሰው እንዳይጎበኘው ክልከላ መጣሉን ፓርቲው አንድነት አሳውቋል።

ፖለቲከኛና ሚስማር ሲመታ ይጠብቃል የሚሉ ወገኖች የነጻነት ታጋዩ የሞራል ፅናትና ጥንካሬ ከመቼውም በላይ መድረሱን አድንቀው፤ ፋሽስት ወያኔ የደረሰበት የወረደና የዘቀጠ የፍርሃት ደረጃ ግን በእስር ቤት አጉሮ እያሰቃያቸው ያሉትን የነፃነት ታጋዮች እስካለማመን አድርሶታል ያላሉ። እውነት አስፈሪ ናት የሚሉት እነዚሁ ወገኖች ሕገመንግስታችን የሚሉትን ተረት ተረት እንኳ ሳይቀር ከፋሽስት ወያኔ በተሻለ ሁኔታ የነጻነት ታጋዩ አንዷለም አራጌ አሳምሮ እንደሚያውቀውና እያከበረው መሆኑን የሚያውቀው ሕሊናቸው ጫፍ ከሌለው ፍርሃት ውስጥ እንደከተታቸውም ጨምረው ጠቁመዋል።


Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar