mandag 25. november 2013

“አንዱዓለም አራጌ በትግራይ ሕዝብ የሚወደድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ነው” አብርሃ ደስታ

ከመቀሌ ኢትዮጵያ በየጊዜው በፌስቡክ እና በተለያዩ ድረገጾች ወቅታዊ መረጃዎችን በማድረስ የሚታወቀው አብርሃ ደስታ አንዷአለም አራጌ በትግራይ ሕዝብ የሚወደድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ነው አለ።
በአሁኑ ወቅት የ ዕድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት በማረሚያ ቤት የሚገኘውና በዚህ አመት የዘ-ሐበሻ እና የኢሳት ተከታዮች የዓመቱ ምርጥ ሰው በሚል ሽልማት ያገኘው አንዷለም አራጌ በትግራይ ሕዝብ ዘንድም ከፍተኛ አክብሮት የተሰጠው ፖለቲከኛ መሆኑን አብርሃ ደስታ ገልጿል።
“ከትግራይ ሰዎች ባሰባሰብኩት መረጃ መሰረት ባሁኑ ሰዓት ክብርና አድናቆት የተቸረው የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪ አንዱአለም አራጌ ነው” ሲል በፌስቡክ ገጹ የገለጸው ሌሎች ዝርዝር መረጃዎችን አላስቀመጠም።
ይቅርታ ጠይቅ ተብሎ “ያጠፋሁት ጥፋት ስለሌላ ይቅርታ አልጠይቅም” በሚል በእስር ቤት መስዋትነት የከፈለው አንዷአለም አራጌ ትናንት በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት ያልተሄደበት መንገድ መጽሐፍ በድምቀት ተመርቋል። የአንዷለም አራጌ ያልተሄደበት መንገድ መጽሐፍ በቅርቡ በውጭ ሃገራትም እንደሚሰራጭ ለዘ-ሐበሻ የደረሰ መረጃ ያመለክታል።
አንዱዓለም አራጌ የያዘው የዓላማ ጽናት ብዙ ተከታዮች እንዲኖሩት ያደረገ ቢሆንም፤ እየከፈለ እንዳለው መስዋትነት ግን ከ እስር እንዲፈታ ለመጠየቅ፣ ፊርማ በማሰባሰብ፣ ሰላማዊ ሰልፍ በመውጣትና በሌሎችም በየከተማው የሚደረጉ እንስቃሴዎች ቀዝቃዛ መሆናቸው ያስቆጫል ሲሉ አንድ አስተያየት ሰጪ ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል።
ምንጭ ዘ-ሀበሻ ድረ ገፅ

Ingen kommentarer:

Legg inn en kommentar