ኢሳት ዜና :-
በኦሮምያ ደግሞ ከ205 በላይ ወረዳዎች ሲኖሩ ከ4 ቢሊዮን ብር በላይ ይሰበሰባል። በትግራይ ከ38 ወራዳዎች ከ600 ሚሊዮን ብር በላይ ፣ በደቡብ ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ሲዋጣ፣ በአዲስ አበባ የሚወጣው ደግሞ እስከ 2 ቢሊዮን ብር ይደርሳል። በመላ አገሪቱ በሚገኙ ወረዳዎች ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ የሚወጣ ሲሆን፣ ለፋውንዴሽኑ ከተበጀተው 300 ሚሊዮን ብር ውጭ ያለው ከ9 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ የት እንደሚገባ እንደማይታወቅና ቁጥጥር የሚያደርግ አካል አለመኖሩንም ምንጮች ገልጸዋል።
ደሃውበምግብውድነት: ነጋዴውበግብር አርሶአደሩ በማዳበሪያ እዳ እየተሰቃዩ ባለበት ጊዜ ይህን መክፈል አይቻልም በማለት ተቃውሞ ያስነሱ ሰዎች፣ ተቃውሞቸአውን የሚሰማቸው አካል አላገኙም። አንዳንድ ዜጎች ገንዘብ የከፈሉበትን ደረሰኝ ለኢሳት በመላክ፣ ዝርፊያው እንዲቆም ህዝቡ ተቃውሞ እንዲያሰማ እየጠየቁ ነው። የመለስ ፋውንዴሽን፣ የቀድሞውን ጠ/ሚ መለስ ዜናዊን የሚዘክሩ ስራዎችን የመስራት አላማ አለው። ፋውንዴሽኑ በህዝብ ፈቃድ እና ከመንግስት በሚሰጥ ገንዘብ ይሰራል ተብሎ ቢነገረም፣ ህዝቡ ለማዋጣት ፈቃደኛ ባለመሆኑ በግዴታ እንዲያዋጣ እየተደረገ ነው። ከህዝብ ፈቃድ ውጭ የተሰራ ፋውንዴሽን ፣ ኢህአዴግ እስካለ ጊዜ ብቻ እንደሚቆይ የሚናገሩት አስተያየት ሰጪዎች፣ ፋወንዴሸኑ ከደሃው ኢትዮጵያዊ ገንዘብ መሰብሰቢያና ሃብት ማካበቻ መሆኑንም አክለዋል።
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar