ፍኖተ ነፃነት
በሃዋሳ ከተማ በእስር ላይ የሚገኙትን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ አባላትን ሁኔታ ለመመልከት ወደ ወደ ሃዋሳ እስር ቤቶች ያመሩት የሰብዓዊ መብት ጉባዔ ሀላፊዎች እስረኞቹን ለማግኘት እንደማይችሉና ከማንም ጋር እንዳይገናኙ ትዕዛዝ በመተላለፉ ምክንያት ታሳሪዎቹን ማግኘት እንዳልተቻለና የጣቢያ ሀላፊዎቹን ለማናገር የተደረገውም ጥረት እንዳልተሳካ አስረድተዋል፡
አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ(አንድነት)ባሳለፍነው ሳምንት ሰኔ 15 ቀን 2006ዓ.ም በሃዋሳ ከተማ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በእስር ላይ የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ አባላት ‹‹ፍትህን ተነፍገን ትግላችን አይቆምም ››በማለት ዛሬም ለ4ኛ ቀን በርሀብ አድማ ላይ ናቸው፡፡አባላቱ በቁጥጥር ስር ከዋሉበት ቅዳሜ እለት ጀምሮ በረሀብ አድማ ላይ ሲሆኑ በትላንትናው እለት ሰኞ ሰኔ 16 ቀን 2006 ዓ.ም በሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው በኢ/ፌ/ዲ/ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 27(1-ሀ)32/1-ሀ/እና 257 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በሚል የአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ዐ/ሕግ ክስ ተመስርቶባቸው የዋስትና መብታቸው ተነፍጎ በእስር እንዲቆዩና ዓቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለሰኔ 20 ቀን 2006 እንዲያሰማ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ በማስተላለፉ ወደ እስር ቤት እንዲመለሱ ተደርጓል፡፡
Ingen kommentarer:
Legg inn en kommentar