søndag 10. november 2013

ወይ ጣጣችን!!!

1391526_1474862899405800_948440420_n






























ወይ ጣጣችን!!!
በሳውዲ አረቢያ ኢትዮያውያን ላይ እየደረሰ ያለው አበሳ እጅግ አሳዛኝ ነው፡፡ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ “አንድ ኢትዮጵዊ  በሳውዲ ፖሊሰሶች ተገድሏል” ብለው በኢትየጵያ የሳውዲን አምባሳደር ማብራሪያ ሲጠይቁ አስገረሙኝ፡፡ እርሳቸው እንኳ እየተናገሩ ባለበት ቅስበት በርካቶች በሞት ሽረት ጣር ላይ መሆናቸውን ሳውዲ ሳይሄዱ ስልክም ሳይደውሉ በልጃቸው ፌስ ቡክ ጎራ ብለው ቢያዩ ይረዱ ነበር፡፡
ሳውዲዎች በአሁኑ ሰዓት እየገደሉ ያሉት የክፉ ቀን መጠለያ የደህናው ጊዜ ኢንቨስት ማድረጊያ የሆነቻቸውን ኢትዮጵያ ልጆች መሆኑን ግንዛቤ ያላቸው አይመስሉም፡፡
ኢትዮጵያ ለሳውዲ አረቢያ ምን ማለት እንደሆነች የድሮውን እንኳ ብንተወው በአሁኑ ሰዓት የሳውዲ ሃብታሞች በሀገራችን እንዴት እንዴት እየፈነጩባት እንደሆነ ልብ ማለት ብቻ በቂ ነው፡፡
ዞሮ ዞሮ እኔ በበኩሌ በእነርሱ አልፈርድም፡፡ የምፈርደው በገዛ መንግስቴ ነው፡፡ መንግስታችን ልክ ራሱ ሲያቆስል እንደሚያደርገው የጉዳታችንን መጠን እየቀነሰ ነገሩን ከማለባበሰ ኮስተር ብሎ ዜጎቹን ከጥቃት ለመከላከል ፈጠን ያለ ርምጃ ቢወስድ ባይጸድቅ እንኳ ከኩነኔ ይድን ነበር፡፡
ከሁሉ ከሁሉ የሚበልጠው ደግሞ የላኛው ነውና፤ በሳውዲ የምትገኙ ወገኖች ፈጣሪ ይቺን መከራ ያሳልፍላችሁ!!

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar