ዲቦራ ለማ ከኖርዌ
ኖቨበር 04 2013
ታሪክ ሥንመለከት ቀደም
ሲል የነበሩት የዓለም መንግሥታትና ገዢዎች ከነበራቸው የስልጣን ጥማትና የህዝባቸው የአስተሳሰብ ማነስ የተነሳ ዘርን፤ ሀይማኖትን
ቀለም፤ የፖለቲካ አመለካከትንና ሌላም መስፈርቶችን እንደመጨቆኛ መሣሪያ
ይጠቀሙባቸው ነበር። ይህንንም እንዲያደርጉ የረዳቸውና የጠቀማቸው የዓለም የፖለቲካ አመለካከት በሁለት ጎራ በመከፈሉ
ነበር። ሁለቱ የፖለቲካ አመለካከት ጎራዎች የምእራቡ ዓለም ኢምፔሪያሊዝምን ሲከተል የምስራቁ ዓለም ደግሞ ሶሻሊዝምን ይከተል ነበር።
ሁለቱም የየራሳቸው
የፖለቲካ አመለካከት ሲኖራቸው ህዝባቸውን የሚያናንቁበት የብዙሀን ሚዲያ አንዱ አንዱን እየኮነነና እያጣጣለ ህዝባቸው ወደ ሥልጣንናቸው
እንዳይመጣበቸው በትኩረትና በጥበብ ህዝባቸውን ይጨቁኑ ነበር። ይሁን እንጂ ምእራባዊያን ምስራቃዊያንን በረቀቀ ፖለቲካ ካንበረከኩ
በኋላ ዲሞክራሲ በሚል ፍልስፍና ዓለምን ወደ አንድ አቅጣጫ አምጥተዋል፣ በመሆኑም የፖለቲካ መዘውሩ በምእራባዊያን እጅ በተለይ በአሜሪካን
ቁንጮነት ይዘወራል።
ኢትዮጵያ አንዷ የዓለም
ክፍል ወይም ሀገር በመሆኗ ይህ ክስተት ተከናውኖባታል። የነበሩት ገዢዎች ከነበራቸው የፖለቲካ ንቃተ ህሊና ማነስ ለራስ ብቻ በማሰብ
ህዝቡን በዘር፤ በቋንቋ፤ በሀይማኖት፤ በፖለቲካ ልዩነት በመፍጠርና አድሎ በማድረግ ሲጨቁኑ ወደ በትረሥልጣናቸው ማንም ድርሽ እንዳይል
ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ ወደ በትረሥልጣናቸው የመጣውን ሁሉ በጥይትና በእስራት፤ በግርፋት በማሰቃየት ህይወቱን ሲያጠፉ ቆይተዋል። የሚፈሩትንና የራሳቸው ወገን ለማድረግ የሚፈልጉትን ዘርም ሆነ ግለሰብ ደግሞ ሥልጣንና
መሬት በመሥጠት አፉን እንዲዘጋ ክንዱን እንዳይዘረጋ ያደርጉት ነበር።
ዛሬ በሃያ አንደኛው ክፍለ
ዘመን ውስጥ የዓለም መንግሥታት የሚለፈልፉት የፖለቲካ ሥርዓት ዲሞክራሲ ማለት የህዝብ የሥልጣን የበላይነት፤ ባለሥልጣንን ለመሾምም
ሆነ ለማውረድ ሀይል ያለው መሆኑ ሲሆን የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ይህንን ሁኔታ ለይሥሙላ በወረቀት አሣምሮ ቢፅፈውም በተግባር ደግሞ
እራሱ ያወጣውን ህግ እራሱ ሲሽረው ይታያል። ስልጣን ከተቆናጠጠበት ቀን ጀምሮ ይህ ነው የማይባል ወንጀሎችን እየፈጸም ይገኛል ለምሣሌ፦ኢትዮጵያን
ወደብ ዓልባ አድርጎ ማስቀረት፤ መሬቷን ለሱዳን ቆርሶ በመሥጠት፤ ሕዝቦችን ከቤት ንብረታቸው ማፈናቀል፣ ዘርን ከዘር ማጋጨትና ማጋደል፤
የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ማድቀቅ፤ የሙስና ንቅዘትን ማስፈን፤ ግለሰቦች የማንኛውም የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅት አባል እንዳይሆኑ
መገደብ፤ የትምህርት ጥራትን መግደል፤ የምርጫ ሂደትን ማዛባትና ውጤቱን አለመቀበል፤ የማህበረሰቡን መብት መግፈፍ ማለትም ሃሣብን በነፃነት የመፃፍንና የመገለፅን፤
ሰላማዊ ሰልፍን መከልከልና መገደብ ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው።
እጅግ የሚያሳዝነው ግን
ይህ ሁሉ እየተፈፀመብን በሰላማዊ መንገድ ብሶታችንን ለዓለም ህዝብና መንግሥት ብሎም እነኚህን ሁሉ ለሚያደርግብን ለራሱ ለወያኔ
መንግሥት ድምፃችንን ለማሰማት ብንፈልግም እንኳን ጩኅታችሁንና ድምፃችሁን ለማሰማት ከኔ ፈቃድ ማግኘት አላባችሁ በማለት ህገ መንግስቱን
በሚጻረር ሁኔት ሲያጉላላ ከቆየ በኋላ በእርሱ ችሮታ ፈቃድ እንደሰጠ
በማስመሰልና የህዝብን መብት በመጣስ ከዚህ በፊት ሲፈፅማቸው የነበሩት ድርጊቶች ሁሉ የገዢውን ፓርቲ ማንአለብኝነት ቢገልፁም በዚህ
በያዝነው በአዲሱ ዓመት 2006 እና ባሳለፍነው 2005 ዓ.ም ከፈፀማቸው ጥቂቶቹ አንድነት ለዲሞክራሲ
ለፍትህ ፓርቲ የሶስት ወር መርሐ ግብር በያዘው ሐገራዊ ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፎች የመሰብሰቢያ አዳራሾችን፤ አደባባዮችና መንገዶችን ሁሉ የኔ ናቸው በማለት በአዳራሾቹ
ልትሰበሰቡባቸው መንገዶችንም ልትሄዱባቸው አትችሉም ብሎ በመከልከል ማን አለብኝነቱን በይፋ አስመስክሯል።
በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲ ተከራይቶት የነበረውን ቢሮ ከተራ ግለሰብ በማይተናነስ ድርጊት የወያኔ ካድሬን በመላክ
ግቢውን ቀድሜ የተከራየሁት እኔ ነኝ በማለት ውዝግብ በመፍጠር ፖሊስ መሐከላቸው ገብቶ ጉዳዩ እስኪፈታ ድረስ ግቢውን በመቆጣጠር
ዜጎች ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው ቢሮ ከፍተው የሚንቀሳቀሱበትን ጊዜ በአልባሌ ውዝግብ በተዘዋዋሪ የመብት እረገጣ በማካሄድ
የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በማንገላታትና በማሰር ድርጅቶቻቸውንም በመዝጋት የአንባገነናዊ ስርአት መሆኑን አሳይተዋል። እንዲሁም የአንድነት
ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የብሔራዊ ምክር ቤት አባልና በሚሊዩኖች ድምጽ ለነጻነት ሕዝባዊ ንቅናቄ በተለያዩ ከተሞች
በመንቀሳቀስ ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉት መምህር አቶ አበበ
አካሉ 14/02/06 ዓ.ም የደህንነት መስሪያ ቤት አባላት ነን
ባሉ ሶስት ቅጥረኞች የግድያ ሙከራና አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው
ለፍኖተ ነጻነት ይፋ አድርገዋል፡፡
ሰላማዊው ታጋይ እንደተናገሩት
በምሳ ሰዓት ኮተቤ መሳለሚያ አካባቢ ለስራ ጉዳይ ሲንቀሳቀሱ ህገ ወጦቹ ያሽከረክሯት የነበረችን ላንድክሩዘር መኪና የእግረኛ መንገድ እንድትዘጋ በማድረግ አቶ አበበን በሀይል በመኪናው በመጫን ወደ ማያውቁት ሰዋራ ቦታ በመውሰድ ቤቶች በሚሰሩበት አካባቢ ከመኪናዋ በማውረድ ሲሚንቶ ላይ በማስተኛት በሰላማዊ
መንገድ የሚያካሂዱትን ትግል እንዲያቆሙ ይህ ካልሆነም ‹‹ በሽብርተኝነት በመወንጀል መንግስትን በሀይል ለማውረድ ትሰራለህ›› በማ
ለት እንደሚወነጅሏቸው በመንገር በቃላት ለምግለጽ በሚያስቸግር ሁኔታ
ድብደባ እየተፈራረቁ እንዳካሄዱባቸው ተናግረዋል፡፡
መምህር አበበ ከቀኑ 6፡30
እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ግለሰቦቹ ሽጉጥ ደግነውባቸውና የማያውቁትን
የአልኮል ቃና ያለው ፈሻሽ ነገር በመጋትና ከሲሚንቶ ጋር አጣብቀው በመርገጥ
የግድያ ሙከራ ካደረጉባቸው በኋላ ምሽት ላይ በመኪና አውጥተው እንደጣሏቸው ለፍኖተ ነጻነት ተናግረዋል፡፡
የወያኔ መንግስት ዲሞክራሲን ለይስሙላ በመስበክ
ሐገራዊ ጥሪ እያሰማ ልማታዊ መንግስታችን ልማታዊ መሪያችን ፈጣኑ
እድገታችን በማለት ህብረተሰቡን በውሸት ፕሮፓጋንዳ በማዶንቆር በተግባር ግን የህብረተሰቡን የሰብአዊ መብት በአደባባይ መርገጡን
አይን ያወጣ የማፍያ ስርአት መሆኑን እያስመሰከረ ነው ከዚህም በላይ በሐገራችን ውስጥና እንዲሁም ሸሽተው ወደጉረ ቤት ሐገራት የሄዱትን
ወገኑች እጁን በማስረዘም ይዞ በማስመጣትና በእስራትና ግርፋት በማንገላታት
የሚያጠፋውን የሰው ህይወት ለህዝብ ይፋ ሆነው ያልተሰሙ ብዙ ወንጀሎች ቤቱ ይቁጠረው የኢትዮጵያዊያንን ወኔ በሚፈታተን ሁኔታ ላይ
ያለው የወያኔ አገዛዝ ስርአት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ በሰላማዊ እንዲሁም በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሱ ወገኖች ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን አንድ በመሆን ለሐያ ሁለት አመታት የበሰበሰውን
ስርአት በቃ የምንልበት ጊዜው አሁን ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar