torsdag 28. november 2013

አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ጠቅላይ ሚንስትር የሚሆኑት መቸ ነው?!!!

NOV 28,2013
du_pm_haile_mar_desነፍሳቸውን ይማረውና(ድንገት ነፍስ ካላቸው፣መንፈስ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ነው)የቀድሞውና ያሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ በሞት ካረፉና ካረፍናቸው ጀምሮ ታላቋ ኢትዮጵያ ያለ ሀገረ ገዥ የቀረች ይመስላል፡፡ሆደ ቡቡነታቸውን ለመለስ ዜናዊ ሲነፋረቁ ያረጋገጥንላቸው ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ወንበሩ ላይ ቢቀመጡም እንደ ሁለት ወር ህጻን ከተጎለቱበት አላንቀሳቅስ ያላቸውን እርኩስ መንፈስ ሁለት ሰባት ቢታዘዝለት መልካም ነበር፣ነገር ግን ሰውየው በኢየሱሴ የዳኑ ናቸውና ጸበልን ከዚያው በጸበልህ የሚሉ መሆናቸው እኛ የእርሳቸውን ታማኞች መፍትሄ እንዳናዘጋጅ አድርጎናል፡፡ከሰሞኑ ደግሞ ይህ እርኩስ መንፈስ ምንም አላናግራቸው በማለቱ ጭንቀታችን የከፋ አድርጎታል፣መላ ያለህ ሁሉ ወዲ በል፡፡እርስዎስ ቢሆኑ በዚህ ቀውጢ ሰኣት ያልነገሱ መቸ ሊነግሱ ነው፡፡እኔ እንደው የእርስወ ነገር አያስችለኝምና ትንሽ ምክር ቢጤ ጣል ላድርግለዎት፣የ2007 ምርጫ ደርሶ ሱናሜው ሳይጠርግዎት ጠቅላይ ሚኒስትርነትን ቢሞክሯት መልካም ነው እላለው፡፡አይተ በረከት ስሞንስ እስከመቸ ነው የስሁል ሚካኤልን መንበር ተረክበው ሲሽሩና ሲሾሙ ምን አለበት አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝን ጠቅላይ ሚንስትር ቢያደርጓቸው፡፡(ስሁል ሚካኤል በጎንደር የነገስታት ዘመን ከትግራይ የመጡ መስፍን ሲሆኑ ከኋላ ሆነው ሲሾሙና ሲሽሩ የነበሩ ጉልበታም ናቸው)፡፡በመጨረሻም ለሃይለማሪያም ደሳለኝ የማስተላልፈው መልዕክት ቢኖረኝ እንደሚከተለው ይጠቃለላል፣ታሪክዎ ሲጻፍ ቤተ መንግስቱን ከሚጠብቁት ወታደሮች የተለየ አይሆንምና በጊዜ መላ ቢያበጁ፣ባይሆን ምን ማድረግ እንዳለብዎት ከጠፋብዎ አኔን ያማክሩኝ፡፡የሚሰማን የለምእንጅ ባለ ራዕይውንም መክረናቸው ነበር፡፡ምን ያደርጋል ምክራችን ይዘውት ሽል አሉ እንጅ፡፡Gashaw Mersha

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar