tirsdag 29. oktober 2013

የኢትዮጲያ ወዳጆች በሙሉ እንዲገኙ የከበረ ጥሪ እናቀርባለን

በቅርቡ ከኢትዮጲያ ኦጋዴን/ሶማሌ ክልል በድብቅ ወጥቶ በስዊዲን ቴሌቪዥን የተላለፈው ዶክመንተሪ ፊልም የዓለም ህብረተሰብን ያስደነገጠና ያስቆጣ በመሆን የወያኔን አረመኔአዊ አገዛዝ በድጋሚ አጋልጧል ።
ይህ ሁኔታ በጉራፈርዳ ፣ በቤንሻንጉል ፣ በአሶሳ ፣ በወልቃይት ፣ በኦሮሞ ፣ በአማራ ህዝብ እንዲሁም በመላ ዜጎች ላይ እየተፈፀመ ያለውን የጅምላ ጭፍጨፋ አጉልቶ አሳይቶል ።
በመሆኑም የዓለም አቀፍ ሕግ ኮሚሽን ኮሚሽነርና የሕግ ጠበቃ Jurist Stellan Gärde ወያኔ በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ስለሚቀርብበት አግባቦችና ቅድመ ዝግጅቶች ላይ ለኢትዮጲያዊያን ማብራሪያ በመስጠት ተዛማጅ መረጃዎችንም ለማጠናቀር በስብሰባው ላይ ይገኛሉ ።
በተጨማሪም በወያኔ እስር ቤት የተሰቃዩት ማርቲን ሸቤ ስላሳለፉት መከራና በዚሁ ዙሪያ የፃፉትን መፀሃፍ ይዘው በመቅረብ ማብራሪያ ይሰጣሉ ።
ዶክተር ሙሉዓለም አዳም በኖርዌይ የፖለቲካ አክቲቪስት ፣ መቶ አለቃ አበረ አዳሙ በኢትዮጵያ ፖሊስ በኃላፊነቶች የሠሩና የኢ.ፒ.ፒ.ኤፍ (EPPF) መሥራችና የአመራር አባል የነበሩ፣ ጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ የኢሳት የሰብዓዊ መብት ጉዳይ አዘጋጅ የሰብዓዊ መብት ጥሰትን በተመለከተ በቪዲዮ የተደገፈ ማብራሪያ ያቀርባሉ ።
አዘጋጅ የኢትዮጲያ ዴሞክራሲያዊ መድረክ
በዚህ ውይይት የኢትዮጲያ ጉዳይ የሚያሳስበው ዜጋና የኢትዮጲያ ወዳጆች በሙሉ እንዲገኙ የከበረ ጥሪ እናቀርባለን ።
የሃገር በባህል ምግብ ቡናና ሻይ ተዘጋጅቷል ቀን ኖቬምበር 2- 2013 ዓ .ም ቦታ Stockholm, Hallunda Folketshus ሰዓት ከቀኑ 13.00 ጀምሮ .
Sweden
Image

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar