ኖቬምበር 10, 2013
ዲቦራ ለማ/ከኖርዌ ቬስትነስ
የኢትዮጵያ ዜጎች በሃገራቸው
ከሚደርስባቸው የፍትህ መጓደል ግፍና የህግ የበላይነት አለመከበር የዘር መድሎ እንዲሁም ዜጎች ከቀያቸው መፈናቀል በሃገራቸው እንደ
ሶስተኛ ዜጋ መቆጠር ከመሣሰሉት በደሎች እራሳቸውን ለማዳንና ለማቆየት የዜጎች መፈናቀልና መሰደድ አማራጭ ሆኗል። በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ
ህዝብ በየበረሃው፤ በባህር፤ በየመንገዱ ይሞታል፤ በአጋጣሚ እድል ብሎለት ነፍሱን አትርፎ ወደ ስደት የገባውም እየተነቀፈ፤ እየተዋረደ፤
እየታሰረ አልፎ ተርፎ በስደት ምድር በግፍ በሰቆቃ በየመንገዱ ግርፋቱና እንግልቱ እየጨመረ መጥቷል።
በሳኡዲ አረብያ በወገኖቻችን
ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍና በደል ልብን የሚሰብርና እጅግ የሚያሰቅቅ ነው ሰው በሰው ልጅ ላይ ይህን ያህል ጭካኔ ይፈፅማል ተብሎ
የማይጠበቅ ትልቅ በደል ነው እስከመቼ ወገኖቻችን ያጨፈጨፋሉ በየጎዳናውስ ደማቸው ደመከልብ ሆኖ ይቀራል እስከመቼስ የዜጎች በየመንገዱ
ያልቃሉ እህቶቻችንስ እስከመቼ ይደፈራሉ ወገን ምን ማድረግ አለብን ኧረ እንማከርና ይህንን ሰው በላ ለዜጎች የማይቆረቆር መንግስት
ከጉያችን ፈንቅለን ለመጣል ሁላችንም የሐገራችንን እና የዜጎቿን የተዋረደ ክብር ለማስመለሥ ጠንክረን መታገል አለብን መቼም ይህ
የወንድሞቻችን መከራና ህመም ያላመመው ሰው ያለ አይመስለኝም ሁላችንም ክፉኛ እንደተቆጣን አምርረን ወያኔን ካገራችን ማስወገድ መቻል
አለብን።
ላለፉት ሁለት አስርተ አመታት
የወያኔ አምባገነን መንግሥት በስደት በየቦታው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን በተለይ ሰሞኑን በሳኡዲ አረብያ በዜጎች ላይ ለተከታታይ
አምስት ቀናቶች እየተፈፀመ ላለው ሞትና እንግልት እንዲሁም በየመንገዱ ደማቸው እየፈሰሰ ላለው ወገኖቻችን በዋናነት ተጠያቂው መሆናቸውን
ማወቅ አለባቸው ጊዜው ሲደርስ እንፋረዳቸዋለን። እግዚአብሄር በሳኡዲ ለሚሰቃዩ ወገኖቼ ሁሉ እንዲሰርስላቸው እና የጨካኞችን ጡንቻ
እንዲይዝላቸው እለምናለሁ።
እግዚአብሄር ሐገራችንን ይባርክልን
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar